03/03/2023
ሸበል በረንታ ወረዳ
ማርች 8
አለም አቀፍ የሴቶች ቀን ዛሬ የካቲት 24/06/2015ዓ/ም በወረዳ ደረጃ ከቀበሌ ከወረዳ ከመጡ ሴቶና የወረዳ አመራሮች ጋር በመሆን ሞቅ ደመቅ ባለ መልኩ ተከብሯል። በእለቱ ሴቶች በሀገራዊ የመልካም አስተዳደርና የልማት ግንባታ ዙሪያ ያላቸውን ጉልህ ሚንና አቅም ታሪክን በማጣቀስ ለበአሉ የምድረክ መክፈቻ ያደረጉት የወረዳችን ብልፅግና ፓርቲ ጽ/ቤት ሀላፊ አቶ ባንተላይ ደምሰው ናቸው። የሸበልበረንታ ወረዳ ሴ/ህ/ማ/ጉ/ጽ/ቤት ሀላፊም ሴቶች በአለም የሰላምና የልማት እውደት ውስጥ የሚያሳርፉት አሻራ ከሁሉም በላይ እንደሆነና ይህ ልፋታቸውና ድካማቸው ግን ዛሬም በሚገባው ልክ ቦታ እየተሰጠው ባለመሆኑ ወደፊትም ብዙ የምንሰራቸው ስራወች በመኖራቸው ዛሬም ጠንክረን በአንድነት ልንታግል ይገባል ብለዋል። በእለቱ በትምህርታቸው ከፍተኛ ውጤት ላመጡ ሴት ተማሪዎች የማበረታቻ ሽልማት በማበርከት በአሉ ተጠናቋል።