Mortena Jeru Werda Communication

Mortena Jeru Werda Communication Contact information, map and directions, contact form, opening hours, services, ratings, photos, videos and announcements from Mortena Jeru Werda Communication, Government Organization, Moretena Jeru, north Shewa, Martinez, CA.

A leading role in the Queen's Communication Information Sector: Integrating our vision for the success of our mission by raising public awareness of basic police strategies and programs by raising public awareness of basic police strategies and programs

ጳጉሜ 2 የመንሰራራት ቀን አከባበር
09/07/2026

ጳጉሜ 2 የመንሰራራት ቀን አከባበር

 #ጳጉሜን2   እነዋሪ፤ጳጉሜ 2/2018(ሞ.ጅ.ወ.መ.ኮ) በሰሜን ሸዋ ዞን በሞረትና ጅሩ ወረዳ“ የማንሰራራት ቀን” በተለያዩ ፕሮግራሞች ድምቀት ተከበረ  ጳጉሜን 2" የማንሰራራት ቀን" በወ...
09/07/2026

#ጳጉሜን2

እነዋሪ፤ጳጉሜ 2/2018(ሞ.ጅ.ወ.መ.ኮ) በሰሜን ሸዋ ዞን በሞረትና ጅሩ ወረዳ“ የማንሰራራት ቀን” በተለያዩ ፕሮግራሞች ድምቀት ተከበረ

ጳጉሜን 2" የማንሰራራት ቀን" በወረዳው የተከናወኑ ዋና ዋና የልማት ስራዎችን በመጎብኘት በታላቅ ድምቀት ተከብሯል።

በወረዳው እየተከናወኑ ያሉ አበይት የልማት ስራዎች የተጎበኙ ሲሆን የወረዳችንን የኢኮኖሚ ምሶሶ የሚያጠናክሩና የአርሶ አደሩን የኑሮ ደረጃ ወደ ላቀ ደረጃ የሚያሸጋገሩ እና በእንሰሳት ማድለብ ዘርፍ የተሰማሩ ወጣቶችን የስራ እድል ተጠቃሚ ያረጉ ተስፋ ሰጪ ፕሮጀክቶች ተጎብኝተዋል።

በጉብኝቱ ከተቃኙ ዋና ዋና የልማት ፕሮጀክቶች እንደ ሀገርም እንደ ክልልም የመጀመሩያ የሆነውን እና በመጠናቀቅ ላይ ያለው የጅሩ አግሪ ቢዝነስ ካምፓኒ ተጎብኝቷል።
ይህ ካምፓኒ ወረዳው በስንዴ ምርታማነቱ የሚታወቅ እንደመሆኑ መጠን፣ ካምፓኒው ወደ ሥራ መግባቱ ለወረዳችን አርሶ አደሮች ይገጥማቸው የነበረው እንግልትና የገበያ እጥረት ማስቀረት የሚችል እንዲሁም ክልሉ በግብርናው ዘርፍ እያሳየ ያለውን ኦመርታ ወደ ላቀ ደረጃ እያሸጋገረ በመሆኑን ከማሳየት ባለፈ ኢንዱስትሪው ዕድገት ትልቅ አቅም የሚፈጥር፤ ለበርካታ ዜጎችም የሥራ ዕድል በማስገኘት ጉልህ ሚና የሚያመጣ ነው።

"በግብርናው ዘርፍ የተመዘገቡ አበረታች ስኬታማ ስራዎች ከተረጅነት ወደ ምርታማነት ለተሟላ ሀገራዊ ሉዓላዊነት ለመሻገር ዋነኛ አቅም የመሆኑ ትልቅ ማሳያ የሆነው እና ግብርናን ከኋላቀር አሰራር ወደ ዘመናዊ የግብርና ሥርዓት ለማሸጋገር የቀበሌ የግብርና መዋቅሮችን ማዘመንና የአርሶ አደሩን የቴክኖሎጂ ተጠቃሚነት ማሳደግ ወሳኝ ነው። በዚህ መሠረት “ቤቴን በራሴ አቅም” በሚል መርህ በ2018 የተጀመረውን የአርሶ አደር ማሰልጠኛ ተቋማት ግንባታ በወረዳው በሁለት ቀበሌ ላይ ከ15 ሚሊዮን ብር ላይ በሆነ ወጭ የተገነባው እና በመጠናቀቅ ላይ ያለው የማንጉዶ ቀበሌ የአርሶ አደር ማጠሰልጠኛ ተቋም ተጎብኝቷል።
የወጣቶች ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ 2.3 ሚሊዮን ብር በላይ በሆነ ወጭ በማድለብ ለተሰማሩ ወጣቶች የሸድ ግንባታና የቁም እንሰሳ ግዥ በመፈፀም ወደ ስራ የተገባበት ኢንተርፕራይዝም የጉብኝቱ አካል ነበር።

አንድ ወረዳ ለአንድ ፕሮጄክት በኢኔሸቲፍ ተግባር የተገነባውን ህፃናት ማቆያ ግንባታም በጉብኝቱ ተካቷል።

እነዚህ መሰል ፕሮጀክቶች መጠናቀቃቸውና የልማት እንቅስቃሴዎች መስፋፋታቸው የወረዳችንና የሀገራችን የማንሰራራት ጉዞ እውነተኛ ማሳያዎች መሆናቸው በነበረው ጉብኝት ተመላክቷል።

የአካባቢያችንን ልዩ ፀጋ እና እምቅ የተፈጥሮና የግብርና ሀብት ወደ ተጨባጭ የኢኮኖሚ አቅም የሚቀይሩ የልማት ስራዎቻችን በላቀ ትጋት ይቀጥላሉ።

ጳጉሜ 1 «የእምርታ ቀን» በሰብል ልማት የመስክ ጉብኝት ሞረትና ጅሩ ወረዳ በድምቀት ተከበረ**‎‎እነዋሪ፤ጻጉሜ/1/2018 የምግብ ዋስትናን ለማረጋገጥና አርሶ አደሩን ከዕርዳታ ጥገኝነት በማ...
09/06/2026

ጳጉሜ 1 «የእምርታ ቀን» በሰብል ልማት የመስክ ጉብኝት ሞረትና ጅሩ ወረዳ በድምቀት ተከበረ**

‎እነዋሪ፤ጻጉሜ/1/2018 የምግብ ዋስትናን ለማረጋገጥና አርሶ አደሩን ከዕርዳታ ጥገኝነት በማውጣት የተረጂነት አስተሳሰብን በዘላቂነት ለመቀነስ ያለመ «የእምርታ ቀን» በሰብል ልማት የመስክ ጉብኝት ሞረትና ጅሩ ወረዳ በገርባ ቀበሌ ድምቀት ተከብሯል።
‎በእለቱ ተገኝተው ንግገግር ያደረጉት የሞረትና ጅሩ ብልጽግና ፓርቲ ቅ/ቤት ኃላፊ አቶ ወርቃለማሁ ሐይሌ
‎ሀገራችን ኢትዮጵያ ባለፉት የለውጥ ዓመታት ያጋጠሟትን በርካታ ተፈጥሯዊና ሰው ሰራሽ ፈተናዎች በጽናት አልፋ፣ በፖለቲካው፣ በኢኮኖሚውና በማኅበራዊ ዘርፎች ተጨባጭ ስኬቶችን ማስመዝገብ ችላለች። የትናንት ድሎቻችን የጽናታችን ማሳያ ሲሆኑ፣ የዛሬው ጥረታችን ደግሞ ነገን በጽኑ መሠረት ላይ የመገንባት አቅም ፈጥሮልናል።
‎አክለውም የጳጉሜን ወቅት የነበሩንን ጉድለቶች በመገምገም፣ ያመጣናቸውን ስኬቶችና ያሉንን ሀብቶች ፈትሸን ወደ ላቀ የልዕልና ምዕራፍ የምንሸጋገርበት የቁርጠኝነት ጊዜ ነው።​የዘመኑ የጳጉሜን አከባበር ሀገራችን 7ኛውን ሀገራዊ ምርጫ በስኬት አጠናቅቃ፣ በህዝብ ሙሉ ድምፅ እውቅና ያገኘው ፓርቲ የህዝቡን አደራ በታማኝነት ለመፈጸም በተዘጋጀበት እና ሀገራዊ የምክክር መድረኩ በተሳካ ሁኔታ በተጠናቀቀበት ወቅት መከበሩ ልዩ ያደርገዋል ብለዋል ። በመሆኑም እያንዳንዱ የጳጉሜን ቀን ይህንኑ የማንሰራራትና ልዕልና መልእክት የሚያንጸባርቅ በመሆኑ፣ ሁላችንም እጅ ለእጅ ተያይዘን ኢትዮጵያን ወደ ተመኘናት የከፍታ ማማ ከፍ ልናደርጋት ይገባል።

‎የሞረትና ጅሩ ወረዳ ግብርና ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ካሱ አበበ በተካሄደው የመስክ ጉብኝት አራት ቀበሌዎችን የሚያገናኝ 3100 ሄክታር በላይ መሬት ላይ በዘመናዊ አሰራርና በምርጥ ዘር የተዘራው የሰብል ልማት በጥሩ ጤንነትና የዕድገት ቁመና ላይ እንደሚገኝ ተመላክቷል። ይህም የአካባቢው አርሶ አደሮች በምርትና ምርታማነት ላይ እያመጡት ያለውን አወንታዊ ለውጥ የሚያሳይ ከመሆኑም በላይ ለከፍተኛ ምርት ተስፋ ሰጭ እና ሰብሉም በጥሩ ቁመና ላይ ይገኛል ብለዋል።

‎ይህ በዘመናዊ የግብርና ቴክኖሎጂዎችና በተሻሻሉ አሰራሮች የተከናወነው የሰብል ልማት ንቅናቄ በርካታ ኢኮኖሚያዊና ማህበራዊ ጠቀሜታዎች እንዳሉት ጠቁመዋል።

‎በስፋትና በምርጥ ዘር የተከናወነው ልማት ምርታማነትን በመጨመር የአርሶ አደሩን የኢኮኖሚ አቅም ያጎለብታል ብለዋል።

‎ የተሻሻለ ምርት የሚያስገኝ በመሆኑ በአካባቢው የምግብ ዋስት ከማረጋገጥ አንፃር አስተዋፅኦዉ የጎላ እንደሆነ ኃላፊው ገልፀዋል። የሚገኘው ከፍተኛ ምርት የአካባቢውን ገበያ የሚያረጋጋና የዋጋ ንረትን በመቀነስ ረገድ የጎላ ፋይዳ እንደሚኖረዉ አቶ ካሱ ገልፀዋል።

‎ይህ የብበል ቁመና እንደ ሀገር የተጀረውን የውለጥ ሂደት የወረዳችንን አምራችነትና የምግብ ዋስትና የማረጋገጥ ራዕይ በተግባር የሚያሳይ ከመሆኑም በላይ የያዘውን ልማትና የህዝባችንን የጽናት ጉዞ የሚያሳይ እንደሆነም የጉብኝቱ ተሳታፊዎች ጠቁመዋል።

‎ #ጳጉሜን1 #የእመርታቀን #የኢትዮጵያ መንሰራራት #ከተረጂነት ወደ አምራችነት ሞረትና ጅሩ #የስንዴልማት #ምግብሉዓላዊነት

📚"አንድ ደርዘን ደብተር ለአንድ ተማሪ!" በጎ አድራጎት ዘመቻ በሞረትና ጅሩ ወረዳ ተጠናክሮ እንደቀጠለ ነው!"ሰውን ለመርዳት ሰው  መሆን ብቻ በቂ ነው " ወጣት ዮሴፍ ኩችም​የነገ አገር ተ...
09/06/2026

📚"አንድ ደርዘን ደብተር ለአንድ ተማሪ!"
በጎ አድራጎት ዘመቻ በሞረትና ጅሩ ወረዳ ተጠናክሮ እንደቀጠለ ነው!
"ሰውን ለመርዳት ሰው መሆን ብቻ በቂ ነው " ወጣት ዮሴፍ ኩችም
​የነገ አገር ተረካቢ ታዳጊዎችንና ህጻናትን መደገፍ የሁላችንም ተግባርና ኃላፊነት ነው! የመማሪያ ቁሳቁስ ማሟላት ለማይችሉ ውድ ተማሪዎቻችን የሚውል የደብተር ማሰባሰብ ዘመቻ በሞረትና ጅሩ ወረዳ ተነሳሽነት ተጀምሮ በተሳካ ሁኔታ በመከናወን ላይ ይገኛል.
​ይህን አገራዊና ማህበራዊ ጥሪ በተግባር በመደገፍ ረገድ፦
• ​ወጣት ዮሴፍ ኩችም 4(አራት) ደርዘን ደብተር በማበርከት የበጎ አድራጎት ቻሌንጁን በታላቅ ቅንነትና አጋርነት ተቀላቅለዋል።
• ​ሁሌም ለህዝብና ለማህበረሰብ ጥሪ ፈጣን ምላሽ የሚሰጠው የከተማችን ነዋሪ የሆነው ወጣት ዮሴፍ ከልብ የመነጨ ምስጋናችንን እያቀረብን፤ ፈጣሪ በበረከት ይጎበኝህ በወጣ ይተካ እንላለን!
​🇪🇹"በጎነትና አብሮነት ለኢትዮጵያ ከፍታ!" ??🇹
​ #የሞረትና ጅሩ ወረዳ_አስተዳደር #በጎነት

✨ ሀገርን ለመገንባት ዛሬ ታዳጊዎችን መደገፍና እነሱ ላይ መስራት  የሁላችንም የዘወትር ተግባር  ሊሆን ይገባል! ✨​በወረዳችን በታላቅ ተነሳሽነት የተጀመረውና በተሳካ ሁኔታ እየቀጠለ የሚገኘ...
09/05/2026

✨ ሀገርን ለመገንባት ዛሬ ታዳጊዎችን መደገፍና እነሱ ላይ መስራት የሁላችንም የዘወትር ተግባር ሊሆን ይገባል! ✨
​በወረዳችን በታላቅ ተነሳሽነት የተጀመረውና በተሳካ ሁኔታ እየቀጠለ የሚገኘው የትምህርት መማሪያ ቁሳቁስ የማሰባሰብ የበጎ አድራጎት ዘመቻ፣ ዛሬም የብዙዎችን ልብ እያገኘ ይገኛል። ይህንን የደግነት ጥሪ ሰምተው በሩቅ ቢሆኑም በልባቸው ለታዳጊዎች የቀረቡ ወገኖቻችን አጋርነታቸውን በተግባር እያሳዩን ነው።
​👏 የእለቱ ድንቅ ስራ!
በአዲስ አበባ ከተማ የሚኖረው ውድ ወንድማችን አቶ አበበ በጋሻው "እኔም ለወገኔ አለሁ!" በማለት 2 (ሁለት) ደርዘን ደብተሮችን በማበርከት ቻሌንጁን በይፋ ተቀላቅሏል!
​👇👇👇
🚩 "በጎነትና አብሮነት ለኢትዮጵያ ከፍታ" የሚለውን መሪ ቃል በተግባር ላሳየኸው ወንድማችን አቶ አበበ በጋሻው ፦
ለአሳየኸው ፈጣንና ቀና ምላሽ፣ እንዲሁም ለታላቅ አጋርነትህ ከልብ የመነጨ የላቀ ምስጋናችን ይድረስህ! ፈጣሪ በሰጠህ ላይ በረከትን ያብዛልህ፣ ይጨምርልህ!
ለዚህ ቅንና በጎ ተግባር ሁላችሁም የወንድማችንን አርዓያ ብትከተሉ ብዙ መማር መማር የማችሉ ህጻናትን እንታደግ!

የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ እነዋሪ ቅርንጫፍ ለተማሪዎች የመማሪያ ደብተርና ቁሳቁስ ድጋፍ አደረገ​"በጎነትና አብሮነት ለኢትዮጵያ ከፍታ!" በሚል መሪ ቃል የተጀመረውን የክረምት የበጎ ፍቃድ ቻሌን...
09/05/2026

የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ እነዋሪ ቅርንጫፍ ለተማሪዎች የመማሪያ ደብተርና ቁሳቁስ ድጋፍ አደረገ
​"በጎነትና አብሮነት ለኢትዮጵያ ከፍታ!" በሚል መሪ ቃል የተጀመረውን የክረምት የበጎ ፍቃድ ቻሌንጅ ​የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ እነዋሪ ቅርንጫፍ በማህበራዊ ኃላፊነት አገልግሎቱ በትምህርት ቁሳቁስ እጥረት ምክንያት ከትምህርት ገበታቸው ለሚስተጓጎሉ ተማሪዎች የሚውል የመማሪያ ደብተርና ቁሳቁስ ድጋፍ አድርጓል።
​በዛሬው እለት በተካሄደው በርክክብ ሥነ-ሥርዓት የቅርንጫፉ ባልደረባ አቶ ሙሉጌታ 20 ደርዘን ደብተር ለወረዳው ም/አስተዳደሪና የገንዘብ ጽ/ቤት ኃላፊ ለአቶ ተመስገን ዲናና ለወረዳው ሴቶች ህጻናትና ማህበራዊ ጉዳይ ጽ/ቤት ኃላፊ ወ/ሮ ደስታ ሀይሉ አስረክበዋል።

​ ባንኩ የማህበራዊ ኃላፊነቱን ለመወጣት ቀደም ሲልም ተመሳሳይ ድጋፎችን ሲያደርግ መቆየቱን ተመላክቷል፣
​በርክክብ ሥነ-ሥርዓቱ ላይ የተገኙት የወረዳው ምክትል አስተዳዳሪና እና የገንዘብ ጽህፈት ቤት ኃላፊ አቶ ተመስገን ዲና በበኩላቸው፤ የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በክረምቱ የበጎ ፈቃድ አገልግሎት ንቁ ተሳታፊ በመሆን ለተማሪዎች ላደረገው ድጋፍና ላበረከተው ከፍተኛ አስተዋጽኦ ምስጋና አቅርበዋል።
​ #የኢትዮጵያ ንግድባንክ #የእነዋሪቅርንጫፍ #ማህበራዊኃላፊነት #የክረምትበጎፈቃድ #ትምህርትለወደፊት
የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ሁሌም የሚተማመኑበት ባንክ!

‎በወረዳው ከ10ሺህ በላይ የደለቡ እንስሳትና የእንስሳ ተዋጽኦ ምርቶች ለዘመን መለወጫ ለበዓል ገበያ ይቀርባሉ ተባለ፦‎‎​እነዋሪ ነሐሴ 29/2018 ዓ.ም ለ2019 የዘመን መለወጫ በአል ከ1...
09/04/2026

‎በወረዳው ከ10ሺህ በላይ የደለቡ እንስሳትና የእንስሳ ተዋጽኦ ምርቶች ለዘመን መለወጫ ለበዓል ገበያ ይቀርባሉ ተባለ፦

‎​እነዋሪ ነሐሴ 29/2018 ዓ.ም ለ2019 የዘመን መለወጫ በአል ከ10 ሺህ በላይ እንስሳትና የእንስሳ ተዋጽኦ ለገበያ ዝግጁ መሆናቸውን የሞረትና ጅሩ ወረዳ የእንስሳትና ዓሣ ሀብት ልማት ጽሕፈት ቤት አስታወቀ።

‎በወረዳዉ ለ2019 የዘመን መለወጫ በዓል ገበያ የሚያስፈልገውን የእንስሳት አቅርቦት በበቂ ሁኔታ ለማቅረብ ታቅዶ ሲሰራ መቆየቱን የጽሕፈት ቤቱ ኃላፊ አቶ ስንታየሁ ከፈለኝ ገልጸዋል።

‎ለበዓሉ የሚቀርቡት የዳልጋ ከብት 10 ሺህ 500፣በግ 25 ሺህ 687፣ፍዬል 8 ሺህ 450፣የደለቡ የስጋ ዶሮ 18 ሺህ 400፣ እንቁላል 1.3 ሚሊዮን ፣ቅቤ 287 ኪሎ ግራም አይብ 427 ኪሎ ግራም ለገበያ ዝግጁ ሆነዋል ብለዋል።

‎የወረዳው እንስሳናዓሳ ሀብት ልማት ፅ/ቤት ኃላፊ አክለው እንደገለፁት የወረዳችን አርሶ አደር ከሰብል ስራው በተጨማሪ እንስሳት ድልብ ላይ ትኩረት ሰጥቶ እንዲሰራ በሰፊው ግንዛቤ በመፍጠር በወረዳችን በሁሉም ቀበሌዎች በዓላትን ታሳቢ በማድረግ አርሶ አደሩ እንስሳት ድልብ ስራ ላይ በሰፊው መስራቱን ቀጥሏል ብለዋል።

‎መልካም አዲስ አመት!!!

"የስራ እድል ፈጠራ ላይ የሚታዩ ማነቆዎችን ለመፍታት በወረዳው ያሉንን ፀጋዎች በመጠቀም ነባራዊ ሁኔታዎችን እየለን መስራት  ይጠበቅበናል" አቶ ተመስገን ዲና የሞረትና ጅሩ ወረዳ ም/አስተዳዳ...
09/04/2026

"የስራ እድል ፈጠራ ላይ የሚታዩ ማነቆዎችን ለመፍታት በወረዳው ያሉንን ፀጋዎች በመጠቀም ነባራዊ ሁኔታዎችን እየለን መስራት ይጠበቅበናል" አቶ ተመስገን ዲና የሞረትና ጅሩ ወረዳ ም/አስተዳዳሪና የገንዘብ ጽ/ቤት ኃላፊ

የሞረትና ጅሩ ወረዳ ስራ ክህሎት ጽ/ቤት የ2018 በጀት ዓመት እቅድ አፈፃፀም ግምገማ እና የ2019 ዓ.ም እቅድ ትውውቅ መድረክ አካሂዷል።

የሞረትና ጅሩ ወረዳ ም/አስተዳዳሪና የገንዘብ ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ተመስገን ዲና እንደገለፁት የስራ እድል ፈጠራ ችግር ለመቅረፍ ያሉንን ፀጋዎች በመጠቀም ነባራዊ ሁኔታዎችን እየለን መምራት ይጠበቅበናል በማለት የስራ እድል ፈጠራ ላይ ለውጥ በማስመዝገብ የዜጎችን ኑሮ ለመቀየር ከተቋም እስከ ቀበሌ አመራሩ ያለው መዋቅር በቁርጠኝነትና በትብብር መስራት ይጠበቅበታል ብለዋል።

የሞረትና ጅሩ ወረዳ ስራ ክህሎት ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ደርብ አሻህርገጥ የ2018 በጀት ዓመት እቅድ አፈፃፀም እና የ2019 ዓ.ም እቅድ ያቀረቡ ሲሆን በ2018 ዓ/ም 3300 ስራ ፈላጊ ወጣቶችን በቋሚና በጊዜዊ የስራ እድል ለመፍጠር ታቅዶ ከዚህ ወስጥ በቋሚነትና በጊዜዊነት ለ3450 ወጣት ስራ እንደተፈጠረ በቀረቡት ሪፖርት ገልፀዋል።

አክለውም አቶ ደርብ በ2019 በጀት አመት በቋሚ እና በጊዜያዊ አጣቃላይ 3542 ወጣቶች ወደስራ ለማስገባት እቅድ ተይዞ እየተሰራ መሆኑን ተናግረዋል።አሁን ላይ ባለፉት ሁለት ወራትም ከ443 በላይ ስራ ፈላጊዎችን መመዝገብ መቻላቸውን ተናግረዋል።

የመድረኩም ተሳታፊዎች እንደገለፁት የስራ እድል ማጣት እና የኑሮ ውድነት እየተባባሰ መሄድ በርካታ ማህበራዊ ኢኮኖሚያዊ እና ፖሰቲካዊ ቀውሶችን ስለሚያስከትል ዘርፉን በልዩ ትኩረት በተደረጀ በተቀናጀ በአግባብ መምራት እና መስራት እንደሚገባ በማንሳት ወደ ስራ ያልገቡ ወጣቶችን ለይቶ በማደራጀት ለ2019 በጀት አመት ወደ ስራ ለማስገባት ትኩረት ሰተን እንሰራለን ብለዋል።

የስራ ክህሎት ጽ/ቤት ባለሙያዎች እንደገለፁት በ2018 በጀት አመት የተሻለ አፈፃፀም እንዳለ ገልፀው ለቀጣይ የተያዙ እቅዶችን ለማሳካት ከቀበሌው አመራር ጋር ተቀናጅተው እንደሚሰሩ ተናግረዋል።

በመድረክ መሪዎቹ የተነሱ ሀሳቦች ላይ የማጠቃለያ ሀሳብ በመስጠትና ቀጣይ አቅጣጫ በማስቀመጥ መድረኩ ተጠናቋል።

ሕልማችን እና ሀሳባችን ሁል ጊዜም ቢሆን ትልቅ ሊሆን ይገባል - በ12ኛ ክፍል ማጠናቀቂያ ፈተና 566.19 ያመጣው ተማሪ ቢራራ ወልዴእነዋሪ፣ ነሐሴ 28፣ 2018 (ሞ/ጅወመኮ) የምናቅደው ነ...
09/04/2026

ሕልማችን እና ሀሳባችን ሁል ጊዜም ቢሆን ትልቅ ሊሆን ይገባል - በ12ኛ ክፍል ማጠናቀቂያ ፈተና 566.19 ያመጣው ተማሪ ቢራራ ወልዴ

እነዋሪ፣ ነሐሴ 28፣ 2018 (ሞ/ጅወመኮ) የምናቅደው ነገር ትልቅ ከሆነ የሚመጣው ውጤትም በዚሁ ልክ ትልቅ ይሆናል አለ በ12ኛ ክፍል ማጠናቀቂያ ፈተና በተፈጥሮ ሳይንስ ዘርፍ 566.19 ያመጣው ተማሪ ቢራራ ወልዴ፡፡

በአማራ ክልል በሰሜን ሸዋ ዞን በእነዋሪ አጠቃላይ 2ኛና መሰናዶ ት/ቤት ተማሪ የሆነው ቢራራ ወልዴ በ2018 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና ከፍተኛ ውጤት በማምጣቱ መደሰቱን ለተቋማችን ሚዲያ ገልጿል፡፡

"ለ12ኛ ክፍል ማጠናቀቂያ ፈተና የተዘጋጀሁበት መንገድ ውጤታማ አድርጎኛል፤ ጥሩ ውጤት እንደማመጣም ጠብቄ ነበር" ይላል ተማሪ ቢራራ፡፡

ጥናት ላይ በሚሆንበት ሰዓት በትኩረት እንደሚያጠና የሚገልጸው ተማሪው÷ በጥናት ሰዓቱ ማስታወሻ የመያዝ እና ጥያቄዎችን የመስራት እንዲሁም ደጋግሞ የማንበብ ልምድ እንዳለው አስረድቷል፡፡

ጥያቄዎችን መስራት እና ማስታወሻ መያዝ ለውጤታማነቱ እንደረዳው በመግለጽ፤ "ሁል ጊዜ ያለፋቸውን የትምህርት ደረጃዎች ደጋግሜ በማጥናቴ ከፍተኛ ውጤት እንዳመጣ አግዞኛል" ብሏል፡፡
"እኔ በራሴ ሁልጊዜ የማስበው እና ትኩረቴ ሁሉ ትምህርቴ ላይ ብቻ ነበር፤ ከትምህርት ውጪ ሌላ ነገር ሌላ ስራ እንድሰራ አስቼግሩኝም፤ ትኩረታችን በሙሉ ትምህርት ላይ በመሆኑም ውጤታማ ሆነናል" ብሏል፡፡

ከጓደኞቹ ጋር በጋራ እንደሚያጠና የሚናገረው ተማሪ ቢራራ÷ ትምህርት ቤቱ እና መምህራንም አስፈላጊውን ድጋፍ እንደሚያደርጉላቸው ጠቁሟል፡፡

"እናት እና አባቴ አርሶ አደር ናቸው፤ እነሱ አርሶ አደር ቢሆኑም በትምህርት ዘርፍ እኔም ትምህርት ላይ ትኩረት እንዳደርግብቻ ይመክሩኛል " ሲል ገልጾ÷ ወላጆቹ የየምሚያስፈልገውን ነገር እንደሚያሟሉለት፣ እንደሚጠይቁት፣ እንደሚከታተሉት እና እንደሚመክሩት ተናግሯል፡፡

"ከዝግጅት ባለፈ በትምህርት ዘመኑ የማመጣውን ከታች ክፍል ጀምሮ የማመጣውን ውጤት ደብተሮቼ ላይ ሁሉ እጽፍ ነበር፤ሁል ጊዜም ስናቅድ ትልቅ ነገር ነው ማቀድ ያለብን" የሚለው ተማሪ ቢራራ÷ ዶክተር የመሆን ሕልም እንዳለው ተናግሯል፡፡

በህክምና ዘርፍ ጥሩ ቦታ መድረስ እንደሚፈልግ እና ከልጅነቱ ጀምሮ ሕልሙ የህክምና ዶክተር መሆን እንደነበር አጽንኦት ሰጥቷል፡፡

ከ‎156 ሚሊየን ብር በላይ ገቢ ለመሰብሰብ አቅዶ አየሰራ መሆኑን የወረዳው ገቢዎች ጽ/ቤት አስታወቀ።‎‎እነዋሪ ነሀሴ 28/2018 (የሞጅወመኮ)በሰሜን ሸዋ ዞን በሞረትና ጅሩ ወረዳ ገቢዎች ...
09/03/2026

ከ‎156 ሚሊየን ብር በላይ ገቢ ለመሰብሰብ አቅዶ አየሰራ መሆኑን የወረዳው ገቢዎች ጽ/ቤት አስታወቀ።

‎እነዋሪ ነሀሴ 28/2018 (የሞጅወመኮ)በሰሜን ሸዋ ዞን በሞረትና ጅሩ ወረዳ ገቢዎች ጽ/ቤት 156 ሚሊየን 932ሺ 986 ገቢ ለመሰብሰብ አቅዶ አየሰራ መሆኑን አስታውቋል።

‎የሞረትና ጅሩ ወረዳ ገቢዎች ፅ/ቤት ሀላፊ አቶ መኩሪያ እንደገለፁት ወረዳዉ በ2019 በጀት ዓመት 156ሚሊዬን 932 ሺህ 986 ብር ለመሰብሰብ አቅዶ ከሀምሌ 1 እስከ ነሀሴ 27/2018 ድረስ 13 ሚሊዬን 584 ሺህ 286.78 ብር መሰብሰብ መቻላቸውን ገልጸዋል።

‎በበጀት አመቱ ዉስጥ የሚሰበሰብ ገቢ ከቀጥታ ታክስ 136 ሚሊዬን 889 ሺህ 855 ብር፣ ቀጥታ ካልሆኑ ታክሶች 5 ሚሊዬን 065 ሺህ 277 ብር እንዲሁም ታክስ ካልሆኑ ገቢዎች 14 ሚሊዬን 977 ሺህ 854 ብር መሆኑን ሀላፊው ገልፀዋል።

‎በመጨረሻም አዲሱ የግብር ጥናት ጨምሮ ሲመጣ ነጋዴዎች ቅሬታ ቢያቀርቡም መድረክ በመፍጠር እና በማወያየት እስካሁን 350 ነጋዴዎች መክፈላቸውን ገልጸው ያልከፈሉ ነጋዴዎቸ ግብር የሚከፍለው ለሀገራችን እድገትና ለውጥ መሆኑን በመገንዘብ የህልውና ጉዳይ እንደሆነና በወቅቱ ግብራቸውን እንዲከፍሉ መልዕክት አስተላልፈዋል።

Address

Moretena Jeru, North Shewa
Martinez, CA
251116880051

Telephone

+251116880051

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Mortena Jeru Werda Communication posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Shortcuts

Share