05/08/2022
የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ብልፅግና ፓርቲ ቅ/ጽ/ቤት ሴቶች ሊግ ከክልሉ ወጣቶች፣ ሴቶችና ህፃናት ጉዳዮች ቢሮ ጋር በመተባበር በሆሞሻ ወረዳ ቱመት ቀበሌ ችግኝ ተተከለ
*****
(አሶሳ፣ ሀምሌ 29/11/2014 ዓ.ም) የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ብልፅግና ፓርቲ ቅ/ጽ/ቤት ሴቶች ሊግ ከክልሉ ወጣቶች፣ ሴቶችና ህፃናት ጉዳዮች ቢሮ ጋር በመቀናጀት በአሶሳ ዞን ሆሞሻ ወረዳ ቱመት ቀበሌ በመገኘት የአረንጓዴ አሻራቸውን አስቀምጠዋል።
ፕሮግራሙን ወ/ሮ ከልቱም ባበክር የክልሉ ብልፅግና ፓርቲ ሴቶች ሊግ ጽ/ቤት ኋላፊ እና ወ/ሮ አበራሽ ደጃስ የክልሉ ሴቶች፣ ህፃናትና ወጣቶች ጉዳይ ቢሮ ም/ኃላፊ ተገኝተው አስጀምረዋል።
ወ/ሮ ዘይነባ ባበክር የሆሞሻ ወረዳ ብልፅግና ፓርቲ ሴቶች ሊግ ጽ/ቤት ኋላፊ እንደገለፁት በወረዳው በተደረገው ንቅናቄ የወረዳውና የቱመት ቀበሌ ከልጅ እስካዎቂ በነቂስ በመውጣት በዛሬው ቀን ብቻ 4 ሺህ 5 መቶ ችግኝ መትከል መቻሉን ገልፀዋል ።
በያዝነው የክረምት ወቅት እንደ አሶሳ ዞን ዘጠኝ ወረዳዎችና አሶሳ ከተማ አስተዳደር 10 ሺህ ችግኞችን ለመትከል እቅድ ተይዞ እየተሰራ መሆኑን ገልፀው፤ ከችግኝ ተከላ ባሻገር ደም መለገስ፣ የአቅመ ደካማ ቤቶችን ማደስ፣ ለትምህርት የደረሱ ህፃናት ወደ ትምህርት ገበታ እንዲመለሱ እና የቦንድ ግዥም መፈፀም እንዳለበት አሳስበዋል።
ወ/ሮ አበራሽ ደጃስ የክልሉ ሴቶች፣ ህፃናትና ወጣቶች ጉዳይ ም /ኋላፊ በችግኝ ተከላ ወቅት ተገኝተው መልዕክት ባስተላለፉበት ወቅት የዚህ ክረምት በጎ ፍቃድ ስራ አረንጓዴ አሻራ ከማስቀመጥ ባሻገር ሰላም ከሌለ የመጀመሪያ የችግር ገፈት ቀማሾች ሴቶቼና ህፃናት ስለሆኑ ሴቶች ለሰላም ዘብ በመቆም አጋርነታቸውን እንዲወጡ አሳስበዋል።
መረጃው፦የክልሉ ብልጽግና ፖርቲ ጽ/ቤት