በካማሺ ዞን የዳምቤ ወረዳ መንግስት ኮሙንኬሽን ጽ/ቤት

  • Home
  • Greece
  • Agálo
  • በካማሺ ዞን የዳምቤ ወረዳ መንግስት ኮሙንኬሽን ጽ/ቤት

በካማሺ ዞን የዳምቤ ወረዳ መንግስት ኮሙንኬሽን ጽ/ቤት በካማሺ ዞን የዳምቤ ወረዳ የመንግስት ኮሙንኬሽን ጽ/ቤት

የኢትዮጵያ ሕዝብ ስላከበረን አብዝተን ማክበር፣ ባከበረን ልክ ታምነን መገኘት አለብን፡- ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)*********************የኢትዮጵያ ህዝብ በምርጫ ወቅ...
20/06/2026

የኢትዮጵያ ሕዝብ ስላከበረን አብዝተን ማክበር፣ ባከበረን ልክ ታምነን መገኘት አለብን፡- ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)
*********************

የኢትዮጵያ ህዝብ በምርጫ ወቅት ያሳየው ታማኝነት እና ፍቅር የመንግሥት አገልግሎት እንዲሻሻል እና ሌብነት እንዲቀንስ ባለው ፍላጎት በመሆኑ፣ ይህን አደራ መጠበቅ ካልተቻለ ቀጣይነት አደጋ ላይ እንደሚወድቅ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር) ለከፍተኛ የሥራ ኃላፊዎች አሳስበዋል።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ በንግግራቸው ወቅት አሁንም በየተቋማቱ በእጅ መንሻ እና በብልሹ አሰራር ምክንያት የሚማረሩ ዜጎች መኖራቸውን ተናግረው የኢትዮጵያ ህዝብ ስላከበረን አብዝተን ማክበር፣ ስላከበረን አብዝተን ማገልገል፣ ባከበረን ልክ ታምነን መገኘት አለብን ሲሉ አስጠንቅቀዋል።

ቴክኖሎጂን ማስፋፋት ዋነኛ ጥቅሙ ሰብዓዊ ንክኪን በመቀነስ ሌብነትን ማስቀረት መሆኑን የገለጹት ጠቅላይ ሚኒስትሩ፣ የቢሮክራሲ መጉላላት ዜጎችን ለከፍተኛ ብስጭትና ለአደጋ እንደሚዳርግ አስገንዝበዋል።

በመሆኑም እያንዳንዱ ተቋም ራሱን ፈትሾ የቴክኖሎጂ አጠቃቀሙን በማሳደግ የህዝቡን የቅሬታ ምንጭ በአስቸኳይ ማድረቅ እንዳለበትና አሁን የተመዘገቡት ድሎች የህዝቡ ፍላጎት 1 በመቶ ብቻ መሆናቸውን አስገንዝበዋል።

Ethiopian Broadcasting Corporation #ኢትዮጵያ

የዳምቤ ወረዳ ሴቶች፣ ህጻናትና ወጣቶች ጉዳይ ጽህፈት ቤት ለአቅመ ደካማና ለወላጅ አልባ ህፃናት የገንዘብ ድጋፍ አደረገጽህፈት ቤቱ በወረዳው ለሚገኙ አቅመ ደካማና ወላጅ አልባ ህፃናት የገንዘ...
20/06/2026

የዳምቤ ወረዳ ሴቶች፣ ህጻናትና ወጣቶች ጉዳይ ጽህፈት ቤት ለአቅመ ደካማና ለወላጅ አልባ ህፃናት የገንዘብ ድጋፍ አደረገ

ጽህፈት ቤቱ በወረዳው ለሚገኙ አቅመ ደካማና ወላጅ አልባ ህፃናት የገንዘብ ድጋፍ በማድረግ ማህበራዊ ኃላፊነቱን አሳይቷል። ድጋፉ ህፃናት ትምህርታቸውንና ዕለታዊ ኑሯቸውን በተሻለ ሁኔታ እንዲቀጥሉ ያግዛል ብሏል።

በድጋፉ ስነ-ሥርዓት ላይ የተገኙት የዳምቤ ወረዳ ምክትል ዋና አስተዳዳሪ አቶ ቡራቃ ተደሰ ድጋፍ የተደረገላቸው ህፃናት የማበረታቻ መልዕክት በማስተላለፍ፣ ትምህርታቸውን በትጋት እንዲከታተሉ፣ ተስፋ እንዳይቆርጡ እና ለወደፊቱ የሀገር ጠቃሚ ዜጎች መሆናቸው አሳስበዋል።

በተጨማሪም አቅመ ደካሞችንና ተጋላጭ ህፃናትን መደገፍ የሁሉም ማህበረሰብ የጋራ ኃላፊነት መሆኑን ገልጸዋል።

የጽህፈት ቤት ኃላፊ ወይዘሮ ሀልካ ስልካ በሰጡት አስተያየት፣ ድጋፉ ተጋላጭ ህፃናትን በመደገፍ የተሻለ የኑሮ እድል ለመፍጠር የታለመ መሆኑን ገልጸዋል። በቀጣይም ተመሳሳይ የድጋፍ ስራዎችን ከመንግስት፣ ከባለድርሻ አካላትና ከበጎ ፈቃደኞች ጋር በመተባበር እንደሚቀጥሉ አስታውቀዋል።

የተደረገው ድጋፍ በህፃናቱ ፊት ተስፋን ለማጠናከር፣ የማህበራዊ አንድነትን ለማጎልበት እና ማንም ህፃን በችግር ምክንያት ከትምህርትና ከመሰረታዊ ፍላጎቶቹ እንዳይርቅ ያለመ ተግባር መሆኑ ተገልጿል።

በዳምቤ ወረዳ የህጻናት ክትባት ዘመቻ በተጠናከረ ሁኔታ እየተካሄደ ነውበዳምቤ ወረዳ ጤና ጥበቃ ጽሕፈት ቤት አስተባባሪነት የህጻናትን ጤና ለማጠናከርና በሽታ የመካላከል አቅም ለመዳበር የተዘጋ...
20/06/2026

በዳምቤ ወረዳ የህጻናት ክትባት ዘመቻ በተጠናከረ ሁኔታ እየተካሄደ ነው

በዳምቤ ወረዳ ጤና ጥበቃ ጽሕፈት ቤት አስተባባሪነት የህጻናትን ጤና ለማጠናከርና በሽታ የመካላከል አቅም ለመዳበር የተዘጋጀው የክትባት ዘመቻ በወረዳው በተጠናከረ ሁኔታ እየተሰጠ ይገኛል።

በዘመቻው ውስጥ የጤና ባለሙያዎች፣ የጤና ኤክስቴንሽን ሰራተኞች እና የማህበረሰብ መሪዎች በቅንጅት በመስራት ሁሉም የታለሙ ህጻናት ክትባቱን እንዲያገኙ ጥረት እያደረጉ ነው።

የክትባት አገልግሎት የህጻናትን ህይወት ከአደገኛ በሽታዎች በመጠበቅ ጤናማ ትውልድ ለመፍጠር ከፍተኛ አስተዋፅኦ እንዳለው ተገልጿል።

ስለሆነም ሁሉም ወላጆች የተዘጋጀውን የክትባት መርሃ ግብር በመጠቀም ልጆቻቸውን በወቅቱ እንዲያስከትቡ ጥሪ ቀርቧል።

የዳምቤ ወረዳ ገቢዎች ጽሕፈት ቤት በአዲሱ የፌዴራል የገቢ ግብር አዋጅ ዙሪያ ለነጋዴዎችና ለባለድርሻ አካላት ግንዛቤ ሰጠዳምቤ፣ ሰኔ 11/2018 ዓ.ም – የዳምቤ ወረዳ ገቢዎች ጽሕፈት ቤት ...
18/06/2026

የዳምቤ ወረዳ ገቢዎች ጽሕፈት ቤት በአዲሱ የፌዴራል የገቢ ግብር አዋጅ ዙሪያ ለነጋዴዎችና ለባለድርሻ አካላት ግንዛቤ ሰጠ

ዳምቤ፣ ሰኔ 11/2018 ዓ.ም – የዳምቤ ወረዳ ገቢዎች ጽሕፈት ቤት አዲስ የተሻሻለውን የፌዴራል የገቢ ግብር አዋጅ በተመለከተ በተለያዩ የንግድ ዘርፎች ላይ ለተሰማሩ ነጋዴዎችና ለሌሎች ባለድርሻ አካላት ሰፊ የግንዛቤ መድረክ አካሂዷል።

በመድረኩ የገቢ አወሳሰን ቡድን መሪ አቶ ጣሊያን ተርሾ አዲሱን የገቢ ግብር አዋጅ በዝርዝር በማብራራት፣ በአዋጁ ውስጥ የተካተቱ አዳዲስ የግብር አሰራሮች፣ የግብር አከፋፈል ስርዓቶች እና በነጋዴዎች ዓመታዊ ገቢ መሰረት የሚተገበሩ የግብር መጠኖችን አብራርተዋል።

የዳምቤ ወረዳ ገቢዎች ጽሕፈት ቤት ኃላፊ አቶ ጌታቸው ጀራታ በበኩላቸው፣ ግብር መክፈል የእያንዳንዱ ነጋዴ ሕጋዊና ዜግነታዊ ግዴታ መሆኑን ጠቅሰው፣ መንግስትም ግብርን በፍትሃዊነትና በግልጽነት የማስከፈል ኃላፊነት እንዳለበት አስገንዝበዋል። አዲሱ አዋጅ የግብር ስርዓቱን የበለጠ ፍትሃዊ፣ ግልጽ እና ተጠያቂነትን የሚያጠናክር መሆኑንም ገልጸዋል።

የዳምቤ ወረዳ ንግድ ጽሕፈት ቤት ኃላፊ አቶ ጎጃም ሰንበት በበኩላቸው፣ አዲሱ የገቢ ግብር አዋጅ ለነጋዴዎች ግልጽና ቀላል የግብር አከፋፈል ስርዓት በመፍጠር የንግድ እንቅስቃሴን እንደሚያበረታታ ገልጸው፣ ሁሉም ነጋዴዎች አዋጁን በመረዳት በትክክል መተግበር እንዳለባቸው አሳስበዋል።

የዳምቤ ወረዳ ሰላም ግንባታ ጽሕፈት ቤት ኃላፊ ሎላሳ አባቴ አዲሱ አዋጅ ሕገ-ወጥ የንግድ እንቅስቃሴዎችን በመከላከል፣ የሕዝብ ሰላምና የሕግ የበላይነትን በማጠናከር ከፍተኛ አስተዋጽኦ እንደሚኖረው ገልጸዋል።

ተሳታፊዎችም በአዋጁ ዙሪያ ያላቸውን ጥያቄዎችና አስተያየቶች በማቅረብ ከባለሙያዎች ማብራሪያ ያገኙ ሲሆን፣ መድረኩ የግብር ሥርዓቱን በጋራ ለማጠናከርና የፈቃደኝነት የግብር ክፍያ ባህልን ለማሳደግ ጠቃሚ መሆኑ ተገልጿል።

የ8ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና በዳምቤ ወረዳ መስጠት ተጀመረ(ዳምቤ — ሰኔ 11/2018 ዓ.ም) በዳምቤ ወረዳ የ2018 ዓ.ም የ8ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና ዛሬ በሁሉም የፈተና ጣቢያዎች በሰላማዊ፣ ...
18/06/2026

የ8ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና በዳምቤ ወረዳ መስጠት ተጀመረ

(ዳምቤ — ሰኔ 11/2018 ዓ.ም) በዳምቤ ወረዳ የ2018 ዓ.ም የ8ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና ዛሬ በሁሉም የፈተና ጣቢያዎች በሰላማዊ፣ በሥርዓትና በተሟላ ዝግጅት ተጀምሯል።

በፈተናው አጀማመር ላይ የተቋቋመው የወረዳ ፈተና ቦርድ በተለያዩ የፈተና ጣቢያዎች በመገኘት የፈተና አሰጣጥ ሂደቱን በቅርበት ተከታትሏል።

ቦርዱም ፈተናው በህግና በደንብ መሠረት፣ በፍትሃዊነት፣ በግልጽነትና በከፍተኛ ጥንቃቄ እንዲካሄድ አስፈላጊ ክትትልና ድጋፍ እያደረገ መሆኑን ገልጿል።

የወረዳው ትምህርት ጽሕፈት ቤት ሀላፊ አቶ ጆቴ ካምሳ ፈተናው ያለምንም መስተጓጎል እንዲካሄድ ከሚመለከታቸው አካላት ጋር በቅንጅት መሥራቱን ገልጾ፣ ተማሪዎችም በመረጋጋት፣ በራስ መተማመንና በሥነ ምግባር ፈተናቸውን እንዲወስዱ አሳስቧል።

የወረዳው ምክትል ዋና አስተዳዳሪ አቶ ቡራቃ ተደሰ ለፈተናው ስኬታማ አፈጻጸም አስተዋጽኦ እያደረጉ ላሉ መምህራን፣ የፈተና ተቆጣጣሪዎች፣ የጸጥታ አካላት፣ ወላጆችና ለመላው የዳምቤ ወረዳ ህብረተሰብ ምስጋና ገልጿል። ተማሪዎችም በትጋትና በተስፋ ፈተናቸውን በመፈተን የሚጠበቅባቸውን ውጤት እንዲያስመዘግቡ መልካም ምኞት አስተላልፏል።

ለ35ኛ ጊዜ የሚከበረው የህጻናት ቀን በዳምቤ ወረዳ ደማቅ በሆነ መልኩ ተከበረበዳምቤ ወረዳ ለ35ኛ ጊዜ የሚከበረው የህጻናት ቀን በተለያዩ ማህበራዊና ትምህርታዊ ዝግጅቶች ደማቅ በሆነ መልኩ ...
17/06/2026

ለ35ኛ ጊዜ የሚከበረው የህጻናት ቀን በዳምቤ ወረዳ ደማቅ በሆነ መልኩ ተከበረ

በዳምቤ ወረዳ ለ35ኛ ጊዜ የሚከበረው የህጻናት ቀን በተለያዩ ማህበራዊና ትምህርታዊ ዝግጅቶች ደማቅ በሆነ መልኩ ተከብሯል። በበዓሉ ላይ አመራሮች፣ የሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ባለሙያዎች እና በርካታ ህጻናት ተሳትፈዋል።

የዳምቤ ወረዳ ሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ጽህፈት ቤት ኃላፊ ወይዘሮ ሀልካኔ ስልካ እንደገለጹት፣ ህጻናት የዛሬ አበባ የነገ ፍሬ በመሆናቸው በቂ እንክብካቤ፣ ጥበቃና ትምህርት ሊያገኙ ይገባል ብለዋል። ህጻናት በአካል፣ በአእምሮና በስነ-ምግባር በተሟላ ሁኔታ እንዲያድጉ የቤተሰብና የማህበረሰብ ሚና ከፍተኛ መሆኑንም አስገንዝበዋል።

የወረዳ ብልጽግና ፓርቲ ሴቶች ክንፍ ኃላፊ ወይዘሮ ሮቤ ቦጂ ስለ ህጻናት ጉልበት ብዝበዛ የሚያስከትለውን አሉታዊ ተፅዕኖ ገልጸው፣ ህጻናት ከማንኛውም ዓይነት ብዝበዛና ጥቃት እንዲጠበቁ ሁሉም አካላት በጋራ መስራት እንዳለባቸው ጠቁመዋል።

የዳምቤ ወረዳ ምክትል ዋና አስተዳዳሪ አቶ ቡራቃ ተደሰ በበዓሉ ላይ በተገኙበት ወቅት ለህጻናት የማበረታቻ መልእክት አስተላልፈው፣ የሀገር የወደፊት ተስፋ የሆኑት ህጻናት በትምህርት፣ በስነ-ምግባርና በችሎታ እንዲጎለብቱ የሚያስችል ምቹ አካባቢ መፍጠር የሁሉም ኃላፊነት መሆኑን ገልጸዋል።

በመጨረሻም የ35ኛው የህጻናት ቀን ክብረ በዓል የህጻናት መብትን፣ ጥበቃንና ልማትን በማስተዋወቅ እንዲሁም ህጻናት ለተሻለ ነገ እንዲዘጋጁ የሚያግዙ መልዕክቶች በመተላለፍ ተጠናቋል።

የዳምቤ ወረዳ ብልጽግና ፓርቲ የአባላት አፈጻጸም ግምገማ አካሄደ ******(ሰኔ 9/2018 ዓ.ም — ዳምቤ) በዳምቤ ወረዳ ብልጽግና ፓርቲ የአባላት አፈጻጸም ግምገማ አካሂዷል።በግምገማው የወ...
16/06/2026

የዳምቤ ወረዳ ብልጽግና ፓርቲ የአባላት አፈጻጸም ግምገማ አካሄደ
******

(ሰኔ 9/2018 ዓ.ም — ዳምቤ) በዳምቤ ወረዳ ብልጽግና ፓርቲ የአባላት አፈጻጸም ግምገማ አካሂዷል።

በግምገማው የወረዳው ብልጽግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ጽህፈት ቤት ኃላፊ አቶ ምህረት ወልደ የአባላት ሂደቱን አፈጻጸም የሚያሳይ ሪፖርት አቅርበው ከተሳታፊዎች ጋር ውይይት አካሂዷል።

በመድረኩ የዳምቤ ወረዳ ዋና አስተዳዳሪ አቶ ዋና ዱጉማ በሰጡት አስተያየት የምርጫ ሂደቱን ተነገረው በልማት ዙርያ ሰፊ ማብራሪያ ሰጥተው፣ ለቀጣይ ሥራዎች የሚያግዙ አቅጣጫዎችን አስቀምጠዋል።

ግምገማው ጥንካሬና ክፍተቶች በመለየት በቀጣይ ሥራዎች ላይ የተሻለ አፈጻጸም ለማረጋገጥ መነሻ እንደሚሆን ተገልጿል።

ተሳታፊዎች በበኩላቸው ሰላምን በማስከበር እና የዳምቤ ጉዳይ በዳምቤ ይፋታል በሚለው መርህ የተዘጋጀው ሰነድ በወረዳው ህዝብ ዘንድ አዎንታዊ ለውጥ ማምጣቱን አስከትለው ቀጣይም በትጋት እንዲተገበር አስተያየት ሰጥቷል።

በዳምቤ ወረዳ ሁለት አዳዲስ ቅድመ አንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች ግንባታ ሊጀምር ነው(ሰኔ 8/2018 ዓ.ም — ዳምቤ) በዳምቤ ወረዳ የትምህርት ሽፋንን ለማሳደግና የህፃናትን የመማር እድል ለ...
16/06/2026

በዳምቤ ወረዳ ሁለት አዳዲስ ቅድመ አንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች ግንባታ ሊጀምር ነው

(ሰኔ 8/2018 ዓ.ም — ዳምቤ) በዳምቤ ወረዳ የትምህርት ሽፋንን ለማሳደግና የህፃናትን የመማር እድል ለማስፋት የሚያስችሉ ሁለት ቅድመ አንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች ግንባታ ለማስጀመር የርክክብ ስነ-ስርዓት ተካሂደዋል።

የክልሉ ትምህርት ቢሮ ምህንድስ አቶ አበበ አድማሱ እንደገለጹት፣ በ24 ሚሊዮን ብር ወጪ የሚገነቡት እነዚህ ትምህርት ቤቶች በሚቀጥለው የትምህርት ዘመን ተማሪዎችን ለመቀበል ዝግጁ እንዲሆኑ ታቅዷል።

የግንባታ ስራውን የሚያከናውነው ባዘዘው ሙሉጌታና ጓደኞቹ ጠቅላላ ስራ ተቋራጭ ኮንትራክተር ሲሆን፣ ስራውን በጥራትና በወቅቱ ለማጠናቀቅ ቁርጠኛ መሆኑን ገልጿል።

የዳምቤ ወረዳ ምክትል ዋና አስተዳዳሪ አቶ ቡራቃ ተደሰ በበኩላቸው፣ በወረዳችን በዕቅድ ሁሉት ቅድመ አንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ለመስራት ወስነን በህዝብ ተሳትፎና በማህበረሰብ ጉልበት ዘጠኝ ቅድመ አንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶችን መገንባቱን ጠቅሰው፣ የክልሉ ትምህርት ቢሮ ድጋፍ አመሰግነዋል።

በዚህ መሠረት በወረዳው የህፃናት ትምህርት ተደራሽነትን በማሻሻል የተሻለ የመማር አካባቢ ለመፍጠር ከፍተኛ አስተዋፅኦ እንደሚያበረክት ጠቁመዋል።

የዳምቤ ወረዳ ፖሊስ ጽህፈት ቤት የ11 ወራት የስራ አፈጻጸም ርፖርት ገመገመ***(ሴነ 8/2018 ዓ.ም — ዳምቤ) የዳምቤ ወረዳ ፖሊስ ጽህፈት ቤት ከሐምሌ 1/2017 ዓ.ም እስከ ግንቦት 1...
15/06/2026

የዳምቤ ወረዳ ፖሊስ ጽህፈት ቤት የ11 ወራት የስራ አፈጻጸም ርፖርት ገመገመ
***

(ሴነ 8/2018 ዓ.ም — ዳምቤ) የዳምቤ ወረዳ ፖሊስ ጽህፈት ቤት ከሐምሌ 1/2017 ዓ.ም እስከ ግንቦት 1/2018 ዓ.ም ያከናወናቸውን የ11 ወራት የስራ አፈጻጸም ገምግሟል።

ሪፖርቱን ሳጅን ሂካ ጀሬኛ ያቀረቡ ሲሆን፣ በተቋሙ ውስጥ የተሰሩ ዋና ዋና ስራዎችን በምስልና በመረጃ በማስደገፍ ለአመራሮችና ለፖሊስ አባላት አቅርበዋል።

ተሳታፊዎች ሰፊ ውይይት በማድረግ ግብረመልስ ሰጥተዋል። በግምገማውም የወረዳው ፖሊስ አዛዥ ኮማንደር ወገር ፖሊኖ ተገኝተው አስተያየት ሰጥቷል ፣ የፖሊስ አባላትና ሌሎች የጸጥታ አካላት ከማህበረሰቡ ጋር በመቀናጀት ስርቆት፣ ዘረፋ እና ሌሎች ወንጀሎችን ለመከላከል ያደረጉትን ጥረትም አድንቀዋል።

በቀጣይም የጸጥታ ስራዎችን በተጠናከረ መልኩ እንዲቀጥሉ እና ለሙያቸው ክብር በመስጠት ህብረተሰቡን በታማኝነት እንዲያገለግሉ አሳስበዋል።

የጽህፈት ቤቱ ህዝብ ግንኙነት ኦፊሰር ኮማንደር ዳዊት ሞገስ፣ በግምገማው የተለዩ ጠንካራ እና ደካማ ጎኖች ለቀጣይ ዓመት እቅድ ግብዓት እንዲሆኑ አሳስበው፣ ከፖሊስ ስነ-ምግባር ውጭ የሚንቀሳቀሱ አባላት በህግና በደንብ መሰረት እንዲስተናገዱ አመራሩን አሳስበዋል።

የዳምቤ ወረዳ ትምህርት ጽህፈት ቤት ለ6ኛና 8ኛ ክፍል ክልላዊና በሔራዊ ፈተና ዝግጅት ኦረንቴሽን ሰጠ——(ሰኔ 8/2018 ዓ.ም — ዳምቤ) የዳምቤ ወረዳ ትምህርት ጽህፈት ቤት 6ኛ ክፍል ክል...
15/06/2026

የዳምቤ ወረዳ ትምህርት ጽህፈት ቤት ለ6ኛና 8ኛ ክፍል ክልላዊና በሔራዊ ፈተና ዝግጅት ኦረንቴሽን ሰጠ
——

(ሰኔ 8/2018 ዓ.ም — ዳምቤ) የዳምቤ ወረዳ ትምህርት ጽህፈት ቤት 6ኛ ክፍል ክልላዊ ና 8ኛ ክፍል በሔራዊ ፈተና በተሳካ ሁኔታ ለማስፈጸም የተመለመሉ መምህራን፣ ሱፐርቫይዘሮች እና ፖሊስ አባላት አጠቃላይ ኦረንቴሽን ሰጥቷል።

የጽህፈት ቤቱ ሀላፊ አቶ ጆቴ ካምሳ የመክፈቻ ንግግር በማድረግ ፈተናው በጥራት፣ በግልጽነት እና በታማኝነት እንዲካሄድ የሁሉም ተሳታፊዎች ሚና ከፍተኛ መሆኑን አሳስበዋል።

የወረዳው ፈተና ክፍል ሀላፊ አቶ ዳኜ ኦልጅራ የፈተና አሰጣጥ ሂደትን በተመለከተ ሰፊ ማብራሪያ ሲሰጡ፣ የስርዓት ትምህርት አቅም ትግበራ ዋና ስራ ሂደት ቡድን መሪ አቶ ዮሴፍ ጃላታ ደግሞ ለመምህራን፣ ሱፐርቫይዘሮችና ፖሊስ አባላት የስራ ድርሻና ሀላፊነት ዙሪያ ገለጻ አድርገዋል።

በመጨረሻም የትምህርት ጽህፈት ቤት ምክትል ሀላፊ አቶ ወርቅና ከሳሳ የማጠቃለያ መልዕክት በማስተላለፍ 6ኛ ክፍል ፈተና ከሰኔ 15-16 እና 8ኛ ክፍል ፈተና ከሰኔ 11-12/2018 ዓ.ም እንደሚሰጥ በማሳሰብ ሁሉም አካላት የተሟላ ቅድመ ዝግጅት እንዲያደርጉ ጥሪ አቅርበዋል።

Address

Agálo

Telephone

+251980248884

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when በካማሺ ዞን የዳምቤ ወረዳ መንግስት ኮሙንኬሽን ጽ/ቤት posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Share