27/02/2026
የመሠረታዊ የኅብረት ሥራ ማህበራት የአባላት መነሻ ቁጥር አወሳሰን
*
በኅብረት ሥራ ማበራት አዋጅ ቁጥር 985/2009 አንቀፅ 7 ንዑስ አንቀፅ 2 እና 3 እና በአንቀፅ 8 ንዑስ አንቀፅ 1 የተደነገገው
እንደተጠበቀ ሆኖ በማምረት ወይም አገልግሎት በመስጠት ወይም በማምርት እና አገልግሎት በመስጠት ተግባር ላይ የተሰማሩ ኅብረት ሥራ ማህበራት አባላት የመነሻ ቁጥር እንደሚከተሉትን ይሆናል፤
ሀ) በእንሰሳት እና እንሰሳት ተዋፅኦ የሚደራጁ የኅብረት ሥራ ማህበራት አባላት የመነሻ ቁጥር 80 ሰው ይሆናል፡፡
ለ) በሰብል እና የደን ውጤቶች የሚደራጁ የኅብረት ሥራ ማህበራት አባላት የመነሻ ቁጥር 100 ሰው ይሆናል፡፡
ሐ) በአከባቢ መሰረት አድረገው የሚደራጁ የሸማቾች የኅብረት ሥራ ማህበራት የአባላት የመነሻ ቁጥር 250 ሰው ይሆናል፡፡
መ) ተቋምን መሰረት አድረገው የሚደራጁ የሸማቾች የኅብረት ሥራ ማህበራት የአባላት የመነሻ ቁጥር 100 ይሆናል፡፡
ሠ) በአከባቢ መሰረት አድረገው የሚደራጁ በገንዘብ ቁጠባና ብድር የኅብረት ሥራ ማህበራት የአባላት የመነሻ ቁጥር 100 ሰው
ይሆናል፡፡
ረ) ተቋምን መሰረት አድረገው የሚደራጁ በገንዘብ ቁጠባና ብድር የኅብረት ሥራ ማህበራት የአባላት የመነሻ ቁጥር 80 ሰው
ይሆናል፡፡
ሰ) በመኖሪያ ቤቶች የኅብረት ሥራ ማህበራት የሚደራጁ አባላት የመነሻ ቁጥር በገጠር 50 በከተማ 24 ይሆናል፡፡
ሸ) የሁለገብ የገበሬዎች ኅብረት ሥራ ማህበራት የሚደራጁ አባላት የመነሻ ቁጥር 250 ይሆናል፡፡
ቀ) በአትክልትና ፍራፍሬ እና በመስኖ ሥራዎች ላይ የኅብረት ሥራ ማህበራት የሚደራጁ አባላት የመነሻ ቁጥር 50 ይሆናል፡፡
በ) የተለያዩ ቋሚ እና አላቂ ሀብቶችን መሰረት አድርገው የሚደራጁ የኅብረት ሥራ ማህበራት ባለው ሀብት እና በአዋጭነት ጥናት መሰረት የመነሻ ቁጥሩን አግባብ ያለው ባለስልጣን ይስናል፡፡ ሆኖም መነሻ ቁጥሩ ከ10 ሰው ማነስ አይችልም፡፡
በዚህ አንቀጽአንቀጽ 49 ንኡስ አንቀጽ 1 የተደነገገው እንደተጠበቀ ሆኖ ከአዋጅ 985/2009 አስቀድሞ የተደራጁ አባላት የመነሻ ቁጥር እንዳስፈላጊነቱ አዋጭነቱን መሰረት በማድረግ የአባላት ቁጥር እንዲጨምር አግባብ ያለው ባለስልጣን ክትትልና ድጋፍ ያደርጋል፡፡