25/04/2026
ብዙ ግዜ ሰሜን ሸዋ ላይ ስለምትገኘው ትንሿ መንደር ስጽፍ "ትንሿ ጋዛ" እላት ነበር።
በሰሜን ሸዋ ገርበ ጉራቻ መዳረሻ የምትገኘው እና ነዋሪዎቿም በቁጥር ከአምስት ሺህ የማያልፍ
ግና በሺህ የሚቆጠር ምስኪን መንገደኞች የሚገ ደሉ ባት ፣ ሾፌሮች ፣ መንገደኞች እርጉዝ እናት ፣ የ3 አመት ህጻን ታግተው ሚሊዮኖች የሚከፈልበት ፣ ከአመት በፊት በአንድ ቀን ሰማንያ ሰዎች ታግተው ሰማንያ ሚሊየን ብር የተጠየቀባት ። አንድም ቀን አጋቾች ግን ያልተያዙባት ስለ ትንሿ የ "አሊዶሮ" መንደር በተደጋጋሚ ጥያቄ አንስቸ ነበር ።
አሁን ምላሹ ግልጽ እየሆነ ነው ። ማን ያግታል ፣ ማን ባንክ ውስጥ ሆኖ ገንዘቡን ያዘዋውራል ፣ መረጃው እንዳይወጣ ማን እንዲያዘገይ ያደርጋል ከነ ስማቸው እንመጣባቸዋለን።
Viv Gumaa