የአንዳቤት ወረዳ ፖሊስ ታክቲክ ወንጀል ምርመራ ክፍል

  • Home
  • Philippines
  • Andabet
  • የአንዳቤት ወረዳ ፖሊስ ታክቲክ ወንጀል ምርመራ ክፍል

የአንዳቤት ወረዳ ፖሊስ ታክቲክ ወንጀል ምርመራ ክፍል Government Office

ያልተቋጨው ጉዞ!.....=========================ዕለቱ የካቲት 17 ቀን 2014 ዓ.ም. አንዳቤት ወረዳ ሽሜ ሞሻ ቀበሌ፣ የአካባቢው ማህበረሰብ በስራ ላይ ተጠምዷል ግማሹ በተፈ...
05/07/2023

ያልተቋጨው ጉዞ!.....
=========================
ዕለቱ የካቲት 17 ቀን 2014 ዓ.ም. አንዳቤት ወረዳ ሽሜ ሞሻ ቀበሌ፣ የአካባቢው ማህበረሰብ በስራ ላይ ተጠምዷል ግማሹ በተፈጥሮ ሃብት ልማት ፣ ግማሹ በእርሻ ስራ ላይ ተስማርቶ ሁሉም እንደየ ስራው ባህሪ የየግል ስራውን ያከናውናል። በአካባቢው ያሉ ህጻናትም በበኩላቸው ከብቶችን ሲጠብቁ፣ በጫካው እና በየሸንተረሩ ሲጫወቱ ይስተዋላል። እንዲህ እየሆነ የእኩለ ቀኑ ሰዓት ደረሰ። ሰዓቱ ከቀኑ 6፡00 ሰዓት ነው። ከዚሁ ቀበሌ እግዚአብሔር አብ ተብሎ ከሚጠራው ስፍራ። ስራ ላይ የቆየው ማህበረሰብ ለምሳ ሰዓት ወደየቤቱ እየሄደ ነው። በአካባቢው የነበሩ ህጻናት በጫካው እንደ ነገሩ ያገኙትን እንጨት እየለቀሙ ነበር። ከጫካው እንጨት ሲለቅሙ እስካሁን ያልተለመደ አዲስ ነገር አገኙ በፎጣ የተሸፈነ ጫካ ውስጥ ተኝቶ የተገኘ ሰው። ይህ ሰው ምን ሆነ? ቀርበው ለማየት ፍርሃት ቢያድርባቸውም እንደምንም ብለው ቀርበው ሲመለከቱት ፊቱ እና አፍንጫው አካባቢ ጉዳት የደረሰበት ሞቶ የተገኘ ሰው። በሁኔታው ተደናግጠው ሰው እንዲደርስላቸው ጩኸት ሲያሰሙ የአካባቢው ማህበረሰብ ደርሶ ማንነቱን ማወቅ ያልቻሉት ሰው ሞቶ የተገኘ መሆኑን ለቀበሌያቸው የኮ/ፖሊሲንግ ኦፊሰር በስልክ እንዲደርስላቸው አሳውቀው። የቀበሌው ፖሊስ ኦፊሰርም ወዲያውኑ ፈጥኖ ደርሶ ሰው መሞቱን ካረጋገጠ በኋላ ለወረዳ ፖሊስ ጽ/ቤት መርማሪ ፖሊስ እንዲደርስለት በሪፖርት አሳወቀ። ጉዳዩን የደረሰው የምርመራ ክፍል ፖሊስ ወደ ቦታው በመሄድ ከወንጀል ስፍራው ሲያጣራ የሟችን ማንነት ማወቅና መለየት አልቻለም። መታወቂያም ሆነ ማንነቱን የሚገልጽ መረጃ ማግኘት አልቻለም ነገሩ ግራ የሚያጋባ ነውለአካባቢው ማህበረሰብም ትልቅ ጥያቄ ሆኖበታል። ትንሽ እንደቆየ ከስፍራው ብጫቂ ወረቀት አገኘ። ነጠላ ስም የያዘች፣ የሟችን ይሁን የተጠርጣሪ ማንነትን ግን ማግኘት አልተቻልም ነገሩ አወዛጋቢ ነው።
የካቲት 22 ቀን 2014 ዓ.ም. ለፖሊስ አዲስ ጥቆማ ደረሰው የሟችን ማንነት የሚገልጽ ። ሟች ባምላኩ አለባቸው ገላዬ ከተወለደበት አንዳቤት ወረዳ ደረባ ቀበሌ ከ6 ዓመት በላይ ይኖር የነበረው በኦሮምያ ክልል ውስጥ ነው። የሚተዳደረውም በጉልበት ስራ ሆኖ በቀን የሚያገኛትን ገቢ በባንክ እየቆጠበ እንደሚያስቀምጥ ትንሽ ወንድሙ ያስረዳል።
ሟች እንዴት ከኦሮሚያ ክልል መጥቶ ሞተ?
ለሟች የአክስቱ ልጅ የሆነው የሚኖረው አንዳቤት ወረዳ አንዳቤት ከተማ ውስጥ ነበር ምንም ዓይነት የመተዳደሪያ መስክ የለውም። ለቀን ስራ በሚል ሟቹ ካለበት ወደ ኦሮሚያ ክልል ይሄድና ሟች ባምላኩ አለባቸውን ያገኘዋል። ሟችም ወንድሜ እንኳን መጣህልኝ ብሎ በደስታ ከተቀበለው በኋላ ለሳምንታት ቆይተው ሟችን ቤተሰቦቹ ደካማ ስለሆኑ መጠየቅ እንዳለባቸው ተነጋግረው ፣ ሟችም ቤተሰቦቹን መጠየቅ እንደሚፈልግና ከአክስቱ ልጅ ጋር አብረው ወደ አንዳቤት እንደሚሄዱ ጋምቤላ ላለው ትንሽ ወንድሙ በስልክ ነግሮት ጉዞ ይጀምራሉ። ከሟቹ ገንዘብ እንዳለው የተረዳው የአክስት ልጅ የሆነው አዲስ አበባ ሲደርሱ "ወንድሜ ያጠራቀምከውን ገንዘብ በባንክ አስገባልኝ እና ቦታ ልግዛልህ" ብሎ ያታልለዋል። ወንድሜ ስጋየ ነው ብሎ ያመነው ሟች ለተጠርጣሪው በአካውንቱ 430000 ብር (አራት መቶ ሰላሳ ሽህ ብር) ያስገባለታል። ለሶስት ቀናት አብረው ሲጓዙ ከሰነበቱ በኋላ አንዳቤት ከተማ ሽሜ ሞሻ ቀበሌ ሲደርስ የካቲት 16 ቀን 2014 ዓ.ም. ገዳይ የሆነው የአክስት ልጅ ገና ከቤተሰቦቹ ሳይደርስ ሟች ባምላኩ አለባቸው የተባለውን ከመንገድ ጫካ ውስጥ እንደገደለው ለፖሊስ ጥቆማ ይደርሰዋል።
ይህንን ጥቆማ የደረሰው ምርመራ ቡድን የተለያዩ የቴክኒክ፣ የሰው፣ የሰነድና የኤግዚቪት ማስረጃዎችን በስፋት አስደግፎ በተጠርጣሪ ማማሩ/ክንዳለም ሃይሌ በተባለው ምርመራውን አጣርቶ ለሚመለከተው የፍትህ አካል ይልካል። ጉዳዩን የተመለከተው የደቡብ ጎንደር ዞን ፍትህ መምሪያ በተጠርጣሪው ክስ መስርቶ ሲያከራክር ከቆየ በኋላ የደ/ጎንደር ዞን ከፍተኛ ፍ/ቤት ዛሬ ሰኔ 28 ቀን 2015 ዓ.ም. በዋለው ችሎት በተከሳሽ ማማሩ/ክንዳለም ሃይሌ ላይ ራሱንም ያስተምራል ሌላውንም ማህበረሰብ ያያስጠነቅቃል በሚል የ20 ዓመት ጽኑ እስራት የወሰነበት መሆኑን መረጃው ያስረዳል።

17/06/2023
ለህግ አለመታዘዝ ያለው ተጠያቂነት!==========================በደ/ጎንደር ዞን አንዳቤት ወረዳ ለህግ ያለመታዘዝና መቃወም ወንጀል የፈጸመ ግለሰብ በእስራት ተቀጣ።ነገሩ እንዲህ ...
16/06/2023

ለህግ አለመታዘዝ ያለው ተጠያቂነት!
==========================
በደ/ጎንደር ዞን አንዳቤት ወረዳ ለህግ ያለመታዘዝና መቃወም ወንጀል የፈጸመ ግለሰብ በእስራት ተቀጣ።
ነገሩ እንዲህ ነው ተከሳሽ እንግዳው ምናለ ሞላ ነዋሪነቱ በአንዳቤት ወረዳ በቅሎ ፍለጋ ቀበሌ ሲሆን ከዚህ ቀደም በህገወጥ የጦር መሳሪያ ወንጀል ተከስሶ የደ/ጎንደር ዞን ከፍተኛ ፍ/ቤት በገደብ ቢያስተምረውም ከድርጊቱ ባለመቆጠቡ የጦር መሳሪያ በመግዛት ጥር 10 ቀን 2015 ዓ/ም አንዳቤት ወረዳ በቅሎ ፍለጋ ቀበሌ ላይ ሁለት ንጹሃን ሰዎችን በጥይት በማቁሰል ድርጊቱን ይፈጽማል።
በተጠረጠረበት የመግደል ሙከራ ወንጀል ፖሊስ እንደሚፈልገው ሲያውቅ ከአካባቢው የተሰወረ ቢሆንም በዚህም ፖሊስ አስፈላጊ የሆኑትን ማሥረጃዎችን በማሰባሰብ ምርመራ አጣርቶ የፍ/ቤት መያዣ ትዕዛዝ በማውጣት ክትትል ሲያደርግ ቆይቶ የካቲት 09 ቀን 2015 ዓ.ም. በደረሰው ጥቆማ የተቀናጀ የጸጥታ ሃይልና ፖሊስ ተጠርጣሪውን ለመያዝ ወደቦታው በማቅናት ከመኖሪያ ቤቱ የሄደ ሲሆን ተጠርጣሪውም ወዲያውኑ የጸጥታ ኃይሉ ላይ ጥይት ተኩስ ይጀምራል።
በዕለቱ የተሰማራው የጸጥታ ኃይልና ፖሊስ ጥበብና ትዕግስት በተሞላበት መንገድ ከያዘው የጦር መሳሪያ ጋር በቁጥጥር ስር ለማዋል ችሏል።
ተጠርጣሪው ከፈጸመው የግድያ ሙከራ ሌላ ለጸጥታ ኃይሎች በህግ አልታዘዝም ብሎ በፈጸመው ወንጀል ፖሊስ ምርመራውን አጣርቶ ለሚመለከተው የፍትህ አካል በመላክ ክስ እንዲመሰረትበት አድርጓል። ጉዳዩን የተመለከተው የአንዳቤት ወረዳ ፍ/ቤት ሰኔ 08 ቀን 2015 ዓ.ም. በዋለው ችሎት በተከሳሽ እንግዳው ምናለ ላይ የአንድ ዓመት ከአንድ ወር አስራ አምስት ቀን ጽኑ እስራትና ሀለት ሽህ አምስት መቶ ብር እንዲቀጣ እንዲሁም የያዘው የጦር መሳሪያ ለመንግስት ገቢ እንዲሆን የወሰነበት ሲሆን በሁለት ሰዎች ላይ የፈጸመው የግድያ ሙከራ ወንጀል ምርመራውን አጣርቶ ለሚመለከተው አካል የላከ መሆኑን ፖሊስ አስታውቋል።

በአንዳቤት ወረዳ የስርቆት ወንጀል የፈፀሙ ተጠርጣሪዎች እጅ ከፍንጅ በቁጥጥር ስር ዋሉ።፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨ተጠርጣሪዎች 1ኛ ቻሌ ዓለም ዋለ አድራሻው እስቴ ወረዳ በል...
03/06/2023

በአንዳቤት ወረዳ የስርቆት ወንጀል የፈፀሙ ተጠርጣሪዎች እጅ ከፍንጅ በቁጥጥር ስር ዋሉ።
፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨
ተጠርጣሪዎች 1ኛ ቻሌ ዓለም ዋለ አድራሻው እስቴ ወረዳ በልታ ሙሳፋ ቀበሌ ልዩ ጎጡ ዳሞት፣ 2ኛ ደባልቄ ውብሸት አዝመራው እስቴ ወረዳ መካነኢየሱስ ቀበሌ የተባሉት ከእስቴ ወረዳ ተነስተው አንዳቤት ወረዳ አንዳቤት ከተማ ቀበሌ ልዩ ቦታው አንዳቤት ገበያ ጌሾ የሚገዙ በመምሰል የግል ተበዳይ ይርዳው ማለፊያ የተባለው ሊሸጥ ያመጣውን ጤፍ ግምቱ 3100 ብር ( ሶስት ሽህ አንድ መቶ ብር) የሚያወጣውን ከተጫነች አህያ አውርደው ተሸክመው ይዘው ሊሄዱ ሲሉ ዛሬ ግንቦት 26 ቀን 2015 ዓ.ም. በግምት ከጧቱ 3፡00 ሰዓት እጅ ከፍንጅ ተይዘዋል።
ለገበያ የሚመጣው የወረዳችን ማህበረሰብ ከተለያዩ ወረዳዎች እና ቀበሌዎች ያለ አግባብ ለመበልጸግ የማጭበርበር እና የስርቆት ወንጀል የሚፈጽሙ ግለሰቦች ሊመጡ ስለሚችሉ ግብይት በሚፈጸምበት ጊዜ ከተለያዩ አጭበርባሪዎች እና ኪስ አውላቂ ሌቦች ጥንቃቄ እንዲያደርግ መልዕክታችን ነው።
፨፨፨፨፨፨ የአንዳቤት ወረዳ ፖሊስ ፨፨፨፨፨፨፨
ግንቦት 26 ቀን 2015 ዓ/ም
አንዳቤት

በደ/ጎንደር አስ/ዞን አንዳቤት ወረዳ፣ በአሩታ ቀበሌ ማህ/አቀ/ፖ/አገልግሎት ማዕከል የሰላም ቀን በድምቀት ተከበረ።ሚያዝያ 28 ቀን 2015 ዓ.ም.አንዳቤት፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨...
06/05/2023

በደ/ጎንደር አስ/ዞን አንዳቤት ወረዳ፣ በአሩታ ቀበሌ ማህ/አቀ/ፖ/አገልግሎት ማዕከል የሰላም ቀን በድምቀት ተከበረ።
ሚያዝያ 28 ቀን 2015 ዓ.ም.
አንዳቤት
፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨
በአንዳቤት ወረዳ አሩታ ቀበሌ ማህ/አቀፍ ፖሊስ አገልግሎት ማዕከል የሰላም ቀን በድምቀት ተከበረ። የሰላም ቀን ሊከበር የቻለው ከ2010 ዓ.ም. ጀምሮ እስከ 2015 ዓ.ም. ያለምንም ሁኔታ ወንጀል ያልተፈፀመበት ከወንጀል ስጋት ነጻ የሆነ ቀበሌ በመፈጠሩ ነው ሲሉ በአንዳቤት ወረዳ የአሩታ ቀበሌ ማህበረሰብ ክፍሎች አስተያየታቸውን ጠቅሰዋል።
በአንዳቤት ወረዳ የአሩታ ቀበሌ ማህበረሰብ አቀፍ ፖሊስ አገልግሎት ማስተባበረያ ኦፊሰር ም/ሳጅን ወንድምሁነኝ ማስረሻ እንደገለጹት በቀበሌው የተለያዩ ወንጀሎችን ልንቀንስ የቻልነው ከአመራሩ ጋር ተግባብተን በመስራት፣ ልዩ ልዩ አደረጃጀቶችን በመፍጠር፣ አመራሩ ጎጦችን ተከፋፍሎ የዕለት ከዕለት ችግሮችን በመፍታቱ እንዲሁም በየቀጠናው ለማህበረሰቡ የግንዛቤ ትምህርት በመፍጠራችን ይኸው በተከታታይ አምስት ዓመታት ወንጀልን በመቀነስ ቀበሌውን ከወንጀል ስጋት ነጻ አድርገናል ሲሉ ገልጸዋል።
በፕሮግራሙ የደቡብ ጎንደር ዞን የፖሊስ ከፍተኛ አመራሮች፣ የወረዳ ፖሊስ አመራሮችና አባላት፣ የወረዳ የሴክተር መ/ቤት አመራሮች፣ የሃይማኖት አባቶችና የአሩታ ቀበሌ ማህበረሰብ ተገኝተዋል።

በደመቀና በአማረ ሰርግ ልጅን ድሮ አበባን እንደማየት የመሰለ ትልቅ ጸጋ የለም። በሃገራችን በተለያዩ ባህላዊ ትውፊቶች በሰርግ ስነስርዓት ጋብቻ ይፈጸማል። ይህ መልካም ተግባር ሆኖ እያለ ለሰ...
21/04/2023

በደመቀና በአማረ ሰርግ ልጅን ድሮ አበባን እንደማየት የመሰለ ትልቅ ጸጋ የለም። በሃገራችን በተለያዩ ባህላዊ ትውፊቶች በሰርግ ስነስርዓት ጋብቻ ይፈጸማል። ይህ መልካም ተግባር ሆኖ እያለ ለሰርግ እና ለደስታ በሚል ሰበብ የሚተኮሰው ጥይት እንደ ባህል ተቆጥሮ ከጥቅሙ ይልቅ መዘዙ የከፋ እየሆነ መጥቷል።
በዛሬው ዕለት በአንዳቤት ወረዳ የተፈፀመው አሳዛኝ ተግባር በሰርግ ሰበብ በተተኮሰ ጥይት ለህይወት መጥፋት እና ለአካል ጉዳት ዳርጓል።
ዕለቱ ሐሙስ ሚያዝያ 12 ቀን 2015 ዓ.ም. አንዳቤት ወረዳ በቅሎ ፍለጋ ቀበሌ ልዩ ቦታው መርገዶ ማርያም ተብሎ ከሚጠራው ስፍራ አቶ ክንዱ ታደሰ የተባሉት ግለሰብ ወንድ ልጃቸውን ባማረና በደመቀ ሰርግ ድረው ወዳጅ ዘመዶቻቸውን እንዲሁም በአካባቢው ያሉ ጎረቤቶቻቸውን ጠርተው በወጉና በባህሉ መሰረት ይጫወታሉ። ጨዋታን ጨዋታ ሲያደምቀው ቆይቶ ድንገት ያልታሰበ ክስተት ተከሰተ። በዕለቱ በሰርጉ የተጠሩት ሰርገኞች የአካባቢው ሰዎች ቢሆንም ከሰርጉ ባለቤት ጋር ዝምድና የላቸውም በጎረቤትነት ግን ተጠርተዋል። ከሰርጉ መካከል አንደኛው ግለሰብ አብራራው የጦር መሳሪያ ይዟል። ይኸው ግለሰብ በደመቀው ጨዋታ መካከል ለሰርጉ ማድመቂያ በሚል ጥይት ይተኩሳል። በዚህ በተተኮሰው ጥይት የአንድ ሰው ህይወት ጠፍቷል፣ የአንድ ሰው ደግሞ አካል ጉዳት ደርሷል። በዚህ የተነሳ ሰርጉ ከደስታ ወደ ሃዘን ተለወጠ፣ በሰርጉ የተጠራው ሰውም ተበተነ። የሟች ቤተሰቦችም ከፍተኛ የሆነ መሪር ሃዘን ገጠማቸው። እንግዲህ ከአጉል ባህል፣ ከግንዛቤ ጉድለትና ከኋላ ቀርነት አስተሳሰብ የተነሳ የጥይት ተኩስ እያመጣ ያለው መዘዝና ጣጣ ማህበረሰቡን በኢኮኖሚ፣ ማህበራዊ እና ፖለቲካዊ ቀውስ ውስጥ እየከተተው ይገኛል።
ውድ የወረዳችን ማህበረሰብ ክፍሎች ከጥይት ተኩስ የሚገኘው ትርፍ፣ ጥቅም ምንድን ነው? ለዚህ አስተያየት ስጡበት።
" ከአንዳቤት ወረዳ ፖሊስ"
ሚያዝያ 13 ቀን 2015
አንዳቤት

19/04/2023
የውንብድና ወንጀል የፈጸሙ ተጠርጣሪዎች በቁጥጥር ዋሉ።መጋቢት 17 ቀን 2015 ዓ/ምአንዳቤት፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨በአንዳቤት ወረዳ የውንብድና ወንጀል ፈጽመዋል ተብለው የተጠ...
26/03/2023

የውንብድና ወንጀል የፈጸሙ ተጠርጣሪዎች በቁጥጥር ዋሉ።
መጋቢት 17 ቀን 2015 ዓ/ም
አንዳቤት
፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨
በአንዳቤት ወረዳ የውንብድና ወንጀል ፈጽመዋል ተብለው የተጠረጠሩ ሶስት ተጠርጣሪዎች በቁጥጥር ስር ዋሉ።
የወረዳው ፖሊስ ጽ/ቤት ታክ/ወንጀል ምርመራ ክፍል ኃላፊ ም/ኢ/ር ተስፋየ ገዳሙ እንደገለጹት ተጠርጣሪዎች መጋቢት 16 ቀን 2015 ዓ.ም. በግምት ከምሽቱ 3፡00 ሰዓት ሲሆን አንዳቤት ወረዳ አንዳቤት ከተማ ልዩ ቦታው ቀጠና 2 ተብሎ ከሚጠራው ስፍራ በአንድ የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ውስጥ የሚሰራ ሰራተኛ ወደ ቤቱ እየተንቀሳቀሰ ባለበት አራት ሆነው የግል ተበዳዩን በመደብደብ አንድ ሳምሰንግ ጋላክሲ A21 ሞባይል ቀምተው ከወሰዱ በኋላ ሞባይሉን ከግል ተበዳዩ ግለሰብ ቀምቶ የወሰደውን ጨምሮ ሁለቱ ተጠርጣሪዎች ሲያመልጡ ሌሎች ሁለት ተጠርጣሪዎች ወዲያውኑ ሊያዙ ችለዋል።
በተሰወሩት ተጠርጣሪዎች ፖሊስ በአደረገው ጠንካራ ክትትል ሞባይሉን ቀምቶ ወስዶ የነበረው ተጠርጣሪ ዛሬ መጋቢት 17 ቀን 2015 ዓ.ም. አንዳቤት ወረዳ ወፍጫሜ ቀበሌ ሲንቀሳቀስ ከእነ ሞባይሉ እጅ ከፍንጅ በፖሊስ ቁጥጥር ስር ውሏል። በተጠርጣሪዎቹ ላይ ፖሊስ አስፈላጊ የሆኑትን ማስረጃዎች በመሰብሰብ ምርምራ እያጣራ መሆኑን አስታውቋል።

18/03/2023
በህገ-ወጥ መንገድ የጦር መሳሪያ ሲያዘዋውሩ የነበረው ግለሰብ በቁጥጥርስር ዋለ።በደቡብ ጎንደር ዞን አንዳቤት ወረዳ በቀን 7/7/2015 ዓ.ም ከጧቱ 12፡00ስዓት መነሻውን ደብረታቦር በማድረ...
17/03/2023

በህገ-ወጥ መንገድ የጦር መሳሪያ ሲያዘዋውሩ የነበረው ግለሰብ በቁጥጥር
ስር ዋለ።
በደቡብ ጎንደር ዞን አንዳቤት ወረዳ በቀን 7/7/2015 ዓ.ም ከጧቱ 12፡00
ስዓት መነሻውን ደብረታቦር በማድረግ ህገወጥ የጦር መሳሪያና ጥሬ ብር
በባጃጅ ሲያዘዋውሩ የተገኘው ግለሰብ በቁጥጥር ስር ዋለ፡፡
የአንዳቤት ወረዳ ፓሊስ ጽ/ቤት የታክቲክ ወንጀል ምርመራና ክፍል ኃላፊ
ምክትል ኢንስፔክተር ተስፋየ ገዳሙ ይህን ወንጀል የፀጥታ መዋቅሩና የፓሊስ
አባላት ማህበረሰቡ በሰጠው ጥቆማ መሰረት በቅንጅት በተደረገ ፍተሻ መጋቢት
7 ቀን 2015 ዓ.ም ከጧቱ 12፡00 አንዳቤት ወረዳ ጎኖ ቀበሌ ልዩ ቦታው ጎኖ ጤና ጣቢያ ፊት ለፊት ተብሎ ከሚጠራው ስፍራ ሶስት ክላሽ ንኮቭ እና ለዚህ ተግባር የሚውል
አንድ መቶ ሃያ አምስት ሽህ ብር በቁጥጥር ስር መዋሉን ገልፀዋል፡፡
በዚህም ህገወጥ መሳሪያ ዝውውርን ወንጀልን ለመከላከል የፀጥታ አካሉና
ማህበረሰቡ በጋራ በመስራትና ህገ-ወጦችን ለህግ ማቅረብ መቻል አለብን
ብለዋል፡፡
ቀጣይም ይህን ተግባር ለማስቆም የጸጥታ አካሉ ያለውን ቁመና አጠናክሮ
እድሚያስቀጥል ተናግረዋል፡፡
መጋቢት08/2015 ዓ.ም

17/03/2023

Address

Andabet

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when የአንዳቤት ወረዳ ፖሊስ ታክቲክ ወንጀል ምርመራ ክፍል posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Share