Embassy of Ethiopia, Sweden

Embassy of Ethiopia, Sweden It is a governmental organization with many stakeholders in the world. Official page of the Ethiopian Embassy in Stockholm, Sweden

20/07/2022
18/07/2022

Congratulations to all Ethiopians on winning GOLD at the world athletics championship by our heroines.

12/07/2022
11/07/2022

የ20/80 ባለሶስት መኝታ የጋራ መኖሪያ ቤት ዕጣ አለመውጣትን አስመልክቶ የተሰጠ ማብራሪያ
*************************

እንደሚታወቀው የከተማ አስተዳደሩ ባሳለፍነው ሳምንት የ20/80 የ14ኛ ዙር የ40/60 3ኛ ዙር የጋራ መኖርያ ቤት እጣ ማውጣቱ ይታወሳል።

ይህንን ተከትሎ በ20/80 ፕሮግራም የባለሶስት መኝታ ቤት ተመዝጋቢዎች በእጣው አለመካተትን መነሻ በማድረግ ከአንዳንድ ግለሰቦች የደረሰንን የግልፅነት ጥያቄ አስመልክቶ የሚከተለውን ማብራርያ ለማቅረብ እንወዳለን፡-

👉 በዚህ ዙር ለ20/80 የቤት ፕሮግራም ሙሉ ለሙሉ እጣ የወጣባቸውና የተስተናገዱት የ1997 ተመዝጋቢዎች ብቻ ናቸው።

👉 የ2005 የ20/80 ተመዝጋቢዎች ግን ከስቱዲዮ ጀምሮ ባለአንድ፣ ባለሁለት እና ባለሶስት መኝታ በሙሉ በእጣ ውስጥ አልተካተቱም።

👉 የ40/60 የቤት ፕሮግራም ግን በ2005 ዓ.ም ብቁ የሆኑ ሙሉ ለሙሉ በእጣ ተካተው በዚህ ዙር የእጣ አወጣጥ በ40/60 ባለአንድ ባለሁለትና ባለሶስት መኝታ ቤቶች እጣ እንደወጣላቸው ልብ ሊባል ይገባል።

👉 ስለሆነም በዚህ ዙር ያልተስተናገዱት 1997 ዓ.ም የተመዘገቡ ባለሶስት መኝታ ተመዝጋቢዎች ብቻ ናቸው።

👉 ይህም የሆነበት ዋነኛ ምክንያት በ12ኛ ዙር እጣ የ1997 ባለሶስት መኝታ ተመዝጋቢዎችን ሙሉ ለሙሉ አስተናግደናል በሚል መነሻ መረጃቸው የተሟላ የሆኑት ተስተናግደው የባለሶስት መኝታ ፕሮግራም ተዘግቶ ነበር።

👉 ከዚህ በኋላ በ1997 ተመዝጋቢዎች ውስጥ በ20/80 ባለሶስት መኝታ እጣ ሊወጣለት የሚችል ተመዝጋቢ የለም በሚል ቤቶቹን በሚያስተዳድረው ቦርድ ውሳኔ ፕሮግራሙ ከሲስተም ውጪ እንዲሆን ተደርጓል።

👉 በዚህም ምክንያት በዚህኛው (በ14ኛ) ዙር እጣ ማስተናገድ አልተቻለም።

ነገር ግን ከተዘጋ በኋላ ከባንክ የተገኘው መረጃ ጥቂቶች ቢሆኑም ቁጠባ በመቀጠላቸው ብቁ የሆኑ ጥቂቶች ተገኝተዋል።

👉 በአሁን ሰአትም ምዝገባው ከባንክ በሚወሰድበት (በሚከለስበት ወቅት) በተገኘው መረጃ ከ1997 ተመዝጋቢዎች መሃከል ጥቂት ሰዎች በአግባቡ እየቆጠቡ ያሉና ብቁ የሆኑ የ20/80 ተመዝጋቢዎችን ማግኘት ተችሏል።

👉 ስለሆነም አስተዳደሩ እነኚህን ተመዝጋቢዎች ምንም እንኳን ፕሮግራሙ በይፋ የተዘጋ ቢሆንም ከባንክ በተገኘው መረጃ መሰረት በአግባቡ እስከቆጠቡ ድረስ ማስተናገድ እንደሚገባ ያምናል።

👉 ነገር ግን ከመረጃ ውስንነትና በሲስተሙ ላይ የሚያስከትለውን ተጨማሪ የመረጃ መመሰቃቀል ለመከላከል ሲባል ወደ በኋላ ተመልሶ ሲስተሙን ለቀሩት ጥቂት ቆጣቢዎች ብቻ መክፈት አስፈላጊ ሆኖ ባለመገኘቱ ምክንያት እነዚህን ተመዝጋቢዎች ለብቻቸው በልዩ ሁኔታ ልናስተናግድ ይገባል የሚል ውሳኔ ላይ ተደርሷል።

👉 ስለሆነም የ1997 ተመዝጋቢ ሆናችሁ ባለሶስት መኝታ ቤቶች በአግባቡ የቆጠባችሁ አስተዳደሩ በሚያወጣው ፕሮግራም በልዩ ሁኔታ የምትስተናገዱ መሆኑን እያሳወቅን፤ ህብረተሰቡ ይህንን አስመልክቶ አንዳንድ የሚናፈሱ የተሳሳቱ መረጃዎች ራሱን እንዲጠብቅ ለማሳሰብ እንወዳለን!!

👉 በተጨማሪም ዘርፉን የሚመሩ አመራሮች ተጨማሪ መረጃዎችን በተለያዩ ሚድያዎች የሚያደርሱ መሆኑንም እናሳውቃለን!!

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር
ሐምሌ 03 ቀን 2014 ዓ.ም

የቪዲዮ መረጃዎቻችንን ለማግኘት ትክክለኛውን የዩቲዩብ ቻናላችንን ሰብስክራይብ ያድርጉ
https://www.youtube.com/c/EBCworld/
ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የቴሌግራም ቻናላችንን ይቀላቀሉ
https://t.me/EBCNEWSNOW
የተመረጡ አጫጭር የቪዲዮ መረጃዎቻችንን ለማግኘት ትክክለኛውን የቲክቶክ አካውንታችንን ይከተሉ
https://www.tiktok.com/

11/07/2022
03/07/2022

አቶ ሽመልስ አብዲሳ 4ኛውን የአረንጓዴ አሻራ መርሐ-ግብር በክልል ደረጃ አስጀመሩ
***********************

የኦሮሚያ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ሽመልስ አብዲሳ 4ኛውን የአረንጓዴ አሻራ ችግኝ ተከላ መርሐ-ግብር በክልል ደረጃ በኢሉ አባቦር ዞን ያዮ ወረዳ አስጀምረዋል።

ርዕሰ መስተዳድሩ መርሐ-ግብሩን ባስጀመሩበት ወቅት ባስተላለፉት መልእክት፣ በአረንጓዴ አሻራ መርሐ-ግብር የተሠራውን ሥራ አጠናክሮ በማስቀጠል የደን ሽፋንን ለማሳደግ መሥራት እንደሚገባም ተናግረዋል።

በክልሉ በዚህ ዓመት እስካሁን ከ1.1 ቢሊዮን በላይ ችግኞች መተከላቸውንም ገልጸዋል።

የኢሉባቦር ዞን አስተዳዳሪ አቶ እንዳልካቸው ተፈሪ፣ የዞኑን ነዋሪዎች ተጠቃሚ የሚያደርጉ የልማት ሥራዎች መከናወናቸውን ተናግረዋል።

በዞኑ ያለውን የያዮ ደን በማልማት ከካርቦን ሽያጭ የውጭ ምንዛሬ ለማግኘት እና የአካባቢውን አርሶ አደሮች ተጠቃሚ ለማድረግ ትኩረት ተሰጥቶ እየተሠራ ስለመሆኑም ገልጸዋል።

የኦሮሚያ ግብርና ቢሮ ኃላፊ አቶ አበራ ወርቁ በበኩላቸው፣ ባለፉት ሦስት አመታት በክልሉ 9 ቢሊዮን ችግኞችን መትከል እንደተቻለ ገልጸው፣ ከዚህ ውስጥ ከ7 ቢሊዮን በላይ ፀድቀዋል ብለዋል።

አረንጓዴ አሻራ የአርሶ አደሩን ምርት እና ምርታማነት በማሳደግ እና የሥራ ዕድል በመፍጠር ረገድ ጉልህ አስተዋጽኦ ማበርከቱን መናገራቸውንም ኦቢኤን ዘግቧል።

በዚህ ዓመት ከባለፈው ውስንነት በመማር የተለያዩ ጥቅም ያላቸው 4.8 ቢሊዮን ችግኞችን ለመትከልዝግጅት መደረጉም ተገልጿል።

የቪዲዮ መረጃዎቻችንን ለማግኘት ትክክለኛውን የዩቲዩብ ቻናላችንን ሰብስክራይብ ያድርጉ
https://www.youtube.com/c/EBCworld/
ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የቴሌግራም ቻናላችንን ይቀላቀሉ
https://t.me/EBCNEWSNOW
የተመረጡ አጫጭር የቪዲዮ መረጃዎቻችንን ለማግኘት ትክክለኛውን የቲክቶክ አካውንታችንን ይከተሉ
https://www.tiktok.com/

03/07/2022

አምባሳደር ስለሺ በቀለ የሹመት ደብዳቤያቸውን ለአሜሪካኑ ፕሬዚዳንት ጆ ባይደን አቀረቡ
******************

በአሜሪካ የኢትዮጵያ ባለሙሉ ስልጣን አምባሳደር ስለሺ በቀለ የሹመት ደብዳቤያቸውን ለአሜሪካኑ ፕሬዚዳንት ጆ ባይደን አቀረቡ።

አምባሳደር ስለሺ በቀለ የአሜሪካ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ አንቶኒ ብሊንከን ከባለቤታቸው ጋር ባዘጋጁት የትውውቅ ሥነ-ስርአት ላይም ታድመዋል።

አምባሳደሩ በዚሁ ወቅት በአሜሪካ ውጭ ጉዳይ መስሪያ ቤት የአፍሪካ ጉዳዮች ረዳት ፀሀፊ አምባሳደር ሞሊ ፊ ጋር በሁለትዮሽ ጉዳዮች ላይ ውጤታማ ውይይት ማድረጋቸውን ከውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።

https://www.youtube.com/c/EBCworld/
ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የቴሌግራም ቻናላችንን ይቀላቀሉ
https://t.me/EBCNEWSNOW
የተመረጡ አጫጭር የቪዲዮ መረጃዎቻችንን ለማግኘት ትክክለኛውን የቲክቶክ አካውንታችንን ይከተሉ
https://www.tiktok.com/

Adress

Birger Jarlsgatan 39
Stockholm
11145

Öppettider

Måndag 09:00 - 17:30
Tisdag 09:00 - 17:30
Onsdag 09:00 - 17:30
Torsdag 09:00 - 17:30
Fredag 09:00 - 17:30

Aviseringar

Var den första att veta och låt oss skicka ett mail när Embassy of Ethiopia, Sweden postar nyheter och kampanjer. Din e-postadress kommer inte att användas för något annat ändamål, och du kan när som helst avbryta prenumerationen.

Kontakta Organisationen

Skicka ett meddelande till Embassy of Ethiopia, Sweden:

Dela