Konta Police Media communication

Konta  Police Media communication This social media message to the community is about crime and the seriousness of crime as well! It is a media outlet that provides up-to-date information.

ቀን 19/02/2018 ዓ/ም የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ የስልጠና ኦረንተሽን መስጠቱ ተገለፀ ።         አድስ አበባ ጥቅምት 18/2018 ዓ/ምየኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ ለሁሉም የክልል ፖሊስ...
29/10/2025

ቀን 19/02/2018 ዓ/ም
የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ የስልጠና ኦረንተሽን መስጠቱ ተገለፀ ።
አድስ አበባ ጥቅምት 18/2018 ዓ/ም
የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ ለሁሉም የክልል ፖሊስ ኮሚሽነሮች የስልጠና ኦረንተሽን መስጠቱ ተገልጿል።
ለሁሉም ክልል ፖሊስ ኮሚሽነሮች የተሰጠውን ስልጠና ቀደም ስል ለፌደራል ለአድስ አበባና ድረዳዋ ፖሊስ አባሎችና አመራሮች መሰጠቱን አስታውሰው በስልጠናው ግንዛቤ ውጤታማ ስራ እየተሰራ መሆኑ ተገልጿል ።
የተሰጠው የስልጠና ኦረንተሽን በሀገራዊ ጄኦ-ስትራቴጂያዊ ቁመና ላይ መሠረት ያደረገ በመሆኑ ቀጣይ እስከ ወረዳዎችና ከተማ አስ/ር መዋቅሮች በሚሰጠው ስልጠና ሁሉም የፖሊስ አመራሮችና መኮንኖች እንድሁም የፖሊስ አባሎች እንደሚሳተፉ ነው የተገለፀው።
የስልጠና ኦሬንተሽን የተሰጠው በኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ ዋና መስሪያ ቤት ስሆን ክቡር የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ ኮሚሽን ኮሚሽነር ጀነራል ደመላሽ ገ/ሚካኤል ስልጠናው ሀገራዊ አህጉራዊና አለም አቀፋዊ ሁኔታዎችን በማጠን ፖሊሳዊ ተልዕኮን ለመፈፀም የሚያስችል አቅም ለመፍጠር እንደሚያግዝ ነው የገለፁት።
የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ አስተዳደር እና ልማት ጠቅላይ መምሪያ ኃላፊ ም/ኮሚሽነር ጀነራል ነብዩ ዳኜ የስልጠናውን መርሃግብር በማብራራት የሰለጠነ የሰው ኃይል ያለበት የፖሊስ ተቋም ፖሊሳዊ አገ/ትን በብቃት በመስጠት ብሔራዊ ጥቅም የማስጠበቅ ግዳጁን መወጣት ይችላል ስሉ አብራርተዋል።
መረጃው የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ ዋናው መ/ቤት ስሆን
ዘገባው የኮንታ ዞን ፖሊስ ህዝብ ግንኙነት ነው።
ጥቅምት 19/2018 ዓ/ም

ቀን 19/02/2018 ዓ/ም ከወንጀል ድርግትና ከትራፊክ አደጋ መከላከል እንድችሉ ግንዛቤ ማስጨበጫ ተሰጠ።     ኮንታ ዞን ፖሊስ ኮሙኒኬሽን                ኮንታ-አመያ       በ...
29/10/2025

ቀን 19/02/2018 ዓ/ም
ከወንጀል ድርግትና ከትራፊክ አደጋ መከላከል እንድችሉ ግንዛቤ ማስጨበጫ ተሰጠ።
ኮንታ ዞን ፖሊስ ኮሙኒኬሽን
ኮንታ-አመያ
በቀን 18/2/2018 ዓ/ም ከኮንታ ዞን ኮንታ ኮይሻ ወረዳ ደልባ ገነት ቀበሌ ለተውጣጡ የማህበረሰብ ክፍሎች በወንጀልና ትራፊክ አደጋ መከላከል ዙሪያ የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና መሰጠቱ ተገልጿል።
የግንዛቤ ማስጨበጫ የሰጡት የኮንታ ኮይሻ ወረዳ ፖሊስ ጽ/ቤት አመራሮች ከኢትዮጵያ ፌዴራል ፖሊስ ኮይሻ መብራት ኃይል ግድብ ግንባታ ፕሮጀክት ጥበቃ 10ኛ ረጅመን 1ኛ ሻንበል አመራሮች ጋር በመሆን ሲሆን በአንዳንድ ከባድና ቀላል የወንጀል ድርግቶች ማ/ሰቡ እንደት መከላከል እንዳለበትና በአከባቢው የፕሮጀክት ስራ መኖር የተሽከርካሪ እንቅስቃሴ እንድበዛ ምክንያት በመሆኑ መንገዱን ስጠቀሙ ማድረግ ስለሚገባቸው ጥንቃቄ ጭምር የግንዛቤ ማስጨበጫ ተሰጥቷል። በዚሁ የግንዛቤ ማስጨበጫ መድረክ ላይ በቀበሌው የማ/ሰብ ደህንነት ፖትሮል/ ቅኝት/ እና ገለልተኛ አማካሪ ቡድን መልሶ የማደራጀትና ወደ ስራ የማስገባት ስራ ጭምር ተሰርቷል።
መረጃው የኮንታ ኮይሻ ወረዳ ፖሊስ ጽ/ቤት ነው
ዘገባው የኮንታ ዞን ፖሊስ ህዝብ ግንኙነትና ገጽታ ግንባታ ዲቪዥን ነው
ጥቅምት 19/2018 ዓ/ም

27/10/2025

አስቸኳይ እና ልብ የሚሰብር ጥሪ!
የ8 አመቱ ሕፃን ልዑል ሚካኤል ተወስዷል! 🚨

የወዳጃችን ቤተሰብ በከፍተኛ ሰቆቃ ውስጥ ይገኛል!
ለዓመታት በሰላማዊ ወዳጅነቱ የምናውቀው የጓደኛችን (Ase Ayu) የእህት ልጅ የሆነው የ8 ዓመቱ ሕፃን ልዑል ሚካኤል ግርማ ተወስዷል።

ቦታና ጊዜ:

* አካባቢ: ገርጂ የረር አካባቢ
* ልዩ ቦታ: ጉርሙ ሠፈር፣ ከግቢ ውስጥ
* ጊዜ: ቅዳሜ ከቀኑ 8፡30 ሰዓት (በኢትዮጵያ አቆጣጠር)

የሕፃኑ ልዑል መለያ ምልክቶች:
* ዕድሜ: 8 ዓመት
* መልኩ: ጠይም
* በመወሰጃ ሰዓት የለበሰው ልብስ: ቀይ ቲሸርት እና ጅንስ ሱሪ

የሕፃኑ እናት ልጇ ልዑልን በእንባ እየነደደች እና በታላቅ ጭንቀት እየጠበቀች ነው። "ልጄን አግኙልኝ!" ብላ የምታደርገው ለቅሶ የሁላችንንም ልብ የሚነካ ነው።

ጉዳዩ ለሕግ አካላት ቀርቦ ክትትል እየተደረገበት ቢሆንም፣ የልዑልን ደህንነት ለማረጋገጥ የእናንተ የወዳጆቻችን ትብብር ወሳኝ ነው።

የተጠቀሱትን ምልክቶች በመያዝ ሕፃን ልዑል ሚካኤልን የሚመስል ልጅ ካያችሁ ወይም የት እንዳለችሁ ፍንጭ ሊሆን የሚችል ማንኛውም መረጃ ካላችሁ፣ እባካችሁ ወዲያውኑ አሳውቁ!

መረጃ የምትሰጡበት መንገድ:
* የእናትየውን ስልክ ቁጥር ቀጥታ በመደወል:
* 0911 16 00 63
* 0923 52 22 49

ይህን ጥሪ በግል የፌስቡክ ገፃችሁ በማጋራት የእናቲቱን እና የመላ ቤተሰቡን ስቃይ እንጋራ!

🙏🙏🙏

🌴🌴🌴

ቀን 16/02/2018 ዓ/ምየግምገማ ማጠቃለያ መድረክ በኮንታ ዞኑ ፖሊስ መምሪያ  መደረጉ ተገለፀ።       ኮንታ ዞን ፖሊስ ኮሙኒኬሽን                  ኮንታ_አመያ      ከቀን...
26/10/2025

ቀን 16/02/2018 ዓ/ም
የግምገማ ማጠቃለያ መድረክ በኮንታ ዞኑ ፖሊስ መምሪያ መደረጉ ተገለፀ።
ኮንታ ዞን ፖሊስ ኮሙኒኬሽን
ኮንታ_አመያ
ከቀን 26/1/2018 ዓ/ም ጀምሮ በኮንታ ዞን ፖሊስ መምሪያ እና በታችኞቹ ሶስት ወረዳዎችና ሁለት ከተማ አስ/ር ፖሊስ ጽ/ቤቶች የተደረገ የግምገማ ማጠቃለያ መድረክ ተካሔደ።
በተደረገው የ2017 ዓ/ም አፈፃፀም የማጥራት ግምገማ ከዞን ፖሊስ መምሪያ ጀምሮ እስከታችኞቹ መዋቅሮች በተሰጠ የግምገማ አስተያየትና ውሳኔ መሠረት የተዘጋጀ ሰነድ በዞኑ ፖሊስ አዛዥ ም/ኢ/ር ደምሴ ደሳለኝ ቀርቧል።
ተዘጋጅቶ ከቀረበው ሰነድ በተገለጸው መሠረት
በኮንታ ዞን ፖሊስ መምሪያና በታችኞቹ መዋቅሮች በአፈፃፀም በአመለካከት እና በስነ-ምግባር ጉድለት ጎልቶ የታዩ ክፍተቶች ላይ የተደረገው ግምገማ ውሳኔው በህስ በማስጠንቀቂያ በዲስፕሊንና ከኃላፊነት ማንሳትን ያካተተ መሆኑ ጭምር ነው የተገለፀው።
በግምገማ ማጠቃለያ መድረክ ላይ የተገኙ የሶስት ወረዳዎችና ሁለት ከተማ አስተዳደር የሰላም የፀጥታና ሚሊሻ ጽ/ቤት ኃላፊዎች ፖሊስ አዛዦችና አመራሮች አጠቃላይ የፖሊስ ስራ ማትኮር ባለባቸው የፖሊስ ወንጀል መከ/ል በወንጀል ምርመራ በወንጀል መረጃ አሰባሰብና በትራፊክ አደጋ መከላከልና ቁጥጥር ስራዎች ላይ የሚታዪ ክፍተቶች በይበልጥ መቀናጀትና የህዝብ ተሳትፎን የሚጠይቅ መሆን ስላለበት የመቀናጀት ክፍተቶች ታርመው የዞን መዋቅር የድጋፍ ስራዎች ላይ ትኩረት ሊሰጠው ይገባል ስሉ አስተያየታቸውን ሰጥተዋል።
አቶ ወንድማገኝ ወጁ የዞኑ ም/አስተዳዳሪና የገቢዎች መምሪያ ኃላፊ የማጥራት ግምገማ ማጠቃለያ መድረክ ላይ በተገኙበት በቀረበው ሰነድ ዙሪያ ሐሳብና አስተያየት ተቀብለው ቀጣይ በበጀት አመቱ መደገም የሌለባቸው ስህተቶች በተሰጠው ውሳኔ መሠረት ታርመው የዞኑ መንግስትና ህዝብ የሚጠብቀውን ፖሊሳዊ አገ/ት በተቀናጀና በተጠናከረ መንገድ መስጠት የሚችል የፖሊስ ተቋም የተገነባበት ግምገማ በመሆኑ ፍትሐዊ እና ተደራሽ የሆነ አገ/ት መስጠት ይጠበቃል ነው ያሉት።
አቶ እስራኤል ጮንቄ የዞኑ ሰላም ፀጥታና ሚሊሻ መምሪያ ኃላፊ እንደገለፁት በአፈፃፀም በአመለካከት እና በስነ_ምግባር ታንፆ አቅሙን የገነባው የፖሊስ ኃይል የአገልጋይነት መንፈስ ተላብሶ የህዝቡን ሰላም ወዳድነትን በመልካም አጋጣምነት ተጠቅሞ በቅድመ ወንጀል መከላከል ስራ ከፖሊስ ጎን በማድረግ በመቀናጀት መፈፀምን ይጠይቃል ስሉ ገልጿሉ።
በተደረገው ግምገማ ቀጣይ ከኃላፊነት በተነሱበት አመራሮችን የመተካት እና በተቋሙ መመሪያ መሠረት ስራ እንደሚሰራ የተገለፀ ሲሆን በተያዘው በጀት አመት ለህዝብ የሰላምና ፀጥታ ጥበቃ ጠንካራ የመፈፀም አቅም ያለው የፖሊስ ኃይል ሆኖ መገኘት ያስፈልጋል ነው የተባለው።
የማጥራት ግምገማ ሪፖርት ማጠቃለያ ፕሮግራም መድረክ በዞኑ ፀጥታ መምሪያ ኃላፊ እና በዞን ም/አስተዳዳሪ የስራ መመሪያ ተሰጥቶ ተጠቃሏል።
ዘገባው የኮንታ ዞን ፖሊስ ህዝብ ግንኙነት ነው
ጥቅምት 16/2018 ዓ/ም

22/04/2024

መያዝያ 14 ቀን 2016

በኮንታ ዞን እና በከፋ ዞን ከአጎራባች ቀበሌዎች ጋር በወቅታዊ ፀጥታ ዙሪያ የጋራ የሆነ መድረክ አካህዷል።

ኮንታ አመያ -ሚያዚያ 14/2016 ዓ/ም በኮንታ ዞን አመያ ዙሪያ ወረዳና በከፋ ዞን ጠሎ ወረዳ ከአጎራባች ቀበሌዎች ጋር በወቅታዊ ፀጥታ ዙሪያ የጋራ የሆነ መድረክ አካህዷል።

በወረዳዎችንና በቀበሌዎችን የተወሰኑ ጥቃቅን ፀጥታን የሚደፈርሱ ነገሮች በኮንታ ዞን አመያ ዙረያ ወረዳ ጋዳ ሽንበራ ቀበሌና በከፋ ዞን ጠሎ ወረዳ ጫማ ቀበሌ ደንበር አከባቢ የሚፈጠሩ ችግሮችን በጋራ ሆነው የመከላከል ሥራ አጠናክረን መሠራት እንዳለባችው ተወያይተዋል።

አሁን ላይ የተጀመረው የሁሉቱ አጎራባች ቀበሌዎች ስብሰባው ቀጣይነት ያለውና በወቅታዊ ፀጥታ ዙሪያ ወቅቱን ጠብቀው ሁለቱም ዞን ና ወረዳ በቅርብ ክትትል በማድረግ ችግሮችን በተቻለ መጠን ለመቀነስና ለማጥፋት ከፍተኛ ትግል እንደሚደረግ ተወያይተዋል።

የኮንታ ዞን ዙሪያ ወረዳ ሠላም ና ፀጥታ ጽ /ቤት ኃላፊ የሆኑ አቶ ገረመዉ ቀፀላ ጨምሮ ከአጎራባች ወረዳ ከነበሩ ፀጥታ አካላት ጋር የጋራ ውይይት እንደሚቀጥልና ጥንካራያቸው ከወትሮ የበለጠ እንደሚደረግ መግባባት ላይ ተደርሷል

በስብሰባው መድረክ የአመያ ዙረያ ወረዳ ፖሊስ አዛዥ ኢ/ር በቀለ በለጠ ፣ ሠላምና ፀጥታ ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ገረሙ ቀፀላ እንድሁም የፍትህ ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ገዛኸኝ ገሠሠ በከፍ ዞን ጠሎ ሠላም ና ፀጥታ ጽ/ቤት ተወካይ አቶ ሙሉጌታ ቾከለ እና የወረዳው ፖሊስ ማህበረሰብ አቀፍ ወንጀል መከላከል ማሰተባበረያ ኃላፊ ዋና ሳጅን ጌታችው ገብሬ አንድ ላይ በጋራ ሆነው መድረኩን በመምራት የጋራ አቋም ተይዟል።

የዘገበዉ የዞኑ ፓሊስ ህዝብ ግንኙነት ነው ።

በኮንታ ዞን አመያ ከተማ እሰተዳደር የሰውን ህይወት  የማጥፋት ወንጀል የፈፀሙ  ባልና ምስት  በዛሬው ዕለት በዋለው ችሎት በፅኑ በእስራት ተቀጡ።(ኮንታ-አመያ ) መያዝያ 3/2015 ዓ/ም በ...
11/04/2023

በኮንታ ዞን አመያ ከተማ እሰተዳደር የሰውን ህይወት የማጥፋት ወንጀል የፈፀሙ ባልና ምስት በዛሬው ዕለት በዋለው ችሎት በፅኑ በእስራት ተቀጡ።

(ኮንታ-አመያ ) መያዝያ 3/2015 ዓ/ም በኮንታ ዞን አመያ ከተማ አስ/ር አመያ 01 ቀበሌ ነዋሪ የሆኑት ባልና ሚስት ተከሳሾች 1ኛ ወ/ሮ አባይዳር በየኔ 2ኛ አቶ ገዛኸኝ ገሳላ ሲሆኑ ሟች ወጣት አዳኔች አየለ ከ2013 ዓ/ም ጀምሮ ያለምንም ክፊያ የቤት ሰራተኛነት ሆና እያገለገለች የቆየች ስትሆን በቀን 25 /11/2014 ዓ/ም ከጠዋት ጀምራ የቤት ስራዋን እየሰራች በሠላም የዋለችውን ማታ ከምሽቱ በግምት 4: 00 ሠዓት አከባቢ ተከሳሾቹ ሟቿን በገመድ አንቀው ከገደሉ በኃላ የወንጀሉ ድርጊት እንዳይወጣ የተለያዬ ቴክኒኮችን በመጠቀም ለመሸፈን ቢሞክሩም ዋ/ሳ/ን አሰፉ አሉላ የራሱን የምርመራ ጥበብ በመጠቀም በሰው እና በሰነድ ማስረጃ አጣራቶ ለሚመለከተው የፍትህ አካል በመላኩ ክስ ተመሰርቶባችዋል።

የኮንታ ዞን ልዩ ልዩ ወንጀልች ዐ/ህግ የሆኑት አቶ ሀብታሙ ሀደሮ አክለው ተከሳሾቹ በፈፀሙት ነፈስ ግድያ ወ/ል ከፖሊሰ ጋር በቅንጅት በመሠራት ከፍተኛ ፍ/ቤት ክስ በመሰርተናል ብለዋል።

የክሱን ግራ እና ቀኝ ሲመለከት የቆየው የኮንታ ዞን ከፍተኛ ፍ/ቤትም ተከሳሾችን ያርማል ሌሎችንም ያሰተምራል በማለት መያዝያ 3 /8/2015 ዓ/ም በዋለው ችሎት 18 ዓመት ፅኑ እሰራት እንድቀጡ ወስኗል።

ህብረተሰቡ ወንጀል ከመፈፀሙ በፊትም ሆነ ወንጀል ከተፈጸመ በኃላ ጥቆማ በመሰጠት እና ምስክር ሆኖ ጥፉተኞች በህግ እንዲጠየቁ ከፖሊስ ጎን እና ከፍትህ አካላት ጋር ተባብሮ መሰራት ይገባል ስል የኮንታ ዞን ፖሊስ አዛዥ ኮ/ር ብርሃ ዘለቀ መልዕክት አሰተላልፈዋል።

የዘገባው:- ኮንታ ዞን ፖሊስ መምሪያ ህዝብ ግንኙነት ነው።

🛎🛎🛎🛎   የፖሊስ  መልዕክት!!  🛎🛎🛎🛎🛎🛎🛎🛎🛎🛎🛎🛎🛎🛎🛎🛎🛎🛎🛎🛎🛎🛎🛎🛎🛎🛎በክርስተና ዕምነት ተከታዮች ዘንድ በድምቀት የሚከበረው የደመራና የመስቀል በዓል ፈፅሞ ሠላማዊ እንዲሆን ቅድመ ዝግ...
24/09/2022

🛎🛎🛎🛎 የፖሊስ መልዕክት!! 🛎🛎🛎🛎🛎
🛎🛎🛎🛎🛎🛎🛎🛎🛎🛎🛎🛎🛎🛎🛎🛎🛎🛎🛎🛎🛎

በክርስተና ዕምነት ተከታዮች ዘንድ በድምቀት የሚከበረው የደመራና የመስቀል በዓል ፈፅሞ ሠላማዊ እንዲሆን ቅድመ ዝግጅት መጠናቀቁ ተገለፀ፡፡

☦️☦️☦️☦️☦️☦️☦️☦️☦️☦️☦️☦️☦️☦️☦️☦️☦️☦️☦️☦️☦️
(ኮንታ-አመያ) መስከረም፡15 /2015 ዓ.ም ኮንታ ዞን ፖሊስ ሚዲያና ኮሙንኬሽን

በክርስትና እምነት ተከታዮች ዘንድ በድምቀት የሚከበረው የመስቀል በዓል ከየትኛውም ስጋት ነፃ በሆነ መልኩ እንዲከበሩ ለማድረግ የፀጥታ መዋቅሩ በዞኑ ዉስጥ ባሉት በሁሉም መዋቅሮች የቅድመ ዝግጅት ተግባር አጠናቅቆ ወደ ስራ መገባቱን የዞን ፖሊስ መምሪያዉ ገልፀዋል።

የዞኑ ፖሊስ አዛዥ ም/ኢ/ር ባሳ በየነ እንደገለፁት በዓሉ በተለይ በክርስትና ቤተ እምነት ተከታዮች ዘንድ በልዩ ድምቀት የሚከበር በዓል እንደመሆኑ መጠን የበዓሉ ታዳሚያን ያለምንም ከፀጥታ ስጋት ነፃ ሆነው በዓሉን እንዲያከብሩ የዞኑ ፖሊስ መምሪያ ከተለያዩ ከፀጥታ መዋቅሮችና ከባለድርሻ አካላት ጋር በመቀናጅት የደመራና የመስቀል በዓል ሰላማዊ በሆነ መንገድ በድምቀት እንዲከበር አስፈላጊውን ቅድመ ዝግጅት ማጠናቀቁን አስታውቋል ።

አክለዉም አዛዡ የመስቀል በዓል ከዋዜማው ጀምሮ የእምነቱ ተከታዮች በአደባባይ የደመራ በዓልን ለማክበር በሚወጡበ ወቅት እኩይ ተግባር ለመፈፀም የሚፈልጉ አካላት ማንኛዉንም የፀጥታ ችግር እንዳይፈጥሩ ሁሉም የፀጥታ አካላትና ማህ/ሰቡ ተቀናጅቶ መስራቱ አስፈላግ በመሆኑ ሰላም ወዳዱ የዞኑ ህዝብ ቤቱንና አከባቢዉን ከወንጀልና ከእሳት አደጋ በመጠበቅ በዓሉ በሰላም እንዲከበር ከፀጥታ አካላት ጎን በመቆም የተለመደውን ትብብር እንዲያደርጉ ጥሪ ያቀረቡት አዛዥ መላው የዞናችን ህዝቦች በበዓሉ አከባበር ወቅት አጠራጣሪ ሁኔታዎች በሚኖሩበት ጊዜ በአቅራቢያቸዉ ለሚገኙ ለፖሊስ አባላት ጥቆማ በመስጠት እንዲተባበሩ ጭምር አሳስበዋል፡፡

በመጨረሻም አዛዡ ለመላዉ የክርስትና ዕምነት ተከታዮች በሙሉ በዓሉ የሠላም ፣ የፍቅር ፣ የመተሳስብ ፣ የስኬትና እንዲሁም የተቸገሩትን የምንጠይቅበት ክብረ በዓል እንዲሆንልን በዞኑ ፖሊስ መምሪያው ስም የመልካም ምኞታቸውን አስተላልፈዋል ።

✍️✍️ዘገባው የኮንታ ዞን ፖሊስ መምሪያ ሚዲያና ኮሙዩኒኬሽን ነው

የወንጀልንና ትራፍክ አደጋን በጋራ እንከላከል የሁል ጊዜ መለዕክታችን ነዉ !!

12/09/2022
12/08/2022
ከሁሉም መንግስት መዋቅሮችና ከባለድርሻ አካላት ጋር ተቀናጅቶ በመስራት የዞኑን ሠላምና ደህንነት ማረጋገጥ እንደምቻል የዞኑ ፖሊስ መምሪያዉ ገለፀ (ኮንታ-አመያ) ሐምሌ 04/2014ዓ/ም ኮንታ...
11/07/2022

ከሁሉም መንግስት መዋቅሮችና ከባለድርሻ አካላት ጋር ተቀናጅቶ በመስራት የዞኑን ሠላምና ደህንነት ማረጋገጥ እንደምቻል የዞኑ ፖሊስ መምሪያዉ ገለፀ

(ኮንታ-አመያ) ሐምሌ 04/2014ዓ/ም ኮንታ ዞን ፖሊስ ሚዲያና ኮሙዩኒኬሽን

በኤላ ሀንቻኖ ወረዳ ፖሊስ ጽ/ቤት አድስ የተደራጀ የፖሊስ ማነጅመንት ከወረዳዉ ፊት አመራሮች ጋር የትዉዉቅና ቀጣይ ስራ አቅጣጫዎች ላይ የዉይይት መድረክ ተካህዷል።

በመድረኩም ላይ የተሳተፉ የዞኑ ፖሊስ አዛዥ የወረዳዉ ፖሊስ ማነጅመንትና የወረዳዉ ፊት አመራሮች ጋር የጋራ ዉይይት በጭዳ ከተማ የተካሄደ ሲሆን በዉይይቱም በተደራጀ ሁኔታ ስራ ለመጀመር የጋራ መግባባት ላይ መደረሱ ተገልጸዋል ።

በመድረኩም ላይ ከዞን ጀምሮ የወረዳዉን ፖሊስ በዘላቅነት በሰዉ ኃይል እና በሎጀስትክ በማደራጀት በህዝብ ዘንድ እምነት የሚያገኝ ነፃና ገለልተኛ የህዝብ ዉግንና ያለዉ ተቋም ለማድረግ በሚሰሩ ተቋም ግምባታ ስራዎች ላይም የወረዳዉ ፍት አመራሮች ሚና ከፍተኛ መሆኑን በማንሳት አስፈላግዉ ድጋፍ እንድደረግም ተጠይቋል ።

ወረዳው አድስ ከተደራጁት መዋቅሮች አንዱ እንደመሆኑ መጠን ቀጣይነት ባለው ስራዎች የአቅም ግምባታ ስልጠናዎችና ድጋፎችን እንደሚያደርጉም ቃል በመግባት ስራ ለማስጀመር ለዞኑ ፖሊስ መምሪያ ካለዉ ውስን ሀብት በመቀነስ ከ300 ሺህ ብር በላይ የሚገመት የቁሳቁስ ድጋፍ በማበርከት ዉይይቱ ተጠናቋል።

በጀግንነት መጠበቅ በስብዓዊት ማገልገል !!

ዘገባው ኮንታ ፖሊስ ሚዲያና ኮሙዩኒኬሽን ነው

ወንጀልንና የትራፍክ አደጋን በጋራ እንከላከል የሁል ጊዜ መልዕክታችን ነው!

አድስ የተዋቀሩ ወረዳዎችን በሎጀስትክ     መደገፉ ተገብ እንደሆነ ተገለፀ ።(ኮንታ-አመያ)ሰኔ 27/2014ዓ/ም ኮንታ ዞን ፖሊስ ሚዲያና ኮሙዩኒኬሽን ዛሬ በኮንታ ኮይሻ ወረዳ ፖሊስ ጽ/ቤት...
04/07/2022

አድስ የተዋቀሩ ወረዳዎችን በሎጀስትክ
መደገፉ ተገብ እንደሆነ ተገለፀ ።

(ኮንታ-አመያ)ሰኔ 27/2014ዓ/ም ኮንታ ዞን ፖሊስ ሚዲያና ኮሙዩኒኬሽን

ዛሬ በኮንታ ኮይሻ ወረዳ ፖሊስ ጽ/ቤት አድስ የተደራጀ የፖሊስ ማነጅመንት ከወረዳዉ ፊት አመራሮች ጋር የትዉዉቅ መድረክ አካህዷል።

በመድሩኩም ላይ የዞኑን ፖሊስ አዛዥ ጨምሮ ከመምሪያ የወረዱ ከፍተኛ አመራሮች ፣ የወረዳዉ ፖሊስ ማነጅመንትና የወረዳዉ ፊት አመራሮች ጋር የጋራ ዉይይት በኮይሻ ከተማ የተካሄደ ሲሆን በዉይይቱም በተደራጀ ሁኔታ ስራ ለመጀመር የጋራ መግባባት ላይ መድረሱ ተገልጸዋል ።

አመራሩ በቀጣይ ስራ አቅጣጫ ዙሪያ የስራ መመሪያና ስምሪት በመስጠት ከዞኑ ፖሊስ መምሪያ ለድጋፍ የተሰጠዉን ንብረት ኮምፕዉተር ከኔፕርንተር ፣ ባለሁለት እግር ሞተር ሳይክልና ሌሎች ቁሳቁሶችን ጨምሮ ከ250ሺህ ብር በላይ የሚገመተዉን ንብረት በድጋፍ መልክ አስረክበዋል ።

የዞኑ ፖሊስ መምሪያው አዛዥ ም/ኢ/ር ባሳ በየነ እንደገለፁት ህብረተሰቡን በተሰጠን ኃላፊነት በማገልገል ፖሊሳዊ ሚናን መወጣት ያስፈልጋልና ለዚሁም ጠንካራ አቋም ያለ ሀይል እንደመሆኑ መጠን የተጀመረውን የለውጥ ጉዞ ማስቀጠል ይኖርብናል ስሉ አሳስበዋል ።

አክለውም አዛዡ ወረዳው አድስ ከተደራጁት መዋቅሮች አንዱ እንደመሆኑ መጠን ቀጣይነት ባለው ሁኔታ ድጋፎችን እንደሚያደርጉም ቃል ገብቷል።

ዘገባው ኮንታ ፖሊስ ሚዲያና ኮሙዩኒኬሽን ነው

ወንጀልን በጋራ እንከላከል የሁል ጊዜ መልዕክታችን ነው

በኮንታ ዞን በ3ቱም ወረዳዎች ለህዝባችን ፈጣን ምላሽ ለመስጠት መዋቅሮችን ለህብረተሰቡ ማውረድ አስፈላጊ በመሆኑ የዞኑ ፖሊስ መምሪያው በተደራጁ ፖሊስ ጽ/ቤቶች የማኔጅመንት አመራሮች ምደባ ማ...
22/06/2022

በኮንታ ዞን በ3ቱም ወረዳዎች ለህዝባችን ፈጣን ምላሽ ለመስጠት መዋቅሮችን ለህብረተሰቡ ማውረድ አስፈላጊ በመሆኑ የዞኑ ፖሊስ መምሪያው በተደራጁ ፖሊስ ጽ/ቤቶች የማኔጅመንት አመራሮች ምደባ ማድረጉ ተገለፀ ።

(ኮንታ-አመያ ) ሰኔ 15/2014 ዓ/ም ኮንታ ዞን ፖሊስ ሚዲያና ኮሙኒኬሽን

በዚህም መሠረት :-

👉 በአመያ ዙሪያ ወረዳ :-

1ኛ ም/ኢ/ር/ ደሳለኝ ዳዋና የስነ-ምግባርና ተቋማዊ ለዉጥ ስራዎች አስተባባር
2ኛ ም/ኢ/ር አሸናፍ ወቲቻ ማ/አ/ወ/መ/ል ማስተባበሪያ ኃላፍ
3ኛ ዋ/ሳ/ን ታምራት ዱባቼ የወ/ምርመራ ማስተባበሪያ ኃላፍ
4ኛ ዋ/ሳ/ን በላቸዉ መገኖ የት/ፍ/ቁ/አ/መ/ል ማስተባበሪያ ኃላፍ
5ኛ ዋ/ኢ/ር ግድሶ አመሌ የሰ/ሃ/ስ/አ/ማስተባበሪያ ኃላፍ
6ኛ ዋ/ሳ/ን ፈለቀ ጣምሩ የል/ዕቅ/ዝ/ግ/ግ/ማስተባበሪያ ኃላፍ
7ኛ ም/ኢ/ር ደግፌ ደድሶ የወ/መ/ኢንተሌጀንስ ማስተባበሪያ ኃላፍ
8ኛ ረ/ኢ/ር ኡፋይሴ ኃይሌ የሴቶች፣ህፃናትና ወጣቶች ጉዳይ ቡድን መሪ

👉 በኤላ ሃንቻኖ ወረዳ :-

1ኛ ረ/ኢ/ር አለማየሁ አድሱ የስነ-ምግባርና ተቋማዊ ለዉጥ ስራዎች አስተባባር
2ኛ ዋ/ኢ/ር ዘገዬ ደምሴ ማ/አ/ወ/መ/ል ማስተባበሪያ ኃላፍ
3ኛ ዋ/ሳ/ን አሰፋ አሉላ ወ/ምርመራ ማስተባበሪያ ኃላፍ
4ኛ ም/ኢ/ር ላምበቦ ፋንታ የት/ፍ/ቁ/አ/መ/ል ማስተባበርያ ኃላፍ
5ኛ ረ/ኢ/ር አሸናፍ ደሳለኝ የሰ/ሃ/ስ/አ/ማስተባበሪያ ኃላፍ
6ኛ ረ/ኢ/ር መካሻ ሃዳዬ የል/ዕቅ/ዝ/ግ/ግ/ማስተባበሪያ ኃላፍ
7ኛ ሳ/ን ተክሌ ደመቆ የወ/መ/ኢንተልጀንስ ማስተባበሪያ ኃላፍ
8ኛ ዋ/ሳ/ን ያምሮት ደምሴ የሴቶች፣ህፃናትና ወጣቶች ጉዳይ ቡድን መሪ

👉 ኮንታ ኮይሻ ወረዳ :-

1ኛ ም/ኢ/ር ጎበዜ ጎሎሮ የስነ-ምግባርና ተቋማዊ ለዉጥ ስራዎች አስተባባር
2ኛ ዋ/ሳ/ን ከበደ ለጮ ማ/አ/ወ/መ/ል ማስተባበሪያ ኃላፍ
3ኛ ዋ/ሳ/ን አስራት አበበ የወ/ምርመራ ማስተባበሪያ ኃላፍ
4ኛ ሳ/ን ደምሴ ደሱላ የት/ፍ/ቁ/አ/መ/ል ማስተባበሪያ ኃላፍ
5ኛ ም/ኢ/ር መሰለች ኩኬ የሰ/ሃ/ስ/አ/ ማስተባበሪያ ኃላፍ
6ኛ ረ/ኢ/ር በየነች ኃ/ሚካኤል የል/ዕቅ/ዝ/ግ/ግ/ማስተባበሪያ ኃላፍ
7ኛ ረ/ኢ/ር ሲሳይ ባታላ የወ/መ/ኢንተሌጀንስ ማስተባበሪያ ኃላፍ
8ኛ ዋ/ሳ/ን አሰገደች ትግሮ የሴቶች፣ህፃናትና ወጣቶች ጉዳይ ቡ/መሪ በመሆን ኃላፊነት የተሰጣቸው ሲሆን :-
በ3ቱም ወረዳዎች ለአሰራር ስርዓት እንዲያመች መዋቅሮችን ሙሉ ማድረግ አስፈላጊ በመሆኑ የዞኑ ፖሊስ መምሪያው የማኔጅመንት አባላትን ማደራጀቱን ገልፀዋል ።

የዞኑ ፖሊስ አዛዥ ም/ኢ/ር ባሳ በየነ እንደገለፁ በ3ቱም ወረዳዎች ኃላፍነት የተሰጣቸዉ አካላት የህዝቡ ጥያቄ በቅርበት ፈጣን ምላሽ ለማግኘት መሆኑን ከግንዛቤ ዉስጥ በማስገባት በተለወጠ መንፈስ ወደ ስራ መግባት እንደሚያስፈልግ ተናግረዋል ።

አክለውም አዛዡ ከዚሁ ከአመራር ምደባ ጋር አያይዘው ህብ/ሰቡም ምደባው ህዝብን እንጂ በትዉልድ አከባቢ የማይገደብ መሆኑን በመረዳት አዲስ ተመድቦ በአመራርነት ወደየወረዳችሁ የሚመጡ አመራሮችን በመደገፍና በመተጋገዝ መረጃዎችን በመለዋወጥ የህዝባችንን ሰላምና ደህንነት ለማረጋገጥ ከወትሮ በበለጠ መልኩ መስራት ይኖርብናል ስሉ ገልጸዋል ።

✍️ ዘገባው ኮንታ ዞን ፖሊስ ሚዲያና ኮሙኒኬሽን ነው

Address

Konta

Telephone

+251900944791

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Konta Police Media communication posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Share

Category