Harari Regional State Innovation and Technology Agency

Call Directions Website

Harari Regional State Innovation and Technology Agency This is official page of Harari Regional State Innovation and Technology Agency

የባይናንስ የሳይበር ጥቃት፡ ለዓለም አቀፍ የክሪፕቶ ኢንዱስትሪ እና የዲጂታል ንብረት ደህንነት ትልቅ ማንቂያ ደወል!​የዓለማችን ትልቁ የክሪፕቶከረንሲ ልውውጥ መድረክ የሆነው ባይናንስ (Bin...
30/10/2026

የባይናንስ የሳይበር ጥቃት፡ ለዓለም አቀፍ የክሪፕቶ ኢንዱስትሪ እና የዲጂታል ንብረት ደህንነት ትልቅ ማንቂያ ደወል!

​የዓለማችን ትልቁ የክሪፕቶከረንሲ ልውውጥ መድረክ የሆነው ባይናንስ (Binance) - እስከ 2026 አጋማሽ ድረስ ከጠቅላላው የክሪፕቶ ገበያ ከ35% እስከ 36% የሚደርስ ግዙፍ ድርሻ የሚቆጣጠር ተቋም ሲሆን፤ በከፍተኛ የሳይበር ጥቃት መመታቱ መላውን የዲጂታል ፋይናንስ ዓለም ያስደነገጠ ታሪካዊ ክስተት ሆኗል።

በጥቃቱም ወደ 6.3 ቢሊዮን ዶላር የሚገመት የክሪፕቶ ንብረት መጥፋቱ በሰፊው እየተዘገበ ይገኛል። ምንም እንኳን ባይናንስ የደንበኞቹን ገንዘብ ደህንነት ለማረጋገጥ እና የሚደርሰውን ኪሳራ ሙሉ በሙሉ እንደሚሸፍን ገልጾ ፈጣን የማስተካከያ እርምጃዎችን እየወሰደ ቢሆንም፤ ይህ ክስተት በሳይበር ደህንነት ዓለም ውስጥ ሰፊ ውይይት ያስነሳ አሳሳቢ ጉዳይ ሆኗል።

​ዓለም አቀፍ መገናኛ ብዙኃን እና የዘርፉ ባለሙያዎች እንደሚተነትኑት፣ የዓለማችን ግዙፍ የደህንነት መዋቅር ያላቸው ተቋማት ራሱ በጠላፊዎች (Hackers) ኢላማ መሆናቸው የሳይበር አጥቂዎች ስልት ከጊዜ ወደ ጊዜ እየተራቀቀ እና አደገኛ እየሆነ መምጣቱን በግልጽ ያሳያል።

​በተጨማሪም፣ የክሪፕቶ ዓለም ማዕከል የሆነው ግዙፍ ተቋም መጎዳቱ ለሌሎች ትናንሽም ሆኑ አጠቃላይ የዲጂታል ልውውጥ መድረኮች ትልቅ ትምህርት ሰጥቷል። በዚህም መሰረት ሌሎች ተቋማት የደህንነት ሥርዓታቸውን ከወዲሁ በአግባቡ እንዲፈትሹ፣ የባለብዙ ደረጃ ጥበቃ (Multi-layered Security) ቴክኖሎጂዎችን እንዲተገብሩ እና ለተመሳሳይ ድንገተኛ አደጋዎች ሁልጊዜ ዝግጁ እንዲሆኑ ጥሪ ቀርቧል። የዲጂታል ንብረቶች ገበያ ከጊዜ ወደ ጊዜ እየሰፋ ሲሄድ የሳይበር ደህንነት ስጋቶችም አብረው ስለሚያድጉ፣ ጥብቅ የቁጥጥር ማዕቀፎች እና የማይበገር (Resilient) የቴክኖሎጂ አሰራሮች መዘርጋት የግድ መሆኑ ታምኖበታል።

INSA- የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አስተዳደር

30/10/2026
30/10/2026
ክብርት ሚኒስትር ፍሬሕይወት ታምሩ የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ታለንት ልማት ኢንስቲትዩት በጠንካራ ሕጋዊና ተቋማዊ መሠረት ተደራጅቶ ወደ አገልግሎት እንዲገባ ስትራቴጂያዊ አቅጣጫ ሰጡ፡፡የኢኖቬሽንና...
30/10/2026

ክብርት ሚኒስትር ፍሬሕይወት ታምሩ የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ታለንት ልማት ኢንስቲትዩት በጠንካራ ሕጋዊና ተቋማዊ መሠረት ተደራጅቶ ወደ አገልግሎት እንዲገባ ስትራቴጂያዊ አቅጣጫ ሰጡ፡፡

የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስትር ክብርት ፍሬሕይወት ታምሩ ከልዑካን ቡድናቸው ጋር በቡራዩ የሚገኘውን የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ታለንት ልማት ኢንስቲትዩትን የጎበኙ ሲሆን፤ ማዕከሉ ከአራት ዓመታት በፊት ተመርቆ እስካሁን የታለመለትን አገልግሎት መጀመር ያልቻለበትን ተቋማዊ ክፍተቶችና ወቅታዊ ዝግጁነቱን በጥልቅ ገምግመዋል።

በተለይም ተቋሙን ወደ ሥራ ማስገባት ከሕንፃዎች ጥገናና ከመሣሪያዎች ማሟላት ባለፈ፤ ከመደበኛ ትምህርት ቤቶችና ዩኒቨርሲቲዎች የሚለይበትን ስትራቴጂያዊ ሚና በግልጽ በመለየት፣ ከመላው ሀገሪቱ በSTEM እና በቴክኖሎጂ ልዩ ተሰጥኦ ያላቸውን ወጣቶች በማብቃት ለኢትዮጵያ ዲጂታል ትራንስፎርሜሽን ተጨባጭ እሴት እንዲያበረክቱ ማስቻል እንዳለበት አስገንዝበዋል።

በተጨማሪም በአስቸኳይ ስቲሪንግ ኮሚቴ ተቋቁሞ የተቋሙን የሕግ፣ የአደረጃጀት፣ የመዋቅርና የበጀት ዝግጅት የማጠናቀቅ እንዲሁም የፋሲሊቲዎችና የንብረት ቆጠራ በማካሄድ ተቋሙ ወደ ሙሉ አገልግሎት እንዲገባ የሚያስችሉ ሥራዎች በትይዩ እንዲከናወኑ አቅጣጫ ሰጥተዋል፡፡

“ፈተናዎችን ተሻግረን ውጤት አስመዝግበናል፤ ቀጣዩ ትኩረታችን የዜጎችን የላቀ ተጠቃሚነት ማረጋገጥ ነው”አቶ ኦርዲን በድሪየሀረሪ ክልል ርዕሰ መስተዳድር
30/10/2026

“ፈተናዎችን ተሻግረን ውጤት አስመዝግበናል፤ ቀጣዩ ትኩረታችን የዜጎችን የላቀ ተጠቃሚነት ማረጋገጥ ነው”

አቶ ኦርዲን በድሪ
የሀረሪ ክልል ርዕሰ መስተዳድር

21ኛው ብሔር ብሔረሰቦች እና ህዝቦች ቀንን አስመልክቶ በሚደረጉ መድረኮች ዙሪያ የአሰልጣኞች ስልጠና መድረክ ተካሄደ።***የብሔር  ብሔረሠቦች እና ህዝቦች ጋር ተያይዞ ከየ ተቋሙ ለተወጣጡ ተ...
29/10/2026

21ኛው ብሔር ብሔረሰቦች እና ህዝቦች ቀንን አስመልክቶ በሚደረጉ መድረኮች ዙሪያ የአሰልጣኞች ስልጠና መድረክ ተካሄደ።
***

የብሔር ብሔረሠቦች እና ህዝቦች ጋር ተያይዞ ከየ ተቋሙ ለተወጣጡ ተሳታፊዎች የአሰልጠኞች ስልጠና መድረክ በፐብሊክ ሰርቪስ ቢሮ አዘጋጅነት ተካሄዷል።

የስልጠና መድረኩ ብዝሃነትን መሰረት ያደረጉ የውይይት መድረኮች እና የህዝቦች አንድነት እንድጠነክር ብዝሃነት ዙሪያ ለህብረሰቡ ግንዛቤ ለማስጨበጥ ያለመ ነው ተብሏል።

በመድረኩ ላይ ንግግር ያረጉት የፐብሊክ ሰርቪስ እና የሰዉ ሀብት ልማት ቢሮ ምክትል ሀላፊ ዶክተር ከማል አብዱልባሲጥ የብሔር ብሔረሰቦች እና ህዝቦች ቀን ህብረተሰባዊ ፌዴራሊዝምን ለማጠናከር እና የልማት ስራዎችን በጋራ ለማፋጠን ትልቅ መድረክ መሆኑ ገልጿል።

​የብሔር ብሔረሰቦች እና ህዝቦች ቀን ሲከበር ሀገራችን የምትከተለውን ህብረ-ብሔራዊ የፌዴራል ስርአት ለማስረፅ ሰፊ የአስተምህሮ መድረኮችን ማስፋት እና የእያንዳንዱን ማህበረሰብ ግንዛቤ ማሳደግ ወሳኝ ሚና እንዳለዉ ጠቁመዋል።

​በተፈጥሮ የተጎናጸፍነውን ብዝሃነት እንደ መልካም አጋጣሚ በመውሰድ፣ የጋራ ውበታችን እና የዕድገታችን መሰረት ማድረጉ ተገቢ መሆኑን የጠቆሙት ዶክተር ከማል
አሁን ላይ የተጀመሩትን የልማት ስራዎች ላይ በጋራ በመሳተፍ እና በመደገፍ ለሀገራዊ ብልጽግና ማብቃት አሁን ላይ የሚጠየቀው ታሪካዊ ሃላፊነት መሆኑንም አስገንዝበዋል።

በመድረኩ ላይ የብዝሃነት አስተዳደር እና ጠንካራ የፌዴራል ግንባታ ዙሪያ ያተኮረ መነሻ ፅሁፍ ቀርቦ በተሳታፊዎች ሰፊ ውይይት ተደርጎበታል።

Harari Mass Media Agency
19/02/19

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) የኢትዮጵያን የአርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ራዕይ በሶስተኛው ሩሲያ–አፍሪካ ጉባኤ አቀረቡየኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በሶስተኛው የሩ...
29/10/2026

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) የኢትዮጵያን የአርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ራዕይ በሶስተኛው ሩሲያ–አፍሪካ ጉባኤ አቀረቡ

የኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በሶስተኛው የሩሲያ–አፍሪካ ጉባኤ ባደረጉት ንግግር ኢትዮጵያ በሰው ሠራሽ አስተውሎት ዘርፍ ያላትን ራዕይ በማስረዳት ከሩሲያ ዩኒቨርሲቲዎችና የምርምር ተቋማት ጋር በትምህርትና በምርምር መስኮች የጋራ ትብብር እንዲደረግ ጥሪ አቅርበዋል።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ በንግግራቸው፤ የቴክኖሎጂ ትብብር መሠረተ ልማቶችን ከመገንባት ባለፈ፣ እነዚህን ሥርዓቶች ማስተዳደር፣ ማስኬድና መቆጣጠር የሚችሉ የሀገር ውስጥ ባለሙያዎችን ማፍራት እንዳለበት አስገንዝበዋል።

በዘመናችን የእውቀትና የቴክኖሎጂ አቅም ማለት በከፍተኛ ደረጃ ከሰው ሠራሽ አስተውሎት ጋር የተያያዘ መሆኑን ያነሱት ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) የኤአይ ቴክኖሎጂዎች አሁን ባለው መንገድ መገንባታቸው የትኞቹ ቋንቋዎች በቴክኖሎጂው እንደሚወከሉና የማን ማንነትና ተሞክሮ እንደሚካተት እንደሚወስን ገልጸዋል።

“አንድ አፍሪካዊ ተመራማሪ በሕዝባችን ቋንቋ የኤአይ መፍትሔዎችን መፍጠር መቻል አለበት። ተቋሞቻችንም እነዚህ መፍትሄዎች የእኛን መረጃ እንዴት እንደሚጠቀሙ መወሰን አለባቸው” በማለት የአፍሪካ ቋንቋዎችና የመረጃ ባለቤትነት ያላቸውን ወሳኝ ሚና አጉልተዋል።

በተጨማሪም ኢትዮጵያ የመደመር የሰው ሠራሽ አስተውሎት ዩኒቨርሲቲ (Medemer University of Artificial Intelligence) እያቋቋመች መሆኑን ያስታወቁት ጠቅላይ ሚኒስትሩ፤ የሩሲያ ዩኒቨርሲቲዎችና ተቋማት በማስተማርና በምርምር ከኢትዮጵያ ጋር እንዲሠሩ ጋብዘዋል።

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ፈጠራና ምርምር በላቦራቶሪዎች ውስጥ ብቻ ተወስነው መቅረት እንደሌለባቸው፣ ወደ ምርትና ንግድ ተግባራዊ ሥራዎች መሸጋገር እንዳለባቸው አስገንዝበዋል።

29/10/2026

"በሀረሪ መሶብ አንድ ማዕከል ፈጣን እና ቀልጣፋ አገልግሎት እያገኘን ነው"- ተገልጋዮች

29/10/2026

Address

Harar

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Harari Regional State Innovation and Technology Agency posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Shortcuts

Share