14/08/2026
🥀 ኢንቨስትመንትዎን/ንግድዎን ለማሳደግ አቅደዋል?
ከዋልያ የካፒታል ዕቃ ፋይናንስ ንግድ ሥራ አ.ማ ማሽኖችን በሊዝ ፋይናንስ ለማግኘት ማሟላት የሚጠበቅብዎ መስፈርቶች:-
👉 አሰራሩን መገንዘብ:- በአክሲዮን ማህበሩ አገልግሎቶችና አሰራሮች ላይ ሙሉ ግንዛቤ መያዝ፤
👉 ክህሎትና ገበያ:- መሣሪያውን/ማሽኖችን ለመጠቀም በቂ ክህሎት ያላቸውና ለሚያመርቱት ምርት /ለሚሰጡት አገልግሎት/ በቂ ገበያ ያላቸው፤
👉 የነዋሪነት መታወቂያ:- በሚሰሩበት ከተማ ቋሚ ነዋሪ የሆኑና የሚኖሩበት ቀበሌ የነዋሪነት መታወቂያ ያላቸው፤
👉 ዲጂታል መታወቂያ:- የፉይዳ ምዘገባ መታወቂያ
👉 ዕድሜና ችሎታ:- ዕድሜያቸው ከ18 ዓመት በላይ የሆኑና የመስራት አቅም/ችሎታ ያላቸው፤
👉 የጋብቻ ሁኔታ:- የጋብቻ ሁኔታን (ያገቡ /ያላገቡ) የሚገልጽ ህጋዊ ማስረጃ የሚያቀርቡ፤
👉 ቲን ናምበር:- የግብር ከፋይነት መለያ ቁጥር ፣
👉 የንግድ ስራ ፈቃድ:- የታደሰ የንግድ ፈቃድ ያላቸው፤
👉የንግድ ምዝገባ ሰርተፍኬት:- በዘርፋ ለመነገድ የተመዘገቡበት የንግድ ምዝገባ ወረቀት፤
👉 የዘመኑን ግብር ስለመከፈሉ እና የግብር ክሊራንስ ማስረጃ ፤
👉 የማህበር ሰነዶች:- በማህበር የተደራጁ ከሆኑ(ብቻ) በንግድ ህጉ መሠረት ህጋዊ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ ማስረጃዎች (የመተዳደሪያ ደንብ እና የመመስረቻ ጽሑፍ) ማቅረብ የሚችሉ፤
👉 የማምረቻ/መሸጫ ቦታ:- መሰረተልማቱ የተሟላ በቂ የማምረቻና የመሸጫ ቦታ (የራስ፣ የኪራይ፣ የመንግስት ሸድ፣ የቤተሰብ) ያላቸው፤
👉 የማሽን ዋጋ መጠን:- እንዲገዛ የሚጠየቀው ማምረቻ መሳሪያ ዋጋ ከ25 ሺህ እስከ 17 ሚሊዮን ብር ብቻ የሆነ፤
👉 ቅድመ ክፍያ ቁጠባ:- የሚገዛላቸውን የካፒታል ዕቃ ጥቅል ዋጋ ከ20 እስከ 50 በመቶ ቅድመ ክፍያ መቆጠብ የሚችሉ፤
👉 የመድን ሽፋን:- ለመሳሪያው የመድን ሽፋን የሚገቡና የዕድሳት ወጭን ለመክፈል ፈቃደኛ የሆኑ /መተማመኛ የሚሰጡ/፤
👉 የንግድ ዕቅድና ዝርዝር:- የንግድ ስራ ዕቅድ እና ከ5 ሚሊዮን ብር በላይ ለሆኑ ፕሮጀክቶች ፕሮፖዛል ማቅረብ የሚችሉ፤ ለሚገዛው ማሽንም ዝርዝር መግለጫ ማቅረብ የሚችሉ፤
👉 የሥራ ማስኬጃ አቅም:- የስራ ማስኬጃ ብድር ፈላጊዎች የሥራ ማስኬጃ ብድሩን ከፋይናንስ ተቋማት ስለማግኘታቸው ወይም በራሳቸው ገንዘብ መስራት የሚያስችላቸው አቅም እንዳላቸው ማረጋገጫ ማቅረብ የሚችሉ፤
👉 የመልካም ተበዳሪነት ታሪክ:- ከአበዳሪ የፋይናንስ ተቋማት የመልካም ተበዳሪነት ታሪክ ያላቸው፤ ነባር ኢንተርፕራይዞች ከማንኛውም አበዳሪ ተቋም የተበደሩት ብድር ካለ ከፍለው ያጠናቀቁ ወይም በአግባቡ እየከፈሉ ያሉና በብድር ዘመናቸው በፋይናንስ ተቋማት የቁጠባ ባህል ያላቸው፤
👉 የሂሳብ መዝገብ:- ነባር ኢንተርፕራይዞች የሂሳብ መዝገብ ያላቸውና መዝገባቸውንም ያስመረመሩ፤ አዲስ ከሆኑ ሂሳብ መዝገብ የሚያዘጋጁና በቀጣይም ለማስመርመር ፈቃደኛ የሆኑ፤
👉 ኢንቨስትመንትና ንብረት:- በታዳጊ መካከለኛ ኢንተርፕራይዞች ደረጃ ያሉና የኢንቨስትመንት ፈቃድ ተሰጥቷቸው የመስሪያ ቦታ ያላቸው ወይም ያመቻቹ ከሆነ የንግድ ሥራ ፈቃድና ሀብት ማፍራቸውን የሚሳይ ንብረት ያላቸው፤
👉 የዕድገት ደረጃ ማረጋገጫ:- የዕድገት ደረጃቸው በጥቃቅንም ይሁን በአነስተኛ ጀማሪ፤ ታዳጊና የበቃ ስለመሆኑ ከሚመለከተው አካል ማረጋገጫ የምስክር ወረቀት/ህጋዊ ደብዳቤ ማቅረብ፤
👉 የሥራ ሁኔታ:- ሙሉ ጊዜያቸውን ባቀረቡት ንግድ ሥራ መስክ ማዋል የሚችሉ ወይም የመንግስት ሰራተኛ ያልሆኑ፤
📌 ማሳሰቢያ:-
➩ እነዚህን መስፈርቶች ካሟሉ በአክሲዮን ማህበሩ የደንበኞች መመዘኛና ማረጋገጫ (KYC) ግምገማ መሰረት ተመልምለው የካፒታል ዕቃ ተጠቃሚ ይሆናሉ፡፡
🏆ምንጭ:-
🇪🇹 ዋልያ የካፒታል ዕቃ ፋይናንስ ንግድ ሥራ አ.ማ