מועדון קריאה באמהרית - አማርኛ አንባቢያን ክለብ

  • Home
  • Israel
  • Beit Shean
  • מועדון קריאה באמהרית - አማርኛ አንባቢያን ክለብ

מועדון קריאה באמהרית - አማርኛ አንባቢያን ክለብ Contact information, map and directions, contact form, opening hours, services, ratings, photos, videos and announcements from מועדון קריאה באמהרית - አማርኛ አንባቢያን ክለብ, Library, שדרות הארבעה, Beit Shean.

הייעוד שלנו במועדון קריאה באמהרית הינו עידוד בשימור השפה על ידי הרגלי שיח ופיתוח תרבות הקריאה באמהרית.
የአማርኛ እንባቢያን ክለብ ፕሮጀክት አላማችን የአማርኛን ቋንቋን ውይይት ወይም ንግግርን ልምዶች እንዲጠበቅ እና የመጻሕፍቶች ማንበብ ባህል እንዲዳብር ለማድረግ ነው።

በእስራኤል ሀገር ደስ በሚል መልኩ የፋሲካ በዓል ይከበራል፣ የአማርኛ አንባቢያን ክለብ ፕሮጀክት የመሠረተው እና ዋና ስራ አስከያጁ የቤተ እስራኤል ማህበረሰብ (እትዮጵያ እይሁዳውያን) የባህል...
06/04/2026

በእስራኤል ሀገር ደስ በሚል መልኩ የፋሲካ በዓል ይከበራል፣ የአማርኛ አንባቢያን ክለብ ፕሮጀክት የመሠረተው እና ዋና ስራ አስከያጁ የቤተ እስራኤል ማህበረሰብ (እትዮጵያ እይሁዳውያን) የባህል ልብስን ልብሶ እንኳን ለፋሲካ በዓል አደረሳችሁ፣ ነፃነቱን፣ ፍቅሩን ሰላሙን ይስጣችሁ ይስጠን እያለ እስራኤል ሀገሩን ሁኖ ይመርቃል🌷🍷።

ዛሬ ስግድ በዓል በቅዱሷ እየሩሳለም ተከበረ።ታዋቂ እስራኤላውያዋ ጋዜጠኛ ሲቫን ራሃቭ ሜኢር ስለ ስግድ በዓል በአማርኛ ትርጉም ጋር፡תזכורת ליום הסיגד / סיון רהב מאיר:היו...
20/11/2025

ዛሬ ስግድ በዓል በቅዱሷ እየሩሳለም ተከበረ።
ታዋቂ እስራኤላውያዋ ጋዜጠኛ ሲቫን ራሃቭ ሜኢር ስለ ስግድ በዓል በአማርኛ ትርጉም ጋር፡

תזכורת ליום הסיגד / סיון רהב מאיר:

היום, כ"ט בחשוון - חוגגים את ה"סיגד".
בזכות יהודי אתיופיה, יש לנו בכל שנה תזכורת: הסיגד נחגג 50 יום אחרי יום כיפור.
ביום הזה יהדות אתיופיה מתכנסת ליום של צום, תפילה וחשבון נפש, יום שבו זוכרים את אלה שנספו בדרך לירושלים.
כולנו, מכל העדות, יכולים להתברך מהתזכורת החשובה הזו:
מה הבטחנו לעצמנו לפני 50 יום, והאם אנחנו בכיוון הנכון?
ואיפה אנחנו נמצאים, במסע הפרטי והכללי שלנו, לעבר ירושלים, לעבר עולם מתוקן יותר?

የምናስታውሰው በስግድ በዓል / ሲቫን ራሃቭ ሜኢር፡

ትናት ምሸት ጀምሮ እስከ ዛሬ 20.11.25 ዓ-ም ስግድ በዓልን እናከብራለን።
በኢትዮጵያውያን እይሁዳውያን ወይም በቤተ እስራኤል እድል በየዓመቱ ማሳሰቢያ አርገን ሁላችን በዓሉን እናከብራለን፡ ስግድ የሚከበረው ከአስተራይ ቀን ወይም በዮም ዮም ኪፑር 50 ቀናት በኋላ ነው።
በዚህ ቀን ኢትዮጵያውያን እይሁዳውያን ወደ ቅዱስ እየሩሳሌም በመጓዝ መንገድ ወገኖቻችን ለቀሩት በማስታወስ፣ በጾም፣ በጸሎት እና በራስን፣ በህብረተሰብ ሁኖ የመመራመር እና እስኪ እግዚአብሔር ይቅርታ፣ ማረን ለሚባልበት ቀን ይሰበሰባሉ።
ሁላችንም፣ የሁሉም ቤተ እስራኤላውያን የሆናችሁ ልዩ ህብረተሰብ እና ጎሳዎች፣ በዚህ ጠቃሚ ክቡር በዓል መባረክ እና ማስታወስ እንችላለን፡-
ከ 50 ቀናት በፊት ለራሳችን ምን ቃል ገባን፣ እና በትክክለኛው መንገድ ላይ ነን?
እና እኛ በግል መንገድ እግዚአብሔርን በመለመን እና ዛሬ ደሞ በአጠቃላይ ህብረተሰብ እስራኤል ህዝብ በመሆናችን አምላክ እግዚአብሔርን ማረን እንላነን፣ ወደ ቅዱስ እየሩሳሌም በምናደርገው ጉዞ ላይ ጀምረን፣ እንዲሁም የበለጠ ወደተሻሻለ አለም ተራምደናል፣ እችን አመት እስቲ የት ነን ያለነው? ብለንም መጠየቅ አለብን፣ መልካም የስግድ በዓል ይሁንልን።
סיון רהב מאיר - Sivan Rahav Meir

ዛሬ ምሸት ጀምሮ እስከ ነገ ማታ የአስተራይ ቀን ወይም በዕብራይስጥ ዮም ሃኪፑሪም የሚባል ቀናት ይከበራል በይሁዳውያን ወይም በቤተ-እስራኤል ኃይማኖት በጣም የተቀደሰ ቀን ነው። ሰው በሰው ይ...
01/10/2025

ዛሬ ምሸት ጀምሮ እስከ ነገ ማታ የአስተራይ ቀን ወይም በዕብራይስጥ ዮም ሃኪፑሪም የሚባል ቀናት ይከበራል በይሁዳውያን ወይም በቤተ-እስራኤል ኃይማኖት በጣም የተቀደሰ ቀን ነው። ሰው በሰው ይቅርታ የሚጠይቅበት፣ ኀጢአት ለፈጸመው ለአምላክ ይቅር እስቲ ማረይ የሚባለበት፣ በጾም በጸሎት የሚዋልበት እና የሚታደርበት ቀን ነው።
እና፣ እኛ አማርኛ እንባቢያን ክለብ ፕሮጀክት ምክራችን አስተራይ ቀን ከጾም ከጸሎት ጭምር ስልክ ሞባይል ዘግተን መጽሐፍ 📚ማንበብ የምንችልበት እድል ጊዜ ነው።
አገራችን ሰላም ትሁን፣ መልካም የአስተራይ ቀን ይሁንልን፣ ቀለል ያለ ጾም እና እግዚአብሔር አምላክ ከጥሩ ምዝገባ ይጻፈን።
አሜን።

(צילום: ארז בן סימון)

በእስራኤል አገር በዚህ ወር፣ ሰኔ 2025 ዓ-ም፣ "የዕብራይስጥ መጽሃፍ ሳምንትን" በሚል ወራት ይከበራል። እኛ ደሞ የአማርኛ አንባቢያን ክለብ አባላት ባገኘነው አጋጣሚ መጽሃፎች ጊዜ፣ መጽሃ...
30/06/2025

በእስራኤል አገር በዚህ ወር፣ ሰኔ 2025 ዓ-ም፣ "የዕብራይስጥ መጽሃፍ ሳምንትን" በሚል ወራት ይከበራል። እኛ ደሞ የአማርኛ አንባቢያን ክለብ አባላት ባገኘነው አጋጣሚ መጽሃፎች ጊዜ፣ መጽሃፎች የሚነበቡበት፣ የሚከበሩበት ቀን ምክንያት በመጠቀም የዕብራይስ ሆነ የአማርኛ ሥነ ጽሑፍን ተደራሽ በማድረግ ላይ የመጽሐፍ ሳምንት በተባለው በዚህ በዓል ላይ እያከበርን እንገኛለን፣ ዕብራይስጥም አማርኛ መጽሃፎችን አብሮ በንባብ እና በአክብሮት ለህብረተሰብ መግለጽ ጋር።
እና ስለዚህ፣ እናተም አማርኛ አንባቢያን ክለብ ገጽ ተከታዮቻችን በጣም በልዩ ሁኔታ የወደዷቸው መጽሃፎች ልትመክሯቸው የምትፈልጉ ካላችሁ እስቲ አሳትፉን፣ በእርግጥ በዕብራይስጥ እና በአማርኛ መጽሃፎች ሊሆኑ ይችላሉ። የመጽሃፍ ምክሮችዎን ቢያካፍሉን በጣም ደስተኞች ነን።
መልካም የዕብራይስጥ እና የአማርኛ መጽሃፎች የሚከበሩበት ጥሩ በዓል ይሁንልን።

שלום לעוקבות ולעוקבים היקרים של מועדון קריאה באמהרית!אחרי תקופה ארוכה של הפסקה אנחנו נרגשים לבשר: מועדון הקריאה באמהרית ...
10/06/2025

שלום לעוקבות ולעוקבים היקרים של מועדון קריאה באמהרית!
אחרי תקופה ארוכה של הפסקה אנחנו נרגשים לבשר: מועדון הקריאה באמהרית חוזר לפעול!
האירועים הקשים של 7 באוקטובר 2023 והמצב הביטחוני שפקד את ישראל הותירו חותם עמוק בלב כולנו. מתקפת הטרור של חמאס, שכללה חדירה לשטח המדינה, רצח, טבח וחטיפת אזרחים באכזריות קשה זעזעה כל אחד ואחת מאיתנו. בתקופה הזו, נאלצנו לקחת צעד אחורה מהעשייה התרבותית ומהמפגשים האהובים שלנו, אבל הרוח היא לא נשברה.
ועכשיו, הגיע הזמן לחזור.
לחזור לספרים. לטקסטים. לשיח הקהילתי שמקרב בינינו, מעשיר אותנו ומזכיר לנו מי אנחנו.
בקרוב נחדש את המפגשים בספריות העירוניות ברחבי הארץ ונמשיך לעדכן אתכם כאן עם תכנים, המלצות ואירועים.
ישראל עדיין במלחמה. ליבנו עם החטופים, וכולנו תקווה לשובם המהיר. דווקא בעת הזו חשוב שנשמור על הרוח התרבותית שלנו. היא חלק בלתי נפרד מהחוסן שלנו כקהילה וכחברה.
תישארו איתנו. אנחנו כאן וחוזרים בענק.

ሰላም ውድ የአማርኛ አንባቢያን ክለብ ተከታዮቻችን!
ከረዥም እረፍት በኋላ ለማሳወቅ የምንፈልገው አለን፡ የአማርኛ አንባቢያን ክለብ ወደ ስራችኝ እየተመለስነ ነው።
በጥቅምት 7 ቀን 2023 የተከሰተው አስቸጋሪ ሁኔታ በእስራኤል ላይ የደረሰው ጦቅነት እና አሳፋሪ የሆነ በሽብር ፈጣሪዎች እስራኤላውያን ዜጎችን ግድያ በሁሉም ልባችን ላይ ትልቅ አሻራ ጥሏብናል። የሃማስ የሽብር አሸባሪ ጥቃት ወደ እስራኤል ደንበር ጢሶ ወደ ሀገር ውስጥ ዘልቆ በመግባትን፣ ግድያን፣ ሰላማዊ ዜጎችን በታላቅ ጭካኔ ማፈን መድፈርን አፍኖ መጠለፍን ወደ ጋዛ ውስጥ በግድ መውሰድን፣ እያንዳንዳችንን አስደንግጦናል፣ አሳፍሮናል። በዚህ ወቅት ከባህላዊ እንቅስቃሴዎቻችን እና ከተወዳጅ ስብሰባዎቻችን ወይም ማህበራዊ ግንኙነታችን አቋርጦብናል፣ አንድ እርምጃ ለመውሰድ ተገደን ነበር፣ የሀገር ደህንነትን ለመጠበቅ ላይ ተሳትፎ ያደረግነበት መንገዶች የሚጠቅሱ ቅስቃሳወች አብረን በመሳተፍ። መቼም ጦርነት ቢሆንም መንፈሳችን ግን አልተሰበረም።
እና አሁን፣ ለመመለስ ጊዜው ነው እያልን፣ ወደ መጽሐፍት አለም ። ወደ ጽሑፎች። የሚያቀራርብን፣ የሚያበለጽገን እና ማንነታችንን የሚያስታውሰን የማህበረሰብ ንግግር እየመለስነ ነው።
በቅርቡ በመላው እስራኤል ሀገር ላይ በሚገኙ የማዘጋጃ ቤት ቤተ-መጻሕፍት ውስጥ ስብሰባዎችን ወይም ግንኙነታችን እንቀጥላለን፣ እና ሁላችሁ ተከታዮቻችን እኛ ጋር ሁኑ። በእስራኤል ሀገር አሁንም በጦርነት ላይ ነች። ልባችን በሃማስ ሽብር ፈጣሪ ከታፈኑት ታጋቾች እህት ወድሞቻችን ጋር ነን ያለን፣ እና ሁላችንም በፍጥነት እንዲመለሱ ተስፋ እናደርጋለን። በተለይም በዚህ ጊዜ የባህል መንፈሳችንን መጠበቅ አስፈላጊ ነው፣ እንደ ማህበረሰብ እና እንደ ማህበራዊ ኑሮ - የእኛ የመቋቋም ዋና አካል ያለን ሰዎች ነን።
ከእኛ ጋር ሁኑ፣ እኛ እዚህ ነን፣ ተመልሰናል።

תמונה: מאחת ממפגשי הקריאה בספריית יפו ד'.

שבוע הספר העברי 2024.שבוע הספר העברי הוא אירוע המתקיים בישראל מדי שנה במהלך חודש יוני, במסגרתו מוקמים ירידי ספרים ברחובו...
23/06/2024

שבוע הספר העברי 2024.

שבוע הספר העברי הוא אירוע המתקיים בישראל מדי שנה במהלך חודש יוני, במסגרתו מוקמים ירידי ספרים ברחובות הערים, ובהם מיוצגות מרבית הוצאות הספרים בישראל, המוכרות את ספריהן במחירים מוזלים.

בנוסף למכירת הספרים, מתקיימים במהלך תקופה זו אירועים ספרותיים מגוונים, כגון מפגשים עם סופרים, ערבי קריאה וטקסי הענקת פרסים לסופרים ועוד.

את שבוע הספר באמהרית ציינו לראשונה בישראל ובעולם לפני 5 שנים, ב 2019.

אנחנו הולכים ומתעצמים ומביאים לבמה בכבוד רב את השפה אמהרית, את הספרות אמהרית גם בשבוע ספר זה. מוזמנים לגשת לספריית תל אביב-יפו (יפו ד') או ספריית עפולה ולקרוא מבחר ספרים באמהרית, ספריות שבהם אנחנו מועדון קריאה באמהרית דאגנו שלספרים הללו יהיה להם מקום ופינת קריאה בתוך הספרייה.

אם יש לכם ספרים באמהרית שהייתם ממליצים עליהם נשמח שתציינו אותם כאן בתגובות נשמח מאוד.

אבל אנחנו במועדון קריאה הפעם לפי בקשת עוקבים רבים לכבוד שבוע הספר העברי הפעם נמליץ בפוסט הבא שלנו על ספר בעברית שעוסק בנושא קהילה אתיופית. שבוע ספר שמח.

የዕብራይስጥ መጽሐፍቶች የሚከበሩበት ሳምንት ቀናት፣ 2022 ዓ-ም።

የዕብራይስጥ መጽሐፍቶች የሚከበሩበት ሳምንት ቀናት በየአመቱ በሰኔ ወራት በእስራኤል ሀገር የሚካሄድ ዝግጅት ነው። በተለያዩ ከተሞዎች ጎዳናዎች ላይ የመጽሐፍ አውደ ርዕይ ይካሄዳሉ፣ በእስራኤል የሚገኙ አብዛኛዎቹ የመጽሐፍ አሳታሚዎች ወይም ደራሲዎች የሚወከሉበት እና መጽሐፎቻቸውን በቅናሽ የሚሸጡበት ክቡር ቀን ነው።

በዚህ ወቅት ከመጻሕፍት ሽያጭ በተጨማሪ የተለያዩ የሥነ ጽሑፍ ዝግጅቶች ይከናወናሉ፤ ለምሳሌ ከጸሐፊዎች ወይም ደራሲዎች ጋር ደስ በሚል ስብሰባ ግንኙነት ይደረጋል፣ የጋራ ንባብ ምሽቶች እና ለጸሐፊዎች የሽልማት ሥነ ሥርዓቶች እና ሌሎች ሌሎችን ዝግጅቶች ይደረጋሉ።

በአማርኛ ቋንቋ መጽሐፍቶች ሳምንት ቀናት ለመጀመሪያ ጊዜ በእስራኤል እና በአለም አቀፍ ዙሪያ የተከበረው ከሶስት አመት በፊት በ 2019 ዓ-ም ነበር። አስገራሚ ለአማርኛ ቋንቋ ተናሪዌች እና አንባቢዎች አስኮሪ እንደነበር ሁላችን እናስታውሳለን።

እንዲሁም፣ በዚህ የመጽሐፍ ሳምንት ቀናት ላይ የአማርኛ ቋንቋን፣ የአማርኛ ስነ-ጽሁፍን በታላቅ ክብር እያጠናክርን ወደ ሰፊ መድረክ እያመጣን፣ ቋንቋዎን እያዳበርን ነው ያለነው።

እናተ የአማርኛ ፕሮጀክታችን ተክታታዮቻችን እስራኤል ባለው ወደ ቴል አቪቭ-ጃፋ(ጃፎ ዳሌት) ከተማ ቤተመጻሕፍት ወይም አፉላ ከተማ ቤተመጻሕፍት ሄደችሁ በአማርኛ አንባቢያን ክለብ ፕሮጅክታችን የተዘጋጁ አማርኛ ቋንቋ መጽሐፎችን ማንበብ ትችላላችሁ።

እንዲሁም፣ በአማርኛ ልዩ የሆኑ መጽሐፍቶች ለንባብ የምትመክሯቸው መጽሐፍቶች ካላችሁ እዚህ ኮሜንት ላይ ብትጠቅሷቸው ደስ ይለናል።

እኛ ዛሬ በተለየ መንገድ አማርኛ እንባቢያን ክለብ የዕብራይስጥ መጽሐፍቶች የሚከበሩበት ሳምንት ቀናት በመሆኑ ምክንያት በማድረግ በብዙ ተከታዮች ጥያቄ መሰረት ላይ በሚቀጥለው ፖስታችን በዕብራይስጥ ቋንቋ የኢትዮጵያን ማህበረሰብ የሚመለከት መጽሐፍ ለንባብ እንዲሆናችሁ እንመክራለን።

መልካም ንባብ፣ እንኳን የመጽሐፍቶች የሚከበሩበት ሳምንት ቀናት አደረሰን።

18/04/2024

በልእስቲ ቦታ ያዝ💪🏼

15/04/2024

እግዚአብሔር ይስጣችሁ❤️🙏🏾

14/03/2024

ደስ የሚል ምክር🙏🏾
ተከታዮቻችን የአንባቢዎን መምህር ወይም ደራሲ ስም የምታውቁ ካላችሁ አሳትፉን።
"ከመፈረምህ በፊት አንብብ
ከማመንህ በፊት አረጋግጥ
ስትወያይ ሁን አስተዋይ
ስትወስን ቆራጥ ሁን"

07/03/2024

ሻሎም ሻሎም፣ ሰላም፣ ሰላም።
እስራኤላዊ አርሶ አደር ዮራም ፔሬጽ የሚባል ጎበዝ ገበሬ በኢትዮጵያ ("ፈረንጅ ጎረቤት")።
ቋንቋ፣ ባህል ማወቅ እና ግብርና ጥሩ ፍሬ ያፈራል።
EBS

ዛሬ ምሸት ጀምሮ እስከ ነገ ማታ የአስተራይ ቀን ወይም በዕብራይስጥ ዮም ሃኪፑሪም የሚባል ቀናት ይከበራል በይሁዳውያን ኃይማኖት በጣም የተቀደሰ ቀን ነው። ሰው በሰው ይቅርታ የሚጠይቅበት፣ ኀ...
24/09/2023

ዛሬ ምሸት ጀምሮ እስከ ነገ ማታ የአስተራይ ቀን ወይም በዕብራይስጥ ዮም ሃኪፑሪም የሚባል ቀናት ይከበራል በይሁዳውያን ኃይማኖት በጣም የተቀደሰ ቀን ነው። ሰው በሰው ይቅርታ የሚጠይቅበት፣ ኀጢአት ለፈጸመው ለአምላክ ይቅር እስቲ ማረይ የሚባለበት፣ በጾም በጸሎት የሚዋልበት እና የሚታደርበት ቀን ነው።
እና፣ እኛ አማርኛ እንባቢያን ክለብ ፕሮጀክት ምክራችን አስተራይ ቀን ከጾም ከጸሎት ጭምር ስልክ ሞባይል ዘግተን መጽሐፍ 📚ማንበብ የምንችልበት እድል ጊዜ ነው።
መልካም የአስተራይ ቀን ይሁንልን፣ ቀለል ያለ ጾም እና እግዚአብሔር አምላክ ከጥሩ ምዝገባ ይጻፈን።
አሜን።

(ፎቶ፡ EPM)

Address

שדרות הארבעה
Beit Shean
10900

Telephone

+972507616588

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when מועדון קריאה באמהרית - አማርኛ አንባቢያን ክለብ posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Organization

Send a message to מועדון קריאה באמהרית - አማርኛ አንባቢያን ክለብ:

Share

Category