Gurage Zone Culture and Tourism

Gurage Zone Culture and Tourism የጉራጌ ዞን ባህላዊ እሴቶት ፣ ታሪካዊ እና ተፈጥሮአዊ የቱሪስት መስህቦች ይቃኙበታል።

31/05/2026
“የቅረርየ”(ነፍሴ የሚወዳት የጉራጌ የሥራና የበጎ አድራጎት ፍልስፍና) የጉራጌ የሥራ ሰውነት መነሻው “የቅረርየ” ይመስለኛል:: “የቅረርየ” “ቅረረ” ከሚለው ቃል የወጣ ሆኖ ትርጉሙ ማለዳ ማ...
31/05/2026

“የቅረርየ”
(ነፍሴ የሚወዳት የጉራጌ የሥራና የበጎ አድራጎት ፍልስፍና)

የጉራጌ የሥራ ሰውነት መነሻው “የቅረርየ” ይመስለኛል:: “የቅረርየ” “ቅረረ” ከሚለው ቃል የወጣ ሆኖ ትርጉሙ ማለዳ ማለት ነው፤ “የቅረርየ” ደግሞ ‘የማለዳ ሥራ’ እንደ ማለት ነው፡፡ ይህ ፍልስፍና የጉራጌን የሥራ ስነ-ምግባርና ማኅበራዊ ትስስር የሚያሳይ ማኅበረሰባዊ እሴት ነው። በማኅበረሰቡ ዘንድ ማልዶ መነሳትና ለሥራ መሰማራት ለራስ ብቻ ሳይሆን ለሌሎችም መትጋትን፣ መረዳዳትን፣ በታማኝነት መሥራትን ማዕከል ያደረገ ነው።

… በከተሞች በተለይም እንደ ሆቴል፣ አትክልት ቤት፣ ሱቅ፣ ወዘተ. ባሉ አገልግሎት ሰጪ ድርጅቶች ተገልጋዩ በሚፈልጋቸው ሰዓት ስንዱ ሁነው የሚጠብቁት (ከሌሊት 9:00 ጀምሮ) ማልደው በመነሳት የራቀውን በማቅረብ፣ የጎደለውን በማሟላት በሚያዘጋጁ ትጉሃን አማካይነት ነው፡፡ … ብዙ ሰው ጉራጌ በከተማ በንግድ ሥራ ያለው እንዲህ ዓይነቱ ትጋት ካገሩ ከወጣ በኋላ የተማረው ይመስለዋል፤ ሀቁ ግን ከቀዬው ከወላጆቹ የወረሰው ልምዱ፣ ባህልና መገለጫው፣ የአያቶቹ ውርስና ማንነቱም ጭምር ነው፤ የዚህ አንዱ ማሳያ ደግሞ “የቅረርየ” ነው፡፡

… ማልዶ ይነሳል፣ መደበኛ የደቦ/የማኅበር ሥራ ከመውጣቱ በፊት ኢ-መደበኛ ሥራዎች (ለምሳሌ፡- ለከብቶች መኖ ማዘጋጀት/ሣር ማጨድ፣ አጥር ማጠር፣ የማገዶ እንጨት ማቅረብ፣ ...) ይሠራል፡፡ ከሁሉ በላይ የአቅመ ደካሞችን፣ የእማወራዎችንና የአካል ጉዳተኞችን እርሻ የሚያርሰውና ደካሞችን የሚረዳው በዚሁ ክፍለ-ጊዜ ነው፡፡

ከዚያ በጊዜ የደቦ ሥራ ይወጣል፣ አያረፍድም፤ በኅብረት ወይም በደቦ ሥራ ጊዜ “ከእኔ በላይ ለባልንጀሬ” በሚል መንፈስ የተጣማሪው ማሳ ላይ ከአንጀቱ ሲሠራ ይውላል፣ አይለግምም፣ በሙሉ ኃይሉ ይሠራል፡፡ እጅግ የሚደንቀው ደግሞ ‘ሰዓት ደረሰ’ ብሎ የጀመረውን ሳይፈጽም ከቤቱ አይገባም፤ ሥራ የሚያበቃው ሲመሽ ወይም ‘ለዓይን ያዝ’ ሲያደርግ እንጂ፤ ‘ሰዓት ደረሰ’ ብሎ በፍጹም ጥሎ አይሄድም፤ … ድንገት መሽቶ ያደረ ሥራ ቢኖር በማግስቱ “የቅረርየ” ወጥቶ ይፈጽማል፡፡

… አሁን አሁን ግን በአገር ቤት ያ ሁሉ የለም፣ ተትቷል ይባላል፤ … ማልዶ መነሳቱ፣ መረዳዳቱ፣ ሰዓት ማክበሩ፣ ከልብ መሥራቱ ቀረ አሉ፤ ያ ልምድ ነበር ሆኗል፤ … በተቃራኒው ለሥራ አርፍዶ መውጣት፣ በየምክንያቱ መቆም/መቀመጥ፣ አረቄ ጠጥቶ እየተንገዳገዱ መሥራት፣ ሳይመሽ ሥራ ጥሎ መግባት ባህል ሆኗል አሉ፤ … ይህ ብዙዎች የሚጋሩት ስጋትና እውነት እንጂ ሀሜት ብቻ አይደለም።

… እንዲያ መሆኑ አግባብ አይደለም! … ደግም አይደል! ... የኋላው (የአገርቤቱ) ካልጸና መች የፊቱ (የከተማው) ይሰምርና? … መሠረት ከተናወጠ ነገን ዘልቆ ማየት እንዴት ይታሰባል? … ይህ ሁኔታ “… የቀደመው ትጋታችን ትተናልና ወዮልን! …” የሚያስብል ነው፡፡ የከተማው በትጋቱ ሲጸና (እንደ ጥንቱ ባይሆንም)፤ የአገርቤቱ ጉራጌ ምን ነካው? ለምን ይሆን ወደኋላ ያለው? … ያ የነበረው ተመልሶ እንዲመጣስ ምን እናድርግ? ማለት ያሻል! … ጊዜ የሚሰጠው ጉዳይ አይደለም!

… ለዚህ ችግር እንደ ምክንያት፡- የተሳሳተ አመለካከት፣ የአረቄና የጫት ሱሰኝነት፣ የከተማ ጥገኝነት፣ የከተማ ነዋሪ ቤተሰብ/ዘመድ የሸማችነት (consumerism) ባህል ተጽዕኖ፣ በገጠር ያለው ወጣት እዚያው ሠርቶ መለወጥን ትቶ ወደ ከተማ የመሰደድ ዝንባሌ፣ የነባር ባህላዊ እሴቶች መሸርሸርና ለወጣቱ ትውልድ በሚገባ ሳይተላለፍ መቅረት፣ … ይጠቀሳሉ፤
በዶክተር ደርብ ወ/ዮሀንስ
ከሀሪ ዲጂታል የተወሰደ

27/05/2026

የጉራጌ ዞን #ባህል ኪነት ቡድን የባህል አምባሳደሮች እናመሠግናለን።

ሀይማኖታዊ በዓላት ለቱሪዝም ሀብት እድገት የሚያበረክቱት አስተዋጽኦ ከፍተኛ በመሆኑ በዓላቱ ይበልጥ በድምቀት ለማክበር በትኩረት እንደሚሰራ የጉራጌ ዞን ባህልና ቱሪዝም መምሪያ አስታወቀ።የጉራ...
27/05/2026

ሀይማኖታዊ በዓላት ለቱሪዝም ሀብት እድገት የሚያበረክቱት አስተዋጽኦ ከፍተኛ በመሆኑ በዓላቱ ይበልጥ በድምቀት ለማክበር በትኩረት እንደሚሰራ የጉራጌ ዞን ባህልና ቱሪዝም መምሪያ አስታወቀ።

የጉራጌ ማህበረሰብ እምቅ ባህላዊ እሴቶችን በማልማት፣ በመንከባከብና በማስተዋወቅ የአለም ቅርስ ለማድረግ ታቅዶ እየተሰራ መሆኑ ተጠቁሟል።

ግንቦት 29/2018 (ወልቂጤ)በየአመቱ በድምቀት የሚከበረው 8ኛው "አረፋን በጉራጌ" ልዩ የበዓል ፌስቲቫል በጉራጌ ዞን ገደባኖ ጉታዘር ወለኔ ወረዳ በጥላሞ ቀበሌ ተካሂዷል።

በፕሮግራሙ የተገኙት የጉራጌ ዞን ባህልና ቱሪዝም መምሪያ ኃላፊ ወ/ሮ መሰረት አመርጋ እንደገለፁት በጉራጌ ብሔር ዘንድ በድምቀት የሚከበሩ ሀይማኖታዊ በዓላት በቱሪዝም ሀብት እድገት ላይ ከፍተኛ አስተዋጽኦ እያበረከቱ ይገኛል።

ከእነዚህ ሀይማኖታዊ በዓላት አንዱ የአረፋ በዓል ሲሆን በስራ ምክንያት ተራርቀው የነበሩ ቤተሰቦች የሚገናኙበት፣ የተጣሉ ወገኖች የሚታረቁበት፣ የተቸገሩ ወገኖች የሚረዱበት እንዲሁም አብሮነትን በተግባር የሚገለጽበት ተናፋቂ በዓል እንደሆነ ገልፀዋል።

ጎረቤታሞች በዘር፣ በሀይማኖትና በማንነት ሳይለያዩ በዓሉ በድምቀት ለማክበር ከቅድመ ዝግጅት ጀምሮ እስከ በዓሉ ድረስ የሚከናወኑ ተግባራት በጋራ በማሰናዳት ማህበራዊ ግንኙነታቸውን ያጠናክራሉ ብለዋል።

ይህንን ተከትሎ የእምነቱ ተከታዮች ሌሎች ወዳጆቻቸውን አስከትለው ከያሉበት ተሰባድበው ወደ ቀዬያቸው የሚያመሩት።

ሀገር ቤት ያሉ ቤተሰቦች ሁሉም እንደ አቅሙ ለበዓሉ ድምቀት ኃላፊነት እንደሚሠጠው የገለፁት ኃላፊዋ ሴቶች ቆጮ፣ ቂቤ፣ አይቤ፣ የጎመን ክትፎ፣ ሚጥሚጣ፣ የወለል ምንጣፍ፣ የልብስ አጠባ፣ የቤት ንፅህና እና ሌሎች ተግባራት ያከናውናሉ ብለዋል።

ወንዶች ደግሞ የእርድ ከብት ከመግዛት ባለፈ ቤቱን የማደስ፣ አጥር የማጠር፣ የማገዶ እንጨት የማዘጋጀት ተግባር እንደሚያከናውኑ አስረድተዋል።

በመሆኑም በዓሉ ከእምነቱ ተከታዮች ባለፈ የሌላ ቤተ እምነት ተከታዮች በናፍቆት የሚጠብቁት በዓል መሆኑን ገልፀዋል።
ይህንን በዓል ይበልጥ እንዲደምቅና ጎልቶ እንዲወጣ የሁለቱ ጉራጌ ዞኖች መንግስት በየአመቱ በፌስቲቫል እንደሚከበ ተናግረዋል።

8ኛውን የአረፋ በጉራጌ ልዩ የበዓል ፌስቲቫል በጉራጌ ዞን ገደባኖ ጉታዘር ወለኔ ወረዳ አስተዳደር በጥላሞ ቀበሌ በድምቀት ማክበር ተችሏል ብለዋል።

በዓላቱ በፌስቲቫል ደረጃ መከበራቸው ያሉንን ሀብቶች ከማስተዋወቅ ባለፈ በዓላቱ ሀይማኖታዊና ባህላዊ ይዘታቸውን እንደተጠበቀ ለተተኪ ትውልድ ለማስተላለፍ መልካም አጋጣሚ እንደሚፈጥር አውስተዋል።

እንደ ኃላፊዋ ገለፃ በዘንድሮ የአረፋ በዓል ከ600 ሺህ በላይ ቱሪስቶች ዞኑን የጎበኙ ሲሆን ቱሪስቶቹ በባህላዊ ልብስ፣ በእደ ጥበብ ውጤቶች እና በአገልግሎት ሰጪ ተቋማት በሚፈጽሟቸው ግብይቶች ከአንድ ቢሊዮን ብር በላይ ገቢ ያስገኛሉ።

እነዚህ በዓላት የጉራጌን ማህበረሰብ ታሪክ፣ እንግዳ ተቀባይነትና ልዩ የባህል እሴቶች ለዓለም ለማስተዋወቅ ትልቅ አስተዋጽኦ እንደሚያበረክቱ ገልፀዋል።

በተለይም የማህበረሰቡ መገለጫ፣ የበዓላቱ ድምቀት እና የቱሪስቶች ናፍቆት የሆነውን የጉራጌ "ክትፎ" በተባበሩት መንግስታት የትምህርት፣ የሳይንስና የባህል ድርጅት (UNESCO) በዓለም የማይዳሰስ ቅርስነት ለማስመዝገብ የተጀመሩ የቅድመ ዝግጅት ስራዎች መጠናቀቃቸው ወ/ሮ መሰረት ተናግረዋል።

በቀጣይ በዞኑ የሚገኙ የሚዳሰሱና የማይዳሰሱ ቅርሶች በማልማትና በማስተዋወቅ የዞኑ የቱሪዝም ዘርፍ እድገት ይበልጥ ለማሳደግ በትኩረት ይሰራል ብለዋል።

መረጃው ነጉራጌ ዞን መንግስት ኮምኒኬሽን መምሪያ ነው።

27/05/2026

የኢደል-ዓድሃ(አረፋ) የኢድ ሶላት በጉራጌ ዞን በሁሉም አካባቢዎች ካለምንም የፀጥታ ችግር በሠላም መጠናቀቁ የዞኑ ሰላምና ፀጥታ መምሪያ አስታወቀ።

መምሪያው ፀሃይና ዝናብ ሳይበግራቸው ወደ ዞኑ የሚገቡ እንግዶችን ሲያስተናግዱ ለነበሩ የፖሊስና የፀጥታ አባላትንም በልዩ ሁኔታ አመስግኗል።

ግንቦት 19/ 2018 ዓ/ም (ወልቂጤ)፦ የዘንድሮው አረፋ ኢድ ሶላት በዞኑ በሁሉም አካባቢዎች ህዝበ ሙስሊሙ ካለምንም የፀጥታ ችግር በሠላም ማጠናቀቁ የጉራጌ ዞን ሰላምና ፀጥታ መምሪያ ገለፀ።

የእምነቱ ተከታዮች በዓሉን ያለምንም የፀጥታ ስጋት እንዲያከብሩ ጥምር የፀጥታና ደህንነት የጋራ ግብር ኃይሉ አስቀድሞ ባወጣው እቅድ መሰረት፣ በበዓሉ ዋዜማ ግብይት በሚበዛባቸው አካባቢዎች፣ በመስጂዶች እና በሌሎች ስፍራዎች አስፈላጊውን የሰው ኃይል በመመደብ ስራውን ሲያከናውን መቆየቱ ተገልጿል።

በበዓሉ ዋዜማም ሆነ በበዓሉ ዕለት ምንም ዓይነት የተለየ ወንጀል አለመመዝገቡ የዞኑ ሰላምና ፀጥታ መምሪያ አረጋግጧል።

የጉራጌ ዞን ሰላምና ፀጥታ መምሪያ ኃላፊ አቶ ነጋ አሰፋው እንደገለፁት የዞኑ ህዝብ ለሰላም ያለው ቁርጠኝነትና ከፀጥታ መዋቅሩ ጋር ያለው ቅንጅት እያደገ በመምጣቱ የዞኑ ሰላም ከወትሮው በተለየ መልኩ መሻሻሉን አስገንዝበዋል።

በዞኑ በሁሉም አካባቢ ያሉ የፖሊስና ሌሎች የፀጥታ አካላት ዝናብና ፀሃይ ሳይበግራቸው ለበዓሉ ወደ ዞናችን የሚገቡ እንግዶችን ከማስተናገድ ጀምሮ በሶላት ቦታዎች ምንም አይነት የፀጥታ ችግር እንዳይፈጠር በማድረጋቸው የተለየ ምስጋና ይገባቸውል ብለዋል።

በበጀት ዓመቱ በዞኑ የተከበሩ ልዩ ልዩ በዓላት እና ስኬታማ ኩነቶች በሠላም እንዲጠናቀቁ ህብረተሰቡ ፣የመረጃና ደህንነት አካላት፣ወጣቶችና የእምነት ተቋማት፣ ከፀጥታ አካላት ጋር በመሆን ላደረጉት ያልተቋረጠ ድጋፍ መምሪያው ምስጋናውን አቅርቧል።

27/05/2026
1447ተኛው የኢደል-ዓድሃ(አረፋ)በዓል ምክኒያት በማድረግ በጉራጌ ዞን ገደባኖ ጉታዘር ወለኔ ወረዳ ጥላሞ ቀበሌ "አረፋን በጉራጌ" ልዩ የበዓል ፌስቲቫል እየተካሄደ ይገኛል!!ግንቦት 19/20...
27/05/2026

1447ተኛው የኢደል-ዓድሃ(አረፋ)በዓል ምክኒያት በማድረግ በጉራጌ ዞን ገደባኖ ጉታዘር ወለኔ ወረዳ ጥላሞ ቀበሌ "አረፋን በጉራጌ" ልዩ የበዓል ፌስቲቫል እየተካሄደ ይገኛል!!

ግንቦት 19/2018(ወልቂጤ)

በየዓመቱ በጉራጌዎች ዘንድ በድምቀት የሚከበረው "አረፋን በጉራጌ" ልዩ የበዓል ፌስቲቫል የዘንድሮውን በጉራጌ ዞን ገደባኖ ጉታዘር ወለኔ ወረዳ ጥላሞ ቀበሌ እየተከበረ ይገኛል!!

በዓሉ በእስልምና እምነት ተከታዮች ዘንድ በመላ ሀገሪቱ በተለያዩ ሃይማኖታዊ ሥነ-ሥርዓቶች ነው እየተከበረ የሚገኘው፡፡

የአረፋ በዓል በጉራጌ ህዝብ ዘንድ በልዩ ድምቀት የሚከበር ሲሆን ከሃይማኖታዊ አከባበሩ በተጨማሪ ባህላዊ ይዘቶቹም የጎሉ ናቸው!!

የዘምድሮው ለስምንተኛ ጊዜ በገደባኖ ጉታዘር ወለኔ ወረዳ ጥላሞ ቀበሌ እየተካሄደ የሚገኘው "አረፋን በጉራጌ" ልዩ የበዓል ፌስቲቫል በሁለቱ የጉራጌ ዞኖች ፣በገደባኖ ጉታዘር ወለኔ ወረዳ፣ በወልቂጤ ዩኒቨርሲቲ እና በጉልባማ ትብብር መዘጋጀቱ ተጠቁሟል።

አረፋ ከሃይማኖታዊ አከባበሩ ባሻገር የጉራጌ ተወላጅ የእምነቱ ተከታዮች ወደ ቤተ ዘመዶቻቸው የሚመለሱበት፣ዚያራ የሚያደርጉበት፣ምርቃትንም የሚሸምቱበት፣ስለ አካባቢያቸው ልማት የሚወያዩበት፣የተቸገሩ ጎረቤቶቸውንና ዘመዶቻቸው የሚረዱበት ደማቅ በዓል ነው!!

በፕሮግራሙ የጉራጌ ዞን ዋና አስተዳዳሪ ክቡር አቶ ላጫ ጋሩማ፣የምስራቅ ጉራጌ ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ ሙስጠፋ ሀሰን፣የጉራጌ ዞን ህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ዋና አፈ ጉባኤ ኸይሩ መሀመድ፣የጉራጌ ዞን እስልምና ጉዳዮች ከፍተኛ ምክር ቤት ፕሬዝዳንት ሼህ አባስ ያሲን፣የጉራጌ ዞን ባህል ቱሪዝም መምሪያ ሀላፊ ወይዘሮ መሠረት አመርጋ፣የገደባኖ ጉታዘር ወለኔ ወረዳ ዋና አስተዳዳሪ አቶ ሚፍታ ሁሴን ጨምሮ የሁለቱ ጉራጌ ዞኖች ከፍተኛ አመራሮ፣የወረዳና ከተማ አስተዳደር አመራሮች እንደዚሁም ሌሎች ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች እየተሳተፉ ይገኛል።

27/05/2026

መልካም የአረፋ በአል!!

Address

Wolkite
PERSONAL

Opening Hours

Monday 09:00 - 17:00
19:00 - 19:00
Tuesday 09:00 - 18:30
19:00 - 20:00
Wednesday 09:00 - 18:30
19:00 - 19:00
Thursday 09:00 - 18:30
19:00 - 20:00
Friday 09:00 - 18:30
19:00 - 20:00
Saturday 03:00 - 02:45

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Gurage Zone Culture and Tourism posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Organization

Send a message to Gurage Zone Culture and Tourism:

Share