14/05/2026
https://www.facebook.com/share/p/1CozxQQRob/
በጽንፈኞች የሀሰት ፕሮፖጋንዳ የሚደፈርስ ሰላምም ሆነ የሚሸረሸር የህዝቦች አብሮነት የለም!- የሀረሪ ክልል የመንግስት ኮሙዩኒኬሽን ጉዳዮች ጽ/ቤት
ጽንፈኞች በሚነዙት የሀሰት ፕሮፖጋንዳ የሚደፈርስ ሰላምም ሆነ የሚሸረሸር የህዝቦች አብሮነት እንደማይኖር ሊገነዘቡት ይገባል ሲል የሀረሪ ክልል የመንግስት ኮሙዩኒኬሽን ጉዳዮች ጽ/ቤት ገለፀ።
የጽ/ቤቱ ኃላፊ አቶ ሔኖክ ሙሉነህ እንዳሉት የክልሉ መንግስት የህዝብን ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ በተሰሩ ስራዎች ፍህሃዊነትን ያረጋገጡ በርካታ ስኬቶች ተመዝግበዋል።
በተለይም በልማቱ የተገኙ ስኬቶች ህዝቡ ለዘመናት ሲያነሳቸው የቆዩ ጥያቄዎች መሆናቸውን ጠቅሰዋል።
ህዝቡም የክልሉ መንግስት እያስመዘገባቸው የሚገኙ ስኬቶች ራሱ እየመሰከረ ባለበት ወቅት አንዳንዳ ''እኛ እናውቅልሃለን'' የሚሉ ጽንፈኞች የሀሰት ፕሮፖጋንዳቸው በመንዛት ለማደናገር እየተውተረተሩ ይገኛሉ ብለዋል።
መቃወም እንጀራቸው ያደረጉ እነኚህ ጽንፈኞች የህዝብን ሳይሆን የራሳቸውን ጥቅም ለማስጠበቅ የሚፈልጉ አካላት መሆናቸው ህዝቡ በሚገባ እንደተገነዘበ ሊያውቁት ይገባል ሲሉ ተናግረዋል።
ከእነዚህ አካላት ምኞትም በተዋለዱና በተጋመዱ ህዝቦች መካከል ቅራኔ እንዲፈጠርና ሰላም እንዲደፈርስ በማድረግ አላማቸውን ማሳካት መሆኑ መረዳት አስፈላጊ ነው ብለዋል።
ስለሆነም ለህዝብ ጥቅም የቆሙ በማስመሰል በማህበራዊ ሚዲያ የተለያዩ የጥላቻ እና ከእውነት የራቁ መረጃዎችን እያሰራጩ የሚገኙ አካላትን አላማ መገንዘብ ለህግ እንዲቀርቡ የተለመደ ትብብሩን እንዲያደርግ ጠይቀዋል።