FDRE Ministry Of Justice Diredawa Branch

  • Home
  • FDRE Ministry Of Justice Diredawa Branch

FDRE Ministry Of Justice Diredawa Branch Contact information, map and directions, contact form, opening hours, services, ratings, photos, videos and announcements from FDRE Ministry Of Justice Diredawa Branch, Government Organization, Ethiopia, .

የጠቅላላ ጉባዔ ጥሪ/ ለፌዴራል ጠበቆች በሙሉበፌዴራል የጥብቅና አገልግሎት ፍቃድ አሰጣጥ እና አስተዳደር አዋጅ ቁጥር 1249/2013 መሰረት የጠበቆች ማህበር የተቋቋመ ሲሆን፣ ማህበሩን ስራ ...
31/12/2021

የጠቅላላ ጉባዔ ጥሪ/ ለፌዴራል ጠበቆች በሙሉ
በፌዴራል የጥብቅና አገልግሎት ፍቃድ አሰጣጥ እና አስተዳደር አዋጅ ቁጥር 1249/2013 መሰረት የጠበቆች ማህበር የተቋቋመ ሲሆን፣ ማህበሩን ስራ ከማስጀመር አንፃር የማህበሩን የመጀመሪያውን ጠቅላላ ጉባኤ የሚጠራው ፍትሀ ሚኒስቴር መሆኑን በአዋጁ አንቀፅ 59 (1) ላይ ተመልክቷል፡፡
በዚሁ መሰረት ከፍትሕ ሚኒስቴር፣ ከኢትዮጵያ የህግ ባለሙያዎች ማህበር እና ከኢትዮጵያ ጠበቆች ማህበር የተውጣጡ የስራ ሃላፊዎች እና ባለሙያዎች የተካተቱባቸው አብይ እና ንዑሳን ኮሚቴዎች ተዋቅረው የማህበሩን የመጀመሪያ ጠቅላላ ጉባኤ ለማካሄድና ማህበሩን ስራ ለማስጀመር የሚያስችሉ የተለያዩ ተግባራትን ሲያከናውን የቆየ ሲሆን በዚሁ አግባብ የማህበሩ የመጀመሪያ ጠቅላላ ጉባዔው ጥር 8 ቀን 2014 ዓ.ም ከጠዋቱ 2፡30 ጀምሮ በአዲስ አበባ ከተማ ቦሌ ክፍለ ከተማ 24 ቀበሌ በሚገኘው ኮከብ አዳራሽ ይካሂዳል፡፡
በአዋጁ አንቀፅ 52(3) መሰረት ማኅበሩ ሁሉንም የፈዴራል ጥብቅና ፍቃድ የተሰጣቸውን ጠበቆች እና የጥብቅና ድርጅቶች በአባልነት ያቀፈ በመሆኑ ማናቸውም የፌዴራል ጥብቅና ፈቃድ ያላችሁ ጠበቆችና የጥብቅና ድርጅቶች በጉባኤው ላይ እንድትሳተፉ ይህ ጥሪ የተላለፈ ሲሆን፣ ጉባኤው የተሳታፊዎች ቁጥር ግምት ውስጥ ሳይገባ በጉባኤው ላይ በተገኙ አባላት የሚካሄድና የተለያዩ ውሳኔዎችን የሚያሳልፍ በመሆኑና ይህም ውሳኔ በሁሉም የፌዴራል ጥበቅና ፈቃድ ባላቸው የህግ ባለሙያዎችና የጥብቅና ድርጀቶች ላይ ተፈፃሚ የሚሆን በመሆኑ፣ ይህንን ተገንዝባችሁ በዚህ ታሪካዊ ጉባኤ ላይ እንድትሳተፉ ፍትህ ሚኒስቴር ጥሪውን ያቀርባል::
በዚህ ጉባዔ ላይ የማህበሩ ስራ አስፈጻሚ አባላት እንዲሁም የማህበሩ ፕሬዘዳንት እና ምክትል ፕሬዘዳንት የሚመረጡ ሲሆን ሌሎችም ክንውኖች የሚካሄዱ መሆኑን በዚህ አጋጣሚ ለመግለጽ እንወዳለን፡፡
የኢ.ፌ.ዲ.ሪ. ፍትሕ ሚኒስቴር

ክፍት ስራ ማስታወቂያ
16/03/2021

ክፍት ስራ ማስታወቂያ

በኢፈድሪ ጠቅላይ ዓቃቤ ህግ የድሬዳዋ ቅ/ፅ/ቤት officail Telegram page ለመቀላቀልወ ይም አባል ለመሆን የሚከተለዉን link/ ማስፈንጠሪያ ይጫኑ
24/01/2021

በኢፈድሪ ጠቅላይ ዓቃቤ ህግ የድሬዳዋ ቅ/ፅ/ቤት officail Telegram page ለመቀላቀልወ ይም አባል ለመሆን የሚከተለዉን link/ ማስፈንጠሪያ ይጫኑ

21/01/2021

በድሬዳዋ ከተማ ቀበሌ 07 ልዩ ቦታው ጫት ተራ ተብሎ በሚጠራው አካባቢ በ 2011 ዓ.ም በድምሩ 37442(ሰላሳ ሰባት ሺህ አራት መቶ አርባ ሁለት ብር) የሚያወጡ ንብረቶችን ያቀጠለ ተከሳሽ በፍርድ ቤት ክስ ተመስርቶበት በ 7 ዓ.ም ከ 8 ወር ፀኑ እስራት እንዲቀጣ ፍርድ ቤቱ ወስኖበታል፡፡

21/01/2021

ተከሳሽ ሰቢር አብዱልቃድር ኢዮጰያንን ለስራ ወደ ውጪ ሀገር ለመላክ ፍቃድ ሳይኖረው ነዋሪነታቸው በኦሮሚያ ክልል አሰላ ዞን አረማ ወረዳ ጩፋ ቀ/ገ/ማህበር የሆኑትን 3 ተበዳየች ወደ ሳውዲ አረቢያ እልካችዋለው ጂቡቲ የባህር ዳርቻ ስትደርሱ እያንዳዳችሁ 1000(አንድ ሺህ ብር) ትከፍላላችሁ በማለት ከሚኖሩበት አካባቢ ወደ አዳማ እንዲመጡ ከዛ ወደ ድሬዳዋ እንዲመጠ አድርጎ ድሬዳዋ ከተማ ቀበሌ 04 ልዩ ቦታው ሼል ተብሎ በሚጠው አካባቢ ይዞችው ሲጎዝ በፖሊስ የተያዙ በመሆኑ ሰውን በህገወጥ መንገድ ለስራ ወደ ውጪ ሀገር መላክ ሙከራ ወንጀል በፌደራል መጀመሪያ ፍርድ ቤት ተከሶ በ 8 ዓመት ፀኑ እስራት እና በ 10000(አስርሺህ ብር) የገንዘብ መቀጮ እንዲቀጣ ጥር 3 ቀን 2013 ዓ.ም በዋለው ችሎት ወስኖበታል፡፡

20/01/2021

ተከሳሽ በሽር ጌደን ሱበኔ የማይገባውን ብልፅግና ለማግኝት በማሰብ ንብረትነቱ የዩኒ ጋዝ ፒኤልሲ የሆነ 1ኛ. የዋጋ ግምታቸው 180000(አንድ መቶ ሰማኒያ ሺህ ብር) የሆኑ 3 ኦኪሲጅን ወደ ፕላት ፎርም ማስተላለፊያ ትቦዎች 2ኛ. የዋጋ ግምቱ 60000(ስልሳ ሺህ) ብር የሆነ የጋዝ ማምረቻ ማሽን መገጣጠሚዎችን ከታሸጉበት 3 ካርቶን ጋር ታህሳስ 21 ቀን 2013 ዓ.ም በግምት ከሌሊቱ 6፡00 ሰዓት በመውሰዱ በከባድ ስርቆት በፌደራል መጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት ተከሶ ክርክር ከተደረገ በኋላ ፍርድ ቤቱ ታህሳስ 30 ቀን 2013 ዓ.ም በዋለው ችሎት ተከሳሽን በ 6 ዓመት ፀኑ አስራት እንዲቀጣ ወስኖበታል፡፡

Address

Ethiopia

3020

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when FDRE Ministry Of Justice Diredawa Branch posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

  • Want your organization to be the top-listed Government Service?

Share