Basketo Zone Health Departement social behavioral change communication

Basketo Zone Health  Departement social behavioral change communication በዚህ ፔጅ የጤና መረጃዎች እና የጤና ተግባቦት ግንዛቤ ይሰራጫል ።

12/01/2026
11/12/2025
This MBD training through free call centers 8756 developed Amref health Africa integration with MOH, EPHI, SERHB & SERPH...
07/12/2025

This MBD training through free call centers 8756 developed Amref health Africa integration with MOH, EPHI, SERHB & SERPHI

06/12/2025

የሄፓታይተስ ቢ ቫይረስ በሸታ
__________

የሄፓታይተስ ቢ ቫይረስ በሸታ በቫይረስ አማካኝነት የሚከሰት ሲሆን ይህ ቫይረስ አጣዳፊ ወይም ሥር የሰደደ የጉበት ኢንፌክሽን ያመጣል።

ሄፓታይተስ ቢ ቫይረስ በሽታ በአብዛኛው የሚተላለፈው በተበከለ ደም ወይም ከሰዉነት በሚወጣ ፈሳሽ አማካኝነት ነው።

በኢትዮጵያ ከአጠቃላይ ሕዝብ ውስጥ ከ8-12% የሚገመተው ለሄፖታይተስ ቢ ቫይረስ በሽታ ተጋላጭ ነው።

በሄፖታይተስ ቢ ቫይረስ በሽታ ከተያዙ እናቶች የተወለዱ ሕፃናት በሄፐታይተስ ቢ ኢሚዩን ግሎቡሊን (HBIG) ካልታከሙ እና ከተወለዱ በኋላ ወዲያውኑ ክትባት ካልተሰጣቸው በወሊድ ጊዜ በበሽታው የመያዝ ዕድላቸው እስከ 90% ይደርሳል።

ከሁሉም አጣዳፊ ሄፓታይተስ ቢ ቫይረስ ኢንፌክሽን ካለባቸው ታካሚዎች ከ5 እስከ 10% የሚሆኑት ሥር የሰደደ ሄፓታይተስ ቢ በሽታ ይይዛቸዋል። አጣዳፊ ሄፓታይተስ ቢ ቫይረስ ኢንፌክሽን የሚከሰትበት ዕድሜ በወጣትነት ጊዜ ከሆነ፣ ሥር የሰደደ ሄፓታይተስ ቢ የመያዝ እድሉ ከፍ ያለ ነው።

ሄፓታይተስ ቢ ቫይረስ በሽታ ሥር የሰደደ ከሆነ፣ የጉበት ጠባሳ ሊፈጠር ይችላል፣ እና በመጨረሻም የጉበት ካንሰር ሊከሰት ይችላል።

▪የሄፖታይተስ ቢ ቫይረስ መተላለፊያ መንገዶች

• ከእናት ወደ ልጅ በወሊድ ጊዜ በሚኖር ንክኪ
• በተሰነጠቀ እና በቆሰለ ቆዳ በንክኪ የሚተላለፍ
• ጥንቃቄ የጎደለው የግብረስጋ ግንኙነት
• ንጽህናቸው ያልተጠበቁ ስለታማ ነገሮችን በጋራ መጠቀም

▪የሄፖታይተስ ቢ ቫይረስ ምልክቶች

ምልክቶቹ ብዙውን ጊዜ ቀላል ናቸው ወይም ጨርሶ ላይታዩ ይችላሉ። ኢንፌክሽኑ በደም ምርመራ ሊረጋገጥ ይችላል።

አብዛኛዎቹ ታካሚዎች የተለመዱ የቫይረስ ሄፓታይተስ ምልክቶች ይታይባቸዋል፣ ይህም፡

• የምግብ ፍላጎት ማጣት፣ ድካም ስሜት
• የሰውነት ምቾት ማጣት፣
• ትኩሳት፣
• ማቅለሽለሽ እና ማስታወክ፣
• በመቀጠልም ጃንዲስ (የቆዳ ቢጫ መሆን)ትኩሳት፣
• የመገጣጠሚያ እና የጡንቻ ሕመም
• የሽንት መጥቆር ያካትታል
ምልክቶቹ ከጥቂት ሳምንታት እስከ 6 ወራት ሊቆዩ ይችላሉ።

▪የሄፖታይተስ ቢ ቫይረስ ምርመራ

ሄፖታይተስ ቢ ቫይረስ በሽታን ለመመርመር እና የጉበት ሥራን ለመከታተል የደም ምርመራዎች ይደረጋሉ ። የጉበት አልትራሳውንድ ወይም ባዮፕሲም(ከጉበት ላይ ቅንጣት በመዉሰድ የሚደረግ ምርመራ ) ሊያስፈልግ ይችላል።

▪ሄፓታይተስ ቢ ቫይረስ በሽታ ሕክምና

እረፍት እና ጤናማ የአኗኗር ዘይቤ በተጨማሪ ይመከራል።
ከባድ የጉበት እብጠት (fulminant hepatitis) ከተከሰተ፣ በአፍ የሚወሰዱ ፀረ-ቫይረስ መድኃኒቶችን መጠቀም የመዳን እድልን ይጨምራል። እንደ ክብደቱ እና በጉበት ላይ እንደደረሰው ጉዳት መጠን የጉበት ንቅለ ተከላ ይደረጋል።

▪የሄፖታይተስ ቢ ቫይረስ መከላከያ መንገዶች

• ክትባት፡ በጣም ውጤታማው የመከላከያ ዘዴ ህጻናት እንደተወለዱ የሚሰጠው የጉበት በሽታ መከላከያ ክትባት ነው፣ በተጨማሪም 6፣ 10 እና 14 ሳምንት እድሜያቸው ላይ ይሰጣል።
• በሰለጠነ ጤና ባለሙያ በጤና ተቋም መውለድ
• ንጽህናቸው ያልተጠበቀ ስለታማ ነገሮችን በጋራ አለመጠቀም
• ጥንቃቄ ያለው የግብረስጋ ግንኙነት
• በበሽታው የተያዙ ሰዎችን ወደ ህክምና መውሰድ ናቸው።



Website: moh.gov.et
Facebook: Ministry of Health,Ethiopia
Twitter: x.com/fmohealth
YouTube: youtube.com/
Tiktok: tiktok.com/

05/12/2025
30/11/2025
30/11/2025
30/11/2025
የማርበርግ ቫይረስ በሽታን ለመቆጣጠርና ለመከላከል ቤት ለቤት የሚደረጉ አሰሳዎች ጉልህ ሚና እንዳላቸው ተገለፀከኢፌዴሪ ጤና ሚኒስቴርና ከህብረተሰብ ጤና ኢንስቲትውት የማርበርግ ቫይረስ በሽታን...
29/11/2025

የማርበርግ ቫይረስ በሽታን ለመቆጣጠርና ለመከላከል ቤት ለቤት የሚደረጉ አሰሳዎች ጉልህ ሚና እንዳላቸው ተገለፀ

ከኢፌዴሪ ጤና ሚኒስቴርና ከህብረተሰብ ጤና ኢንስቲትውት የማርበርግ ቫይረስ በሽታን ለመከላከልና ለመቆጣጠር የሚያስችሉ ሁሉ አቀፍ ድጋፍ እየተደረገ መሆኑን የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ጤና ቢሮ አስታውቋል፡፡

የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ጤና ቢሮ ኃላፊ አቶ እንዳሻው ሽብሩ የማርበርግ ቫይረስ በሽታ በክልሉ በአሪ ዞን ጂንካ ከተማና በደቡብ ኦሞ ዞን ማለ ወረዳ መከሰቱን አውስተው ስርጭቱን ለመቆጣጠርና ለመከላከል በርካታ ተግባራት እየተከናወኑ ይገኛሉ ብለዋል፡፡

በማርበርግ በሽታ ከተያዙ ግለሰቦች ጋር ቀጥታ ንክኪ ያላቸው ሰዎች ከመለየት ጀምሮ በጂንካ አጠቃላይ ሆስፒታልና በኮይቤ መጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል ለይቶ ማቆያና ህክምና ማዕከል በማቋቋም ስርጭቱን ለመግታት እየተሠራ መሆኑን አቶ እንዳሻው ገልፀዋል፡፡

በክልሉ ከማርበርግ ቫይረስ በሽተኞች ጋር ንክኪ እንዳለቸው የተጠረጠሩ ከ350 በላይ ግለሰበች ተለይተው ክትትል እየተደረገ መሆኑን የገለፁት የቢሮ ኃላፊው ቤት ለቤት ክትትል ለ32427፣ በጂንካ ከተማ መውጫና መግቢያ 96,297፣ በጤና ተቋማት 42,542 እና በትምህርት ቤቶች ለ33747 የልየታ ሥራ የተሠራ ሲሆን 162,655 ለሚሆኑ ልዩ ልዩ ህብረተሰብ ክፍሎች ስለበሽታው የግንዛቤ ማስጨበጫ ሥራ ተሠርቷል ብለዋል፡፡

የጤና ሚኒስቴርና የኢፌዴሪ ህብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት በሽታውን ለመከላከልና ለመቆጣጠር እየሰጡ ያሉትን ድጋፍ ያደነቁት አቶ እንዳሻው ለክልሉ የበሽታ ስርጭት ለመቆጣጠርና ለመከላከል ሰባት አምቡላንሶች፣ የኩላልት እጥበት ማሽኖች፣ የጽኑ ህሙማን አልጋዎች፣ ዘመናዊ የሙቀት መለኪያ ማሽኖች፣ ተንቀሳቃሽ ላቦራቶሪ፣ ኬሚስትሪና ሲብሲ ማሽኖች፣ ላውንደሪ ማሽኖች፣ ታብሌቶች፣ኮምፕውተሮች፣ የተለያዩ መድኃኒቶችና ህክምና መገልገያ መሳሪያዎች ድጋፍ መደረጉን ገልፀዋል፡፡

ወረርሽኙ መከሰቱ ከተረጋገጠበት ጊዜ አንስቶ በተለያዩ የጤና ሙያ በከፍተኛ ደረጃ የሰለጠኑ ባለሙያዎች በመላክ የመከላከልና የመቆጣጠር ሥራን እያገዙ መሆናቸው የጠቀሱት አቶ እንዳሻው ድጋፉ ቀጣይነት ያለው ነው ብለዋል፡፡

Adres

Łaskarzew

Telefon

+251916780017

Strona Internetowa

Ostrzeżenia

Bądź na bieżąco i daj nam wysłać e-mail, gdy Basketo Zone Health Departement social behavioral change communication umieści wiadomości i promocje. Twój adres e-mail nie zostanie wykorzystany do żadnego innego celu i możesz zrezygnować z subskrypcji w dowolnym momencie.

Udostępnij