West denbiya woreda court

West denbiya woreda court ለፍትህ መስፈን ሁሉም ድርሻ አለው::
ፍርድ ቤት ደግሞ የፍትህ ሚዛኗ ነው :

ፍትሕን በታማኝነት!!!

 #ሰኞ፡- እኛን እናስተዋውቅዎ (ክፍል አራት)የባለጉዳዮች ግዴታዎች በፍርድ ቤት!ሰላም ውድ የገፃችን ቤተሰቦች🙏! "እኛን እናስተዋውቅዎ" በተሰኘው አምዳችን የፍርድ ቤታችንን አሰራር፣ እሴቶች...
14/09/2026

#ሰኞ፡- እኛን እናስተዋውቅዎ (ክፍል አራት)
የባለጉዳዮች ግዴታዎች በፍርድ ቤት!

ሰላም ውድ የገፃችን ቤተሰቦች🙏! "እኛን እናስተዋውቅዎ" በተሰኘው አምዳችን የፍርድ ቤታችንን አሰራር፣ እሴቶች እና መርሆች ማካፈላችንን ቀጥለናል። ባለፈው ክፍል (ክፍል ሶስት) ላይ የፍርድ ቤት አገልጋዮች የህግ ምክር መስጠት ለምን እንደማይችሉ እና የህግ ግንኙነት ድንበራችንን ማየታችን ይታወሳል። ዛሬ ደግሞ የፍትህ ስርአቱ የተሳለጠ እና ቀልጣፋ እንዲሆን እናንተ ውድ ባለጉዳዮች ወደ ተቋማችን ስትመጡ ልታሟሏቸው ስለሚገቡ መሰረታዊ ግዴታዎች እናወራለን!

የፍርድ ሂደት የተሳካ የሚሆነው ዳኞች እና ሰራተኞች ብቻ ሳይሆኑ፣ ባለጉዳዮችም የሚከተሉትን የድርሻቸውን ሲወጡ ነው፦
#1. የፍርድ ቤቱን ክብርና ስነ-ስርዓት ማክበር፦
ፍርድ ቤት የፍትህ አደባባይ በመሆኑ የፍርድ ቤቱን ክብር የሚመጥን አለባበስ መልበስ፣ በችሎት ውስጥ ፀጥታን ማክበር እና የዳኛውን ትዕዛዝ ያለማንገራገር መፈፀም የሁሉም ባለጉዳይ የመጀመሪያው ግዴታ ነው።
#2. ቀጠሮን ማክበር እና ጊዜን በአግባቡ መጠቀም፦
ለተሰጠዎት ቀጠሮ በሰዓቱ መገኘት ፍትህ እንዳይጓተት ትልቅ አስተዋፅዖ አለው። አንድ ባለጉዳይ ሲዘገይ የራሱን ብቻ ሳይሆን የሌሎችንም ተገልጋዮች ጊዜ ያባክናል፣ የፍርድ ሂደቱንም ያጓትታል::
#3. እውነተኛ ማስረጃ እና ትክክለኛ መረጃ ማቅረብ፦
ለፍርድ ቤቱ የሚሰጡት ማንኛውም ቃል፣ ማመልከቻ ወይም ማስረጃ እውነተኛ መሆን አለበት። ሀሰተኛ ማስረጃ ማቅረብ ፍትህን ከማዛባት ባለፈ በህግ የሚያስጠይቅ ከባድ ወንጀል ነው።
#4. ከህገ-ወጥ አሰራሮች መቆጠብ፦
ባለፈው ክፍላችን እንዳነሳነው፣ ሰራተኞችም ሆኑ ዳኞች ገለልተኛ ሆነው ማገልገል አለባቸው። ስለዚህ ባለጉዳዮችም ይህንን ተረድተው በማንኛውም ሁኔታ ሰራተኞችንና ዳኞችን በስጦታ፣ በጉቦ፣ በዝምድና ወይም በሌላ ህገ-ወጥ መንገድ ለማግባባት መሞከር የለባቸውም። ፍትህ የሚገኘው በእውነት እንጂ በግንኙነት አይደለም!

#ግዴታውን ያወቀና ስርዓቱን ያከበረ ባለጉዳይ ለፈጣን ፍትህ መሰረት ነውና እውነተኛ ፍትህ የሚሰፍነው፣ የፍርድ ቤት አገልጋዮች በገለልተኝነት ፀንተው ሲሰሩ ፣ ባለጉዳዮችም የድርሻቸውን ግዴታ ሲወጡ ነው!

በድጋሚ 2019 ዓመት በሁሉም ረገድ ስኬታማ የምትሆኑበት ዓመት እንዲሆን እየተመኘን(https://www.facebook.com/100064507611552/posts/1497592959067610/?app=fbl)🌼🌼 በቀጣይ ክፍላችን ስንገናኝ እነዚህን ግዴታዎች ማይወጣ ባለጉዳይ ላይ ያለውን የሕግ ተጠያቂነት የምናይ ይሆናል፤ እስከቀጣይ ሳምንት ቸር እንሰንብት 🙏

መስከረም 04 ቀን 2019 ዓ.ም
✍️ ጯሂት
⚖️ "ፍትሕን በታማኝነት!"

🗣️ ሀሳብ አስተያየትዎን በኮመንት ያካፍሉን!
🤝 ቤተሰብ ይሁኑ! አዳዲስና ወቅታዊ መረጃዎችን ለማግኘት የፌስቡክ ገፃችንን ላይክ እና ሼር ያድርጉ👇
[https://www.facebook.com/100064507611552](https://www.facebook.com/100064507611552)

11/09/2026
የፍርድ ቤታችን ዳኞችና አስተዳደር ሰራተኞች እንዲሁም በሀገር ውስጥና ውጭ ላላችሁ ኢትዮጵያውያን በሙሉ እንኳን ለ2019 ዓ.ም አዲስ ዓመት አደረሳችሁ:: ዘመኑ ፍትህ የሰፈነበት የሕግ የበላይ...
10/09/2026

የፍርድ ቤታችን ዳኞችና አስተዳደር ሰራተኞች እንዲሁም በሀገር ውስጥና ውጭ ላላችሁ ኢትዮጵያውያን በሙሉ እንኳን ለ2019 ዓ.ም አዲስ ዓመት አደረሳችሁ:: ዘመኑ ፍትህ የሰፈነበት የሕግ የበላይነት የተረጋገጠበት የስኬት ዘመን እንዲሆንላችሁ እንመኛለን::

የምዕራብ ደምብያ ወረዳ ፍርድ ቤት
🌼🌼🌼እንቁጣጣሽ!🌼🌼🌼

በቅድሚያ እንኳን ለ2019ዓ/ም  የዘመን መለወጫ በዓል በሠላም  አደረሳችሁ  አደረሠን!!        #ረዕቡ| ፍትሕና ተግዳሮቶቹ          #ክፍል 3 ውድ የገፃችን ተከታታዮች ባለፈው  ...
09/09/2026

በቅድሚያ እንኳን ለ2019ዓ/ም የዘመን መለወጫ በዓል በሠላም አደረሳችሁ አደረሠን!!

#ረዕቡ| ፍትሕና ተግዳሮቶቹ
#ክፍል 3

ውድ የገፃችን ተከታታዮች ባለፈው ሳምንት የፍትሕ ተግዳሮቶች በሚል አምድ ቆይታ ማደረጋችን ይታወሳል በዛሬው ቀይታችን ደግሞ ለችግሮች መፋትሔ ያልናቸውን ነጥቦች ልናጋራችሁ ወደድን መልካም ንባብ !!
በዳኝነት ስርዓቱ የሚከሰቱ ችግሮችን ለማስወገድ ሊወሰዱ የሚገባቸው መፍትሔዎች:-
1. ​የህግ ግንዛቤ ማሳደግ፡ ለህብረተሰቡ ስለ መብቱ እና ግዴታው እንዲሁም ተቋማት ስላላቸው ህጋዊ አሰራር ቀጣይነት ያለው ትምህርት መስጠት በዚህ ጉዳይ የምዕራብ ደንቢያ ፍርድቤትም ያለማቋረጥ ዘወትር እየተገበረው የከረመ ተግባራችን ሆኖ የቆየ ቢሆንም በዚህ ዓመትም ይበልጥ አጠናክሮ በመስራት ብዙ ሕገ ወጥ ተግባራትን ማስተካከል ተችሏል።
2. ​ነጻ የህግ ድጋፍ ማጠናከር፡ አቅም ለሌላቸው ደንበኞች የነጻ ህግ ድጋፍ አገልግሎት (Legal Aid) በማስፋፋት የህገ ወጥ ደላሎችን የማህበረሰብ ብዝበዛ ማስቀረት ይህ አገልግሎትም በያዝነው 2018 ዓ/ም በወረዳችን በሳተላይት ደረጃ የቆየ ሲሆን በ2019 በጀት አመት ከጎንደር ዮንቨርስቲ ህግ ትምህርት ቤት ጋር በመተባበር ለመስራት እንቅስቃሴ ተጀምሯል:: ይህም ተግባራዊ ሲደረግ ብዙ ዘርፈ ብዙ ሚና ይኖረዋል። ድምፅ ሌላቸው ወገኖችም ድምፅ መሆን ያስችላል ።
3.​ጥፋት በሚፈጽሙ አካላት ባለሙያዎችና ዳኞች እንዲሁም ባለጉዳዮች ላይ ፈጣን እና ግልጽ በተቀመጡት ሕጎች አግባብ የተጠያቂነት ሥርዓቱን ማጠናከርና የተወሰዱ አስተማሪ እርምጃዎች ማሳወቅ።
4.​የባለሙያዎችን የኑሮ ሁኔታ ማሻሻልና ለሙስና የመጋለጥ እድልን የሚቀንሱ የማበረታቻ ሥርዓቶችን መፍጠር።
5.የሕግ የበላይነትን ማረጋገጥ እና የተቋማቱን መዋቅራዊና የፋይናንስ ነፃነት በሕግ ማስከበር:- በህግ በሚወሰነው መሠረት ከሚሰጡት አገልግሎት ጋር ተመጣጣኝ በቂ በጀት እና ዘመናዊ መሣሪያዎችን ማሟላት ከዚህም ጋር ብቃትና ጥራትን አካቶ ሊሠራ የሚችል የሰው ሀይል ስምሪትን መፈፀም።

በሌላ በኩል በፍርድ ቤት ግቢ እና አካባቢ የሚደረጉ የፍትሕ የደላላ እንቅስቃሴዎችን በጥብቅ በመከታተል እና ህጋዊ እርምጃ በመውሰድ የፍትሕን ሚዛን ሚያዛቡ የገንዘብ ጥመኞችን ሥራ ሙሉ በሙሉ ለማስወገድ በተጠናከረ መልኩ ሲሰራ የቆየና እየተሠራበት ያለ ለወደፌትም ተጠናክሮ የሚሰራ መሆኑን ማሳወቅ እንወዳለን።

👉 የፍትህ ደላሎች ከገጠመዎትም በእወነተኛ መረጃና ማስረጃ ተንተረሰው ይጠቁሙ!!

ጳጉሜ 04 ቀን 2018 ዓ.ም
ጯሂት
​ "ፍትሕን በታማኝነት!"
​👇 እርሶም ሀሳብና አስተያየትዎን በኮሜንት መስጫው ላይ ያካፍሉን!
​@ የፌስቡክ ገጻችንን Like እና Follow በማድረግ አዳዲስና ወቅታዊ መረጃዎችን ያግኙ፦
https://www.facebook.com/profile.php?id=100064507611552

 #ማክሰኞ ''  ምን እናስተካክልልዎ? ክፍል 3​ውድ የገጻችን ቤተሰቦች፣ እንደምን ሰነበታችሁ!በቅድሚያ እንኳን ለ2019 ዓ.ም አዲስ ዓመት ዋዜማ በሰላም አደረሳችሁ! 🌻🌼     ​የተቋማችን...
08/09/2026

#ማክሰኞ '' ምን እናስተካክልልዎ? ክፍል 3
​ውድ የገጻችን ቤተሰቦች፣ እንደምን ሰነበታችሁ!

በቅድሚያ እንኳን ለ2019 ዓ.ም አዲስ ዓመት ዋዜማ በሰላም አደረሳችሁ! 🌻🌼
​የተቋማችንን የአገልግሎት አሰጣጥ ይበልጥ ተደራሽ፣ ፈጣን እና ጥራት ያለው ለማድረግ በሚደረገው ጥረት:- በፍርድ ቤታችን ውስጥ ካሉት ሂደቶች መካከል አንዱና ዋናው ከሆነው ፋይናንስና ንብረት አስተዳደር (ግ/ፋ/ን/አስ) የስራ ሂደት ጋር የሚዲያ ክንፍ ኮሚቴያችን ቆይታ አድርጓል።
​በቆይታችንም:- የሂደቱን ተወካይ ቡድን መሪና ሂሳብ ሰራተኛ የሆኑትን ወ/ሮ አበበች የሻንበልን “የምዕራብ ደምቢያ ወረዳ ፍርድ ቤት ምን እንዲያስተካክልልዎ ይፈልጋሉ?” ስንል ጠይቀናቸዋል። እሳቸውም የሚከተሉትን ዋና ዋና ነጥቦች አብራርተውልናል፡-
​1. የሰው ሀይል እጥረት እና የስራ ጫና
​የሂደቱ ስራ ከፋይናንስ ጋር የተያያዘ በመሆኑ ከፍተኛ የስራ ጫና አለበት።
​ሁለት (2) ክፍት መደቦች በሰራተኛ ያልተሸፈኑ በመሆናቸው፣ ተወካይ ቡድን መሪዋ ከራሳቸው ስራ በተጨማሪ የሂደቱንና የሌላ አንድ ሂሳብ ሰራተኛን ስራ ደርበው (በአጠቃላይ የ2 ሰው ስራ) እየሰሩ መሆናቸውን።​በዚህም ምክንያት የአመት እረፍታቸውን እንኳ በአግባቡ መጠቀም አለመቻላቸውን (ይህንም ኮሚቴያችን በአካል ተገኝቶ ታዝቧል::) የገለፁ ሲሆን አክለውም ከስራ ጫናው በተጨማሪ ከፍተኛ ተጠያቂነት ያለበት ቦታ በመሆኑ ተቋሙ ከሚመለከተው አካል ጋር ተነጋግሮ አስፈላጊውን ጥረት አድርጎ የሰው ሀይል እንዲያሟላላቸው ጠይቀዋል።
በተጨማሪም የቢሮ ችግር ያረጀና ሊፈርስ የቀረበ መሆኑን በመግለፅ ለስራ እጅግ አስቸጋሪ ነው፤ ተፀድቶም ስለማይጸዳ በውስጡ ያሉ ኮምፒውተሮች እና የሂሳብ መዝገቦች በከፍተኛ ሁኔታ ለብልሽት እየተዳረጉ ይገኛሉ።​የኤሌክትሮኒክስ እቃዎች በቫይረስና በአቧራ እየተጠቁ በመሆናቸው ስራዎችን በአግባቡ ለማከናወን መሰናክል ሆኗል ለጤናችንም አደጋ ደቅኗል በማለት ስለበጀት አጠቃቀም ለጠየቅናቸው ጥያቄም ከበጀት አጠቃቀም ጋር ተያይዞ ​በ2018 ዓ.ም የበጀት ዓመት ለስራ ማስኬጃ ከተመደበው 1,279,674 (አንድ ሚሊዮን ሁለት መቶ ሰባ ዘጠኝ ሺህ ስድስት መቶ ሰባ አራት) ብር ውስጥ ለአላቂና ቋሚ እቃዎች (አንድ ላፕቶፕ፣ስምንት ገስት ቸሮች,ጠረፔዛዎች, ወንበሮች,ወረቀት፣ እስክርቢቶ፣ የመዛግብት መክፈቻ ፎልደር፣ ክላሰር፣ ኬንት፣ ለሂሳብ የሚያስፈልጉ ደረሰኞችና ሌጀሮች ወዘተ.) 762,230.17 (ሰባት መቶ ስልሳ ሁለት ሺህ ሁለት መቶ ሰላሳ ብር ከ17 ሳንቲም) ለግዥ ውሏል። ​ይህም ወጭ የግብያ ጥናት ለማድረግ,ግዥ ለመፈፀም, የጨረታ ሰንድ ለመሸጥ, ግዥ ለማፅደቅ, የትራንስፖርት ዕቃ ማስጫኛ, ውል ለማፅደቅ ወዘተ ለሚሄዱ አካላት የሚከፈል አበል፣ የመብራት፣ የውሃ እና የስልክ ወጪዎችን ሳይጨምር ነው በማለት አብራርተውልናል።
​የተገዙ ንብረቶች ጥቅማቸው ለማን ነው? ስንል ላነሳንላቸው ጥያቄ ደግሞ ባለጉዳዩ ቁሳቁሶች ከውጭ አምጣ/ግዛ ቢባል ኖሮ ያወጣ የነበረውን 762,230.17 ብር ያወጣ ነበር ስለዚህ ተጠቃሚው ባለጉዳዩ ነው በማለት መልሰዋል::
​ ስለሆነም ፍትህ ፈላጊው ማህበረሰብ፣ የሚመለከተው የመንግስት አካል፣ በሀገር ውስጥና ከሀገር ውጭ የምትገኙ የግል ድርጅቶች እንዲሁም ባለሀብቶች አሁናዊ ምስሉን በመመልከትና መጦ በመጎብኘት ድጋፍ በማድረግ የበኩላችሁን ትብብር እንድታደርጉልን ጥሪያችንን እናቀርባለን።

​ ጳጉሜ 03 ቀን 2018 ዓ.ም
ጯሂት
​ "ፍትሕን በታማኝነት!"

 #ሰኞ፡- እኛን እናስተዋውቅዎ (ክፍል ሶስት )የፍትህ ሚዛን እና የህግ ድንበራችን!ሰላም ውድ የገፃችን ቤተሰቦች🙏! "እኛን እናስተዋውቅዎ" በተሰኘው አምዳችን የፍርድ ቤታችንን አሰራር፣ እሴ...
07/09/2026

#ሰኞ፡- እኛን እናስተዋውቅዎ (ክፍል ሶስት )
የፍትህ ሚዛን እና የህግ ድንበራችን!

ሰላም ውድ የገፃችን ቤተሰቦች🙏! "እኛን እናስተዋውቅዎ" በተሰኘው አምዳችን የፍርድ ቤታችንን አሰራር፣ እሴቶች እና መርሆች ማካፈላችንን ቀጥለናል። ዛሬ ደግሞ የፍትህ ስርአቱን ንፅህና ስለሚጠብቅ አንድ ጥብቅ አሰራራችን እናስተዋውቃችኋለን፤ ይኸውም የፍርድ ቤት አገልጋዮች እና የባለጉዳዮች የህግ ግንኙነት ድንበር ነው!

ወደ ፍርድ ቤታችን ለጉዳይ ሲመጡ፣ ዳኞችን ወይም የፍርድ ቤት ሰራተኞችን *"እስኪ ምከሩኝ፣ ምን ልስራ? እንዴት ልሞግት?"* ብለው ሲጠይቁ አስተውለው ያውቃሉ? ይህ ከልብ የመነጨ የዕርዳታ ጥያቄ ቢሆንም፣ በህግ ግን በጥብቅ የተከለከለ ነው! ምክንያቱን እናካፍላችሁ፦

#1. ሚዛናችን እንዳያጋድል (ገለልተኝነት)፦
ፍርድ ቤታችን የሁለቱም ወገኖች (ከሳሽም ሆነ ተከሳሽ) እኩል መቆሚያ፣ ገለልተኛ መድረክ ነው\! አንድ ዳኛ ወይም የፍርድ ቤት ሰራተኛ ለአንዱ ወገን የህግ ምክር ከሰጠ፣ ያቺ የፍትህ ሚዛን ወዲያውኑ ታጋድላለች። ዳኝነታችን ማየት ያለበት የቀረበውን ማስረጃ እንጂ የወገንን ፊት አይደለም! እኛን እኛ የሚያደርገን ይኸው ለማንም የማያዳላው ገለልተኝነታችን ነው።

#2. ጥብቅ የህግ ክልከላ እና ተጠያቂነታችን፦
አንድ የፍርድ ቤት ዳኛም ሆነ ሰራተኛ ባለጉዳይን ማማከር በህግ ፈፅሞ የተከለከለ ነው! ሰራተኞቻችን ይህንን ህግ ጥሰው ለባለጉዳይ ምክር ቢሰጡ፣ ከስነ-ምግባር ጥሰት አልፎ **ከባድ የህግ ተጠያቂነት (ቅጣት)** ያስከትልባቸዋል። ስለዚህ አገልጋዮቻችን የህግ ምክር የማይሰጡት ሊረዱዎት ፈቃደኛ ስላልሆኑ ወይም ስለጨከኑ ሳይሆን፣ የፍትህ ስርዓቱን ንፅህና ለመጠበቅ እና ህግን ማክበር ግዴታቸው ስለሆነ ነው!

#3. ለውድ ባለጉዳዮቻችን የተላለፈ ማሳሰቢያ፦
ወደ ፍርድ ቤታችን ሲመጡ መዝገብዎ የት እንደደረሰ፣ ወይም የትኛው ክፍል መሄድ እንዳለብዎ የመረጃ ሰራተኞቻችንን በነፃነት መጠየቅ ይችላሉ፤ በደስታ ያስተናግዱዎታል። ነገር ግን *"ክሴን እንዴት ላዘጋጅ? ምን ብዬ ልከራከር? ማንን ምስክር ልጥራ?"* የሚሉ የህግ ምክሮችን ከዳኞችም ሆነ ከሰራተኞች ከመጠየቅ ይቆጠቡ። የህግ ምክር ከፈለጉ፣ ፈቃድ ካላቸው ጠበቆች ወይም ነፃ የህግ ድጋፍ ከሚሰጡ ተቋማት ማግኘት ይችላሉ።

#ዳኛ መካሪ ከሆነ - ሚዛን ያጋድላል፤ ሰራተኛ ጠበቃ ከሆነ - እውነት ትሰወራለች! እውነተኛ ፍትህ የሚሰፍነው፣ የፍርድ ቤት አገልጋዮች በገለልተኝነት ፀንተው ሲሰሩ ፣ ባለጉዳዮችም ይህንን አውቀው ስርዓቱን ሲያከብሩ ብቻ ነው!::

ጳጉሜ 02 ቀን 2018 ዓ.ም
ጯሂት
"ፍትሕን በታማኝነት!"

🗣️ ሀሳብ አስተያየትዎን በኮመንት ያካፍሉን!
🤝 **ቤተሰብ ይሁኑ\!** አዳዲስና ወቅታዊ መረጃዎችን ለማግኘት የፌስቡክ ገፃችንን ላይክ እና ሼር ያድርጉ👇
[https://www.facebook.com/100064507611552](https://www.google.com/search?q=https://www.facebook.com/100064507611552)

የማዕከላዊ ጎንደር ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤት /High Court Of Central Gondar Page West Dembiya Communication East Dembiya Wereda Court የአማራ ክልል ጠቅላይ ፍርድ ቤት/ Supreme Court of Amhara Region ምዕራብደምብያ ወረዳ ፍርድቤት

ቤተሰብ ይሁኑ!የምዕራብ ደምቢያ ወረዳ ፍርድ ቤትን የፌስቡክ ገፅ በመከተል አዳዲስና ወቅታዊ መረጃዎች ፈጥነው እንዲደርሶት ያድርጉ! ሊንኩን ይጫኑ 👇[https://www.facebook.com/p...
06/09/2026

ቤተሰብ ይሁኑ!
የምዕራብ ደምቢያ ወረዳ ፍርድ ቤትን የፌስቡክ ገፅ በመከተል አዳዲስና ወቅታዊ መረጃዎች ፈጥነው እንዲደርሶት ያድርጉ! ሊንኩን ይጫኑ 👇
[https://www.facebook.com/profile.php?id=100064507611552](https://www.facebook.com/profile.php?id=100064507611552)

West Dembiya Communication Gondar Ketema woreda court page East Dembiya Wereda Court ላይ አርማጭሆ ወረዳ ፍርድ ቤት/Lay Armachiho Woreda Court Page የማዕከላዊ ጎንደር ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤት /High Court Of Central Gondar Page Oromo Special Zone High Court East Gojjam Zone high court/የምስራቅ ጎጃም ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤት Amara supreme Court debre birhan division /የአማራ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ደብረብርሀን ምድብ Dessie City Administration Woreda Court/የደሴ ከተማ አስተዳደር ወረዳ ፍ/ቤት ምዕራብደምብያ ወረዳ ፍርድቤት Wondale Ayalew የአማራ ክልል ጠቅላይ ፍርድ ቤት/ Supreme Court of Amhara Region Alie Endalkachew West denbiya woreda court Chilga woreda Court Page/ጭልጋ ወረዳ ፍርድ ቤት

 #አርብ |  ፍርድ ቤታችን በዚህ ሳምንት   👏 ሰላም ውድ የገፃችን ተከታዮች🙏   የምዕ/ ደም/ወ/ፍ/ ቤት የሚዲያ በባለፈው አርብ ዘገባችን ፍርድ ቤታችን በዚህ አመት በሚል አምድ የ2018...
04/09/2026

#አርብ | ፍርድ ቤታችን በዚህ ሳምንት

👏 ሰላም ውድ የገፃችን ተከታዮች🙏

የምዕ/ ደም/ወ/ፍ/ ቤት የሚዲያ በባለፈው አርብ ዘገባችን ፍርድ ቤታችን በዚህ አመት በሚል አምድ የ2018 ዓ.ም አበይት የስራ ክንውኖችን ይዘንላችሁ ቀርበን ነበር ። በዛሬው ፕሮግሮማችን ደግሞ ፍርድ ቤታችን በዚህ ሳምንት በሚለውን አምዳችን የሳምንቱን አበይት ስራዎች በአጭሩ ይዘን ቀርበናል::

ምንም እንኳን የዳኞች የእረፍት ጊዜ ቢሆንም ዳኞች በወረፋ እየገቡ ከአስተዳደር ሰራተኛው ጋር በመሆን ጠቅላይ ፍርድ ቤቱ በክረምት እንዲሰሩ የፈቀደውን የጉዳይ አይነቶች እንደ ልጅ ቀለብ፣ ዋስትና እና የመሳሰሉትን መሰረት አድርገው በርካታ መዝገቦች እየሰሩ ይገኛሉ።
የክረምት የስራ ጫና መቀነሱን እንደ ጥሩ አጋጣሚ በመውሰድ በዳታ ቤዝ አድምንስትሬሽን ባለሙያዎች በተደረገ ያላሰለሰ ጥረት ወደ CCMS ሲስተሙ እየተመዘገቡ ያሉት የቆዩ መዛግብቶች ብዛት በዚህ ሳምት ተጠናክሮ ቀጥሎ ከ2000 በላይ ሆኗል።
የፍርድ ቤቱ የሚዲያ ክንፍ ኮሜቴ የዘገባ ስራውን እና የየቀን የኦላይን ውይይቱን አጠናክሮ እየሰራ በየቀኑ በወጣላቸው ፕሮግራም መሰረት ዘገባዎች እየተሰሩ ለገፃችን ተከታዮች እያደረሰ የሚገኝ ሲሆን በዛሬው እለት ማለትም ነሐሴ 29 ቀን 2018 ዓ.ም ኮሜቴው በፍ/ቤቱ ፕሬዘዳት ሰብሳቢነት በአካል በመገናኘት 1ኛ/ የሚዲያ ስራውን ኮሜቴው ከጀመርን ጀምሮ ምን ትምህርት አገኘን ? ምንስ ችግር ገጠመን? እንዴትስ እናስተካክል ? 2ኛ/ ኮሜቴው የተሰጠውን ስራ በአግባቡ እየተወጣ ነው ወይ? በሚሉ በ2 አጀንዳዎች ላይ ሰፋ ያለ ውይይት አድርጎ በውይይቱም ኮሜቴዎች በሚዲያ ስራው ጥሩ እውቀት እንዳገኙበት ገልፀው ሊስተካከሉ የሚገባቸውም ዘገባው ለአንባቢያን እንዳያሰለች አጠር ባለ ፅሁፍ ሰፊ ሀሳብ የማስተላለፍ ልምድ ማዳበር እንዳለብን እንዲሁም በ2ኛው አጀንዳ ላይ በኦላይን ውይይቱ ወቅት ሰአት የሚሸራርፉ ኮሜቴዎች ሰአት መከበር እንዳለበት ተወስኗል።
በመጨረሻም የፍርድ ቤቱ ፕሬዘዳንት ጅማሮው መልካም እንደሆነ ገልፀው ወደፊት ከዚህ በበለጠ ተጠናክሮ መሰራት እንዳለበት አሳስበው ለኮሚቴዎች ላቅ ያለ ምስጋና አቅርበው ስብሰባው ተጠናቋል።

ምዕራብ ደንቢያ ወረዳ ፍርድ ቤት
ጯሂት
ነሐሴ 29 ቀን 2018 ዓ/ም
#ተዘጋጀ:- በምዕ/ደ/ወ/ፍ/ቤት ሚዲያ ክንፍ ኮሜቴ

❤️ #ይወዳጁን 👇

https://www.facebook.com/weste.denbiya

የማዕከላዊ ጎንደር ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤት /High Court Of Central Gondar Page የአማራ ክልል ጠቅላይ ፍርድ ቤት/ Supreme Court of Amhara Region Amara supreme Court debre birhan division /የአማራ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ደብረብርሀን ምድብ West Dembiya Communication

04/09/2026

ምዕራብ ደምብያ ወረዳ ፍርድ ቤት ፍትሐ ብሔር መዝገብ ቤት አሁናዊ ገፅታ!!👇

Address

ምዕራብ ደምብያ :-ጯሂት
Gondar

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when West denbiya woreda court posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Shortcuts

Share