Ethiopian Embassy in Riyadh / የኢትዮጵያ ኤምባሲ - ሪያድ

Ethiopian Embassy in Riyadh / የኢትዮጵያ ኤምባሲ - ሪያድ This is the official Facebook handle of the Ethiopian Embassy in Riyadh, Saudi Arabia
(5)

This is the official page of the Embassy of the Federal Democratic Republic of Ethiopia in the Kingdom of Saudi Arabia.

አምባሳደር ዶ/ር ሙክታር ከሳዑዲ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የአፍሪካ ጉዳዮች ዳይሬክተር ጄኔራል ጋር የስንብት ውይይት አካሄዱ==========================(ሪያድ: መስከረም 5 ቀን 2...
15/09/2026

አምባሳደር ዶ/ር ሙክታር ከሳዑዲ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የአፍሪካ ጉዳዮች ዳይሬክተር ጄኔራል ጋር የስንብት ውይይት አካሄዱ

==========================

(ሪያድ: መስከረም 5 ቀን 2018) በሳዑዲ አረቢያ የኢፌዴሪ ልዩ መልዕክተኛና ባለ ሙሉ ሥልጣን አምባሳደር ዶ/ር ሙክታር ከድር በሳውዲ የሥራ ዘመናቸውን በማጠናቀቅ ላይ በሚገኙበት ወቅት ከሳዑዲ አረቢያ ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የአፍሪካ ጉዳዮች ዳይሬክተር ጄኔራል አምባሳደር ሳቅር ቢን ሱለይማን አል ቁረሺ ጋር የስንብት ውይይት አካሂደዋል።

ክቡር አምባሳደር ዶ/ር ሙክታር በሳዑዲ አረቢያ በነበራቸው የሥራ ቆይታ ወቅት ከሳዑዲ አረቢያ ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴርና በተለይም ከአፍሪካ ጉዳዮች ዳይሬክቶሬት ጄኔራል የተደረገላቸውን ትብብርና ድጋፍ በማድነቅ ልባዊ ምስጋናቸውን አቅርበዋል።

ክቡር አምባሳደር ዶ/ር ሙክታር በተለይም አምባሳደር ሳቅር ለኢትዮጵያና ለሳዑዲ አረቢያ የጋራ ግንኙነት ማደግና መጠናከር ላሳዩት ትብብርና ልዩ ትኩረት አድናቆታቸውን ገልጸዋል።

ክቡር አምባሳደር ዶ/ር ሙክታር ይህ የስንብት ውይይት የሁለቱ አገራት የረጅም ጊዜ ወዳጅነትና ትብብር የሚያሳይ መሆኑን ጠቁመው፣ በሥራ ዘመናቸው የተገነቡት ጠንካራ የሥራና የመተማመን ግንኙነቶች ወደፊትም ለቀጣይ ትብብር ጠንካራ መሠረት እንደሚሆኑ ጠቁመዋል።

በተጨማሪም በሁለቱ አገራት መካከል ያለው ታሪካዊ፣ ጂኦግራፊያዊና ባህላዊ ቅርበት በመነሳት የሁለትዮሽ፣ የኢኮኖሚ፣ የፖለቲካ እና የሕዝብ ለሕዝብ ግንኙነቶች በቀጣይም ይበልጥ እንዲጠናከሩ በጋራ መሥራት እንደሚገባ ገልፀዋል።

አምባሳደር ሳቅር ቢን ሱለይማን አል ቁረሺ በበኩላቸው አምባሳደር ዶ/ር ሙክታር በሳዑዲ አረቢያ በነበራቸው የሥራ ዘመን የሁለቱን አገራት ግንኙነት በማጠናከር ላደረጉት ጥረትና አስተዋጽኦ ምስጋና አቅርበዋል።

አምባሳደር ሳቅር በተለይም የኢትዮጵያን የልማት እንቅስቃሴና በቀጠናው ሰላምና መረጋጋት ለማስፈን እያሳየች ያለችውን ቁርጠኝነት አድንቀው፣ በሁለቱ አገራት መካከል ያለው የተለየ ወዳጅነትና ትብብር ወደፊትም እንደሚጠናከር ገልጸዋል።

በመቀጠልም በጋራ የልማት፣ የሰላምና የደህንነት ጉዳዮች ላይ ቅርበት በመፍጠር ለመሥራትና የተጀመሩ የትብብር ሥራዎችን በቀጣይ ለማጠናከር መግባባት ላይ ደርሰዋል።

በመጨረሻም ክቡር አምባሳደር ሳቅር ቢን ሱለይማን አል ቁረሺ አምባሳደር ዶ/ር ሙክታር በቀጣይ በሚኖራቸው የሥራ ስምሪት ስኬታማ እንዲሆኑ ያላቸውን መልካም ምኞት ገልጸዋል።MFAEthiopia Amharic የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴርFBC (Fana Broadcasting Corporate S.C.)Ethiopian Press Agency /የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት/Ethiopian Broadcasting CorporationEthiopian News AgencyThe Ministry of Foreign Affairs of EthiopiaEthiopian Diaspora Service

15/09/2026
14/09/2026
አምባሳደር ዶ/ር ሙክታር ከንጉሥ ሳልማን የሰብዓዊ ድጋፍና እርዳታ ማዕከል ዋና አስተዳደር  ጋር ተወያዩ።=========(ሪያድ፣ መስከረም 3 ቀን 2019 ዓ.ም) በሳዑዲ አረቢያ የኢፌዴሪ ልዩ...
13/09/2026

አምባሳደር ዶ/ር ሙክታር ከንጉሥ ሳልማን የሰብዓዊ ድጋፍና እርዳታ ማዕከል ዋና አስተዳደር ጋር ተወያዩ።
=========

(ሪያድ፣ መስከረም 3 ቀን 2019 ዓ.ም) በሳዑዲ አረቢያ የኢፌዴሪ ልዩ መልዕክተኛና ባለሙሉ ሥልጣን አምባሳደር ዶ/ር ሙክታር ከድር ከንጉሥ ሳልማን የሰብዓዊ ድጋፍና እርዳታ ማዕከል (KSrelief) ዋና አስተዳዳሪና የንጉሣዊ ፍርድ ቤት አማካሪ ከሆኑት ክቡር ዶ/ር አብዱላህ ቢን አብዱልዓዚዝ አል-ረቢዓህ ጋር ተገናኝተው በኢትዮጵያ የአደጋ ሥጋት አመራር ኮሚሽን ተዘጋጅቶ ለKSrelief በቀረበውና ከሳዑዲ አረቢያ የሚመለሱ ዜጎችን ከማኅበረሰባቸው ጋር በማቀናጀት ዘላቂ የኑሮ መሠረት እንዲገነቡ ለማስቻል አላማ ባደረገው ፕሮጀክት ላይ ተወያዩ ።

በውይይቱ ወቅት አምባሳደር ዶ/ር ሙክታር ስለፕሮጀክቱ ዝርዝር ገለጻ አድርገዋል። በገለጻቸውም ፕሮጀክቱ በ18 ወራት ውስጥ 30 ሺህ ተመላሾችን ለመደገፍ ያቀደ መሆኑን አስረድተዋል። ድጋፉም ምግብና አስፈላጊ ቁሳቁሶችን ጨምሮ ጊዜያዊ መጠለያና የመጓጓዣ አገልግሎት መስጠት፣ የሥነ ልቦና ድጋፍ ማድረግ፣ እንዲሁም ተመላሾችን በሙያና በሥራ ፈጠራ ሥልጠና በማብቃት የገቢ ምንጭ እንዲፈጥሩ ማስቻልን እንደሚያካትት ገልጸዋል።

በተመሳሳይ አምባሳደሩ ዜጎችን ወደ አገራቸው መመለስ ብቻውን የተሟላ መፍትሔ እንዳልሆነ ጠቁመው፣ ከማኅበረሰባቸው ጋር በሚገባ ተቀናጅተው ዘላቂ የኑሮ መሠረት እንዲገነቡ ማስቻል የመልሶ ማቋቋሙ ዋና ዓላማ መሆኑን አስረድተዋል።

ይህ አይነቱ ዘላቂ ድጋፍ የተመላሾችን አስቸኳይ ፍላጎት ከማሟላት ባለፈ፣ ለሥራ አጥነት፣ ለኢኮኖሚያዊ ችግርና ለማኅበራዊ ተጋላጭነት የሚዳርጉ መንስኤዎችን ከሥር በመቅረፍ ተመላሾች ዳግም ለአደገኛና ሕገወጥ ፍልሰት የመጋለጥ ዕድላቸውን መቀነስ እንደሚቻል አክለዋል።

አምባሳደር ዶ/ር ሙክታር KSrelief ከዚህ ቀደምና በቅርቡ ለኢትዮጵያ ላደረጋቸው የሰብዓዊ ድጋፎች ምስጋናቸውን ገልጸው፣ የቀረበው ፕሮጀክትም በሁለቱ ወገኖች መካከል ላለው የትብብር ግንኙነት ተጨማሪ ዕድል እንደሚፈጥር ጠቁመዋል።

ክቡር ዶ/ር አብዱላህ አል-ረቢዓህ በበኩላቸው የፕሮጀክቱ በጎ አላማ እንደሚደግፉ ገልጸው፣ የማዕከሉ የቴክኒክ ቡድን የቀረበውን ሰነድ በዝርዝር እንደሚገመግምና ፕሮጀክቱን በምን መልኩ መደገፍ እንደሚቻል ዕቅድ እንደሚያዘጋጅ ገልጸዋል።

በመጨረሻም አምባሳደር ዶ/ር ሙክታር የሥራ ዘመናቸውን ሊያጠናቅቁ መሆናቸውን አሳውቀው፣ ዶ/ር አብዱላህና ማዕከሉ በቆይታቸው ወቅት ላደረጉላቸው ትብብርና ድጋፍ አመስግነዋል።

ማዕከሉ ከኤምባሲውና ከሚመለከታቸው የኢትዮጵያ ተቋማት ጋር ያለውን ትብብር በቀጣይም አጠናክሮ እንዲቀጥል ጠይቀዋል።

12/09/2026

رئيس الوزراء آبي أحمد يلتقي ولي عهد أبوظبي على هامش قمة «بريكس»

التقى رئيس الوزراء الإثيوبي أبي أحمد ولي عهد أبوظبي، سمو الشيخ خالد بن محمد بن زايد آل نهيان، على هامش أعمال القمة الـ18 لمجموعة «بريكس».

وبحث الجانبان أبرز أولويات «بريكس»، إلى جانب سبل تعزيز التعاون متعدد المجالات بين إثيوبيا ودولة الإمارات العربية المتحدة، بما يدعم توسيع الشراكة بين البلدين.
🇪🇹 🇦🇪

12/09/2026
ማስታወቂያወደ ሀገር ለመሳፈር ሊሴፓሴ በማውጣት/በመስጠት ለአሻራ ወረፋ ስትጠባበቁ የነበራችሁ ስማችሁ ቀጥሎ የተዘረዘረ ዜጎች ነገ እለተ እሁድ በቀን (13/09/2026) በኢትዮጲያ ሰዓት አቆ...
12/09/2026

ማስታወቂያ
ወደ ሀገር ለመሳፈር ሊሴፓሴ በማውጣት/በመስጠት ለአሻራ ወረፋ ስትጠባበቁ የነበራችሁ ስማችሁ ቀጥሎ የተዘረዘረ ዜጎች ነገ እለተ እሁድ በቀን (13/09/2026) በኢትዮጲያ ሰዓት አቆጣጠር ከጠዋቱ 1:00 (7:00 AM) ሰዓት መለዝ አከባቢ በሚገኘው የአሻራ መስጫ ማዕከል ቀደም ብላችሁ በቦታው በመገኘት በስማ/አሻራ መስጠት የምትችሉ መሆኑን እንገልፃለን።
ቦታው📌https://maps.app.goo.gl/a81KhiFUmEJhfQnCA?g_st=ic

BEEKSISA
Lammiiwwan gara biyyaa galuuf koppii liiseepaasee baafattanii/Kennitanii eeggachaa jirtan, Guyyaa borii Dilbata/Alhada (13/09/2026) ganama sa'aatii 1:00 AM (7:00 AM) irratti wiirtuu ashaaraa qubaa naannoo Malaz jedhamutti waqtiin dhufuun ashaaraa qubaa kennuu akka dandeessan isin beeksifna.
Iddoon:📌https://maps.app.goo.gl/a81KhiFUmEJhfQnCA

Address

Abu Bakr Al Karkhi, Al Safarat
Riyadh
11693

Opening Hours

Monday 8:30am - 3pm
Tuesday 8:30am - 3pm
Wednesday 8:30am - 3pm
Thursday 8:30am - 3pm
Sunday 8:30am - 3pm

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Ethiopian Embassy in Riyadh / የኢትዮጵያ ኤምባሲ - ሪያድ posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Shortcuts

Share