Los Angeles Baldersu chapter

Los Angeles Baldersu chapter International City Addis Ababa city for all with out displacing resides! Ethiopian public Movement!
(1)

11/05/2025
ጉዳዩ ለሸዋፈራው ደሳለኝ ይቅርታ የማድረግ ያለ ማድረግ አይደለም። ለሳተው ስህተት ይቅርታ ቢጠይቅ ይቅርታውን ማግኘት ይችላል። ትልቁ ችግር ግን የሱን ፊልሞችም ሆነ ትያትሮች ለማየት ስትቀመጥ...
08/31/2025

ጉዳዩ ለሸዋፈራው ደሳለኝ ይቅርታ የማድረግ ያለ ማድረግ አይደለም። ለሳተው ስህተት ይቅርታ ቢጠይቅ ይቅርታውን ማግኘት ይችላል። ትልቁ ችግር ግን የሱን ፊልሞችም ሆነ ትያትሮች ለማየት ስትቀመጥ የቤተክርስቲያን አባቶችህን የሰደበው በእናት ኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያንህ ላይ የተሳለቀውን ነገር እያሰብክ አስችሎህ ከተቀመጥክ ይመችህ🙌

ሸዋፈራው ሃይማኖቱን ሳናጣራ የትኛውንም እምነት የመከተል መብቱን አክብረንለት ምንም affect ሳያደርገን ስንታደም ኖረናል። አሁን ደግሞ ተዘጋጅቶበት አስቦበት አውጥቶ አውርዶ በእቅድ ቤተክርስቲያንን እና አባቶችን መዝለፍ ጀመረ። መቼም ወደ መድረክ ሲወጣ ይሄንን እንደሚናገር ሳያስብበት ሳይዘጋጅበት ነው የሚል ካለ የዋህ ነህ ከማለት ውጪ ሌላ የምለው አይኖርም👐 ጥበብ ምናምን የምትሉን ሰዎች ደግሞ ትክክለኛው ጥበብ እግዚአብሔርን መፍራት ነው ተብሏል😁 የሰራቸውን ፊልሞች ከፈለገ ቸርች ውስጥ ያሳያቸው 😁 ይቅርታ አጠያየቁ በራሱ እስኪ ምን ታመጣለህ የሚል ነው የሚመስለው ምኑም ከልቡ የተጸጸተ ሰው አይመስልም። አንተ በፈለከው መንገድ ተናግረኸው ስታበቃ እኔኮ ለማለት የፈለኩት እንደዚህ ነበር አውዱን ተረዱልኝ ምናምን የሚባሉ ቃላት ስሜት አይሰጡኝም። ቀስትህን ከደጋኑ ከለቀቅከው በኋላ ያደረስከው ጉዳት የሚለካው ተወጊው ላይ ባደረሰው ጉዳት እንጅ በአንተ አወራወር አይደለም👐

እና እኔና መሰሎቼ በጠየቅክበት መንገድ ይቅር ብለንሃል ፊልምህን ግን አናይም👐 የተወሰደው ከደብተራ በየኑ

ሎስ አንጀለስ በቦታው እንድትገኙ ተጋብዛችኋል
05/19/2025

ሎስ አንጀለስ በቦታው እንድትገኙ ተጋብዛችኋል

ይችን ትንሽ ጨዋታ ላካፍላችሁ🍁 በእድሜ የገፉ ገበሬ አባት በእስር ቤት ለሚገኝ ልጃቸው ደብዳቤን ይፅፋሉ። "ልጄ፥ ያው በዚህ ዓመት ድንችና ቲማቲም መትከል አልችልም ምክንያቱም ማሳውን የማረስ...
04/24/2025

ይችን ትንሽ ጨዋታ ላካፍላችሁ
🍁 በእድሜ የገፉ ገበሬ አባት በእስር ቤት ለሚገኝ ልጃቸው ደብዳቤን ይፅፋሉ። "ልጄ፥ ያው በዚህ ዓመት ድንችና ቲማቲም መትከል አልችልም ምክንያቱም ማሳውን የማረስ አቅም ስለሌለኝ፤ አንተ ግን እዚህ ሆነህ ቢሆን ኖሮ ልትረዳኝ እንደምትችል አውቃለሁ"።

ልጅም ለአባቱ መለሰ፦ "አባቴ ሆይ፥ ማሳውን ለማረስ ፈጽሞውኑ እንዳታስብ ምክንያቱም የሰረቅሁትን ገንዘብ በዛ ስፍራ ቀብሬዋለሁና!"።

ታዲያ የእስር ቤቱ አለቃና ፓሊሶች ልጅና አባት የሚመላለሱትን ደብዳቤ ቀድመው አንብበውት ነበር እና በጠዋት ተነስተው ወደ ስፍራው በማቅናት ገንዘቡን ለማግኘት ከዳር እስከ ዳር ማሳውን ቆፈሩ፤ ነገር ግን ምንም አይነት ነገር ሊያገኙ አልቻሉም።

በቀጣዩ ቀንም ልጅ ለአባቱ በድጋሚ ደብዳቤን ጻፈ፦ "አባቴ፣ አሁን ድንችና ቲማቲሙን መትከል ትችላለህ፤ እዚህ ሆኜ ላደርግልህ የምችለው ትልቁ ነገር ይህንን ነው"።

አባትም መለሱ፦ "ሃ.ሃ.ሃ ልጄ ሆይ፥ በርግጥም ብርቱ መሆንህን አውቃለሁ፣ ይኸው በእስር ቤት ሆነህ እንኳን እኔን እንዲያገለግሉኝ ፓሊሶችን ታዛለህ፤ የእስር ቤቱ አለቃና ጀሌዎቹ አካፋና ዶማ ይዘው ማሳውን ሲቆፍሩ በማየቴ ተገርሜአለሁ። የመኸር ጊዜ ምርቱን ለመሰብሰብ ስፈልግ ደግሞ እፅፍልሃለሁ"።

ልብ በል፤

• ሰዎችና ሁኔታዎች አካልህን ያስሩ ይሆናል፤ አእምሮህን ግን ፈጽሞ ሊያስሩ አይችሉም።

• አእምሮህ ታስሮ ከሆነ ግን እንዲለቅህ ራስህን ጠይቀው፤ ያለፈቃድህ አእምሮህን ማሰር የሚችል ኃይል የለምና።

• ጥንካሬ ከሚታየውና ከሚታሰረው አካልህ አይመጣም፤ ከማይታየውና ከማይበገረው አእምሮህ እንጂ።

ትልቁን ኃይል፣ አእምሮህን ያለመሰሰት ሁልጊዜም ተጠቀምበት!

08/23/2024

Save the Day August 31st

Address

Pacific Palisades, CA

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Los Angeles Baldersu chapter posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Organization

Send a message to Los Angeles Baldersu chapter:

Share