Embassy of Ethiopia, Tokyo

Embassy of Ethiopia, Tokyo This is the official page of the Embassy of the Federal Democratic Republic of Ethiopia to Japan.

Prime Minister Abiy Ahmed Ali "The Green Legacy season is upon us. With more than eight billion seedlings raised and rea...
13/06/2026

Prime Minister Abiy Ahmed Ali "The Green Legacy season is upon us. With more than eight billion seedlings raised and ready for planting, let us plant hope for a greener tomorrow."

የአገራችንን ወቅታዊ ሁኔታና ጠቅላላ ምርጫ አስመልክቶ የአገራችንን አቋም የማስገንዘብና ዲፕሎማሲያዊ ድጋፎችን የማስገኘት ተግባራት ተከናወኑ፡፡ጃፓን የኢ.ፌ.ዴ.ሪ. ኤምባሲ ኢትዮጵያ ፈጣን ዕድ...
13/06/2026

የአገራችንን ወቅታዊ ሁኔታና ጠቅላላ ምርጫ አስመልክቶ የአገራችንን አቋም የማስገንዘብና ዲፕሎማሲያዊ ድጋፎችን የማስገኘት ተግባራት ተከናወኑ፡፡

ጃፓን የኢ.ፌ.ዴ.ሪ. ኤምባሲ ኢትዮጵያ ፈጣን ዕድገት በማስመዝገብ በምትገኝበት በዚህ ወቅት የአገር ውስጥ እና የውጭ የጥፋት ሃይሎች የአገሪቱን ልማትና የቀጠነውን ዕድገት ለማደናቀፍ እያሴሩ እንደሆነ ለሚመለከታቸው አካላት አጋልጧል፡፡

በጃፓን የኢ.ፌ.ዴ.ሪ. ባለሙሉ ስልጣን አምባሳደር ዳባ ደበሌ የእነዚህ ጸረ-ሰላም ሃይሎች እኩይ ተግባር ለኢትዮጵያ ብሎም ለቀጣናው ሰላምና መረጋጋት ጠንቅ መሆኑን ለጃፓን የመንግስት አካላት፣ ኤምባሲው ለሚሸፍናቸው አገራት ባለስልጠናት፣ ለጃፓን የልማት ድርጅቶችና ታዋቂ ኩባንያዎች፣ እንዲሁም የሚዲያ አካላትና ተጽዕኖ ፈጣሪ ግለሰቦች አስገንዝበዋል፡፡ እነዚህ አካላት በጉዳዩቹ ላይ በቂ መረጃ አግኝተው የአገራችንን አቋም እንዲደግፉና ጸረ-ሰላም እንቅስቃሴውን እንዲያወግዙም ጠይቀዋል፡፡

ክቡር አምባሳደሩ ካነጋገሯቸው አካላት መካከል የጃፓን ጠቅላይ ሚኒሰትር ልዩ አማካሪ፣ የጃፓን ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የስራ ኃላፊዎች፣ የጃፓን የገዢው ፓርቲ እና የተወካዮች ምክር ቤት ኃላፊዎች፣ የጃፓን መንግስት የልማት ድርጅት የሆነው የጃይካ ሲኒየር ምክትል ፕሬዚዳንት፣ የጃፓን ሚዲያ ተቋማት፣ የላኦ ሕዝቦች ሪፐብሊክ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ሚኒስትር ዴኤታና ሌሎች ከፍተኛ አመራሮች፣ በጃፓን የማይናማር ሚሲዮን መሪ እንዲሁም ተቀማጭነታቸው በጃፓን የሆነ የተለያዩ የዲፕሎማቲክ ማህበረሰብ አባላት ይገኙበታል፡፡

ክቡር አምባሳደሩ ከእነዚህ አካላት ጋር ባደረጓቸው ሰፋ ያሉ ውይይቶች የጥፋት ሃይሎቹ ግንባር በመፍጠር የፌዴራል መንግስቱን ዳግም ወደ ጦርነት በማስጋባት ሰላማችንና ልማታችን ለማደናቀፍ እያደረጉ ስላለው እንቅስቃሴ ማብራሪያ በማቅረብ ግንዛቤ የማስጨበጥ ተግባራትን አከናውነዋል፡፡

በውይይቶቹ የተሳተፉት አካላትም አገራችን የአካባቢውን ሰላምና ጸጥታ በማረጋገጥ ረገድ ግንባር ቀደም ሚና በመጫወት ላይ ያለች አገር እንደሆነች፣ ግጭት ውስጥ መግባት ከጥፋት ውጭ ለማንም የሚያስገኘው ጥቅም እንደሌለና ችግሮች በንግግር፣ በሰላማዊና በሰለጠነ መንገድ መፈታት እንዳለባቸው፣ ቀጣናውን ለማተራመስ የሚንቀሳቀሱ ሃይሎችን ለማጋለጥ ሰላም ወዳድ የአካባቢው አገራት መረጃዎችን መለዋወጥና ተጽዕኖ እንዲፈጠር ማድረግ እንደሚገባና ዓለም አቀፍ ማህበረሰቡም የበኩሉን ድርሻ እንዲወጣ ግፊት ማድረግ እንደሚያስፈልግ አስምረውበታል፡፡

በተመሳሳይ አገራችን ሰባተኛውን ጠቅላላ ምርጫ እ.ኤ.አ. ጁን 1 ቀን 2026 ለማካሄድ ተከታታይ የቅድመ ዝግጅት ስራዎች ሲከናወኑ እንደቆየና እንደተጠናቀቀ፣ በዚህም ሕዝቡ እንደተለመደው ለዴሞክራሲ ሥርዓት ግንባታ ያለውን ቁርጠኝነት በተግባር እንዲያረጋግጥ በቀረበለት ጥሪ መሠረት ከ50 ሚሊዮን በላይ የአገራችን ህዝቦች ቀጣይ መንግስታቸውን ለመምረጥ የምዝገባ ሂደታቸውን ማጠናቀቃቸውን፣ የፖለቲካ ፓርቲዎች በፍትሐዊነት የፖሊሲ አማራጫቸውን ለሕዝብ በማቅረብ እንዲያስተዋውቁ ምቹ ሁኔታዎች እንደተፈጠሩም ክቡር አምባሳደሩ አስገንዝበዋል፡፡

ከዚህ ጋር በተያያዘ የጃፓን መንግስት ለምርጫው ማስፈጸሚያ የሶስት ሚሊዮን የአሜሪካ ዶላር የገንዘብ ድጋፍ ማድረጉ እና አዲስ አበባ በሚገኘው ኤምባሲው በኩል ባወጣው መረጃ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ምርጫውን በማካሄዱና ህዝቡም በምርጫው ስለነበረው ተሳትፎ ምስጋናውን ማቅረቡ ይታወሳል፡፡

በአጠቃላይ፣ በጃፓን የኢ.ፌ.ዴ.ሪ. ኤምባሲ በኩል የኢትዮጵያን ወቅታዊ ሁኔታ አስመልክቶ የተደረገው እንቅስቃሴ የጥፋት ሃይሎቹ የኢትዮጵያን ሰላም ለመበጥበጥና ልማቷን ለማደናቀፍ እንዲሁም ቀጣናውን ለማናጋት እያሴሩና እኩይ ተግባራትን በመፈጸም ላይ እንደሚገኙ ማጋለጥና መንግስት ለኢትዮጵያም ሆነ የቀጣናው ልማትና ብልጽግና እንዲረጋገጥ ለሰላም የሚሰጠውን ቅድሚያና ለሰላም ያለውን ጽኑ አቋም ማስገንዘብ የተቻለበት ነበር፡፡

ኤምባሲው በጃፓንና በሚሸፍናው አገራት ስአገራችን ወቅታዊ ሁኔታና ጠቅላላ ምርጫ ግንዛቤ የማስጨበጥና ድጋፎችን የማሰባሰብ ስራውን በተጠናከረ መልኩ እያከናወነ ነው፡፡

Important Notice for InvestorsThe Ethiopian Investment Commission (EIC) reminds all investors who haven't yet registered...
11/06/2026

Important Notice for Investors

The Ethiopian Investment Commission (EIC) reminds all investors who haven't yet registered on the Digital Investment Service System to complete the process within the one-month window starting June 12, 2026.

Few cities can claim to be both the diplomatic capital of Africa and a gateway to centuries of living history.Addis Abab...
11/06/2026

Few cities can claim to be both the diplomatic capital of Africa and a gateway to centuries of living history.

Addis Ababa is one of them.

Walk through the heart of African unity. Discover a city where heritage inspires innovation, where culture shapes every experience, and where sustainable destinations invite you to travel with purpose.

This is more than a place to visit.

It's a place to connect, explore, and write your own chapter.

Plan your visit at VisitEthiopia.et


Prime Minister Abiy Ahmed Ali:"𝐂𝐎𝐍𝐆𝐑𝐀𝐓𝐔𝐋𝐀𝐓𝐈𝐎𝐍𝐒, 𝐅𝐄𝐋𝐋𝐎𝐖 𝐄𝐓𝐇𝐈𝐎𝐏𝐈𝐀𝐍𝐒 𝐎𝐍 𝐓𝐇𝐄 𝟓 𝐌𝐈𝐋𝐋𝐈𝐎𝐍 𝐂𝐎𝐃𝐄𝐑𝐒 𝐌𝐈𝐋𝐄𝐒𝐓𝐎𝐍𝐄! What we set out to ...
11/06/2026

Prime Minister Abiy Ahmed Ali:

"𝐂𝐎𝐍𝐆𝐑𝐀𝐓𝐔𝐋𝐀𝐓𝐈𝐎𝐍𝐒, 𝐅𝐄𝐋𝐋𝐎𝐖 𝐄𝐓𝐇𝐈𝐎𝐏𝐈𝐀𝐍𝐒 𝐎𝐍 𝐓𝐇𝐄 𝟓 𝐌𝐈𝐋𝐋𝐈𝐎𝐍 𝐂𝐎𝐃𝐄𝐑𝐒 𝐌𝐈𝐋𝐄𝐒𝐓𝐎𝐍𝐄!

What we set out to achieve in three years, we have accomplished in less than two. Since the launch of the 5 Million Ethiopian Coders Initiative on July 23, 2024, Ethiopia has reached 5,005,146 enrollments across Programming, Data Analysis, Android Development, and Artificial Intelligence fundamentals. This is our testament to our people's determination and limitless potential.

This milestone is not where our ambition ends, it is where it accelerates further. With 7 million enrollments by August 2026 firmly within our vision, I call upon every Ethiopian to be part of this national mission.

To our young students, this summer is your opportunity. Do not let it pass idly. Register, learn, and return to your classrooms not just as students, but as certified digital leaders. The courses are free, the certification is internationally recognized.

The future you build starts today!"

ENROLL NOW:
ethiocoders.et/

ክቡር አምባሳደር ዳባ ደበሌ ከAssociation of African Economy and Development (AFRECO) ፕሬዚዳንት Mr. Tetsuro Yano ጋር በጽ/ቤታቸው ተገናኝተው ተወያ...
11/06/2026

ክቡር አምባሳደር ዳባ ደበሌ ከAssociation of African Economy and Development (AFRECO) ፕሬዚዳንት Mr. Tetsuro Yano ጋር በጽ/ቤታቸው ተገናኝተው ተወያዩ።

ክቡር አምባሳደር ባደረጉት ውይይት ኢትዮጵያና ጃፓን የረጅም ጊዜ ወዳጅነት ያላቸው ሀገራት ስለመሆናቸው፣ ኢትዮጵያ ለንግድ፣ ኢንቨስትመንትና ቱሪዝም አመቺ አገር ስለመሆኗ፣ አዳዲስ የቱሪስት መዳረሻዎችን ጨምሮ በአገራችን እየተካሄዱ ስላሉ በርካታ የልማት ሥራዎች፣ የሁለቱን አገራት ግንኙነት የበለጠ ለማጠናከር ኤምባሲው ከጃፓን የመንግሥትና ሌሎች የሚመለከታቸው ተቋማት ጋር እየሠራ መሆኑን፣ በዚህም የጃፓን ባለሀብቶች ወደአገራችን መግባታቸውን ገልጸዋል፡፡ አገራችን በንግድ ኢንቨስትመንት እና ቱሪዝም ያላትን እድል በማስተዋዋቅ የጃፓን ኩባንያዎችን የበለጠ ወደ አገራችን ማስገባት፣ ለምርቶቻችን አዳዲስ የገበያ እድል ማስገኘትና፣ የጃፓን ቱሪስቶች ኢትዮጵያን እንዲጐበኙ ማድረግ በሚቻልበት ሁኔታ ላይም ከማህበራቸው ጋር በጋራ መሥራት እንደሚፈልጉ አንስተዋል፡፡ በተጨማሪም በአገራችንና በአፍሪካ ቀንድ ስላለው ወቅታዊ ሁኔታ እና 7ኛው አገራዊ ምርጫ በሰላማዊና ዲሞክራሲያዊ መንገድ ስለመጠናቀቁ በዝርዝር ተወያይተዋል፡፡

ፕሬዚዳንቱም በበኩላቸው ከጃፓን የሚመለከታቸው አካላት ጋር በመቀናጀት በኢትዮጵያም ሆነ በአፍሪካ ቀንድ የሰላም ግንባታ ላይ መሥራት እንደሚፈልጉ፣ ለዚህም የ TICAD መድረክ የበለጠ አመቺ መሆኑን፣ በንግድ፣ ኢንቨስትመንት፣ ቱሪዝም እና በሌሎች ዘርፎች ላይም ከኤምባሲው ጋር በቅርበት ለመሥራት ዝግጁ መሆናቸውን ገልጸዋል፡፡

Vacancy announcement
11/06/2026

Vacancy announcement

  has licensed its first foreign-owned investment bank, marking a new chapter in the country’s capital market reforms. W...
10/06/2026

has licensed its first foreign-owned investment bank, marking a new chapter in the country’s capital market reforms.

What could the entry of pan-African financial group United Capital mean for investment, business growth, and Africa’s economic integration?
Read more: https://pulseofafrica.info/business/378

የፖሊሲ ጉዳይ ቅኝት - ሰኔ 2፣ 2018 ዓ.ምOffice of the Prime Minister-Ethiopia
10/06/2026

የፖሊሲ ጉዳይ ቅኝት - ሰኔ 2፣ 2018 ዓ.ም
Office of the Prime Minister-Ethiopia

09/06/2026

𝐄𝐭𝐡𝐢𝐨𝐩𝐢𝐚’𝐬 𝐅𝐢𝐧𝐚𝐧𝐜𝐢𝐚𝐥 𝐒𝐞𝐜𝐭𝐨𝐫 𝐓𝐫𝐚𝐧𝐬𝐟𝐨𝐫𝐦𝐚𝐭𝐢𝐨𝐧

住所

3-4-1 Takanawa, Tokyo. Takanawa Kaisei Bldg
Minato-ku, Tokyo
108-0074

営業時間

月曜日 09:00 - 18:00
火曜日 09:00 - 18:00
水曜日 09:00 - 18:00
木曜日 09:00 - 18:00
金曜日 09:00 - 18:00
土曜日 10:00 - 17:00

電話番号

03-5420-6860

ウェブサイト

アラート

Embassy of Ethiopia, Tokyoがニュースとプロモを投稿した時に最初に知って当社にメールを送信する最初の人になりましょう。あなたのメールアドレスはその他の目的には使用されず、いつでもサブスクリプションを解除することができます。

その団体に問い合わせをする

Embassy of Ethiopia, Tokyoにメッセージを送信:

共有する

カテゴリー