13/01/2026
የሀረሪ ክልል ዋና ኦዲተር መ/ቤት ከፌደራል ዋና ኦዲተር እና አዲስ አበባ ቤቶች አስተዳደር ኮርፖሬሽን ጋር የልምድ ልውውጥና የሥራ ዝግጅት አደረጉ
➖➖➖➖➖➖➖➖➖➖➖➖
የሀረሪ ክልል ዋና ኦዲተር መስሪያ ቤት የኦዲት አሠራሩን ለማዘመንና ጥራቱን ለማረጋገጥ የሚያስችሉ ከፌዴራል ዋና ኦዲተር እና ከአዲስ አበባ ቤቶች ኮርፖሬሽን የልምድ ልውውጥና የሥራ ዝግጅት መርሃ-ግብሮችን እያከናወነ ይገኛል።
የሀረሪ ክልል የተገዥነት ኦዲት (Compliance Audit) ዳይሬክተር እና ኦዲተሮች የፌደራል ዋና ኦዲተር ክብርት ወይዘሮ መሰረት ዳምጤ ጋር በአሠራር ዙሪያ ውይይት አድርገዋል።
በውይይቱም በክልሉ የተገዥነት ኦዲት ሥራን ለማስጀመር በሚያስችሉ ሁኔታዎች ላይ በዝርዝር መክረዋል። ለሥራው ስኬታማነት አጋዥ የሚሆኑ የተለያዩ መመሪያዎች (Manuals) እና የሥራ ማስፈጸሚያ ቅጾችንም ከፌደራል ዋና ኦዲተር መስሪያ ቤት የሀረሪ ክልል ዋና ኦዲተር ኦዲተሮች ተረክበዋል።
በተጨማሪ የሀረሪ ክልል ዋና ኦዲተር ተየገዢ ኦዲት ዳይሬክተር እና ኦዲተሮች አዲስ አበባ ቤቶች አስተዳደር ኮርፖሬሽን በመገኘት በተለይም በኮንስትራክሽን ግዢ ኦዲት ዙሪያ ያለውን አሠራር ተመልክቷል። በዚህም ዘርፍ ያለውን ምርጥ ተሞክሮ በመቅሰም በክልላችን ተግባራዊ ለማድረግ የሚያስችል ዝግጅት አድርጓል።
አሁን የተከናወኑ የልምድ ልውውጦች የክልላችንን የኦዲት አሠራር በዕውቀትና በቴክኖሎጂ በመደገፍ የመንግሥትና የሕዝብ ሀብት በአግባቡ ጥቅም ላይ መዋሉን ለማረጋገጥ ትልቅ አቅም የሚፈጥር ነው።
ጥር 5/2018