hulu Contact information, map and directions, contact form, opening hours, services, ratings, photos, videos and announcements from hulu, Government Official, 301 N Ripley Street Apt 917, Alexandria, VA.

11/23/2023

ያውቃሉ? 1 ለሰው ልጅ ለደረስበት በደል፤ አመጽን የጸነሰና ያበዛ፤ ዲያብሎስና ሠራዊቱ ናቸው። ሰይጣን አመጸኛ ሆኖ የሰውን ዘር አመጸኛ አደረገው፤ መኖሪያውና መጠቀሚያው አድርጎ ተገለገለበት። ሰው፤ከሰይጣን እስራት፤በንስሀ፤እራሱን ከፈጣሪው ማስታረቅ አልቻለም። ምድርና በእርሷ ላይ ያለ ሁሉ እግዚአብሔር ወዶ የፈጠረው፤አስተካክሎና ሙሉ አድርጎ ያዘጋጀው ለሰው የዕርፍት ህይዎት መኖሪያ ነበር። ግን ሰው በዕምነት በመታዘዝ ለጥቂት ጊዜ ቢኖርባትም አታድርግ የተባለውን ስላደረገ፤አመጽ ስለሰራ፤ ቃልኪዳኑን ሰለ አፈረሰ፤ፍርድ ተፈረደበት፤ወደ ጨለማው ዓለም ተጣለ፤የእግዚአብሔር ክብር ተለየው፤ለሰይጣን መኖሪያው ሆነ፤ በሰውና በእግዚአብሔር መካከል ህብረት ተቋረጠ። ሆኖም እግዚአብሔር፤ እንደ አባትነቱ፤ በአምሳሉ የፈጠረውንና የሚወደውን ሰው በእራሱ ሊተወው አልፈቀደም። እንደውም በተለያዩ ቃል ኪዳኖች አበረታታው፤ግን ሰው በሰይጣን ተንኮል ተሸነፈ፤ ሠላሙን አጣ፤ ድህንትና ብስቁልና አገኘው፤ መራራነት፤ ክፋት፤ ጥላቻ፤ ቁጣና ቂም ባህሪ ወረሰው። እንደውም ይበልጥ እግዚአብሔርን አለማወቅ፤ መመሪያዎቹን አለመታዘዝ፤ እርሱ ከሚጠላቸው ነገር አለመራቅ፤ በተለይም በጣኦት አምልኮ መታሰር በሰውና በአምላክ መካከል ይጠበቅ የነበረውን ህብረት አደከመው፤ እግዚአብሔርን ሰውን በመፍጠሩ ማዘን ደረጃ አደረሰው ቁጣውንም ጨመረው። ሆኖም፤ በደም በተከፈለ ዋጋ፤ የእግዚአብሔር ልጅ ክርስቶስ ያመኑትን ሁሉ ከዘላለማዊ ሞት አዳነ፤ ያመኑትም ንብረቱ ሆኑ። በአንጻሩ ሰው በክርስቶስ ካላመነ ወይም ምርጫው ዲያብሎስ ከሆነ፤ በህይዎት ዘመን ሁሉ የሚከተለው አመጽ፤ በሽታ፤ ድህነት፤ ርሃብ፤ ጦርነት፤ክፋትና ብሎም ዘላለማዊ ሞት ሆነ። ከእግዚአብሔር ወይም ከዲያብሎስ መምረጥ፤ መወሰን የራሱ የግለሰቡ ምርጫ ሆነ።

ያውቃሉ? እግዚአብሔር አያስገድድም፤ የእርሱ ላልሆነ ሰው ህይወት ጣልቃ አይገባም፤ አያድንም። እግዚአብሔርን ለመምረጥ ግን ቃሉን ማወቅ፤ማመንና መታዘዝ ብቻ ነው። ምርጫችን ወይም ውሳኔአችን የፍቅር አምላክ መከተል ሲሆን፤ ቀሪውን ዘመናችንን በተረጋገጠ መንገድ ቅዱስ ቃሉ ይመራናል። እርሱ አልቻልንም ስንለው ያስችላል፤ አናውቅም ስንለው ያሳውቃል፤ ፍቅሩ ወሰን የለውም፤ ጸጋውም ብዙ ነው፤ እጃችንን ይይዘናል፤ ከእርሱ ሊንጥቀን የሚችል ምንም ሀይል የለም፤ አይኖርም። ስንጸልይ ጽሎታችን ይሰማል መልስም እናገኛለን፤ ከበሽታችን እንፈወሳለን፤ እንደውም በሽታ ወደ እኛ አይመጣም። ከስሞች በላይ ስም የሆነው ብቸኛ የኢየሱስ ክርስቶስ ስም ከእስራት ሁሉ ነጻ ያወጣናል። በእግዚአብሔር እና በልጁ ስናምን የዘላለም ህይዎት ይሰጠናል፤ ሠላማችን፤ ጥበቃችን፤ በረከታችን፤ እምነታችን ከላይ ከመላኮታዊ አባት በፍቅሩ ይፈስልናል። የምንኖረውም ሁሉ እንደ እርሱ ፈቃድና የእውነት መንፈስ በሚሰጠን ጸጋ ነው፤ አንደክምም፤ አንባክንም። ይህ ሲሆን የዚህ ዓለም ገዥ ከእኛ ይሸሻል፤ ማንነታችን የክርስቶስ ስለሚሆን ስይጣን ምንም ማድረግ አይችልም። እንደውም የእግዚአብሔር ቃል ዕውቀታችን በጨመረ መጠን ማንነታችን አዲስና ኢየሱስን የመምስል ማነነት ይሆናል፤ ሁሉ እንደ እርሱ ፈቃድ ይሆናል፤ ክርስቶስን ለብስን እንመላለሳለን። ሞተንም ኖረንም ከአምላካችን የሚለየን ምንም የለም፤ እርሱ ለዘላለም ይኖራል፤ እኛም በልጁ ባኢየሱስ ጥላ ሥር፤ ለዘላለም አብረን በህይዎት እንኖራለን። ስለዚህ ይህን እውነት ማወቅ ግዴታ ነው፣ በእምነት፤ ፈጣሪን በመታዘዝ፤ በቅድስና መኖር መቻል ብቸኛ መንገድ ነው።

Address

301 N Ripley Street Apt 917
Alexandria, VA
22304

Telephone

+13016788254

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when hulu posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Share