Habtamu Taye

Directions Contact the organization

Habtamu Taye Donate Blood save life! Pledge cornea, don't burry it; it will restore sight of person in darkness!

ክቡር ዶ/ር ደረጀ ዱጉማበሚኒስትር ማዓረግ የዲሞክራሲ ስርአት ግንባታ አስተባባሪ ሁነው በመሾምዎ እንኳን ደስ አለዎት::በአዲሱ የአመራር ጉዞዎ የተሟላ ስኬት እመኝልዎታለሁ!
09/10/2026

ክቡር ዶ/ር ደረጀ ዱጉማ
በሚኒስትር ማዓረግ የዲሞክራሲ ስርአት ግንባታ አስተባባሪ ሁነው በመሾምዎ እንኳን ደስ አለዎት::

በአዲሱ የአመራር ጉዞዎ የተሟላ ስኬት እመኝልዎታለሁ!

Congratulations on your reappointment, dear Excellence Dr. Mekdes! Wishing you continued success and impactful leadershi...
08/10/2026

Congratulations on your reappointment, dear Excellence Dr. Mekdes! Wishing you continued success and impactful leadership in advancing Ethiopia’s health sector. 🙏

07/10/2026
06/10/2026

05/10/2026

የ2019 በጀት አመት እቅዶች እና የትኩረት መስኮች የላቀ ተቋምን ለመፍጠር

_________________________________
ሰሚራ በርሀ

የኢትዮጵያ ደምና ህብረህዋስ ባንክ አገልግሎት ተቋሙ የ2018 ዓ.ም በጀት አመት እቅድን በመገምገም እና እርሱን መነሻ በማድረግ የ2019 በጀት ዓመት ዕቅድ እንዲሁም የሶስት አመት የዴቬሎፕመንት እና የኢንቨስትመንት ፕላን አውጥቷል። አገልግሎቱ በሚሰራቸው ስራዎች የታዩ መሻሻሎችን እና አዳዲስ የሚሰጠውን አገልግሎት ተደራሽነት ለማላቅ የተለያዩ ስራዎችን ለመስራት እንዲሁ አቅዷል። በመሆኑም በኢትዮጵያ ደምና ህብረህዋስ አገልግሎት ምክትል ዋና ዳይሬክተር ከሆኑት አቶ ሀብታሙ ታዬ ጋር የሚከተለውን ቆይታ አድርገናል።

አገልግሎቱ ከሚሰራው የደም ማሰባሰብ ስራ እድገት እያሳየ መምጣቱን አቶ ሀብታሙ ይገልጻሉ። በመሆኑም ባለፈው በጀት ዓመት መሰብሰብ የተቻለው ወደ 476,000 ዩኒት የሚጠጋ ደም መሆኑን ያስታወሱት አቶ ሀብታሙ ፤ በ2019 ዓ.ም ከዚህ ከፍ ባለ መልኩ በዚህ በጀት ዓመት ወደ 605 ሺህ ዩኒት ደም ለመሰብሰብ መታቀዱን ይገልጻሉ። ከዚህም ጋር ተያይዞ የደም ልገሳ ስራ ደም ማሰባሰብ ብቻም ሳይሆን ደሙ የሚያልፍበትን የምርመራ ስርዓት ፣ ደህንነቱና ጥራቱ ተጠብቆ ለህክምና ተቋማት እንዲሄድ እና ለታካሚዎች ተደራሽ እንዲሆን ታሳቢ ተደርጎ የታቀደ ነው።

የኢትዮጵያ ደምና ህብረህዋስ አገልግሎት ከደም ልገሳ ባሻገር በሚሰራው የዓይን ብሌንን ልገሳ በተመለከተ አቶ ሀብታሙ ባለፈው በጀት አመት 576 የሚጠጋ የዓይን ብሌን ማንሳት መቻሉን ይጠቅሳሉ። ስለዚህም ከባለፈው በጀት አመት ልምድ በመነሳት እና ካለው ፍላጎት አኳያ ወደ 700 የሚጠጋ የዓይን ብሌኖችን በ2019 ዓ.ም ለመሰብሰብ እና ለታካሚዎች ተደራሽ ለማድረግ ግብ አስቀምጧል። ከዋናው ማዕከል የዐይን ባንክ ባለፈ የጅማ የዐይን ባንክ መገንባት የተቻለበት መሆኑን አስታውሰው ግቡን ለማሳከት እንደሚሰራ ገልጸዋል።

አገልግሎቱ አፋጣኝ ደም ለሚያስፈልጋቸው ታካሚዎች ደም ተደራሽ ከማድረግ እና ደም ለጋሾች እንዲለግሱ ከማድረግ ባለፈ ጥራት ባለው መልኩ መሰብሰብ ላይ የአሰራር ስርኣት በመዘርጋት ላይ እንደሚገኝም አቶ ሀብታሙ ይገልጻሉ። ለዚህም የደም ለጋሾችን ቁጥር ለመጨመር ፣ የግንዛቤ ማስጨበጥ ስራዎችን መስራት ከዚህ ቀደም የነበሩ ስትራቴጂዎችን ማስቀጠል እና አዳዲስ ንቅናቄዎችን እንደሚፈጥር ይገልጻሉ።

ትምህርት ቤቶች አገልግሎቱ ከዚህ ቀደም በተደራጀ መንገድ ደም የሚሰበስብባቸው ቦታዎች መሆናቸውን ጠቅሰው ከትምህርት ቤቶች ጋር እንዲሁም ከመምህራን ጋር ፎረሞችን በማዘጋጀት ግንዛቤ በመፍጠር ትምህርት ቤቶች ደም ልገሳን በባለቤትነት ማስተባበር እንዲችሉ የማድረግ ሥራዎችን አብረው እንደሚሰሩ ጠቁመዋል።

የእምነት ተቋማት ሌላው የደም ልገሳን በስፋት ከሚሰራባቸው ቦታዎች እንደሆኑ የጠቆሙት አቶ ሀብታሙ ከተቋማቱ ጋር በቅርበት የሚሰሩ ሲሆን ፤ በቋሚነት የሚያስተባብሩ እንዳሉም ይገልጻሉ። በዚህም በሰንበት ትምህርት ቤቶች ፣ በመስጊዶች እና በፕሮቴስታንት ቤተክርስትያኖች በማህበር በየሦስት ወሩ ደም የሚለግሱ እምነት ተቋማት ጋር የሚሰራበትን መንገድ አገልግሎቱ እንደሚያመቻች አክለዋል።

የደም ባንኩ በጋራ ከወጣቶች እና የደም ለጋሽ ወጣት ማህበራት ጋር እንዲሁ አብሮ እንደሚሰራ ምክትል ዋና ዳሬክተሩ ይገልጻሉ። በበጎፍቃደኝነት የተደራጁ ብሄራዊ ደምለጋሾች ማህበር እንዲሁም ሌሎች ክበቦች ጋር በየሶስት ወሩ በሚደረጉ የደም ልገሳ ንቅናቄዎች እና መርሀ ግብሮች ጋር በቅርበት አብሮ እንደሚሰራ ገልጸዋል።

የደም ልገሳ ግንዛቤ አሁን ላይ ጥሩ የሚባል ደረጃ ላይ ያለ መሆኑን የገለጹት ምክትል ዋና ዳይሬክተሩ ካለው የህዝብ ቁጥር አንጻር በትኩረት ሊሰራበት የሚገባ መሆኑን በመጥቀስ ከተለያዩ የመገናኛ ብዙሀን ጋር በቅርበት በመስራት እንዲሁም በማህበራዊ ሚዲያ የደም ልገሳን ግንዛቤ የመፍጠር ሥራን እንደሚሰራ ገልጸዋል።

ማዕከሉ የደም ልገሳ ስርዓትን በማሻሻል ረገድ ዲጂታል ሲስተም ይፋ መደረጉን አስታውሰው “አዳኝ” የሞባይል መተግበርያ ለስማርት ስልክ ተጠቃሚዎች በሙሉ ዝግጁ መሆኑን ጠቅሰው በጎፍቃደኞች ደም የሚለግሱበትን ጊዜ ተከታትለው በአቅራቢቸው ወደሚገኝ ማዕከል ሄደው መለገስ የሚችሉበትን ስርዓት ከመፍጠር አልፎ ደም ለጋሾች ግንዛቤ ማግኘት እንዲችሉ መድረክ የፈጠረ መሆኑን ጠቁመዋል። የደም ማሰባሰብ ሥርዓቱ ቋሚ በሆኑ ቦታዎች ማዕከሉ ዓመቱን ሙሉ ባለው ተንቀሳቃሽ ቡድን በአዲስ አበባ በሁሉም ክፍለ ከተሞች ሁሉንም ቀን የሚሰበስብበት ሁኔታ መኖሩንም አቶ ሀብታሙ ይገልጻሉ።

የደም ልገሳ ስርዓትን በማሻሻል ረገድ ማዕከሉ አዲስ አፌሬሲስ ማሽን (Apheresis machine) ማስገባቱን ምክትል ዋና ዳይሬክተሩ ይገልጻሉ። ይህም ቀደም ሲል ከሚሰበሰበው የደም ማሰባሰብ ሥርዓት በተለየ መንገድ የተሻለ ደም ማግኘት የሚቻልበት እንዲሁም የተፈለገውን የደም ተዋጽኦ ብቻ ለይቶ ማውጣት የሚችል ማሽን መሆኑን ገልጸዋል።

እንደ አቶ ሀብታሙ ገለጻ ቀደም ሲል ከአንድ ደም ለጋሽ ከተገኘ 450 ሚሊ ሊትር ደም ፣ ከተሰበሰበ በኋላ የደም የቀይ ደም ሴል ፣ ፕላትሌት (platelet) እና ፕላዝማ (plasma) የሚባለውን የደም ተዋጽኦዎች በማሽን ይለይ ነበር። ይህ አፌሬሲስ ማሽን (Apheresis machine) ግን ለጋሹ ፕሌትሌት ብቻ መለገስ የሚፈልግ ከሆነ ሌሎችን ለይቶ የሚወስድ ሥርዓት በዋናው የደም ባንክ ስራ እንደሚጀምር ምክትል ዋና ዳይሬክተሩ አቶ ሀብታሙ ገልጸዋል። ወደ ስራ የሚገቡት ወደ ሰባት የሚጠጉ ማሽኖቹ ሲሆኑ ለባለሙያዎች ስልጠና መሰጠቱንም ጠቅሰዋል።

ይህም ማሽኑ ቀደም ሲል ከሚሰጠው ደም የተሻለ መጠን ያለው ደም ማግኘት የሚቻልበት እና የደም ተዋጽኦችን በበቂ ሁኔታ ለይቶ ማውጣት የሚያስችል እና የትኛው የደም ተዋጽኦ አይነት በልዩነት ለሚየስፈልጋቸው ዜጎች በቂውን የደም አይነት ለታካሚው መስጠት የሚያስችል መሆኑን አቶ ሀብታሙ ይገልጻሉ። ከዚህም ባለፈ ይህ የደም አሰባሰብ ስርዓት በተለይ ፕሌትሌት አካባቢ የሚስተዋለውን እጥረት ከመቅረፍ አንጻር አስተዋጽኦ እንዳለው ጠቅሰዋል። በይበልጥም በካንሰር ህክምና ላይ ለሚገኙ ታካሚዎች ቁጥር መጨመሩን የገለጹት አቶ ሀብታሙ ከጥቁር አንበሳ የካንሰር ህክምና ማዕከል በአንድ ቀን ብቻ 120 ፕሌትሌት ጥያቄ እንደሚቀርብ ጠቅሰዋል። በመንግስት እና በሌሎች የግል የካንሰር ህክምና ማዕከላት ያለውን ፍላጎት ለማሟላት አፌሬሲስ ማሽን ሥራ ውስጥ ሲገባ በቂ ፕላትሌት በማቅረብ ችግሩን በተወሰነ መልኩ ሊቀርፍ እንደሚችል አቶ ሀብታሙ ይገልጻሉ። አቶ ሀብታሙ አክለውም ፕሌትሌት በባህሪው በአጭር ጊዜ ብቻ የሚቀመጥ በመሆኑ ለጋሾች በየሁለት ሳምንቱ መለገስ እንዲችሉ በማድረግ ከዚህ ቀደም ከአንድ ደም የሚሰበሰበውን የፕላትሌት መጠን እጥረትን እንደሚቀርፍ ጠቅሰዋል።

አቶ ሀብታሙ እያደገ በመጣው በጎፍቃድኛ የደም ለጋሾች ቁጥር በመስከረም ወር ፣ በታህሳስ ወር መጨረሻ እና ጥር ወር እንዲሁም በአጽዋማት ወቅት በተለይም የዐብይ ጾም እና የረመዳን ጾም ደም ለመሰብሰብ አስቸጋሪ የሚሆንባቸው እና በቂ ደም ለጋሽ ለማግኘት አስቸጋሪ የሚሆንባቸው ወቅቶች እንደሆኑ ገልጸዋል። በእነዚህ ወቅቶች ልገሳው በደንብ ተጠናክሮ እንዲቀጥል ትኩረት በመስጠት ወደ ማዕከላቱ በማምራት ደም የመለገስ ባህል ሊኖር እንደሚገባ አሳስበዋል። ማዕከሉም ይህንን ችግር ለመቅረፍ በተለያዩ አደባባዮች ንቅናቄዎችን በማዘጋጀት የደም ልገሳን ግንዛቤ መፍጠር እና የማሰባሰብ ስራ እንደሚሰራ ገልጸዋል። ከዚህም ባለፈ በተለያዩ ማህበራዊ ገጾች ላይ ያሉ ተጽዕኖ ፈጣሪዎችን አምባሳደር በማድረግ ግንዛቤ የማስጨበጥ ስራዎችን እንደሚሰራ እና መልዕክቶችን ለማስተላለፍ በእቅድ መያዙን አቶ ሀብታሙ ገልጸዋል።

የዐይን ብሌን ልገሳን በተመለከተ በሀገር አቀፍ ደረጃ በዋና ማዕከሉ እና የጅማ የዐይን ባንክ ያለ መሆኑን የጠቀሱት አቶ ሀብታሙ ይህ በምስራቅ አፍሪካ ደረጃ ትልቅ የሚባል ተሞክሮ መሆኑን ገልጸዋል። የጅማ የዐይን ባንክ ወደ ስራ ከገባ በኋላ 31 የሚጠጉ የአይን ብሌኖችን ማንሳቱን ገልጸዋል። በተያዘው በጀት ዓመትም ባሉት ቴክኒሻኖች እና የዐይን ብሌን ቀዶ ጥገና ሀኪሞች አማካኝነት ሥራውን አጠናክሮ እንደሚቀጥል ገልጸዋል። ማዕከሉ ቀደም ሲል የሰበሰበውን ብሌን ለጅማ፣ ለሐዋሳ፣ ለጎንደር እና መቐለ ለሚገኘ ሆስፒታሎች እንደሚልክ ያስታወሱት አቶ ሀብታሙ በጅማ ይህ አገልግሎት በመጀመሩ አሁን ላይ ከአዲስ አበባ የሚሰበሰበውን የአይን ብሌን ለሐዋሳ፣ ለጎንደር፣ ለመቀሌ ሆስፒታል እንዲሁም አዲስ አበባ ለሚገኙ የመንግስትና የግል ቀዶ ጥገና ህክምና ለሚሰጡ የጤና ተቋማት እንደሚልክ ገልጸዋል።

በተጠናቀቀው በጀት አመት የክረምት ወራትም በሁለት ወር ውስጥ ወደ 75 የሚጠጋ የአይን ብሌኖችን ማንሳት የተቻለበት እና ለሕክምና ተቋማት በመስጠት ቀዶ ጥገና የተደረገ መሆኑን ገልጸዋል። ይህንንም አጠናክሮ በመቀጠል የተቀመጠውን ግብ ለማሳካት እንደሚሰራ ገልጸዋል።

ማዕከሉ ቃል የሚገቡ ሰዎችንም እንደዚሁ የሚመዘግቡ ሲሆን ፤ ይህንን ስራ በማስቀጠል ባለፈው አመት ወደ ሁለት ሺህ 500 የሚጠጉ ሰዎች ብሌናቸውን ለመለገስ ቃል የገቡበት በጀት ዓመት እንደነበር አስታውሰዋል። በዚህ በጀት ዓመትም ማዕከሉ ወደ አራት ሺህ የሚጠጉ ሰዎች ዐይን ብሌን ለመለገስ ቃል ይገባሉ የሚል ግብ ይዞ እየሰራ ይገኛል። በመሆኑም በሚያደርጋቸው የደም ልገሳ ንቅናቄዎች ጋር አስተሳስሮ የሚሄድ መሆኑን ገልጸዋል። ቀጣይ ህዳር ወርም የዐይን ብሌን ልገሳ ንቅናቄ ወቅት መሆኑን አቶ ሀብታሙ ገልጸዋል።


የዓይን ብሌን ህክምና የሚያስፈልጋቸው ታካሚዎች ቁጥር ከጊዜ ወደጊዜ እጨመረ መምጣቱን የገለጹት ምክትል ዋና ዳይሬክተሩ በዐይን ብሌን ጠባሳ ምክንያት የዐይን ብርሀናቸውን ያጡ ሰዎች ቁጥር ከፍተኛ መሆኑን እና በዚህም ምክንያት ረጅም ወረፋ በየሆስፒታሎቹ እንደሚገኝ ይገልጻሉ። ካለው ከፍተኛ ቁጥር አንጻርም ሁለት የዐይን ባንኮች ብቻ መኖር ፣ የዓይን ብሌን ቀዶ ጥገና ሀኪሞች ቁጥር አነስተኛ መሆን አገልግሎቱን ከሚፈልጉ ታካሚዎች ተደራሽ ለማድረግ አዳጋች እንደሚያደርገው ገልጸዋል። በመሆኑም ማዕከሉ በያዘው የሶስት አመት የዴቨሎፕመንት እቅድ ውስጥ በማስገባት እንደሚሰራበት ገልጸዋል።

በዘርፉ በአፍሪካ ደረጃ በቂ የሚባል ተሞክሮ እንደሌለ የገለጹት አቶ ሀብታሙ በኢትዮጵያ የሚገኘው የዐይን ባንክ በምስራቅ አፍሪካ ብቸኛው የዐይን ባንክ እና ለአፍሪካ ሞዴል የሚሆን አክሬዲትድ የዐይን ባንክ ይሆናል ተብሎ የሚጠበቅ የዓይን ባንክ መሆኑን ገልጸዋል። በማስፋፋት ረገድ ቀደም ሲል መንግስታዊ ባልሆነ ድርጅት የነበረ መሆኑን አስታውሰው ወደ ማእከሉ የመጣው በ2015 መሆኑን ገልጸዋል። በመሆኑም በሶስት አመት ውስጥ ሁለተኛ የዐይን ባንክ መገንባት በአፍሪካ ደረጃ ሲታይ ትልቅ ስኬት እንደሆነ ምክትል ዋና ዳይሬክተሩ ገልጸዋል።

በ2019 ዓ.ም ማዕከሉ ከያዛቸው እቅዶች ባሻገር ያለፈውን የሶስት ዓመት ኢንቨስትመንት ፕላን ገምግሞ የቀጣይ ሶስት አመት ኢንቨስትመንት ፕላንን አስቀምጧል። እንደ አቶ ሀብታሙ ገለጻ ያለፈው የሶስት አመት ኢንቨስትመንት ፕላን በደም ማሰባሰብ ስራ ከፍተኛ ቁጥር ደም መሰብሰብ የተቻለበት መሆኑን ገልጸዋል። በብሌን ማሰብሰብ ረገድም ከዚህ በፊት ቃል የሚገቡ ሰዎች ቁጥር በጣም አነስተኛ ሲሆን 100 የማይደርስበት ጊዜ እንደነበር አስታውሰዋል። በመሆኑም ወደዚህ ተቋም ከመጣ እና ስትራቴጂክ ፕላን ውስጥ ከገባ በኋላ ባለፈው በጀት ዓመት ወደ ሁለት ሺህ 500 አካባቢ ሰዎች ቃል እንዲገቡ የተደረገበት እና የዓይን ብሌን ለመስጠት ፈቃደኛ የሆኑ ፣ ግንዛቤ ያላቸውን ሰዎችን መፍጠር የተቻለበት ነው። የዓይን ብሌን ከማንሳት አንጻርም ከ200 በልጦ እንደማያውቅ የገለጹት አቶ ሀብታሙ ባለፈው በጀት ዓመት ወደ 576 አካባቢ የዓይን ብሌኖችን ማንሳት የተቻለበት በጀት ዓመት እንደነበር ገልጸዋል።

በሚቀጥለው ሶስት ዓመት ኢንቨስትመንት ፕላናን አሁን አገልግሎት እየሰጠ ካለው የደም እና የህብረህዋስ አገልግሎት በተጨማሪ በሚቀጥሉት ሶስት ዓመታት የአካል ክፍል አስተዳደር ሥራን ተቋሙ ወስዶ ይሠራል ተብሎ እንደሚጠበቅ ገልጸዋል። የህብረህዋስ አገልግሎትን በማስፋት ከዓይን ብሌን በተጨማሪ እንደ መቅኔ ወይም ስቲም ሴል ትራንስፕላንትን ከዚህ ዓመት ጀምሮ ወደ ሥራ ለማስገባት የኢንቨስትመንት ፕላን ውስጥ ትኩረት የተሰጠው መሆኑን እና ሌሎች ህብረህዋሶችንም እንደዚሁ አገልግሎቶችን እንደሚያስጀምር ጠቁመዋል።

የሚሰሩ ስራዎች ጥራታቸውን የጠበቁ እና ዓለም አቀፍ ስታንዳርድ ያላቸው እንዲሆኑ ተቋማትን አክሬዲት የማድረግ ሥራዎችን በመልካም አመራር ሥርዓት እንዲሠሩ ማድረግ እና የዓለም አቀፍ ስታንዳርድን ጠብቀው መሥራት እንዲችሉ እንደዚሁ ግብ አስቀምጦ እንደሚሰራበት ገልጸዋል።

የዲጂታል ሥርዓትን በማስፋፋት ረገድ ባለፈው በጀት አመት 35 የሚጠጉ የደም ባንኮች ወረቀት አልባ የሆነ ዲጂታል ሲስተም እንዲጠቀሙ ማድረግ መቻሉን የገለጹት አቶ ሀብታሙ ይህንን አጠናክሮ በመቀጠል ሁሉም ደም ባንኮች ተደራሽ ማድረግን አጠናክሮ እንደሚቀጥል ገልጸዋል። ከህክምና ተቋማት ጋር ያለውን ቅንጅት ማጠናከር ፣ የደም አጠቃቀምን ከህክምና ተቋም ጋር የተሻለ እንዲሆን የማድረግ ሥራዎችን እንደዚሁ ትኩረት ሰጥቶ የሚሰራበት መሆኑን ገልጸዋል። ማዕከሉ ተጠሪነቱ ለጤና ሚኒስቴር እንደመሆኑ በሚሰሩ የሪፎርም ስራዎች የተለያዩ አገልግሎቶችን ለመስጠት የሪፎርም ስራዎችን እንደሚሰራ እና በሜዲካል ቱሪዝም ዘርፍ እንዲሁ በከፍተኛ ትኩረት የሚሰራበት እንደሆነ ገልጸዋል።

አቶ ሀብታሙ እንደገለጹት ምንም እንኳን ማዕከሉ ሙሉ ለሙሉ በበጎፍቃደኛ ደም ለጋሾች የሚሰራ ቢሆንም በሀገር ደረጃ ካለው የህዝብ ቁጥር አንጻር በቂ የሚባል ቁጥር እንዳልሆነ ይገልጻሉ። አንድ በጎ ፍቃደኛ ደም ለጋሽ መደበኛ ደም ለጋሽ ፣ ሪፒት ደም ለጋሽ አልያም አንድ ጊዜ ብቻ የሚለግስ ተብሎ የሚለይ መሆኑን የገለጹት ምክትል ዋና ዳይሬክተሩ አብዛኛው አንድ ጊዜ ለግሶ ለሁለተኛ ጊዜ የለገሰ እና ሪፒት ዶነር የሚባለው መሆኑን ይገልጻሉ። በመሆኑም በየሶስት ወሩ በቋሚነት የሚለግሱ መደበኛ የደም ለጋሾች ቁጥር አነስተኛ የሚባል መሆኑን ጠቅሰዋል። በመሆኑም ከሚሰራው የግንዛቤ ማስጨበጫ ስራ ባሻገር አስቀድመው የጠቀሱት የአፍሬሲስ ማሽን የደሙን መጠን ብቻ ሳይሆን የደም ልገሳ ድግግሞሽንም የሚጨምር ይሆናል። “ ከዚህ ቀደም በየሶስት ወሩ ደም የሚለግስ ሰው ፤ ፕላዝማ መለገስ የሚፈልግ ከሆነ በየሁለት ሳምንቱ መስጠት ይችላል። ምክንያቱም ፕላዝማ በዓመት እስከ 24 ጊዜ መስጠት ይቻላል” በተጨማሪም ይላሉ ምክትል ዋና ዳይሬክተሩ ፕሌትሌትንም እንደዚያ መስጠት የሚቻል በመሆኑ የለጋሾችን ቁጥር መጨመር ያስችላል።

የደም ልገሳ ባህልን በማሳደግ ረገድ ሌሎች ሀገራት ተሞክሮ በሚጠቀሙት የዲጂታል ሥርዓት ያላቸውን የደም ክምችት በየጊዜው የሚያሳውቁ ሲሆን ፤ ዜጎችም ያለምንም ቅስቀሳ የሰው ህይወትን ለማዳን እንደሚረባረቡ ይገልጻሉ። በሀገራችንም ይህንን ባህል ለመፍጠር ተጠናክሮ ሊሰራ እንደሚገባ ገልጸዋል።

01/10/2026

በ2019 በጀት ዓመት 700 የሚጠጉ የዓይን ብሌኖችን ለመሰብሰብ ታቅዷል — አቶ ሀብታሙ ታዬ፣ የኢትዮጵያ ደምና ሕብረህዋስ ባንክ አገልግሎት ምክትል ዋና ዳይሬክተር፡፡
____________________
የኢትዮጵያ ደምና ሕብረህዋስ ባንክ አገልግሎት ባለፈው በጀት ዓመት ካከናወነው የዓይን ብሌን የማንሳት ሥራና ካለው ከፍተኛ ፍላጎት በመነሳት፣ በ2019 በጀት ዓመት 700 የሚጠጉ የዓይን ብሌኖችን ለመሰብሰብና ለታካሚዎች ተደራሽ ለማድረግ ግብ አስቀምጦ እየሰራ ይገኛል።

የአገልግሎቱ ምክትል ዋና ዳይሬክተር አቶ ሀብታሙ ታዬ ከኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት ጋር ባደረጉት ውይይት እንደገለጹት፤ በዘርፉ ያለው አፈፃፀም ባለፈው በጀት ዓመት 576 የሚጠጉ የዓይን ብሌኖችን ማንሳት የተቻለ ሲሆን፣በዘንድሮ በክረምቱ ሁለት ወራት ብቻ 75 ያህል የዓይን ብሌኖች ተሰብስበው ለሕክምና ተቋማት ቀዶ ጥገና ውለዋል።

በበጀት ዓመቱ ከአዲስ አበባ ዋና ማዕከል በተጨማሪ የጅማ የዓይን ባንክ በመገንባት ሥራ ማስጀመር ተችሏል። የጅማ የዓይን ባንክ ወደ ሥራ ከገባ ወዲህ 31 የዓይን ብሌኖችን ማንሳት ችሏል።

ቀደም ሲል ከአዲስ አበባ የሚሰበሰበው የዓይን ብሌን ለጅማ፣ ሐዋሳ፣ ጎንደር እና መቀሌ ሆስፒታሎች ይላክ እንደነበር ፤አሁን ላይ የጅማ ባንክ አገልግሎት በመጀመሩ ዋናው ማዕከል ለሐዋሳ፣ ጎንደር፣ መቀሌ እንዲሁም በአዲስ አበባ ለሚገኙ የመንግስትና የግል የቀዶ ጥገና ሕክምና ማዕከላት አገልግሎቱን እያቀረበ ይገኛል።

ከዚህ ቀደም የዓይን ብሌን ለመለገስ ቃል የሚገቡ ሰዎች ቁጥር ከ100 የማይበልጥ የነበረ ቢሆንም፣ በተደረገው ጥረት ባለፈው ዓመት 2,500 ሰዎች ቃል ገብተዋል። በ2019 በጀት ዓመት ደግሞ ይህንን ቁጥር ወደ 4,000 ለማድረስ እንደታቀደ አቶ ሃብታሙ ያስረዳሉ።

በሕክምናው ዘርፍ ያለው ረጅም ወረፋ፣ የዓይን ባንኮች ቁጥር ማነስ (ሁለት ብቻ መሆናቸው) እና የቀዶ ጥገና ሀኪሞች እጥረት ዋና ዋና የዘርፉ ችግሮች ናቸው ያሉት ምክትል ዋና ዳይሬክተሩ፤ ይህንን ለመቅረፍ ተቋሙ በያዘው የ3 ዓመት የዴቨሎፕመንትና ኢንቨስትመንት ፕላን ውስጥ አካቶ ይሰራል፤ በተጨማሪም መጪው ሕዳር ወር የዓይን ብሌን ልገሳ ንቅናቄ ወቅት በመሆኑ ከደም ልገሳ መርሃ ግብሮች ጋር አስተሳስሮ ግንዛቤ የማስጨበጥ ሥራዎችን ያከናውናል ብለዋል።

ኢትዮጵያ ውስጥ የሚገኘው የዓይን ባንክ በምስራቅ አፍሪካ ብቸኛውና ለአፍሪካ ሞዴል የሚሆን አክሬዲትድ (Accredited) ተቋም እንዲሆን በትኩረት እየተሠራ እንደሚገኝ አቶ ሀብታሙ አብራርተዋል።

17 ዓመታት… ከትንሽ ሚስጥር ወደ ታላቅ ቤተሰብ ❤️ጋሪ ዎሮ እስከ 19… በ20 ግን የራሳችንን ጉዞ ጀመርን።ያ ቀን እንዴት እንደነበረ ዛሬም አልረሳውም። እኔ የ2ኛ ዲግሪ ትምህርቴን አንድ ...
30/09/2026

17 ዓመታት… ከትንሽ ሚስጥር ወደ ታላቅ ቤተሰብ ❤️

ጋሪ ዎሮ እስከ 19… በ20 ግን የራሳችንን ጉዞ ጀመርን።

ያ ቀን እንዴት እንደነበረ ዛሬም አልረሳውም። እኔ የ2ኛ ዲግሪ ትምህርቴን አንድ ዓመት ጨርሼ ለእረፍት ወደ ቤተሰብ መጥቼ ነበር። የጋብቻ አይነቱ ፂፃ በመሆኑ የአስቱ ቤተሰቦች ኣያውቁም፣ ታላቅ እህቷ ኢያዬ ብቻ ምስጢሩ ተነግሯታል።
ከዚያም አስቱና የአጎቴ ልጅ አስካል ረጋሳ በማርያም ቤተክርስቲያን ጀርባ አድርገው አውራ ጎዳናውን ትንሽ አልፈው ጠበቁን። መኪና ቶሎ ስላልመጣ የበቆሎ እሸት ሰርቀው እንደበሉ ነግረውናል:: ሞት ይርሳኝ እና አጣባሹ ወንድሜ ደሳለኝ ወንበሮም ነበር;; እኛም መኪና ተጋፍተን፣ ለአስቱም ቦታ ይዘን፣ የዛኔው ተማሪ (ሁለተኛ ፊግሪ)—ዛሬ ዶክተር—የነበረው አንቢሳ ሙለታ ጋር ተሳፍረን…

ጉዞ ወደ አዲስ!

ያ ጉዞ ግን ብዙ ርቀት የሚያስኬድ የመኪና ጉዞ ብቻ አልነበረም። የሁለት ሰዎች የሕይወት ጉዞ መጀመሪያ ነበር።

ዛሬ 17 ዓመታት ሞልተውናል።

ከዚያ ትንሽ ሚስጥር ዛሬ የአማን፣ የቃል እና የባሮክ እናትና አባት ሆነናል። ❤️

17 ዓመታት የደስታ፣ የፈተና፣ የመማር፣ የመቻቻል፣ የመደጋገፍ እና አብሮ የማደግ ዓመታት።

በእያንዳንዱ ደስታችን ውስጥ፣ በእያንዳንዱ ፈተናችን ውስጥ፣ በእያንዳንዱ የሕይወት መንገድ ላይ አብረን እስከዛሬ መድረሳችን ትልቅ በረከት ነው።

ፍቅር አንድ ቀን የሚጀመር ነገር ነው፤ ትዳር ግን በየቀኑ እንደገና አብሮ የሚመረጥ ጉዞ ነው።

አስቱ፣ ከ17 ዓመታት በፊት በዚያ የጀመርነውን ጉዞ እስከዛሬ አብረሽኝ ስለቀጠልሽ አመሰግናለሁ። ለልጆቻችን የምትሆኚው እናት፣ ለእኔ የምትሆኚው የሕይወት አጋር በመሆንሽ እጅግ አመሰግናለሁ።

17ኛ የጋብቻ ዓመታችን ይባረክ!

ቀሪውን የሕይወታችንን ጉዞም በፍቅር፣ በሰላም፣ በጤና እና በቤተሰብ ደስታ አብረን እንድንቀጥል ፈጣሪ ይርዳን።

ፈጣሪ ይመስገን! 🙏

17 ዓመታት አብረን… እና ጉዞው ገና ይቀጥላል!

አንድነት እንዴት ያምራል! ❤️ጋሪ ዎሮ ከአንድ ሕዝብ ባህላዊ በዓልነት ተሻግሮ የሁሉም የጋራ በዓል እየሆነ ነው!የባህል ውበት በጋራ ሲከበር፣ የአንድነት መሠረት ይሆናል። የጋራ ደስታችን፣ የ...
27/09/2026

አንድነት እንዴት ያምራል! ❤️

ጋሪ ዎሮ ከአንድ ሕዝብ ባህላዊ በዓልነት ተሻግሮ የሁሉም የጋራ በዓል እየሆነ ነው!

የባህል ውበት በጋራ ሲከበር፣ የአንድነት መሠረት ይሆናል። የጋራ ደስታችን፣ የወንድማማችነታችን እና የብዝኃነታችን ውበት ይበልጥ ይጎላል።

📍 የጋሪ ዎሮ በዓል የሚከበርባቸው ቀናት፦

መስከረም 10 -አዲስ አበባ a tone setter
መስከረም 11 – ወንበራ
መስከረም 17–18 – አሶሳ፣ ጉባ፣ ዳንጉር፣ ግልገል፣ ድባጢ እና ቡለን

ጋሪ ዎሮ የባህል ብዝኃነታችንን የምናከብርበት፣ ትስስራችንን የምናጠናክርበትና ደስታችንን የምንጋራበት የጋራ በዓላችን ነው!

የቤኒሻንጉል ጉምዝ ክልል ወገን ዘመዶች እንኳን ለጋሪ ዎሮ በዓል አደረሳችሁ!

#ጋሪዎሮ

ለመላው የክርስትና እምነት ተከታዮች፣ ለደም ለጋሾቻችን፣ ኮርኒያ ለመለገስ ቃል ለገባችሁ እና ለመላው የደምና ሕብረሕዋስ ባንክ ቤተሰብ፦እንኳን ለብርሃነ መስቀሉ በሰላምና በጤና አደረሳችሁ!መስ...
26/09/2026

ለመላው የክርስትና እምነት ተከታዮች፣ ለደም ለጋሾቻችን፣ ኮርኒያ ለመለገስ ቃል ለገባችሁ እና ለመላው የደምና ሕብረሕዋስ ባንክ ቤተሰብ፦

እንኳን ለብርሃነ መስቀሉ በሰላምና በጤና አደረሳችሁ!

መስቀል ለክርስቲያኖች የእምነት ምልክት ብቻ ሳይሆን፣ የፍቅር፣ የመስዋዕትነት፣ የተስፋና የአዲስ ሕይወት ምልክት ነው። በመስቀሉ የተገለጠው የክርስቶስ ፍቅር፣ ለሌሎች ሕይወት መስጠትና ራስን ለሌሎች መስጠትን ያስተምረናል።

ይህንን የፍቅርና የተስፋ በዓል ስናከብር፣ የመስቀሉን መልዕክት በተግባር እንግለጽ።

🩸 ደም በመለገስ ሕይወት እንስጥ።

የደም ለጋሽ የሚሰጠው ደም ለአንድ ታካሚ የሕይወት ተስፋ፣ ለአንድ ቤተሰብ የደስታ ምክንያት፣ ለአንድ ሕይወትም የመቀጠል ዕድል ነው።

👁️ የአይን ብሌን (ኮርኒያ) ለመለገስ ቃል በመግባት ብርሃን እንስጥ።

ከሕልፈታችን በኋላ የአይን ብሌናችንን ለመለገስ የምንገባው ቃል ኪዳን፣ ለሌላ ሰው የማየት ተስፋን ይሰጣል። የእኛ የመጨረሻ ስጦታ ለሌላ ሰው የአዲስ ዓለም መጀመሪያ ነው።

🙏 የደምና የኮርኒያ ለጋሾቻችን ለወገናችሁ ሕይወትና ብርሃን በመስጠታችሁ እናመሰግናለን።

🤝 ለመላው የደምና ሕብረሕዋስ ባንክ ሠራተኞች፣ በየዕለቱ የለጋሾችን ስጦታ ወደ ሕይወትና ተስፋ በመቀየር ላበረከታችሁት የተቀደሰ ኃላፊነት ከልብ እናመሰግናለን።

ደም በመለገስ ሕይወትን፣ የአይን ብሌን ለመለገስ ቃል በመግባት ብርሃንን፣ በፍቅር ደግሞ ተስፋን እንስጥ።

መልካም የብርሃነ መስቀል!

በዓሉ የሰላም፣ የፍቅር፣ የጤናና የተስፋ ይሁንላችሁ!

25/09/2026

የኢትዮጵያ ደምና ሕብረሕዋስ ባንክ አገልግሎት በበጀት ዓመቱ 605 ሺህ ዩኒት ደም ለመሰብሰብ ማቀዱን ገለጸ፡፡
________________________
አዲስ አበባ — የኢትዮጵያ ደምና ሕብረሕዋስ ባንክ አገልግሎት በያዝነው የበጀት ዓመት 605 ሺህ ዩኒት ደም ለመሰብሰብ አቅዶ እየሰራ መሆኑን የአገልግሎቱ ምክትል ዋና ዳይሬክተር አቶ ሀብታሙ ታዬ ገለጹ።

አቶ ሃብታሙ ከጤና ሚኒስቴር የኮሙኒኬሽንና ሕዝብ ግንኙነት ሥራ አስፈፃሚ ጋር ባደረጉት ቃለ ምልልስ እንደገለጹት፤ ከተያዘው ግብ ለመድረስ ሰፊ የህዝብ ግንኙነትና የንቅናቄ ሥራዎች ታቅደዋል።

ባለፈው የበጀት ዓመት 476 ሺህ ዩኒት ደም መብሰብሰቡን ያስታወሱት ምክትል ዋና ዳይሬክተሩ፤ ዘንድሮ ከአምናው ጋር ሲነጻጸር ከ100 ሺህ ዩኒት በላይ ብልጫ ያለው ደም ለመሰብሰብ ታቅዶ ወደ ሥራ መገባቱን ተናግረዋል። በዚህም መሰረት ከሃምሌ 1/2018 ዓ.ም እስከ መስከረም አጋማሽ ባለው ጊዜ ውስጥ ብቻ በሀገር አቀፍ ደረጃ ከ150 ሺህ ዩኒት በላይ ደም መሰብሰብ ተችሏል።

ሆኖም ከመስከረም እስከ ጥቅምት የመጀመሪያ ሳምንት ባለው ጊዜ ልዩ ልዩ ሃይማኖታዊና ሕዝባዊ በዓላት የሚከበሩበት፣ እንዲሁም በትምህርት ተቋማት ተማሪዎች ሙሉ በሙሉ ወደ ትምህርት ገበታቸው የማይገቡበት ወቅት በመሆኑ በተደራጀ መልኩ ደም ለመሰብሰብ ፈታኝ እንደሚሆን ገልጸዋል።
በተለይም የመስቀልና የኢሬቻ በዓላት በሚከበሩበት በዚህ ወቅት የህብረተሰቡ ትኩረት ወደ በዓላቱ በማዘንበሉ ምክንያት የልገሳ መጠኑ እንዳይቀንስ የተለያዩ የደም ልገሳ ዘመቻዎች እየተካሄዱ እንደሚገኝ አቶ ሀብታሙ አስረድተዋል።

በበጀት ዓመቱ የተቀመጠውን ግብ ለማሳካትና የደም እጥረትን ለማስወገድ በህብረተሰቡ ዘንድ ስለ ደም ልገሳ ያለው ግንዛቤ እንዲዳብር ሰፊ የህዝብ ግንኙነት ሥራዎችን መስራት፤ደም በስፋት በሚገኝባቸው ቦታዎች በተደራጀ መልኩ የተለያዩ ፎረሞችን ማካሄድ፤ወጣቶችን በስፋት ለማግኘት በሚዲያና በሶሻል ሚዲያ አማራጮች መጠቀም በተለይ ከፍተኛ ተከታይ ያላቸውን የቲክቶክ (TikTok) እና የማህበራዊ ሚዲያ አንቂዎችን እንደ አምባሳደር በመጠቀም ህብረተሰቡን የማንቃት ሥራ በጋራ ለመስራት ዝግጅቶች መጀመሩን አቶ ሃብታሙ ገልፀዋል፡፡።

በመጨረሻም አቶ ሀብታሙ ታዬ፤ በደም እጥረት ምክንያት የዜጎች ሕይወት እንዳይጎዳና የህክምና አገልግሎቱ እንዳይስተጓጎል ህብረተሰቡ ደም በመለገስ የበኩሉን ሰብአዊ አስተዋጽኦ እንዲያደርግ ጥሪ አቅርበዋል።

Address

Addis Ababa

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Habtamu Taye posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Organization

Send a message to Habtamu Taye:

Shortcuts

Share