የኢትዮጵያ ቆንስላ ጽ/ቤት፤ ጄዳ Ethiopian Consulate General, Jeddah

  • Home
  • Saudi Arabia
  • Jeddah
  • የኢትዮጵያ ቆንስላ ጽ/ቤት፤ ጄዳ Ethiopian Consulate General, Jeddah

የኢትዮጵያ ቆንስላ ጽ/ቤት፤ ጄዳ Ethiopian Consulate General, Jeddah Contact information, map and directions, contact form, opening hours, services, ratings, photos, videos and announcements from የኢትዮጵያ ቆንስላ ጽ/ቤት፤ ጄዳ Ethiopian Consulate General, Jeddah, Consulate & Embassy, 8111، 3210 الشبيلي، حي 8111, Jeddah 23325, Jeddah.

የኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፑብሊክ ቆንስላ ጽ/ቤት - ጅዳ ::
Consulate General of The Federal Democratic Republic of Ethiopia Jeddah القنصلية العامة لجمهورية اثيوبيا الاتحادية الديمقراطية بجدة

የጅዳ ኢ.ፌ.ዲ.ሪ. ቆንስላ ጽ/ቤት  ከቱር ኦፕሬተር ሀላፊ ጋር ውይይት አካሄደ፣የጅዳ ቆንስላ ጄኔራል ጽ/ቤት የቢዚነስ ዲፕሎማሲ ስራ ዘርፍ   መስከረም 5 ቀን 2019 ዓ.ም ከአሁን ቀደም ...
15/09/2026

የጅዳ ኢ.ፌ.ዲ.ሪ. ቆንስላ ጽ/ቤት ከቱር ኦፕሬተር ሀላፊ ጋር ውይይት አካሄደ፣

የጅዳ ቆንስላ ጄኔራል ጽ/ቤት የቢዚነስ ዲፕሎማሲ ስራ ዘርፍ መስከረም 5 ቀን 2019 ዓ.ም ከአሁን ቀደም ከተመለመለው እንዲሁም አገራችንን በቱር ፓኬጁ ውስጥ እንድያስገባ የተደረገው እና አገራችንን ጎብኝቶ ከተመለሰው Al Maha United Travel ዋና ስራ አስፈጻሚ ከሆነው Fawad Iqbal ጋር በካምፓኒው ቢሮ ተገናኝተው ውይይት አካሂዷል። በውይይቱም ወደ አገራችን ቱሮስቶች በሚላኩበት ሁኔታ ላይ እና ከቆንስላ ጄኔራል የሚፈለውገውን ድጋፍ በተመለከተ የሀሳብ ልውውጥ ተደርጓል።

የካምፓኒው ዋና ስራ አስፈጻሚ በበኩላቸው ኢትዮጵያን ለመጎበኘት የተሰጠውን እድል በማመስገን ከተመለሱ በኋላ በርካታ ቱሪስቶችን ወደ ኢትዮጵያ መላኩን ገልጾ፣በአሁኑ ሰዓት ትምህርት ቤት የተከፈተ በመሆኑ በቤተሰብ ደረጃ ሳይሆን በግለሰብ ደረጃ የሚጓዙ ሰዎች መኖራቸውን አስረድተው በማሰባሰብ ለመላክ ጥረት የሚያደርግ መሆኑን አስረድተዋል።
በማጠቃለያውም ካምፓኒው ወደ አገራችን ቱሪስቶችን በመላክ እንድጎበኙ በማድረግ እያበረከተ ላለው አስተዋጽኦ በማመስገን፣ በስራ ሂደት የሚገጥሙ ችግሮችን ለመፍታትና ድጋፍ ለማድረግ ቆንስላ ጽ/ቤቱ ዝግጁ መሆኑን መግለጽ ተችሏል።

የኅብር ቀንና የ2019 ዓ.ም አዲስ ዓመት ከጄዳ እና አካባቢው የዳያስፖራ ማህበረሰብ አባላት ጋር በድምቀት ተከበረ፣ (ጄዳ፣ ጳጉሜ 5 ቀን 2018 ዓ.ም) የኅብር ቀንና የ2019 ዓ.ም አዲስ...
10/09/2026

የኅብር ቀንና የ2019 ዓ.ም አዲስ ዓመት ከጄዳ እና አካባቢው የዳያስፖራ ማህበረሰብ አባላት ጋር በድምቀት ተከበረ፣

(ጄዳ፣ ጳጉሜ 5 ቀን 2018 ዓ.ም) የኅብር ቀንና የ2019 ዓ.ም አዲስ ዓመት በጄዳ እና አካባቢው ከሚኖሩ ከ800 በላይ ኢትዮጵያውያን፣ ትውልደ ኢትዮጵያውያን እና የኢትዮጵያ ወዳጆች ጋር በመሆን “ብዝኃነት፡ የኢትዮጵያ ጌጥ” በሚል መሪ ቃል በድምቀት ተከብሯል።
በስነስርዓቱ ላይ በጄዳ የኢፌዲሪ ቆንስል ጀኔራል ተወካይ አቶ አባተ ማዴቦ ለኅብር ቀን እና ለአዲስ ዓመት የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት አስተላልፈዋል፡፡
በንግግራቸው የዘንድሮው የኅብር ቀን እና የአዲስ ዓመት አከባበር ከቀደሙት ዓመታት ልዩ የሚያደርገው ሀገራችን በ7ኛው ጠቅላላ ምርጫ ሰላማዊ፣ ነፃና ፍትሃዊ በሆነ ሂደት በሕዝብ ይሁንታ ያገኘው ፓርቲ መንግሥት የሚመሠርትበት፣ የተመረጠው መንግሥት ከሕዝብ የተጣለበትን ከፍተኛ ኃላፊነትና ከባድ አደራ ለመወጣት በሚዘጋጅበት፣ እንዲሁም እጅግ መሠረታዊ በሆኑ ጉዳዮች ላይ ሀገራዊ መግባባት ለመፍጠር እየተካሄደ ያለው ሀገራዊ የምክክር ጉባኤ ውጤቶችን ወደ ትግበራ ለማስገባት ጠንካራ ዝግጅት መደረግ ባለበት ታሪካዊ ወቅት መሆኑን ገልፀዋል፡፡
አያይዘውም የአንድ ሀገር ጥንከሬ በተፈጥሮ ሀብት ብቻ ሰይሆን በህዝቦች አንድነት፣ መተባበርና መተሳሰብ መሆኑን፣ ኢትዮጵያ ልዩ ልዩ ባህሎች፣ እሴቶች፣ ታሪኮች፣ ሃይማኖቶች፣ ባህላዊ ሥርዐቶች እና ክዋኔዎች የያዘች ሀገር በመሆኗ ይህንን በዓል ስናከብር እነዚህን እሴቶች የበለጠ ለማጎልበት እና አገራችን የጀመረችውን የብልጽግና ጉዞ እውን ለማድረግ ሁሉም የበኩሉን ሚና እንዲወጣ ጠይቀዋል፡፡
በሌላ በኩል የ2019 ዓም በማስመልከት ባደረጉት ንግግር አዲስ ዓመት ማለት የቀን መቁጠሪያ ቁጥር መቀየር ብቻ እንዳልሆነ፣ አዲስ ዓመት ያለፈውን ዓመት በማስታወስ፣ ከልምዳችን በመማር፣ የተሻለ ነገን በተስፋ ለመቀበል እንደገና የምንጀምርበት ወቅት መሆኑን፣ አዲስ ዓመት አዲስ ቀን ብቻ እንዳልሆነ፤ አዲስ አስተሳሰብ፣ አዲስ ተስፋ እና አዲስ ተግባር መሆኑን፣ በተመሳሳይ የተሳሳትንበትን ለማረም፣ ያሳካነውን ለማጠናከርና የተሻለ ነገን ለመገንባት ይህን አዲስ ዓመት እንደ አዲስ ዕድል ልንጠቀምበት እንደሚገባ አስገንዝበዋል፡፡
በተለይም በውጭ ሀገራት የምትኖሩ ኢትዮጵያውያን ቋንቋችሁን፣ ባህላችሁን፣ እሴቶቻችሁንና ማንነታችሁን በመጠበቅ ለሀገራችን የምችሉትን አስተዋጽኦ እንድታደርጉ በማለት ጠይቀዋል።
አያይዘውም ኢትዮጵያ ከአግድሞሽና ከዝቅታ ጉዞ ተላቃ በሁሉም ዘርፎች ወደ ላቀ የከፍታ ጉዞ ምዕራፍ መሸጋገሯን (ማንሠራራት መጀመሯን)፣ ሀገረ-መንግሥቷን በፅናት እያነፀች መሆኗን፣ በህብረ-ብሔራዊ አንድነት፣ በእኩልነት፣ በፍትሓዊነትና በወንድማማችነት/እህትማማችነት እሴቶች የታነጸ የወል ትርክት እያጎለበተች መሆኗን አብራርተዋል።
በመጨረሻም በዓሉ በተለያዩ የበህል ሙዚቃ እና ውዝዋዜ እንዲሁም የኬክ ቆረሳ ስነስርዓት በማካሄድ የዕለቱ ፕሮግራም ተጠናቋል፡፡

የጅዳ ኢ.ፌ.ዲ.ሪ. ቆንስላ ጽ/ቤት  ከባለሀብት ጋር ውይይት አካሄደ፣   (ጳጉሜ 5 ቀን 2018 ዓ.ም፣ ጄዳ) የጅዳ ቆንስላ ጄኔራል ጽ/ቤት የቢዚነስ ዲፕሎማሲ ስራ ዘርፍ   የAlkhair ...
10/09/2026

የጅዳ ኢ.ፌ.ዲ.ሪ. ቆንስላ ጽ/ቤት ከባለሀብት ጋር ውይይት አካሄደ፣

(ጳጉሜ 5 ቀን 2018 ዓ.ም፣ ጄዳ) የጅዳ ቆንስላ ጄኔራል ጽ/ቤት የቢዚነስ ዲፕሎማሲ ስራ ዘርፍ የAlkhair Trading Co.Ltd ምክትል ሊቀመንበር ከሆኑት Ali A. Bashanfar ጋር ተገናኝተው ውይይት አካሂዷል። በውይይቱም የአገራችን ቡና በመግዛት እና ምርታችንን ለሳውዲ አረቢያ ገበያ በማቅረብ እንዲሁም በማስተዋወቅ ረገድ ላደረጉት አስተዋጽኦ በማመስገን ቡና በማምረት ኢንቨስትመንት ላይ መሳተፍ በሚችሉበት ሁኔታ ላይ የማግባባት ስራ ተሰርቷል።

አቶ Ali A. Bashanfer በበኩላቸው ለተደረገላቸው ገለጻ ከልብ በማመሰገን ከአሁን ቀደም በሀረር ቡና ለማምረት ጥናት አቅርበው ቦታ ለማግኘት ያደረጉት ጥረት ባለመሳካቱ መተዋቸውን ገልጸው አሁን ግን ከሀረር በተጨማሪ ሀዋሳም ለኢንቨስትመንት የተዘጋጀ ቦታ ካለ ለመሳተፍ ዝግጁ መሆናቸውን አስረድተዋል።

በማጠቃለያውም ወደ ኢትዮጵያ ገብተው ኢንቨስትመንት ላይ ለመሳተፍ ያሳዩትን ፍላጎት በማድነቅ የኢንቨስትመንት ቦታዎችን በተመለከተ ከሚመለከታቸው አካላት መረጃ በማግኘት የምናሳውቅ መሆኑን ማስረዳት ተችሏል።

09/09/2026

. 📌ማስታወቂያ📌 *********************

.                                    📌ማስታወቂያ📌                                *********************ተጨማሪም መረጃዎችን በቆንስላ ጽ/ቤ...
08/09/2026

. 📌ማስታወቂያ📌 *********************
ተጨማሪም መረጃዎችን በቆንስላ ጽ/ቤቱ ማኅበራዊ ሚዲያ ገፆች ላይ በሚከተሉት ማስፈንጠሪያ (Link) በኩል ማግኘት የምትችሉ መሆኑን እናሳውቃለን:-
Telegram ( የቴሌግራም ቻናላችን ይቀላቀሉ) :- https://t.me/jedcon
Twitter (በትዊተር ይከተሉን):- https://x.com/EthiopianJeddah?s=20

08/09/2026
በጄዳ የኢትዮጵያውያን ዓለም አቀፍ ትምህርት ቤት በ2018 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ አገር አቀፍ ፈተና ከፍተኛ ውጤት ላስመዘገቡ ተማሪዎች እውቅና ተሰጠ​(ጄዳ፣ ነሐሴ 29 ቀን 2018 ዓ...
04/09/2026

በጄዳ የኢትዮጵያውያን ዓለም አቀፍ ትምህርት ቤት በ2018 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ አገር አቀፍ ፈተና ከፍተኛ ውጤት ላስመዘገቡ ተማሪዎች እውቅና ተሰጠ

​(ጄዳ፣ ነሐሴ 29 ቀን 2018 ዓ.ም) በጄዳ የኢትዮጵያውያን ኮሙኒቲ ማህበር ባዘጋጀው የእውቅና ፕሮግራም የጄዳ ቆንስላ ጄኔራል ጽሕፈት ቤት ተወካይና ዲፕሎማቶች፣ የትምህርት ቤቱ አመራር፣ መምህራን እና ወላጆች በተገኙበት በ2018 ዓ.ም የላቀ ውጤት ላስመዘገቡ ተማሪዎች የእውቅና ሰርተፊኬት ተበርክቶላቸዋል።

​በፕሮግራሙ ላይ የጄዳ ቆንስላ ተወካይ አቶ አባተ ማዴቦ ንግግር ያደረጉ ሲሆን፣ በንግግራቸውም ከብዙ ልፋት፣ ድካም፣ እንቅልፍ አልባ ሌሊቶችና የፈተና ጫናዎች በኋላ የመጣ ውጤት በመሆኑ "እንኳን ደስ አላችሁ" ብለዋቸዋል። ይህ ውጤት ለተማሪዎቹ የሕይወታቸው አዲስና ትልቅ ምዕራፍ መጀመሪያ በመሆኑ በቀጣይም ፈተናዎችን በማለፍ እና የሚገኙ እድሎችን በመጠቀም ለሀገራቸው አለኝታ እንዲሆኑ አስገንዝበዋቸዋል።

​አያይዘውም ለዚህ ውጤት መሳካት ለተጉ የትምህርት ቤቱ አመራር፣ መምህራን፣ ወላጆች፣ ተማሪዎችና አጠቃላይ የትምህርት ማህበረሰብ ከፍ ያለ ምስጋና አቅርበዋል። ለሁሉም ባለድርሻ አካላት እንኳን ደስ አላችሁ በማለት መሰል ስራ በቀጣይም ተጠናክሮ መቀጠል እንዳለበት አሳስበዋል።

​በፕሮግራሙ በጄዳ የኢትዮጵያ ኮሙኒቲ ማህበር ሰብሳቢ አቶ መሀመድኑር ሀሰን፣ የኢትዮጵያ ዓለም አቀፍ ትምህርት ቤት የቦርድ ሰብሳቢ እና የትምህርት ቤቱ ርዕሰ መምህር የእንኳን ደስ አላችሁ መልዕክት አስተላልፈዋል።

​በመጨረሻም የእውቅና ሰርተፊኬት የማበርከት እና የኬክ ቆረሳ ሥነ ሥርዓት በማካሄድ የእለቱ ፕሮግራም ተጠናቋል።

.                                    📌ማስታወቂያ📌                                *********************ተጨማሪም መረጃዎችን በቆንስላ ጽ/ቤ...
02/09/2026

. 📌ማስታወቂያ📌 *********************
ተጨማሪም መረጃዎችን በቆንስላ ጽ/ቤቱ ማኅበራዊ ሚዲያ ገፆች ላይ በሚከተሉት ማስፈንጠሪያ (Link) በኩል ማግኘት የምትችሉ መሆኑን እናሳውቃለን:-
Telegram ( የቴሌግራም ቻናላችን ይቀላቀሉ) :- https://t.me/jedcon
Twitter (በትዊተር ይከተሉን):- https://x.com/EthiopianJeddah?s=20

Address

8111، 3210 الشبيلي، حي 8111, Jeddah 23325
Jeddah
495JEDDAH21411

Opening Hours

Monday 8:30am - 3pm
Tuesday 8:30am - 3pm
Wednesday 8:30am - 3pm
Thursday 8:30am - 3pm
Sunday 8:30am - 3pm

Telephone

+966126653622

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when የኢትዮጵያ ቆንስላ ጽ/ቤት፤ ጄዳ Ethiopian Consulate General, Jeddah posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Organization

Send a message to የኢትዮጵያ ቆንስላ ጽ/ቤት፤ ጄዳ Ethiopian Consulate General, Jeddah:

Shortcuts

Share