Siz Town administration Attorney Office የሲዝ ከተማ አስተዳደር ዐቃቤ ሕግ ጽህፈት ቤት

  • Home
  • Ethiopia
  • Mizan Teferi
  • Siz Town administration Attorney Office የሲዝ ከተማ አስተዳደር ዐቃቤ ሕግ ጽህፈት ቤት

Siz Town administration Attorney Office የሲዝ ከተማ አስተዳደር ዐቃቤ ሕግ ጽህፈት ቤት ህግን አለማወቅ ይቅርታ ሊያስገኝ አይችልም!!!

13/01/2023

ውክልና

ሰዎች በተለያዩ ምክንያቶች ጉዳዮቻቸውን ራሳቸው መፈፀም የማይችሉባቸው ሁኔታዎች ሊገጥሟቸው ይችላል፡፡ ለዚህ መፍትሄ ሆኖ በማገልገል ላይ ያለው ውክልና ነው፡፡ ሆኖም ውክልና በዘፈቀደ የሚደረግ ሳይሆን በህግ በተቀመጠው ሥርአት መሰረት የሚፈፀም ነው፡፡ በዚህ ፅሁፍ ስለ ውክልና ምንነት፣ ስለውክልና አይነቶች፣ ስለውክልና ጠቀሜታ እና ውክልና ቀሪ ስለሚሆንባቸው ሁኔታዎች በአጭሩ እንዳስሳለን፡፡

የውክልና ምንነት

የፍትሐብሔር ህጉ አንቀጽ 2199 መሰረት ውክልና ማለት ተወካይ የተባለው ሰው ወካይ ለተባለው ሰው እንደርሱ በመሆን አንድ ወይም ብዙ ህጋዊ ስራዎችን በወካዩ ስም ለማከናወን ግዴታ ሚገባበት ውል ነው፡፡ በዚህም ተወካዩ ልክ እንደወካዩ በመሆን የወካዩን ሥራዎች በወካዩ ስም ለማከናወን የሚደረግ ውል ነው፡፡
ውክልና ከልዩ የውል ህጎች ውስጥ አንዱ እንደ መሆኑ መጠን አንድ ህጋዊ ውል ሊያሟላቸው ያሚገባውን በፍትሐብሔር ህጉ በአንቀፅ 1678 ስር የተቀመጡትን መስፈርቶች ሊያሟላ ይገባል፡፡ ይኸውም፡-

 ውል ለመዋዋል ችሎታ ያለው ሰው መሆን
 ጉድለት የሌለው ፈቃድ ወይም ስምምነት መኖር
 በቂ የሆነ እርግጠኝነት ያለው የሚቻል እና ህጋዊ የሆነ ጉዳይ መሆን
 የውል አፈፃፀም ፎርም በህግ የታዘዘ ሆኖ እንደ ትዛዙ ባይፈፀም ፈራሽነት የሚያስከትል ሲሆን ህግ በሚያዘው ልዩ ፎርም መሆን ናቸው፡፡

የፍትሐብሔር ህጉ አንቀጽ 2200 ወካይ ለተወካይ የውከልና ስልጣኑን በቃል ወይም በዝምታ ሊሰጥ የሚችል ሲሆን ህጉ የውከልና ስልጣኑ በተለያየ ፎርም መሰጠት አለበት በማለት የሚያዝ ከሆነ ግን ይህ መሟላት ይኖርበታል፡፡

የውክልና አይነቶች

በአጠቃላይ ሁለት አይነት የውክልና ስልጣን ሲኖር ይህም ጠቅላላ እና ልዩ ውክልና በመባል ይታወቃሉ::

1ኛ.ጠቅላላ ውከልና

ይህ ውክልና በጠቅላላ አነጋገር የሚደረግ የውክልና አይነት ነው፡፡ ጠቅላላ ውክልና ተወካይ የአስተዳደር ስራዎችን ብቻ ለመስራት የሚያስችለው የውክልና አይነት ነው፡፡ የፍትሐብሔር ህጉ አንቀፅ 2204 የአስተዳደር ስራዎች የሚባሉት ምን ምን አይነት ስራዎች እንደ ሆኑ በዝርዝር ያስቀመጠ ሲሆን እነዚህም፡-

• የወካዩን ሀብት ማስቀመጥ፣ መጠበቅ
• ከ3 አመት ለማያልፍ ዘመን ማከራየት
• በብድር የተሰጠውን ሀብት መሰብሰብ
• ከሀብቱ የሚገኘውን ገቢ ተቀብሎ ማስቀመጥ
• ለተከፈለ እዳ ደረሰኝ መስጠት
• ሰብሎችን መሸጥ
• ለሽያጭ የተመደቡ የንግድ እቃዎችን ወይም ይበላሻሉ ተብለው የሚታሰቡ ነገሮችን መሽጥ የአስተዳደር ስራዎች ናቸው፡፡

2ኛ ልዩ ውክልና

ይህ ውክልና ወካይ ለተወካይ ከአስተዳደር ስራዎች ውጪ ተወካይ የተለየ ተግባር እንዲፈፅምለት በመግለፅ የሚሰጠው የውክልና አይነት ሲሆን ይህም ልዩ ውክልና የተሰጠው ሰው፡-

• የማይንቀሳቀሱ ንብረቶችን መሸጥ
• አስይዞ መበደር
• ካፒታሎችን ኢንቬስት የማድረግ አክሲዮኖችን የመግዛት የመሸጥ በማሕበር የመግባት
• ስጦታን ማድረግ
• በአንዳንድ ጉዳይ ፍ/ቤት ቀርቦ መከራከር የመሳሰሉ ተግባራትን ለመፈፀም የሚያስችለው የውከልና አይነት ነው፡፡

የወካይ እና የተወካይ ግዴታዎች

የፍትሐብሔር ህጉ በቁጥር 2208 እና ተከታዮቹ መሰረት ተወካይ በርካታ ግዴታዎች አሉበት፡፡ በዋናነት ተወካይ ለወካይ በሚሰራበት ወቅት ጥብቅ የሆነ ቅን ልቦና ሊኖረው እና በውክልና በተሰጠው አደራ ላይ ልክ አንድ የቤተሰብ አባት እንደሚያደርገው ሁሉ በትጋትና በጥንቃቄ መከወን ይጠበቅበታል፡፡ በዚህም ተወካዩ በሚሰራበት ወቅት ለወካዩ ጥቅም ማሰብ እና ወካይ በሰጠው የስልጣን ወሰን ውስጥ ብቻ ተግባሩን ማከናወን የሚጠበቅበት ሲሆን ወካዩ ሳያውቅ በወኪልነቱ ምክንያት ከሚሰራው ስራ አንዳችም ጥቅም መውሰድ የለበትም፡፡ በተጨማሪም ተወካዩ ወካዩ በጠየቀው ጊዜ ሁሉ የስራውን አካሄድ፣ መግለጫ እና ሂሳብ በየጊዜው ማቅረብ ይጠበቅበታል፡፡ በውክልናው ምክንያት የሚያገኛቸውን መረጃዎችም የወካዩን ጥቅም በሚጎዳ መልኩ መጠቀም የለበትም፡፡

በሌላ በኩል ወካዩም ግዴታዎች እንዳሉበት ከፍትሐብሔር ህግ ቁጥር 2219 እና ተከታዮቹ መረዳት ይቻላል፡፡ በዋናነትም ወካዩ ለተወካዩ የድካም ዋጋ ለመክፈል ውል ገብቶ ከሆነ ወይም ተወካዩ በውክልና የፈፀመው በሙያ ውስጥ በተመለከተ የግል ሥራው ከሆነ ወካዩ ለተወካዩ የድካም ዋጋ መክፈል ይጠበቅበታል፡፡ በተጨማሪም ተወካዩ የውክልናው ሥራ ማስኬጃ ወጪ መሸፈን የሚጠበቅበት ሲሆን ተወካዩ ለወካዩ ጥቅምና ለውክልና ስራው መልካም አካሄድ ሲል በወኪልነቱ ከሚገባው የውል ግዴታ ነፃ ሊያወጣው ይገባል፡፡

የውክልና ጥቅም

ውክልና ለወካይ የተለያዩ ጥቅሞችን የሚሰጥ ነው፡፡ ከነዚህ ጥቅሞች መካከል ወካይ በጊዜ እና በቦታ ሳይገደብ በአንድ ጊዜ የተለያዩ ተግባራትን እንዲያከናውን፣ የእውቀት እና ልምድ ማነስ ሳያግደው የተለየ እውቀት እና ልምድ የሚያስፈልገው ስራ በወኪሉ በኩል ማከናወን መቻል፣ በህግ መሰረት ህጋዊ ሰውነት ያገኙ ተቋማት ምንም እንኳን የህጋዊ ሰውነት ቢኖራቸውም እንደ ተፈጥሯዊ ሰው የተለያዩ ተግባራትን ማከናወን የማይችሉ በመሆናቸው በውክልና ስልጣን በተሰጠው ተፈጥሮዊ ሰው ምክንያት ተግባራቸውን በውክልና ማከናወን እንዲችሉ ማድረጉ ይጠቀሳሉ፡፡ በተጨማሪም እድሜቸው ለአካለመጠን ያልደረሱ እና ችሎታ ያጡ ሰዎች ህግ የሚስጣቸው ተወካዮች ጥቅማቸውን እንዲያስከብሩ ማስቻል ውክልና ከሚሰጣቸው ጥቅሞች ውስጥ የሚካተት ነው፡፡

ስለውክልና መቅረት

ውክልና ከተሰጠ በኋላ ለዘላለም ፀንቶ ይኖራል ማለት ሳይሆን በተለያዩ ምክንያቶች ቀሪ ሊሆንባቸው የሚያስችሉ ሁኔታዎች በህጉ ላይ ተዘርዝረው ይገኛሉ፡፡ ከነዚህም ሁኔታዎች መካከል ውክልናን መሻር፣ የውክልና ስልጣንን መተው፣ የወካዩ ወይም የተወካዩ መሞት፣ የወካዩ ወይም የተወካዩ ለመስራት ችሎታ ማጣት ስልጣንን ቀሪ ከሚያረጉ ሁኔታዎች መካካል ናቸው፡፡

ውክልናን መሻር

ወካይ አስፈላጊ መስሎ ሲታየው የሰጠውን የውክልና ስልጣን መሻር እና ለተወካይ የሰጠውን የውክልና ውል እንዲመልስለት ሊያስገድደው ይችላል፡፡ እንደዚህ አይነት ሁኔታዎች ሲፈጠሩ ወካይ ተወካይ በእርሱ እና በ3ኛ ወገኖች ላይ ጉዳት እንዳያደርስ የሰጠውን ውክልና በማንሳት ለሚመለከታቸው አካለት እና በውክልናው ምክንያት ሊጎዱ የሚችሉ ወገኖችን ስለውክልናው መሻር ማሳወቅ ይኖርበታል፡፡ የተሰጠው የውክልና ጊዜ ከማለቁ በፊት የውክልናው መሻር በተወካይ ላይ ኪሳራ አድርሶበት እንደሆነ ወካይ ተወካይ ላይ በውሉ መሻር ምክንያት ለደረሰበት ኪሳራ ካሳ የመክፈል አላፊነት አለበት፡፡ ብዙ ወካዮች ለጋራ ጉዳያቸው የወከሉትን ተወካይ በቂ የሆነ ትክክለኛ ምክንያት ከሌለ በቀር ወካዮቹ በመላ ሳይስማሙበት አንዱ ወካይ ብቻውን ተወካዩን ሊሽረው አይችልም፡፡

የወኪል የውክልና ስልጣኑን መተው

ተወካዩ የውክልናውን ሥራ እንደሚተው ለወካዩ አስታውቆ ወክልናውን ለመተው የሚችል ሲሆን የውክልና ሥራውን መተው በወካዩ ላይ ጉዳት የሚያደርስ ከሆነ ተወካይ ለደረሰው ኪሳራ ካሳ የመክፈል ሀላፊነት አለበት፡፡ ሆኖም ተወካይ የውክልና ስራውን መቀጠሉ በእርሱ ላይ ከፍተኛ ጉዳት እና ኪሳራ የሚያስከትልበት መሆኑ ከታወቀ እና ሥራውንም ለመቀጠል በፍፁም የማያስችል ምክንያት መኖሩ ከተረጋገጠለት ማንኛውንም የጉዳት ኪሳራ እንዲከፍል አይገደድም፡፡ በሌላ በኩል ብዙ ተወካዮች አንድ አይነት ጉዳይ እንዲያከናውኑ ተወክለው እንደሆነ እና ከመካከላቸው አንድኛው የውክልና ስራውን ለመቀጠል በአንድ ምክንያት ያልቻለ እንደሆነና የውክልና ስራውን ካቋረጠ ተቃራኒ ስምምነት ከሌለ በስተቀር የአንዱ መቋረጥ የሌሎቹንም ተወካዮች የውክልና ስልጣን የሚያቋርጥ ይሆናል፡፡

ማጠቃለያ

በአጠቃልይ ውክልና ጊዜን፣ ገንዘብን እና አቅምን በመቆጣብ በዋናነት ወካዩን የሚጠቅም በመሆኑ የታለመለትን አገልግሎት እንዲሰጥ ሁሉም ወገኖች የውክልና ስምምነት በህጉ ላይ የተቀመጡለትን መስፈርቶች እና ሁኔታዎችን ማወቅ እና ማሟላት አለባቸው፡፡

በንቃተ ህግ ትምህርትና ስልጠና ዳይሬክቶሬት የተዘጋጀ

የሲዝ ከተማ አስተዳደር ፍትህ ጽ/ቤት ለሲዝ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ሴትተማሪዎች የአቅም ውስንነትን ለማጎልበት ያለመ ስልጠና ተሰጠ።ጥር 04/ 2015 ዓ.ምሲዝየሴት ተማሪዎችን አቅም ለማ...
13/01/2023

የሲዝ ከተማ አስተዳደር ፍትህ ጽ/ቤት ለሲዝ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ሴት
ተማሪዎች የአቅም ውስንነትን ለማጎልበት ያለመ ስልጠና ተሰጠ።
ጥር 04/ 2015 ዓ.ም
ሲዝ
የሴት ተማሪዎችን አቅም ለማጎልበትና በማህበረሰቡ ዘንድ ያለባቸውን
የባህል፣የልምድና የሌሎች ተፈጥሯዊና ማህበራዊ ውስንነቶችን ለመቅረፍ
ያለመ የትምህርትና ስልጠ ለሴት ተማሪዎች ተሰጠ።
የሲዝ ከተማ አስተዳደር ፍትህ ተቋም ያዘጋጀውን የሴት ተማሪዎችን ሁለንተናዊ
ተሳትፎ ለማሳደግ የሚያስችል ስልጠና ለሲዝ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት
ለሴት ተማሪዎች ሰጥቷል ።
ስልጠናውን የሰጡት የሲዝ ከተማ አስተዳደር ፍትህ ጽ/ቤት የህግ ማርቀቅ
ማስረፅ ና ግንዛቤ መፍጠር የስራ ሂደት አቶ ናትናኤል መለሰ እንደተናገሩት
ስልጠናው በሴት ተማሪዎች ላይ የሚያጋጥሙ ችግሮችንና ያሉባቸውን ዘርፈ
ብዙ ችግሮች መሰረት በማድረግ በተሰራ የዳሰሳ ጥናት መነሻ በማድረግ
እንደሆነ ተናግረዋል።
እንደ ባለሙያው ገለፃ ስልጠናው የሴት ተማሪዎችን ሁሉን አቀፍ አቅም
በማጎልበት በሁሉም ደረጃ ብቁና ተወዳዳሪ የሆኑ ሴት ተማሪዎችን ለመፍጠር
ያለመ እንደሆነ ተናግረዋል።
የሴት ተማሪዎችን አቅም ማጎልበትና ያላቸውን ዕምቅ አቅም አውጥተው
እንዲጠቀሙ በማድረግ የሚደርስባቸውን ማህበራዊና ባህላዊ ተፅዕኖዎችን
በማለፍ ብቁ ና መልካም ተፅዕኖ ፈጣሪ የሆኑ ሴቶችን ለማፍራት ከተምህርት
ቤት ደረጃ ጀምሮ መከታተልና መደገፍ ያስፈልጋል ብለዋል።
የሲዝ ከተማ አስተዳደር ፍትህ /ቤት ባለሙያ ወ/ሮ መሠለች ካሳ እንደተናገሩ
በሴት ተማሪዎች የሚደርሰውን ማህበራዊ ፣ኢኮኖሚያዊ እና ሌሎች ባህላዊ
ተፅዕኖዎችን በመከላከል የሴቶችን አቅም በማጎልበት የማህበረሰቡን
የአመለካከት ችግር መቅረፍ ይገባል ብለዋል።
ሴቶችን ማብቃት የማህበረሰቡን ችግር ለማቃለል አይነተኛ መሳሪያ መሆኑን
ያነሱት የዓቃቢ ህግ ባለሙያዋ ለዚህ ደግሞ ትምህርት ቤቶች ያላቸው ድርሻ
ጉልህ እንደሆነ አስገንዝበዋል ።
በስልጠናው የተሳተፉ ሴት ተማሪዎች በበኩላቸው በተሰጠው ስልጠና
መደሰታቸውን ተናግረው ያሉባቸውን የአቅም ውስንነቶችን በመቅረፍ በተሻለ
ደረጃ ላይ ለማህበረሰቡ በሁሉም ዘርፍ ሞዴል ለመሆን እንዳነሳሳቸው
ምንጭ የሲዝ ከተማ አስተዳደር መንግስት ኮምንኬሽን ጉዳዮች ጽ/ቤት
ተናግረዋል።

28/12/2022
በ 2014 ዓ/ም የሲዝ ከተማ አስተዳደር የገቢወች ባለስልጣን ቅርንጫፍ ለገቢ አሰባሰብ ላደረግነው ላቅ ያለ አስተዋጾ ልዩ ተሸላሚ አድርጎ የእውቅና ሽልማት ስለሰጠን እያመሰገንን ለቀጣይም ለተ...
17/11/2022

በ 2014 ዓ/ም የሲዝ ከተማ አስተዳደር የገቢወች ባለስልጣን ቅርንጫፍ ለገቢ አሰባሰብ ላደረግነው ላቅ ያለ አስተዋጾ ልዩ ተሸላሚ አድርጎ የእውቅና ሽልማት ስለሰጠን እያመሰገንን ለቀጣይም ለተሻለ ስራ የሚያነሳሳን በመሆኑ ለተደረገልን የእውቅና ሽልማት እናመሰግናለን::

በቀን 23/02/2015 ዓ/ም በሲዝ ከተማ አስተዳደር 01 ቀበሌ ሾምስ መንደር በፍትህ አስተዳደር ላይ የሚፈፀሙ ወንጀሎች በሚል ርዕስ በሀሰት መክሰስ ወይም መወንጀል: ሀሰተኛ ምስክርነት: አ...
10/11/2022

በቀን 23/02/2015 ዓ/ም በሲዝ ከተማ አስተዳደር 01 ቀበሌ ሾምስ መንደር በፍትህ አስተዳደር ላይ የሚፈፀሙ ወንጀሎች በሚል ርዕስ በሀሰት መክሰስ ወይም መወንጀል: ሀሰተኛ ምስክርነት: አስተያየት ወይም ትርጉም መስጠት እና በሙግት ጊዜ ማጭበርበር ምንነት እና ያላቸውን የህግ ተጠያቂነት የንቃተ ህግ ወይም የህግ ግንዛቤ በአቶ መሀመድ አብደላ የሲዝ አስተዳደር ፍትህ ጽህፈት ቤት ሀላፊ አማካኝነት ተሰጥቶል::

በዛሬው እለት በቀን 20/02/2015 ዓ.ም በሲዝ ከተማ አስተዳደር 01 ቀበሌ የጦር መሳርያ አስተዳደር እና ቁጥጥር አዋጅ ቁጥር 1177/2012 በማስመልከት የጦር መሳርያ እንዴት እና ከየት...
07/11/2022

በዛሬው እለት በቀን 20/02/2015 ዓ.ም በሲዝ ከተማ አስተዳደር 01 ቀበሌ የጦር መሳርያ አስተዳደር እና ቁጥጥር አዋጅ ቁጥር 1177/2012 በማስመልከት የጦር መሳርያ እንዴት እና ከየት ፍቃድ እንደሚገኝ እና የጦር መሳርያ ያለ ፍቃድ ይዞ መገኘት የሚያስከትለውን የህግ ተጠያቂነት ዙሪያ የንቃተ ሀግ ወይም የህግ ግንዛቤ በአቶ መሀመድ አብደላ የሲዝ ከተማ አስተዳደር ፍትህ ጽ/ቤት ኀላፊ አማካኝነት ትምህርት ተሰጥቶል::

በዛሬው እለት በሲዝ ከተማ አስተዳደር 01 ቀበሌ ሻፓ ቆጪ መንደር የጦር መሳርያ አስተዳደር እና ቁጥጥር አዋጅ ቁጥር 1177/2012 በማስመልከት የጦር መሳርያ እንዴት እና ከየት ፍቃድ እንደ...
01/09/2022

በዛሬው እለት በሲዝ ከተማ አስተዳደር 01 ቀበሌ ሻፓ ቆጪ መንደር የጦር መሳርያ አስተዳደር እና ቁጥጥር አዋጅ ቁጥር 1177/2012 በማስመልከት የጦር መሳርያ እንዴት እና ከየት ፍቃድ እንደሚገኝ እና የጦር መሳርያ ያለ ፍቃድ ይዞ መገኘት የሚያስከትለውን የህግ ተጠያቂነት በተጨማሪም በሀሰት መክሰስ ወይም መወንጀል እና ሀሰተኛ ምስክርነት ምንነት ላይ እና የህግ ተጠያቂነት የሚለው ላይ ትኩረት በማድረግ የንቃተ ሀግ ወይም የህግ ግንዛቤ በአቶ መሀመድ አብደላ የሲዝ ከተማ አስተዳደር ፍትህ ጽ/ቤት ሀላፊ አማካኝነት ትምህርት ተሰጥቶል::

በሲዝ ከተማ አስ/ር የሼይቤንች(የጎማጣ) 1ኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ከ5ተኛ-8ተኛ ክፍል ላሉ ተማሪዎች እና መምህራን ትምህርት ቤት ከእውቀት እና ክሕሎት መቅሰሚያ ከመሆኑም በላይ የስነምግባር ...
25/05/2022

በሲዝ ከተማ አስ/ር የሼይቤንች(የጎማጣ) 1ኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ከ5ተኛ-8ተኛ ክፍል ላሉ ተማሪዎች እና መምህራን ትምህርት ቤት ከእውቀት እና ክሕሎት መቅሰሚያ ከመሆኑም በላይ የስነምግባር ማዕከል ስለመሆኑ በስነ ምግባር የተነጸ ዜጋ ለነገዋ ኢትዮጵያ እንዲሁም ስለ ወንጀል አጠቃላይ የግንዛቤ ማስጨበጫ ትምህርት በሲዝ ከተማ አስ/ር ፍትሕ ጽ/ቤት የሕግ ጥናት ማርቀቅና ማስረጽ ግንዛቤ መፍጠር ዋና የስራ ሂደት በቀን 15/09/2014 ዓ.ም መሥጠት ተችሏል።

19/04/2022

ሰላም ጤና ይስጥልን የማህበራዊ ድረ ገፅ ተከታዮቻችን እንደምን አላችሁ! በዛሬዉ ፅሁፋችን ሰዎች ክርክርና ሙግት ሲገጥማቸው ጉዳዩ ወንጀል ይሁን ፍትሐ ብሔር ባለመለየት የወንጀል ጉዳይን በፍትሐ ብሔር ክርክር ለመፍታት የፍትሐ ብሔር ጉዳይን በወንጀል እንዲጣራ ጥያቄ ሲቀርብ ይስተዋላል፤ እንዲሁም በአስተዳደር ዘርፍ የሚታዩ ጉዳዮችን አንዳንዴ በፍትሐ ብሔር አልፎ አልፎ በወንጀል እንዲታይ አቤቱተታ ሲያቀርቡ ይስተዋላል።
 የፍትሐ ብሔር የህግ ዘርፍ ምንነት፡- ግለሰባዊ ግንኙነቶችን እና መብቶችን እንዲሁም ግዴታዎችን (private relationships, rights and obligations) የሚደነግግና የሚገዛ ሲሆን በዋናነት የንብረት፣ የውል፣ የቤተሰብና ውርስ ህግን እና ከውል ዉጭ ኃላፊነትን የሚመለከቱ ህጎችን አካቶ የያዘ የህግ ዘርፍ ነው፡፡ እነዚህ መብቶች ወይም ግንኙነቶች በአግባቡ እንዲከበሩ እንዲሁም ባለመከበራቸው ምክንያት ጉዳት የደረሰበት አካል ሲኖር መብቱን የሚጠይቅበትን ሥነ-ሥርዓት የሚደነግገው ህግም በዚሁ የህግ ዘርፍ ውስጥ የሚካተት ነው፡፡ በፍትሐ ብሔር ህግ መሰረት የሚፈጠሩ መብቶች ሲጣሱ ወይም ግዴታዎች ሳይከበሩ ሲቀሩ የሚከሰቱ ችግሮች እንደአጠቃላይ የማህበረሰብ ችግር/ጉዳት የሚታዩ ሳይሆኑ በቀጥታ ጉዳቱ የደረሰበት አካል ችግር እንደሆኑ ተደርገው ይወሰዳሉ፡፡ ስለሆነም እንዲህ ዓይነቱን ጥሰት ለመከላከልም ሆነ አስላጊውን ካሳ ለማግኘት የሚያስፈልጉ ህጋዊ እርምጃዎችን መውሰድ በዋናነት ጉዳቱ የደረሰበት አካል ኃላፊነት ነው፡፡
 የወንጀል ህግ ምንነት፡- በአጠቃላይ ማህበረሰብን ከተለያዩ ጉዳቶች ለመጠበቅ ሲባል የሚወጣና እንደወንጀል የሚቆጠሩ ድርጊቶች ወይም አለማድረጎችን የሚዘረዝርና ተፈጽመው ሲገኙ የሚያስከትሉትን ቅጣቶች የሚደነግግ ህግ ሲሆን በድርጊቶቹ መፈጸም ቀጥተኛ ተጎጅዉ አንድ ግለሰብ ቢሆንም እንኳን ጉዳቱ በማህበረሰብ ላይ እንደደረሰ ተደርጎ የሚቆጠር በመሆኑ ወንጀል የፈጸሙ ሰዎች እንዲቀጡ፤ ሌሎች ደግሞ ወንጀል እንዳይፈጽሙ ለማድረግ የሚያስችሉ ድንጋጌዎች እንዲኖረው ተደረጎ የሚወጣ ህግ ነው፡፡
 የአስተዳደር ህግ፡- ውልደትና እድገት ዋና መሰረቱ መንግስት (በተለይም የአስፈጻሚው አካል) በማህበረሰቡ ውስጥ የሚኖረው ማህበራዊ ኢኮኖሚያዊ እና ፖለቲካዊ ኃላፊነት እየጨመረ ከመምጣቱ ጋር ተያይዞ እየጨመረ የመጣው የመንግስት ስልጣን ነው፡፡ መንግስት ማህበራዊ ኃላፊነቱ በጨመረ ቁጥር ይህንኑ ኃላፊነቱን በሚገባ እንዲወጣ የሚያስችለው ስልጣን ሊኖረው እንደሚገባ የታመነ ቢሆንም ነገር ግን መንግስት ስልጣኑ እየጨመረ ሲሄድ የህግ የበላይነትና የግለሰቦች ህገ-መንግስታዊ መብቶች አደጋ ላይ እንዳይወድቁ መጠንቀቅ ያስፈልጋል፡፡ ስለሆነም የአስተዳደር ህግ የመንግስት አካላት በተለይ የአስተዳደር አካላት በህግ ተለይቶ ከተቀመጠላቸው የስልጣን ክልል እንዳያልፉና ኃላፊነታቸውን ፍትሐዊና አግባብ በሆነ መልኩ እንዲወጡ ቁጥጥር የሚያደርግ ህግ ነው፡፡
 የፍትሐ ብሔር ህግ ከወንጀል ህግ ጋር ስላለው ልዩነት፡-
በፍትሐ ብሔር ህግ የተደነገገ መብት በመጣሱ ምክንያት በሚመለከተው አካል ፊት ቀርቦ መብቱን መጠየቅ የሚችለው መብቴ ተጥሷል የሚለው ሰው ሲሆን የወንጀል ድርጊት በተፈጸመ ጊዜ ግን ኃላፊነት ወስዶ አጥፊዎች እንዲቀጡ የሚያደርገው መንግስት ነው፡፡
➾➾➾sources from FDRE Ministry of Justice/ የኢ.ፌ.ዲ.ሪ. ፍትሕ ሚኒስቴር ➾➾➾

ቀን 15/07/2014 ዓ.ም በሲዝ ከተማ አስ/ር ፍትሕ ጽ/ቤት አዘጋጅነት ከፍርድ ቤት፣ ከፖሊስ፣ ከኦሞ ማይክሮ ተቋም እንዲሁም ከኢንተርፕራይዝ ጽ/ቤት ጋር ከRevolving fund እዳ አመ...
24/03/2022

ቀን 15/07/2014 ዓ.ም
በሲዝ ከተማ አስ/ር ፍትሕ ጽ/ቤት አዘጋጅነት ከፍርድ ቤት፣ ከፖሊስ፣ ከኦሞ ማይክሮ ተቋም እንዲሁም ከኢንተርፕራይዝ ጽ/ቤት ጋር ከRevolving fund እዳ አመላለስ፣ ከብድር አጠቃላይ አመላለስ በአሰራር ጥራትና ግልጽነት እንዲሁም የጋራ በሆኑ ጉዳዮች ላይ ውይይት በማድረግ ላይ እንገኛለን።

በሼይ ቤንች መሰናዶ ትምህርት ቤት በትምህርት ቤት ማህበረሰብ ሥለ ሚዘወተረው የስነ መግባር ግድፈት፣ ደንብ ጥሰትና የወንጀል ተጠያቂነት ዙሪያ ባዘጋጀነው ማኑዋል ላይ የንቃተ ሕግ ትምህርት በ...
18/03/2022

በሼይ ቤንች መሰናዶ ትምህርት ቤት በትምህርት ቤት ማህበረሰብ ሥለ ሚዘወተረው የስነ መግባር ግድፈት፣ ደንብ ጥሰትና የወንጀል ተጠያቂነት ዙሪያ ባዘጋጀነው ማኑዋል ላይ የንቃተ ሕግ ትምህርት በሲዝ ከተማ አስ/ር ፍትሕ ጽ/ቤት የሕግ ጥናት ማርቀቅና ማስረጽ ግንዛቤ መፍጠር የስራ ሂደት አስተባባሪ ዐቃቤ ሕግ ናትናኤል መለሰ አማካኝነት ከሼይ ቤንች መሰናዶ ትምህርት ቤት ጋር በመተባበር ማስተማር እና ስኬታማ ውይይት ማድረግ ችለናል።
የሰነዱን ዝርዝር ሀሳብ ሌላ ጊዜ የምናቀርብ ይሆናል።

Address

Siz
Mizan Teferi

Telephone

+251910127280

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Siz Town administration Attorney Office የሲዝ ከተማ አስተዳደር ዐቃቤ ሕግ ጽህፈት ቤት posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Organization

Send a message to Siz Town administration Attorney Office የሲዝ ከተማ አስተዳደር ዐቃቤ ሕግ ጽህፈት ቤት:

Share