Amhara Agricultural Research Institute-ARARI

  • Home
  • Amhara Agricultural Research Institute-ARARI

Amhara Agricultural Research Institute-ARARI The Amhara Agricultural Research Institute (ARARI) was established in 1999/2000 by the ANRS council proclamation no 48/1992 as an autonomous apex body.

The Research Institute is working on technology innovation, adaptation & dissemination.

በአማራ ግብርና ምርምር ኢንስቲትዩት የወጣ የስራ ቅጥር ማስታወቂያ
03/06/2026

በአማራ ግብርና ምርምር ኢንስቲትዩት የወጣ የስራ ቅጥር ማስታወቂያ

29/05/2026
"አንድ ተቋም አካባቢውን  ሳይቀይር ሌላውን ሊለውጥ አይችልም" አቶ ምስጋናው ፈረደ የአዴት ግብርና ምርምር ማዕከል ዳይሬክተርበአማራ ግብርና ምርምር ኢንስቲትዩት የአዴት ግብርና ምርምር ማዕከ...
27/05/2026

"አንድ ተቋም አካባቢውን ሳይቀይር ሌላውን ሊለውጥ አይችልም" አቶ ምስጋናው ፈረደ የአዴት ግብርና ምርምር ማዕከል ዳይሬክተር

በአማራ ግብርና ምርምር ኢንስቲትዩት የአዴት ግብርና ምርምር ማዕከል ከምግብ ስርዓት ማጠናከርያ ፕሮግራም(FSRP) በተገኘ የገንዘብ ድጋፍ ለቀጣይ የመኸር ዓመት የተሻሻሉ ቴክኖሎጅዎችን ለተመረጡ አርሶ አደሮች የርክክብ እና የቅድመ ዝግጅት ስልጠና አካሄደ


ማዕከሉ በይልማና ዴንሳ ወረዳ በሞሰቦ ቀበሌ ፣ሰንቀኛ እና አዴት ዙርያ ለሚኖሩ አርሶ አደሮች ከማዕከሉ የወጡ እና የተላመዱ ቴክኖሎጅዎችን ተጠቃሚ ለማድረግ የተዘጋጀ መድረክ ሲሆን የተመረጡ አርሶ አደሮች ወደፊት ቴክኖሎጅውን ወስደው በአግባቡ በመስራት እና ከባለሙያዎች የሚሰጣቸውን ምክረ ሀሳብ በመተግበር እና በመናበብ የሚሰራ በመሆኑ በዚህም ተፅእኖ ፈጣሪ ቴክኖሎጂዎችን ለማውጣት፣ ለረጅም ግዜ እና ቋሚ የሆነ የሰርቶ ማሳያ እንዲሆም መረጃ መሰብሰብያ ለመፍጠር፣ ለመስክ ጉብኝትና ለማህበረሰቡ ማስተማርያ ሁነው እንዲያገለግሉ ማስቻል ታስቦ የተዘጋጀ ነው።

የአዴት ግብርና ምርምር ማዕከል ዳይሬክተር አቶ ምስጋናው ፈረደ እንደገለፁት አካባቢን ያለቀየረ ተቋም ሌላውን ሊቀይር ሊለውጥ አይችልም በማዕከሉ ዙርያ ያሉ አርሶ አደሮችን ከማዕከል የሚወጡ ቴክኖሎጅዎችን እና ምክረ ሀሳብ በማስረከብ እና በመከታተል አርሶ አደሮች የዘር ምንጭ ሁነው ለአጎራባች ቀበሌዎች ጥራት ያለው ዘር ለማስፋት የዘር ችግርን ለመቅረፍ ታስቦ የተዘጋጀ መሆኑን ተናግረዋል አክለውም ዘርን ለምግብነት ማዋል ትውልድም ሀገርንም መበደል በመሆኑ የተመረጡ አርሶ አደሮች ከግብርና ባለሙያዎች የሚሰጣቸውን ቴክኖሎጂ እና ምክረ ሀሳብ በአግባቡ በመተግበር ከራሱ አልፎ ማሳው ሌሎች አርሶ አደሮች ሰርቶ ማሳያ እንዲሆን እና ሌሎች ሞዴል አርሶ አደሮችን በመፍጠር ጥራት ያለው ዘር ተጠቃሚ እንዲሆኑ መድረግ እንደሚገባ አሳስበዋል።

የአዴት ግብርና ምርምር ማዕከል ተመራማሪ የሆኑት ዳኝነት አማረ (ዶ/ር) አንደገለፁት የስራው ዋና አላማ የአካባቢን አርሶ አደሮች ከተቀናጀ ቴክኖሎጅዎች ተጠቃሚ ሁነው መሰረታዊ የግብርና ለውጥ በማምጣት ለሌሎች አከባቢዎች ተምሳሌት ማድረግ መሆኑን ተናግረዋል።

የአዴት ግብርና ምርምር ማዕከል ምርት እና ምርታማነት የሚጨምሩ ለቅድመ ማስፋት እና ለሰርቶ ማሳያ የተለያዩ ቴክኖሎጅ ለአርሶ አደሩ ያቀረበ ሲሆን እነዝህም የድንች ፣በቆሎ፣ ዳጉሳ፣ስኳር ድንች ፣ቡና፣ አቮካዶ እና የተሳቦ ቀልዝ ዝግጅት እና አመራረት እንዲሆም በዋና ዋና ሰብሎች የተባይና በሽታ መከላከል ላይ ያተኩሩ ናቸው።

በመጨረሻም ወደፊት ምርት እና ምርታማነትን ከመጨመር ባሻገር ጥራቱ የተሟላ ዘር ለማምረት እና የዘር ችግርን ለመቅረፍ ለግብርናው ዘርፍ ወሳኝ በመሆም ሁሉም ባለድርሻ አካላት የበኩሉን ሀላፊነት ለመወጣት የጋራ ስምምነት ላይ ተደረሷል።

በመድረኩም አርሶ አደሮች ፣ የልማና ዴንሳ ወረዳ ግብርና እንስሳት እና ዓሳ ሀብት ልማት ጽ/ቤት ፣ ንግድ እና ገብያ ልማት ስራ እና ክህሎት ጽ/ቤት ፣ገንዘብ እና ኢኮኖሚ ልማት ጽ/ቤት ፣የማዕከሉ ተመራማሪዎች ፣ከኢንስቲትዩቱ የመጡ ተመራማሪ እና የምግብ ስርዓት ማጠናከሪያ ፕሮግራም ባለሙያ ተገኝተዋል።

(በታደሰ ምስጋናው)
mobile pictures

በምግብ ስርአት ማጠናከሪያ ፕሮግራም(FSRP) ድጋፍ የተሰሩ የምርምር ስራዎች አፈፃፀም አበረታች እንደሆነ ተገለፀ በአማራ ግብርና ምርምር ኢንስቲትዩት የምግብ ስርአት ማጠናከሪያ ፕሮግራም (F...
13/05/2026

በምግብ ስርአት ማጠናከሪያ ፕሮግራም(FSRP) ድጋፍ የተሰሩ የምርምር ስራዎች አፈፃፀም አበረታች እንደሆነ ተገለፀ

በአማራ ግብርና ምርምር ኢንስቲትዩት የምግብ ስርአት ማጠናከሪያ ፕሮግራም (FSRP) በ2018 በጀት አመት በ9ወር ውስጥ በእቅድ አካቶ ያከናወናቸውን ተግባሮች የኢንስቲትዩቱ ማኔጅመንታና ተመራማሪዎች እንዲሁም በኢንስቲትዩቱ ስር የሚገኙ የምርምር ማዕከላት ዳይሬክተሮች እና በማዕከል ደረጃ የምግብ ስርአት ማጠናከሪያ ፕሮግራም አስተባባሪዎች በተገኙበት ተገመገመ

የውይይት መድረኩን መንግግር የከፈቱት የኢንስቲትዩቱ ም/ዋና ዳይሬክተር ዶ/ር ስማኝ አስርዴ FSRP የኢንስቲትዩቱን የምርምር ስራ ለማዘን የሚያግዙ የምርምር ፋሲሊቲዎችን በማሟላት የግብርና ስራችን ከተለምዷዊ አሰራር ወጥቶ በቴክኖሎጅ የተደገፈ ሆኖ እንዲዘምን እንደዚሁም በምርምር የወጡ ቴክኖሎጅዎችም ወደ ተጠቃሚው ማህበረሰብ እንዲደርሱ እና የምርምርና ኤክስቴንሽን ግንኙነት እንዲጠናከር የሚያግዙ ስራዎችን ለይቶ እየደገፈ እንደሆነ ገልፀዋል።

ዶ/ር ስማኝ አክለውም የግምገማ መድረኩ በፕሮግራሙ የሚደገፉ ተግባሮች በዝርዝር ሪፖርት ቀርበው የምንወያይበት በመሆኑ ክፍተቶቻችንን የምንሞላበት የተሸሉ አፈፃፀሞችን ደግሞ ልምድ የምንለዋወጥበት ስለሆነ ትኩረት እንደሚሻ በማሳሰብ መድረኩን ከፍተዋል፡፡

በኢንስቲትዩቱ የFSRP ማናጀር ዶ/ር አደባባይ ከበደ በጀት አመቱ በ9 ወር ውስጥ በፕሮግራሙ የበጀት ድጋፍ የተከናወኑ፤ ቴክኖሎጅ ማውጣትና ማላመድ፣ ቴክኖሎጅ ማባዛት፣ ቴክኖሎጅ ማስተዋወቅ ፤በሰው ሀብት አቅም ግንባታ፣ በምርምር መሰረተ ልማት ግንባታ እና ሌሎች በፕሮግራሙ የሚደገፉ ተግባራት የተሰሩ ስራዎችን ሪፖርት በማቅረብ ውይይት ተካሂዷል፡፡

በተመሳሳይ በኢንስቲትዩቱ ስር የሚገኙ የግብርና የምርምር ማዕከላትም በበጀት ዓመቱ በFSRP የበጀት ድጋፍ በቴክኖሎጅ ማውጣትና ማላመድ፣ ቴክኖሎጅ ማባዛት፣ ቴክኖሎጅ ማስተዋወቅ ፤በሰው ሀብት አቅም ግንባታ እና በምርምር መሰረተ ልማት ግንባታ ላይ የተከናወኑ ተግባሮች ዝርዝር ሪፖርት ቀርቧል፡፡ እንደዚሁም በኢንስቲትዩቱ የቲሹ ካልቸር እና የምግብ ሳይንስና ድህረ ምርት አያያዝ ክፍሎች ውስጥ በፕሮግራሙ የሚደገፉ የምርምር ስራዎች ሪፖርት ቀርቦ ውይይት ተደርጓል፡፡ እንደዚሁም በኢንስቲትዩት ደረጃ የቡና ሰብልን ተስማሚ ስነ-ምህዳር ልየታ የተደረገውን ጥናት ሪፖርት ቀርቦ ተገምግሟል፡፡

በውይይት መድረኩም በምግብ ስርአት ማጠናከሪያ ፕሮግራም የበጀት ድጋፍ በየደረጃው ባሉ የምርምር ማዕከላት በበጀት ዓመቱ በእቅድ ተካተው የተከናወኑ የተግባራት አፈፃፀም አበረታች ውጤት እንደታየበት በመግለፅ ቀጣይ ትኩረት እንዲደረግባቸው መግባባት ላይ የተደረሰባቸው የሚለቀቁ ቴክኖሎጅዎች ተገቢው የማስፋት ስራው ተካሂዶ ፈጥነው ወደ ዘር ስርዓት ኢንዲገቡ በትኩረት መስራት እንደሚገባ አቅጣጫ ተሰጥቷል፡፡
ዘገባ ፡-ደሳለኝ አሳየ
ፎቶ:- ታደሰ ምስጋናው

የአማራ ግብርና ምርምር ኢንስቲትዩት እና በአማራ ክልል የሚገኙ የከፍተኛ ትምህርት ተቋማ ፎረም የግብርና ምርምር ስራዎችን በትብብር ለመስራት የሚያስችላቸውን የመግባቢያ ስምምነት ተፈራረሙበአማ...
07/05/2026

የአማራ ግብርና ምርምር ኢንስቲትዩት እና በአማራ ክልል የሚገኙ የከፍተኛ ትምህርት ተቋማ ፎረም የግብርና ምርምር ስራዎችን በትብብር ለመስራት የሚያስችላቸውን የመግባቢያ ስምምነት ተፈራረሙ

በአማራ ክልል የሚሰሩ የግብርና ምርምር ስራዎችን በትብብር በመስራት ውጤታማ ለማድረግ እና የግብርናው ዘርፍ የሚጠይቀውን ቅንጅታዊ አሰራር ለማጠናከር የሚያስችል የመግባቢያ ስምምነት የኢንስቲትዩቱ ምክትል ዋና ዳይሬክተር ዶ/ር ሰማኝ አስረዴ፣ በአማራ ክልል የሚገኙ የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ፎረም ጸሐፊ ዶ/ር ጀጃው ደማሙ እና የባህርዳር ዩኒቨርሲቲ የምርምርና ማሕበረሰብ አገልግሎት ምክትል ፕሬዚደንት ፕሮፌሰር እንየው አድጎ ዛሬ ሚያዚያ 29 ቀን 2018ዓ.ም በባህርዳር ዩኒቨርሲቲ አስተዳደር ግቢ በጋራ ተፈራርመዋል፡፡

የመግባቢያ ስምምነቱን መፈራረም አስፈላጊ የሆነው ከዚህ በፊት የተደረገው የትብብር ስምምነት የቆይታ ጊዜ በማለቁ እና ተጨማሪ የትብብር ማዕቀፎችን በማካተት የበለጠ ተቀናጅቶ ለመስራት በማሰብ መሆኑን ዶ/ር ሰማኝ አስረዴ ተናግረዋል፡፡

ስምምነቱ ሀብትን በጋራ ለመጠቀም እና ለማፈላለግ፣ የሰብአዊ ሀብት ልማት እና ቁሳዊ አቅም ግንባታን ለማጠናከር፣ ችግር ፈች የምርምር እና ፈጠራ ስራዎችን በጋራ ለመስራት እና በአጠቃላይ በክልሉ የሚከናወን የግብርና ምርምር ስራን በትብብር በመስራት ለግብርናው ዘርፍ እድገት ጉልህ ለመጫወት ከፍተኛ ጠቀሜታ ያለው መሆኑን ዶ/ር ሰማኝ አብራርተዋል፡፡

ዶ/ር ጀጃው ደማሙ በበኩላቸው ስምምነቱ የምርምር ኢንስቲትዩቱን እና በአማራ ክልል የሚገኙ ዩኒቨርሲቲዎችን የበለጠ ተቀራርበው እንዲሰሩ የሚያግዝ መሆኑን ገልጸው ለተግባራዊነቱ ሁላችንም መትጋት ይኖርብናል ብለዋል፡፡

የባህርዳር ዩኒቨርሲቲ እና የአማራ ግብርና ምርምር ኢንስቲትዩት በትምህርት እና ስልጠና፣ በምርምር እና በማህበረሰብ አገልግሎት ዘርፎች ጥሩ ትብብር ያላቸው ተቋማት ቢሆኑም ትብብሩን ወደ ላቀ ደረጃ ማሳደግና የበለጠ ተቀራርበን መስራት ይገባናል ያሉት ደግሞ ፕሮፌሰር እንየው አድጎ ናቸው፡፡ የጋራ ስምምነቱን በሚገባ ተግባራዊ ማድረግ ላይ ልዩ ትኩረት መስጠት እንደሚገባም ፕሮፌሰር እንየው አጽንኦት ሰጥተው ተናግረዋል፡፡

የመግባቢያ ስምምነቱ በየቀጠናው የሚገኙ የምርምር ማዕከላት፣ ዩኒቨርሲቲዎች እና በየደረጃው ያሉ የግብርና ተቋማት በጋራ ተቀናጅተው እንዲሰሩ እድል የሚፈጥር ስለመሆኑም ተገልጿል፡፡

የስምምኑቱን አፈጻጸም በየጊዜው መከታተል እና የተገኘውን ውጤት መገምገም፣ የተናጠል እንቅስቃሴዎችን በመቀነስ ለግብርናው ዘርፍ እድገት በትብብር መስራት፣ ሰብአዊ እና ቁሳዊ ሀብትን በጋራ በማቀናጀት ተጨባጭ ለውጥ ማምጣት የስምምነቱ ፈራሚ ተቋማት ኃላፊነት መሆን እንዳለበትም በፊርማ ስነ-ስርአቱ ላይ የታደሙ ባለድርሻ አካላት ተናግረዋል፡
ዘገባ፡ስማቸው ደምስ
ፎቶ:- ታደሰ ምስጋናው

በምርምር የወጡ ቴክኖሎጂዎችን በሰርቶ ማሳያ ለማስተዋወቅ እና ለአርሶ አደሩ ተደራሽ ለማድረግ ቅንጅታዊ አሰራርን ማጠናከር እንደሚገባ ተገለፀበምርምር የወጡ ቴክኖሎጅዎችን በሰርቶ ማሳያ ለማስ...
06/05/2026

በምርምር የወጡ ቴክኖሎጂዎችን በሰርቶ ማሳያ ለማስተዋወቅ እና ለአርሶ አደሩ ተደራሽ ለማድረግ ቅንጅታዊ አሰራርን ማጠናከር እንደሚገባ ተገለፀ

በምርምር የወጡ ቴክኖሎጅዎችን በሰርቶ ማሳያ ለማስተዋወቅ እና ለአርሶ አደሩ ተደራሽ ለማድረግ የፕሮጀክቶች፣ግብርና ቢሮ እና ምርምር ተቋማት በሰርቶ ማሳያ አሰራር ላይ በትብብርና ቅንጅት ለመስራት የውይይት መድረክ ተካሂዷል።

በግብርና ምርምር-ሥርዓት ውስጥ በምርምርና በአርሶ አደር ማሳ ደረጃ ተሞክረው የወጡ ቴክኖሎጂዎችን ወደ አርሶአደሩ ማሳ እንዲደርሱ ለማድረግ የሰርቶ ማሳያ ቦታዎች ወሳኝ ሚና ቢኖራቸውም በተቋማት መካከል በቂ ቅንጅትና ትብብር ባለመኖሩ ቴክኖሎጂዎች በተፈለገው ደረጃ እየተስፋፉ አለመሆኑን ተጠቁሟል።

የፕሮጀክቶችን፣ ግብርና ኤክስቴንሽን እና የምርምር ተቋማትን የቅንጅት መድረኮችን ማጠናከር የግብርና ምርታማነትን ለማሳደግ ትልቅ እምርታ እንደሚኖረው የተገለፀ ሲሆን በምርምር የተገኘ ቴክኖሎጂ ከምርምር እስከ አርሶአደሩ ማሳ ላይ ተግባራዊ እስኪሆን ድረስ ያለው የመረጃ፣ የግብዓትና የክትትል ሰንሰለትን የምያጠናክር ነው ተብሏል፡፡

አዳዲስ ሆነ ነባር በምርምር የተገኙ የሰብል ዝርያዎችም ሆኑ የተሸሻሉ አሰራር ምክረ ሃሳቦች በአጭር ጊዜ ወደ አርሶአደሩ እጅ እንዲደርሱ የተቋማት የተናበበ ዕቅድ ሊኖራቸው እንደሚገባም በውይይት መድረኩ ተነስቷል፡፡

በክልል ደረጃ የምርምር ተቋማት፣የግብርና ኤክስቴንሽን እና ሌሎችፕሮጀክቶች በሰርቶ ማሳያ አሰራር እና ተሳትፎ የሚያረጋግጥ ቋሚ ፕላትፎርሞችን መመሥረት እንደሚገባም ተጠቁሟል።

ውጤታማና ቀጣይነት ያለው የሰርቶ ማሳያ ሥርዓት እንዲኖር ምርምርተ ቋማት በጋራ በማስተባበር የሰርቶ ማሳያ ማሳዎችን እንዲለዩ፣ቴክኖሎጂዎችን በንጽጽር ማሳየት እንዲችሉ ማድረግ፣ የሰርቶ ማሳያ ውጤቶችን ማስተዋወቅ፣ በሰርቶ ማሳያ የሚያጋጥሙ ተግዳሮቶችንበቀጥታ ለማጋራት ዲጂታል መድረክ መቋቋም፣ በጀት፣ ቁሳቁስና የሰው ኃይል አቅምን በማጋራት የሰርቶ ማሳያ አሰራርን ቀልጣፋ ማድረግ እንደሚገባም ተጠቁሟል፡፡

በመድረኩ ከክልል የግብርና ኤክስቴንሽን ኃላፊዎች እና ባለሙያዎች፣ ከምርምር ኢንስቲትዩቱ የመጡ ተመራማሪዎች፣ የምርጥ ዘር አባዥ ድርጅቶች እና ከተለያዩ ፕሮጀክቶች የመጡ ተሳታፊዎች ተገኝተዋል፡፡

የቅጥር ማስታወቂያ የማስታወቂያውን ዝርዝር ለማግኘት በቴሌግራም ቻናላችን ሊንኩን በመጫን መመልከት ይችላሉ https://t.me/ARARIoffical/2610
06/05/2026

የቅጥር ማስታወቂያ

የማስታወቂያውን ዝርዝር ለማግኘት በቴሌግራም ቻናላችን ሊንኩን በመጫን መመልከት ይችላሉ
https://t.me/ARARIoffical/2610

በ12ኛው የአማራ ክልል የግብርና ልማት ባለድርሻ አካላት የግንኙነት አማካሪ ምክር ቤት ጉባኤ ላይ የአማራ ግብርና ምርምር ኢንስቲትዩት የምርምር ውጤቶችን የሚያሳይ አውደ ርዕይ አሳይቷል።አውደ...
27/04/2026

በ12ኛው የአማራ ክልል የግብርና ልማት ባለድርሻ አካላት የግንኙነት አማካሪ ምክር ቤት ጉባኤ ላይ የአማራ ግብርና ምርምር ኢንስቲትዩት የምርምር ውጤቶችን የሚያሳይ አውደ ርዕይ አሳይቷል።

አውደ ርዕዩን በርካታ ባለድርሻ አካላት የጎበኙት ሲሆን ኢንስቲትዩቱ ምን ምን ስራዎችን እየሰራ እንደሆነ እና ግብርናውን ለማሸጋገር የሚረዱ ምን አይነት የምርምር ውጤቶች እንዳሉት ግንዛቤ ያገኙበት ነው።

ግብርናውን ለማሸጋገር የግብርና ባለድርሻ አካላት በህዝብ ወገንተኝነት ስሜትና  በላቀ ቁርጠኝነት ተቀናጅተው መስራት እንዳለባቸው ተገለፀ።12ኛው የአማራ ክልል የግብርና ልማት ባለድርሻ አካላት...
26/04/2026

ግብርናውን ለማሸጋገር የግብርና ባለድርሻ አካላት በህዝብ ወገንተኝነት ስሜትና በላቀ ቁርጠኝነት ተቀናጅተው መስራት እንዳለባቸው ተገለፀ።

12ኛው የአማራ ክልል የግብርና ልማት ባለድርሻ አካላት የግንኙነት አማካሪ ምክር ቤት ጉባኤ በባህርዳር ከተማ ተካሂዷል።

በጉባኤው መግቢያ ላይ የክልሉ ግብርና ቢሮ ኃላፊ አቶ ደረጀ ማንደፍሮ የባለድርሻ አካላት አማካሪ ምክርቤቱ ምርምር፣ ኤክስቴንሽን፣ ከፍተኛ የትምህርት ተቋማትና ሁሉም በግብርናው ዘርፍ ላይ የተሰማሩ ባለድርሻ አካላትን በአንድነት በማስተሳሰር የክልሉን ግብርና የማሸጋገር ትልቅ ኃላፊነት አለበት ብለዋል።

በግብርናው ዘርፍ ላይ የሚሰሩ በርካታ አካላት፣ በክልሉ የግብርና ልምድ እና እውቀት እንዲሁም ለዘርፉ ምቹ የሆነ ፀጋዎች ቢኖሩም ዛሬም ድረስ የምግብ ዋስትና በሚለገው ልክ ያለመረጋገጥ፣ የቴክኖሎጅ ሽግግር በሚጠበቀው ልክ ያለመኖር እና የአርሶ አደሩን ችግር ያለመፍታት አሁንም ድረስ ማነቆ ሆኖ ቀጥላል ያሉት አቶ ደረጀ በዘርፉ ያሉ ችግሮችን ለመቅረፍ ምክርቤቱ መሬት ላይ ወርዶ የሚተገበር ውይይትና ማድረግና ኃላፊነቱን በአግባቡ መወጣት ይገባል ብለዋል።

ሁሉም ባለድርሻ የምክር ቤቱ አባላት በግብርናው ላይ ላይ ትርጉም ያለው ለውጥ ለማምጣት በህዝብ ወገንተኝነት እና በላቀ ቁርጠኝነት በቅንጅት መስራት ይገባቸዋል ያሉት ቢሮ ኃላፊው የኤክስቴንሽን አደረጃጀቱ ጠንካራ እንዲሆን መስራት እንደሚገባ አፅንኦት ሰጥተው ተናግረዋል።

በምርምር ዘርፍ በ11ኛው ጉባኤ የተወሰኑ ውሳኔዎች አፈፃፀም እና የቀጣይ የትኩረት ነጥቦች በአማራ ግብርና ምርምር ኢንስቲትዩት የማህበራዊ ምጣኔ ሀብትና ስርፀት ምርምር ዳሬክቶሬት ተወካይ በዶ/ር ያልፋል ተመስገን በኩል ቀርቧል።

አርሶ አደሩን መሰረት ያደረገ የግብርና ማነቆዎች ልየታ ስለመሰራቱ፣ የተለዩ ችግሮች የምርምር አጀንዳዎች ሆነው ስለመለየታቸውና የምርምር ማዕከላት የእቅዳቸው አካል እንዲያደርጓቸው ስለመሰጠቱ፣ በቀጠና ደረጃ የጋራ መድረኮች ስለመካሄዳቸው እና የምርምር ውጤቶች ወደ አርሶ አደሩ በፍጥነት ተደራሽ እንዲሆኑ የሚያግዙ ስራዎች እየተሰሩ ስለመሆናቸው ዶ/ር ያልፋል ገልፀዋል።

በግብርና ቢሮ በኩል የጥምረቱን ታሪካዊ ዳራ፣ ያከናወናቸው ስራዎችና በ11ኛው ጉባኤ የተወሰኑ ውሳኔዎች አፈፃፀም ሪፖርት በቢሮው የኤክስቴንሽን ዳይሬክተር አቶ ቀኛዝማች መስፍን አማካኝነት ቀርቧል።

የአማካሪ ምክር ቤቱ ቀጣይ ምን አይነት መዋቅር እና አደረጃጀት ሊኖረው እንደሚገባ እና ውጤታማ ሽግግር ለማድረግ የአማካሪ ምክርቤቱ ቅርፅ ምን መስራትና ምን መምሰል እንዳለበት በአማራ ግብርና ምርምር ኢንስቲትዩት ተመራማሪዎች አቶ ሙሉጌታ አለማየሁ እና ዶ/ር ልጃለም አበባው አማካኝነት ቀርቦ ውይይት ተደርጎበታል።

የአማራ ግብርና ምርምር ኢንስቲትዩት ምክትል ዋና ዳይሬክተር ዶ/ር ሰማኝ አስረዴ በኢንስቲትዩቱ በኩል የሚጠበቅብን ድርሻ በአግባቡ ለመወጣት እንሰራለን ብለው ጥምረቱ የግብርናውን ችግር ለመፍታት ትልቅ መሳሪያ ሆኖ የሚያገለግል መሆኑን ተናግረዋል።

ተጨባጭ ለውጥ ለማምጣት ግብ ተኮር ሆኖ መስራት፣ በሰው ሀይል፣ በበጀትና በአላማ ተቀናጅቶ በሙሉ ኃላፊነት ስሜት መስራት እና ጉባኤውን ለሌሎች ስራዎቻችን ማሳለጫ አድርገን መውሰድ ይገባናል ያሉት ደግሞ ዶ/ር ጋሻው ሙጨ የክልሉ የእንስሳትና አሳ ሀብት ልማት ቢሮ ኃላፊ ናቸው።

አቶ ደረጀ ማንደፍሮ በመድረኩ ማጠቃለያ ምን ይዘን ሄድን፣ ምን ሰራን፣ ምን ይዘን ቀረብን የሚለውን በአግባቡ መውሰድ፣ ታች ቀበሌ ድረስ የወረደ ቅንጅት እንዲኖር ማድረግ እና ግንኙነቱ በየጊዜው በማድረግ ለውጤት መትጋት ይገባል ብለዋል።

ግብርና ውስጥ የሚሰሩትን ሁሉንም አካላት ድርሻ እና ሚና በሚገባ ለይቶ ኃላፊነት መስጠት፣ የጋራ መድረክ መፍጠር፣ ወደ ታች ሲወረድ አካባቢያዊ ማድረግ፣ የጋራ መግባባት ከተፈጠረ በኋላ ስራውን ወደ እቅድ መቀየር እና ሚናን በለየ መንገድ ተግባራትን በጥራት መፈፀም እንደሚገባ አቶ ደረጀ አፅንኦት ሰጥተው ተናግረዋል።

በዋናነት የቡና እና ፍራፍሬ ልማት ላይ፣ በእንስስሳት ዘርፍ የሌማት ቱርፋት፣ መነሻ ዘር አቅርቦት እና አሲዳማ አፈር ማከም እና ግብርናን ወደ ቢዝነስ መቀየር ስራን የጋራ የቤት ስራ አድርገን መስራት ይገባናል በማለትም አቶ ደረጀ የቀጣይ አቅጣጫ አስቀምጠዋል።

የአማካሪ ምክር ቤቱ ረቂቅ መመሪያው ሁሉንም ባለድርሻዎች አሳታፊ በሚያደርግ መልኩ በሚገባ ተሰናድቶ ይዘጋጃልም ብለዋል።

በመጨረሻም የአማካሪ ምክር ቤቱ አባላት የቃል ኪዳን ፊርማ በመፈራረም 12ኛው ጉባኤ ተጠናቋል።

ዘገባ :-ስማቸው ደምስ
ፎቶግራፍ:-ታደሰ ምስጋናው

የኢንስቲትዩቱን መረጃዎች ለማግኘት ከስር ያሉ የማህበራዊ ትስስር ገጾችን ይወዳጁ!
ዌብሳይት፡- www.arari.gov.et
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/profile.php?id=100064041610420
LinkedIn፡- linkedin.com/company/arari
ቴሌግራም፦ t.me/ARARIoffical
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/
ትዊተር- https://twitter.com/AmharaResearch
ቲክቶክ፡- https://www.tiktok.com/.official

Address

Ethiopia

527, BAHIR DAR

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Amhara Agricultural Research Institute-ARARI posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

  • Want your organization to be the top-listed Government Service?

Share