Gubalafto Wereda Irrigation and Low Land Area's Office

Gubalafto Wereda Irrigation and Low Land Area's Office ጉባላፍቶ ወረዳ መስኖና ቆላማ አካባቢዎች ልማት ጽ/ቤት/Gubalafto Woreda Irrigation and low land area's Office/

07/17/2025
በዛሬው እለት በ014 ቀበሌ ጊምቦራ አስፋሚካኤል የመስኖ ፕሮጀክት ጥገናን አስመልክቶ የተደረገ የቅድመ ዝግጅት የህዝብ ግንኙነት ተግባራት ተከናወነቀን 10/09/2017 በተግባቦት ላይ የተመሰ...
05/19/2025

በዛሬው እለት በ014 ቀበሌ ጊምቦራ አስፋሚካኤል የመስኖ ፕሮጀክት ጥገናን አስመልክቶ የተደረገ የቅድመ ዝግጅት የህዝብ ግንኙነት ተግባራት ተከናወነ
ቀን 10/09/2017 በተግባቦት ላይ የተመሰረተ የህዝብ ግንኙነት መፍጠርና የመስኖ ተጠቃሚው ማህበረሰብን የግንባታው ባለቤት በማድረግ እና ጠንካራ የመስኖ ውሃ ተጠቃሚዎች ማህበር አመራሮች በማዋቀርና ህጋዊ መሰረት በማስያዝ የግንባታ ጥራትንና ፍጥነትን ማዕከል በማድረግ ለመስኖ ግንባታው ሁሉም የቀበሌው አካል ተባባሪ እንድሆን ሰፊ ውይይት ተደርጓል።

05/09/2025
04/24/2025

በሰሜን ወሎ ዞን ጉባላፍቶ ወረዳ ከ19 ሚሊየን ብር በላይ በሆነ ወጭ እየተገነባ የሚገኘውና 105 ሄክታር ሬት በማልማት 411 አርሶ አደሮችን ተጠቃሚ የሚያደርገው የመስኖ ካናል ግንባታ በተያዘለት ጊዜ ለማጠናቀቅ እየተሰራ ነው።

የወረዳው መስኖና ቆላማ አካባቢዎች ልማት ጽ/ቤት ሀላፊ አቶ ጌታቸው ወንደ የመስኖ ፕሮጀክቱ በአነስተኛ ይዞታ መስኖ ፕሮጀክት/SHIDP/ የገንዘብ ድጋፍ በ19ሚሊየን 968ሺህ 428.48 ብር እየተገነባ ሲሆን ፕሮጀክቱ ሲጠናቀቅ 105 ሄክታር ማልማት የሚችልና 411 አርሶ አደሮችን ተጠቃሚ ማድረግ እንደሚችል በመግለጽ ግንባታው አሁን በጥሩ አፈጻጸም ላይ የደረሰ ሲሆን ለቀሪ ስራዎችን በተያዘላቸው የጊዜ ሰሌዳ በማጠናቀቅ አገልግሎት እንድሰጥ እየሰራን ነው ብለዋል።

04/15/2025
04/11/2025
የጉባላፍቶ ወረዳ ቆላማ አካባቢዎች ልማት ጽ/ቤት በ05 ቂሌ አዳሚ ቀበሌ ቡርቃ በሚገኘው አካባቢ የግፊት አነስተኛ የመስኖ ፕሮጀክት ለመገንባት ከሀራ ከተማ አስተዳደር ጋር የቅድመ ዝግጅት ውይ...
04/06/2025

የጉባላፍቶ ወረዳ ቆላማ አካባቢዎች ልማት ጽ/ቤት በ05 ቂሌ አዳሚ ቀበሌ ቡርቃ በሚገኘው አካባቢ የግፊት አነስተኛ የመስኖ ፕሮጀክት ለመገንባት ከሀራ ከተማ አስተዳደር ጋር የቅድመ ዝግጅት ውይይት አካሄደ።

ይህ ፕሮጀክት 60.5 ሄክታር መሬት ላይ መስኖን በመጠቀም 163 የሚሆኑ አርሶ አደሮችን ተጠቃሚ ለማድረግ ያለመ ነው።

በውይይቱ ላይ የሀራ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ ሙሐመድ ሰኢድ፣ የከንቲባ ጽ/ቤት ኃላፊ ኡመር ተስፋዬ፣ የፋይናንስ ኃላፊ ሰኢድ አስናቀ እንዲሁም የጉባላፍቶ ወረዳ ቆላማ አካባቢዎች ልማት ጽ/ቤት ኃላፊ ጌታቸው ወንዴ እና የጽ/ቤቱ ባለሙያዎች ተገኝተዋል።

የሀራ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ ሙሐመድ ሰኢድ፣ ፕሮጀክቱ በአካባቢው የምግብ ዋስትናን ከማረጋገጡም በላይ የአርሶ አደሮችን የኑሮ ደረጃ በማሻሻል ረገድ ትልቅ ሚና እንደሚጫወት ገልጸዋል። ከንቲባው አክለውም የሀራ ከተማ አስተዳደር ይህንንና መሰል የልማት ሥራዎችን ለመተግበር ቁርጠኛ መሆኑን አረጋግጠዋል።

የጉባላፍቶ ወረዳ ቆላማ አካባቢዎች ልማት ጽ/ቤት ኃላፊ ጌታቸው በበኩላቸው ፕሮጀክቱ ለቀበሌው አርሶ አደሮች ትልቅ ተስፋ የሚሰጥ መሆኑን ጠቁመዋል። ኃላፊው ይህንን ፕሮጀክት በተቻለ ፍጥነት ወደ ትግበራ ለመቀየር ከሀራ ከተማ አስተዳደር ጋር በቅርበት ለመስራት ዝግጁ መሆናቸውን አስታውቀዋል።

በውይይቱ ወቅት ተሳታፊዎቹ ለፕሮጀክቱ ስኬታማነት የሚያግዙ የተለያዩ ሃሳቦችን ያቀረቡ ሲሆን፣ በቀጣይነትም የቴክኒክና ሌሎች ዝርዝር ጉዳዮች ላይ በጋራ ለመስራት ተስማምተዋል።

ይህ የቡርቃ የግፊት አነስተኛ መስኖ ፕሮጀክት ተግባራዊ ሲሆን በአካባቢው የግብርና ምርት በከፍተኛ ደረጃ እንደሚጨምርና የአርሶ አደሮቹ የኑሮ ሁኔታ እንደሚሻሻል ይጠበቃል።

የሀራ ከተማ አስተዳደርና የጉባላፍቶ ወረዳ ቆላማ አካባቢዎች ልማት ጽ/ቤት ይህንን የልማት ሥራ በጋራ በመተባበር ለማሳካት ቁርጠኛ መሆናቸውን አረጋግጠዋል።

ሀራ ከተማ ኮሙኒኬሽን

በጉባላፍቶ ወረዳ ጃርሳ 010 ቀበሌ በሽድፕ ካፒታል በጀት የሚገነባው የመስኖ ካናል ማራዘም ፕሮጀክት የቁፋሮ ስራ ተጀምሯል
03/28/2025

በጉባላፍቶ ወረዳ ጃርሳ 010 ቀበሌ በሽድፕ ካፒታል በጀት የሚገነባው የመስኖ ካናል ማራዘም ፕሮጀክት የቁፋሮ ስራ ተጀምሯል

Address

Wolss
Dessie, WV
NO

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Gubalafto Wereda Irrigation and Low Land Area's Office posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Share