Gena Woreda Health Office

Gena Woreda Health Office This is the official page for Gena woreda health office. This page will be used to distribute information about the office.

22/11/2014በገና ወረዳ የጤና ጉባኤ ተካሄደ። በጉባኤው የሚመለከታቸው አካላት የተገኙ ሲሆን የ 2014 ዓም. አፈጻጸም የተገመገመ ሲሆን የ 2015 ዓ.ም መነሻ እቅድም ቀርቦ የሚመለከታቸ...
29/07/2022

22/11/2014

በገና ወረዳ የጤና ጉባኤ ተካሄደ። በጉባኤው የሚመለከታቸው አካላት የተገኙ ሲሆን የ 2014 ዓም. አፈጻጸም የተገመገመ ሲሆን የ 2015 ዓ.ም መነሻ እቅድም ቀርቦ የሚመለከታቸው አካላት ተፈራርመዋል።

በገና ወረዳ የ ኦንኮሳርኪያሲስ ዘመቻ ስልጠና በመሰጠት ላይ ይገኛል። 23/10/2014 ዓም.በስልጠናው የሚመለከታቸው አካላት ተሳታፊ ሆነዋል ። ዘመቻው ከ ሰኔ 29 / 2014 እስከ ሐምሌ 5...
30/06/2022

በገና ወረዳ የ ኦንኮሳርኪያሲስ ዘመቻ ስልጠና በመሰጠት ላይ ይገኛል። 23/10/2014 ዓም.

በስልጠናው የሚመለከታቸው አካላት ተሳታፊ ሆነዋል ። ዘመቻው ከ ሰኔ 29 / 2014 እስከ ሐምሌ 5 / 2014 ድረስ እንደሚካሄድ ከ ካርተር ሴንተር ያገኘነው መረጃ ያሳያል ።

15/03/2022
በገና ወረዳ የጤና ጉባኤ ተካሄደ ! 02/07/14 ዓ.ም  በገና ወረዳ የጤና ጉባኤ ተካሄደ።  የወረዳው አስተዳደር  አካላት ፣ የጤና ጥ/ጽ/ቤ/ት ማናጅመንት አባላት ፣ ከ ወ/ሃኔ ጤና ጣቢያ...
11/03/2022

በገና ወረዳ የጤና ጉባኤ ተካሄደ !
02/07/14 ዓ.ም

በገና ወረዳ የጤና ጉባኤ ተካሄደ። የወረዳው አስተዳደር አካላት ፣ የጤና ጥ/ጽ/ቤ/ት ማናጅመንት አባላት ፣ ከ ወ/ሃኔ ጤና ጣቢያ እና ከጤና ኬላ የተገኙ ባለሙያዎች እንዲሁም የቀበሌ ስ/አስኪያጅ እና ሊ/መንበር በጉባኤው ተሳትፈዋል። በጉባኤው ላይ የወረዳው 6 ወር የጤና አፈፃጸም ሪፖርት ለ ውይይት የቀረበ ሲሆን በሪፖርቱም ላይ የሚመለከታቸው አካላት ሃሳቦችንና ጥያቄዎችን አንስተው መልስ ተሰጥቶባቸዋል። በመጨረሻም ቀጣይ የትኩረት አቅጣጫዎች ተቀምጠው ውይይቱ ተጠናቋል።

10/12/2021

ልጆዎ በድንገት ነስር ቢነስረው ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን 8 ነገሮች ተግባራዊ ያድርጉ‼️

🛑 ነስርን ብዙ ጊዜ ቤት ዉስጥ በቀላል ዘዴዎች ማቆም ስለሚቻል በመጀመሪያ እርሶ መረጋጋት ይኖርቦታል❗️

🛑 በመቀጠል ልጆዎ ጭንቀላቱን ትንሽ ወደ ፊት ዘንበል አርጎ አፍንጫው አጥንት በታች ያለውን ለስላሳ የ አፍንጫ ክፍል ቢያንስ ለ10 ደቂቃ ጫን አርጎ መያዝ ::

🛑 ቶሎ ከለቀቁ መልሶ ሊደማ ይቺላል

🛑 በዝህ መንገድ ቀላል ነስር ከሆነ ይቆማል ካልተሳካ ግን ለተጨማሪ 10 ደቂቃ አሁንም ደግሞ አፍንጫውን ጫን አርጎ መያዝ ይኖርቦታል

🛑 በሁለት ሙከራዎች ወይም በ 20 ደቂቃ ዉስጥ ካልቆመ በአፋጣኝ ወደ ሆስፒታል ይሂዱ‼️

🛑 ልጆዎ በአፉ እንዲተነፍስ ይንገሩት

🛑 ⚠️ ይጠንቀቁ ❗️ በፍፁም ልጆዎን ወደ ላይ ቀና ማድረግ ወይም ማንጋጠጥ የለበትም:: ምክንያቱም ቀና ስላለ ደሙ ወደ ውጭ አይፍሰስ እንጂ ወደ ዉስጥ በምግብ ቱቦ በኩል በብዛት እንዲፈስ እና ወደ ጨጓራው እንዲገባ ያረጋል ይሄ ደሞ ከፍተኛ የደም ማነስ እና ትውከት ሊያስከስት ይቺላል::

⚠️ ሶፍት ወይም ሌላ ነገር ወደ አፍንጫ አይክተቱ ምክንያቱም እነዚህ ነገሮች መድማቱን ሊጨምሩት ይቺላሉ

⚠️ የልጆን ሁኔታ በቅርበት ይከታተሉ

⚠️ ነስሩ ከቆመ በኋላ ለተወሰነ ሰዓት ልጆ አፍንጫውን እንዳይነካካ እና በኃይል እንዳይናፍጥ ከባድ ነገር እንዳያነሳ ያርጉት

🔺 የልጆች ነስርን መከላከል ይቻላል።

👉 መከላከል ይቻላል ሆኖም ሙሉ ለሙሉ ማስወገድ ግን የሚቻለው በሀኪም ሲታከም ነው::

ስለዚህ መከላከያ መንገዶቹ ምንድናቸው?

📌 ልጆች አፍንጫቸውን ለአደጋ ከሚያጋልጡ ነገሮች ማራቅ
📌 አፍንጫቸውን እንዳይነካኩ ማስተማር
📌 የልጆች ጥፍርን ማሳጠር
📌 የአየር ንብረቱ ደረቅ ከሆነ አፍንጫቸው ዉስጡን ቫዝሊን በመጠኑ መቀባት ወይም እንፋሎት መታጠን
📌 ጉንፋን እና አለርጂን በአግባቡ መታከም
📌 መድሃኒቶችን ያለ ሀኪም ትእዛዝ አለመውሰድ
📌 ቋሚ የህፃናት ሕክምና ክትትል ማድረግ

👩‍⚕️ወደ ሆስፒታል መሄድ ያለበት መቼ ነው ⁉️🏥

🔺 ከላይ እንደ እንደተጠቀሰዉ የማይቆም ከሆነ
🔺 ባንዴ ብዙ ደም መፍሰስ ካለ (ከ1 ስኒ በላይ)
🔺 ልጆዎ ራስ ማዞር እና መሳት ካለው
🔺 ተደጋጋሚ ነስር እና የጥርስ መድማት ካለ
🔺 ቆዳው በቀላል ምት (አደጋ) የሚበልዝ ከሆነ
🔺 ከ 2 ዓመት በታች ነስር ከተከሰተ
🔺 ልጆዎ ከዚህ በፊት የደም ማነስ ካለበት
🔺 ተከታታይ ደም የቀላቀለ ትውከት ካለ

ዶ/ር ፋሲል መንበረ
(በቅዱስ ጳውሎስ ሆስፒታል ሚሊንየም ሜድካል ኮሌጅ ረዳት ፕሮፌሰር እና የህፃናት ስፔሻሊስት ሀኪም)
የደቡብ ክልል ጤና ቢሮ

የፖልዮ ክትባት መሠጠት ተጀመረ።12/02/2014 ዓም.ክትባቱ በሁሉም የገና ወረዳ ቀበሌዋች የሚሠጥ ሲሆን ከ 12/02/2014 እስከ 15/02/2014 ዓም ድረስ ይሠጣል።
22/10/2021

የፖልዮ ክትባት መሠጠት ተጀመረ።
12/02/2014 ዓም.
ክትባቱ በሁሉም የገና ወረዳ ቀበሌዋች የሚሠጥ ሲሆን ከ 12/02/2014 እስከ 15/02/2014 ዓም ድረስ ይሠጣል።

የፖልዮ ዘመቻ ማስጀመርያ ስልጠና ተሠጠ። 11/02/2014ዓም.በስልጠናው ላያ ከ 14ቱም ቀበሌያት የመጡ የጤና ኤክስቴንሽን ባለሞያዋች፣ የመንገድ መሪዋች ፣ ከወ/ሃኔ ጤና ጣቢያ የመጡ ባለሞያ...
21/10/2021

የፖልዮ ዘመቻ ማስጀመርያ ስልጠና ተሠጠ። 11/02/2014ዓም.

በስልጠናው ላያ ከ 14ቱም ቀበሌያት የመጡ የጤና ኤክስቴንሽን ባለሞያዋች፣ የመንገድ መሪዋች ፣ ከወ/ሃኔ ጤና ጣቢያ የመጡ ባለሞያዋች እና ከወረዳው ጤና ጥበቃ ጽ/ቤት የተገኙ አካላት ተሳትፈውበታል ። በስልጠናው ላይም የፖልዮ በሽታ ክትባት እድሜያቸው ከ አምስት አመት በታች ለሆኑ ህጻናት ከጥቅምት 12 እስከ ጥቅምት 15 / 2014 ዓም ድረስ እንደሚሠጥ ተገልጿል።

14/10/2021
03/01/14በገና ወረዳ በ ኮቪድ-19 ክትባት ዙርያ ስልጠና እየተሠጠ ይገኛል። በስልጠናው ላይ የጤና ኤክስቴንሽን ሰራተኞች፣የጤና ባለሞያዋች፣ የወረዳ ጤና ጥበቃ ጽ/ቤት ባለሞያዋች እንዲሁም...
13/09/2021

03/01/14

በገና ወረዳ በ ኮቪድ-19 ክትባት ዙርያ ስልጠና እየተሠጠ ይገኛል። በስልጠናው ላይ የጤና ኤክስቴንሽን ሰራተኞች፣የጤና ባለሞያዋች፣ የወረዳ ጤና ጥበቃ ጽ/ቤት ባለሞያዋች እንዲሁም የሚመለከታቸው የወረዳው አካላት በስልጠናው ተሳታፊ ናቸው። ስልጠናውን ተከትሎ በቀጣይ ቀናት ተጋላጭ ተብለው ለተለዩ አካላት ክትባት የመስጠት ስራዋች የሚሰሩ ይሆናል።

በገና ወረዳ የሚገኙ የ YFS ወጣቶች የፅዳት ዘመቻ አካሄዱ። 20/12/2013 ዓም. ወጣቶቹ የ2013 ዓም. የስራ አፈጻፀማቸውን ከገመገሙ እና የ 2014 ዓም. እቅድ ላይ ከተወያዩ በሁዋላ ...
27/08/2021

በገና ወረዳ የሚገኙ የ YFS ወጣቶች የፅዳት ዘመቻ አካሄዱ። 20/12/2013 ዓም.

ወጣቶቹ የ2013 ዓም. የስራ አፈጻፀማቸውን ከገመገሙ እና የ 2014 ዓም. እቅድ ላይ ከተወያዩ በሁዋላ በ ወልደሃኔ ጤና ጣቢያ የፅዳት ዘመቻ ላይ ተሳትፈዋል።

17/08/2021

ስተረች ማርክ (ሰውነት ላይ የሚወጣ ሸንተረር)
👉 ውድ ስለ ጤናዎ ምን ያውቃሉ ተከታታዮች የሰውነት ሸንተረር ማለት ረዘም፣ ጠበብ፣ ያለ ሰንበር ወይም መስመር ሲሆን አብዛኛውን ጊዜ ከሆዳችን ፣ከጡታቸን ፣ከዳሌ፣ ከጎናችን ፣ከመቀመጫችን እና ከታፋችን ቆዳ ላይ ይወጣል ፡፡
ይህም የሚሆነው ባጋጣሚ ሰውነታችን በከፍተኛ ሁኔታ ክብደት ሲጨምር ወይም ክብደት ሲቀንስ ቆዳችን ከመጠን በላይ ሲለጠጥ /ሲኮማተር ይፈጠራል ፡፡
በአብዛኛውን ከወንዶች ይልቅ ሴቶች ላይ የመፈጠር እድል አለው፡፡
👉 መንስኤው ምንድነው?
📌 እርግዝና
📌 በጉልምስና እና በኮረዳነት ወቅት
📌 በከፍተኛ ሁኔታ ክብደት ጨምሮ መቀነስ
📌 አንዳንድ በሽታዎች (ማርፊን ሲንድረም ፣ኩሺንግ ሲንድረም)
📌 መድሃኒቶች (የኮርቲስቴሮይድ ይዘት ያላቸው መድሃኒቶች)
👉 አጋላጭ ምክንያቶችስ ምንድናቸው?
📌 በቤተስብ ተመሳሳይ ችግር ካለ
📌 የታወቀ የረጅም ጊዜ የቆየ በሽታ ካለ
📌 ክብደት ከእርግዝና በፊት ከፍ ያለ ሲሆን
👉 መከላከያ ዘዴዎቹ ምንድናቸው?
📌 ክብደትን መጠበቅ
📌 የተመጣጠነ ምግብን መጠቀም
📌 በቫይታሚን እና በሚኒራል የበለጸጉ ምግቦችን መመገብ
📌 በቂ ውሃን መጠጣት (8-12) ብርጭቆ ውሃ መጠጣት
👉 በቤት ውስጥ አዘጋጅተን ልንጠቀምባቸው የምንችላቸው ውህዶች ይህም ሲባል በአንድ ጊዜ የሚያጠፋ ሳይሆነ ችግሩን የሚቀንሱ ናቸው፡፡
📌 ቫይታሚን ኤ መውሰድ ወይም በምግብነት መልኩ መጠቀም፡፡
📌 ስኩዋር
👉 አዘገጃጀት
- አንድ ስኒ ስኩዋር ከ¼ ስኒ አልመንድ(ለውዝ) ዘይት ወይም ኮኮናት ዘይት፣የሎሚ ጠብታዎች በመደባለቅ በሳምንት አራት ከቀን በመጠቀም 8-10 ደቂቃ ማሸት
📌 ሬት(አሎቬራ)
- ሬት ሸንተረሩ ያለበት ቦታ መቀባት
📌 የኮኮናት ዘይት

Address

Wokha

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Gena Woreda Health Office posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Share