በጉራጌ ዞን የጌታ ወረዳ የመንግስት ኮምንኬሽን ጉ/ጽ/ቤት

  • Home
  • Ethiopia
  • Wolkite
  • በጉራጌ ዞን የጌታ ወረዳ የመንግስት ኮምንኬሽን ጉ/ጽ/ቤት

በጉራጌ ዞን የጌታ ወረዳ የመንግስት ኮምንኬሽን ጉ/ጽ/ቤት ይህ በጉራጌ ዞን የጌታ ወረዳ የመንግስት ኮሚኒኬሽን ጉዳዮች ፅ/ቤት ነው

‎በጉራጌ ዞን ጌታ ወረዳ 1447ኛው የኢድ አል አደሃ (አረፋ) በዓል በተለያዩ ሀይማኖታዊ ስነ-ስርአት በድምቀት እየተከበረ ነው።‎‎ግንቦት 19/2018 ዓ.ም (ቋንጤ)‎በጌታ ወረዳ በድምቀት ...
27/05/2026

‎በጉራጌ ዞን ጌታ ወረዳ 1447ኛው የኢድ አል አደሃ (አረፋ) በዓል በተለያዩ ሀይማኖታዊ ስነ-ስርአት በድምቀት እየተከበረ ነው።

‎ግንቦት 19/2018 ዓ.ም (ቋንጤ)
‎በጌታ ወረዳ በድምቀት ከሚከበሩ በዓላት አንዱ የአረፋ በዓል ሲሆን የዘንድሮ የ1447ኛው የኢድ አል አደሃ (አረፋ) በዓል የኢድ ሶላት ፕሮግራም በቋንጤ ከተማ እየተካሄደ ይገኛል።

‎በዓሉ በሚያከበሩበት ወቅት የተቸገሩ ወገኖች የሚረዱበት ፈጣሪን የሚለመንበት፣ አንድነትን፣ ወንድማማችነትን የሚሰበክበት በዓል ነው።

‎ለመላው የእስልምና እምነት ተከታዮች በሙሉ እንኳን እንኳን ለ1447ተኛው የኢደል-ዓድሃ (አረፋ)በዓል በሰላም አደረሳችሁ!!

‎ዒድ ሙባረክ!!

በሽታን አስቀድሞ በመከላከል ለህክምና  መድሃኒት የሚወጣውን ከፍተኛ ወጪ ማዳን እንደሚገባ የጌታ ወረዳ ጤና ጥበቃ ጽህፈት ቤት ገለፀ ።18/9/2018ዓ.ም(ቋንጤ)ጽህፈትቤቱ ከማ/ኢ/ክ ጤና ቢ...
26/05/2026

በሽታን አስቀድሞ በመከላከል ለህክምና መድሃኒት የሚወጣውን ከፍተኛ ወጪ ማዳን እንደሚገባ የጌታ ወረዳ ጤና ጥበቃ ጽህፈት ቤት ገለፀ ።

18/9/2018ዓ.ም(ቋንጤ)
ጽህፈትቤቱ ከማ/ኢ/ክ ጤና ቢሮ የበሽታ መከላከልና ጤናን ማጎልበት ዳይረክቶሬት ከዞን ጤና መምሪያ ጋር በመተባበር በጌታ ወረዳ በንጽሕና ግብይት የግብአት አጠቃቀም ፍላጎትና ግንዛቤ መፍጠሪያ መድረክ በቋንጤ ከተማ አካሄደ ።

የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ጤና ቢሮ በሽታ መከላከል ዋና ስራሂደት የሳኒቴሽን ኦፊሰር አቶ በለጠ ወ/ማረያም በበኩላቸው ወረዳው እንደ ሀገር ጽዱ ንጹሕ ኢትዮጵያ ፓይለት ትግበራ ፕሮግራም የተሻለ አፈጻጸም በማስመዝገብ በሀገር ደረጃ ሶስተኛ መዉጣቱ የወረዳው መንግስት ና የጤናው ባለሙያዎች በሰሩት ጠንካራ ስራ ነው ብለዋል ።

አያይዘውም ወረዳው ከተለያዩ የሀገራችን ክፍሎች የጽዱ ኢትዮጵያ ተሞክሮ የተወሰደባት ነች ብለዉ የበሽታ መከላከል ንጹህ ውሃ መጠጣት እና እጅን በሳሙና መታጠብ እንደ ኮሌራ፣ ታይፎይድ እና ተቅማጥ ያሉ በሽታዎችን እስከ 50% ይቀንሳል ብለዋል ።

የእናቶችና የህፃናት ጤና በጤና ተቋማት ውስጥ የWASH አገልግሎት መኖር በወሊድ ወቅት የሚከሰቱ ኢንፌክሽኖችን በመቀነስ የነፍሰ ጡር እናቶችን እና የጨቅላ ህፃናትን ህይወት ይታደጋል ብለዉ የግል መፀዳጃ ቤት መኖር በተለይ ለሴቶች እና ለልጃገረዶች ደህንነትን፣ ግላዊነትን እና ሰብአዊ ክብርን ይጠብቃል ሲሉ አስገንዝበዋል ።

የወረዳው ጤና ቢሮ ምክትል ሀላፊ አቶ ተመስገን ንዳ የንጽህና ግብይት ምርቶችን የምርት “ጥቅም” ለማህበረሰቡ በተገቢዉ ማሳየት ይገባል ብለዉ የሽንት ቤት (SATO pan) አየር የማያስገባ ዲዛይን ሽታን ይቀንሳል፣ ዝንብ አይገባም፣ ክብርን ይጠብቃል ብለዋል

ማህበረሰባዊና ባህርይ ለውጥ በገበያ መር ሳኒቴሽን ላይ ያለው ፍላጎት መፍጠር ይኖርብናል ያሉት ሀላፊው ።

በገበያ ላይ የተመሰረተ የንጽህና አጠባበቅ (MBS) ውስጥ የማህበረሰብ ተሳትፎ ማለት ህዝቡ የመፀዳጃ ቤት ምርቶችን እንዲገዛና እንዲጠቀም ለማድረግ በአካባቢው ያሉ ማህበራዊ ትስስሮችን የመጠቀም ሂደት ማጠናከር ይገባል ብለዋል ።

ወረዳችን ሁሉንም በጽዱ ኢትዮጵያ ስለምናስመርቅ ማህበረሰቡ በሜዳ ላይ መጸዳዳት "ጎጂና አስነዋሪ" መሆኑን በጋራ እንዲስማማ በማድረግ፣ ሁሉም ሰው ወደ ዘመናዊ መጸዳጃ ቤት እንዲቀይር ማህበራዊ ጫና መፍጠር ይኖርብናል ሲሉ አመላክቷል ።

ተሳታፊዎች በበኩላቸው ከሳቶፓ ጋር በተያያዘ ሁሉም ማህበረሰብ የመግዛት ፍላጎት አለው ብለዉ ከበፊቱ በተለየ ሁሉም ማህበረሰብ ተደራሽ እንዲሆን እንደሚሰሩም ተናግሯል

አክለው ማህበረቡ የመጸዳጃ ቤት ጥቅም በጥልቀት ተረተዋል ብለዉ አንድም የግል ቤት ዘመናዊ የመፀዳጃ ቤት የሌለው አይኖርም ብለዋል ።ዘገባው የወረዳው መ/ኮ/ጉ/ጽ/ቤት ነው ።

የጌታ ወረዳ አስተዳደር ለመላው ህዝበ ሙስሊሙ ማህበረሰብ ለ1447ኛ ዓመተ ሂጅራ የኢደል አደሀ አረፋ በዓል የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት አስተላለፈ፡፡ግንቦት 18/2018 ዓ.ም (ቋንጤ)የወረ...
26/05/2026

የጌታ ወረዳ አስተዳደር ለመላው ህዝበ ሙስሊሙ ማህበረሰብ ለ1447ኛ ዓመተ ሂጅራ የኢደል አደሀ አረፋ በዓል የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት አስተላለፈ፡፡

ግንቦት 18/2018 ዓ.ም (ቋንጤ)
የወረዳው ዋና አስተዳዳሪ አቶ በህሩ ኸይረዲን ባስተላለፉት የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት ህዝበ ሙስሊሙ ይህን ታላቅ በዓል ሲያከብር የቀደመ የመደጋገፍና የመተሳሰብ ባህሉን ሳይረሳ ለአቅመ ደካማና ለተቸገሩ ወገኖች ካለው ላይ አካፍሎ በመስጠት የደስታቸው ተካፋይ በመሆን ሊሆን ይገባል፡፡

የአረፋ በዓል ሃይማኖታዊ ክንውን ብቻ ሳይሆን ማህበራዊነት፣ ፍቅርና አንድነት በተግባር የሚታይበት ነው።

በዓሉ በጉራጌ ህዝብ ዘንድ ልዩ ታሪክ ያለውና በድምቀት የሚከበር በዓል ከመሆኑም በላይ በከተማ የሚኖረው የአካባቢው ተወላጅ ወደ ቀዬው በመምጣት ወላጆቹንና ቤተሰቡን የሚያስደስትበትና የሚጠይቅበት ነው፡፡

በመሆኑም በዓሉን ስናከብር ባህላዊ ይዘቱንና ሀይማኖታዊ ቱውፊቱን በጠበቀ መልኩ ማክበር ይጠበቅብናል ያሉት ሀላፊው ለአካባቢያችን ሰላምም ትኩረት ሰጥተን አካባቢያችንን ነቅተን ልንጠብቅ ይገባል ብለዋል፡፡

ለበዓል የሚገቡ የአካባቢው ተወላጆችም ከበዓሉ ጎን ለጎን በወረዳው መንግስት በህዝብና በከተማ የሚኖሩ የአካባቢው ተወላጆች ትብብር የተሰሩና እየተሰሩ ያሉ የመሰረተ ልማት በተለይም የመንገድ፣ የውሃና የት/ቤት ግንባታዎችን በመጎብኘት ሊሆን ይገባል፡፡

በቀጣይም የተጀማመሩትን ፕሮጀክቶች ለማጠናቀቅና ሌሎች አዳዲሶችን ለመጀመር የህብረተሰቡ ንቁ ተሳትፎ ወሳኝ በመሆኑ የአካባቢው ማህበረሰብም ሆነ የከተማ ነዋሪው ከወረዳው መንግስት ጎን እንዲቆም ጥሪያቸውን አስተላልፈዋል፡፡

በዓሉ በ7ተኛው ዙር ሀገራዊና ክልላዊ ምርጫ ዋዜማ እንደመከበሩ ህዝባችን ምርጫው ሰላማዊ፣ ፍትሀዊና ዲሞክራሲያዊ እንዲሁም በህዝቡ ዘንድ ቅቡልነት ያለው እንዲሆን የበኩሉን የዜግነት ሀላፍትና እንዲወጣ አሳስበዋል።

የወረዳችን አርሶ አደሮችም በዓሉን ስናከብር ወቅታዊ የሆኑ የግብርና ተግባሮቻችንን በተለይም የመኸር እርሻ ዝግጅት ላይ ትኩረት ሰጥተን መስራት ይጠበቅብናል፡፡

በመጨረሻም ለመላው የእስልምና እምነት ተከታዮች በሙሉ በዓሉ የሰላም የፍቅር የመተሳሰብና የደስታ እንዲሆን መመኘታቸውን የዘገበው የወረዳው መንግስት ኮ/ጉ/ጽ/ቤት ነው፡፡

የዒድ-አል አድሃ [አረፋ] በዓል ለማክበር  ወደ ጉራጌ ዞን  ጌታ ወረዳ ለሚገቡ እንግዶች እንኳን ደህና መጣችሁ አቀባበል እየተደረገላቸው ይገኛል።‎‎በጌታ ወረዳ ‎ለ1447ኛው ለዒድ-አል አድ...
26/05/2026

የዒድ-አል አድሃ [አረፋ] በዓል ለማክበር ወደ ጉራጌ ዞን ጌታ ወረዳ ለሚገቡ እንግዶች እንኳን ደህና መጣችሁ አቀባበል እየተደረገላቸው ይገኛል።


በጌታ ወረዳ ‎ለ1447ኛው ለዒድ-አል አድሃ [አረፋ] በዓል የሚመጡ እንግዶችን በፍቅርና በክብር እየተቀበለች ትገኛለች።

እንግዶቹ በበኩላቸው ስለተደረገላቸው የቤተሰባዊ አቀባበል ምስጋናቸውን አቅርቧል ።

‎የወረዳው አስተባባሪ አካላት ጨምሮ የወረዳዉ የብልጽግና ፓርቲ እጩ ተወዳዳሪ አካላት ጨምሮ የከተማዉ ወጣቶች አቀባበል እያደረጉ ይገኛሉ።

ከጉራጌ ዞን ትራንስፖርትና መንገድ ልማት መምሪያ ለአረፋ በዓል ወደ ዞኑ ለሚገቡ እንግዶች የተላለፈ አስቸኳይ መረጃ!መምሪያው የላከው መልዕክት ሙሉ ቃል እንደሚከተለው ቀርቧል!ለአረፋ በዓል ተ...
24/05/2026

ከጉራጌ ዞን ትራንስፖርትና መንገድ ልማት መምሪያ ለአረፋ በዓል ወደ ዞኑ ለሚገቡ እንግዶች የተላለፈ አስቸኳይ መረጃ!

መምሪያው የላከው መልዕክት ሙሉ ቃል እንደሚከተለው ቀርቧል!

ለአረፋ በዓል ተጓዦች የተሽከርካሪ እጥረት እንደሌለ ከፌደራል ትራንስፖርትና ሎጀስቲክስ አመራሮች ከሶስቱም ተርሚናሎች ማረጋገጥ ተችሏል።

የክፍያ ንረት እንዳይፈጠር ተጨማሪ አማራጮች የተዘጋጀ መሆኑን ቀደም ሲል የተገለጸ ሲሆን፤ በዛሬው ዕለት ተሳፋሪዎች እንደየአካባያቸው ሰብሰብ ብለው ባለመገኘታቸው መኪና የለም በሚል መደበኛ ስምሪት ተጠቅመዋል።

መምሪያው ተጓዦች አስቀድመን በሰጠነው መረጃ መሰረት ሃምሳም ስልሳም ሆነው በጥቆማ ስልኮቻችን መረጃ በመስጠት አማራጮችን መጠቀም አለባቸው ብሏል።

ሆኖም የአማራጮቹ አላማ ከላይ እንደተገለጸው ተመጣጣኝ ዋጋ ፍለጋና የትራፊክ መጨናነቅ ለመቀነስ እንደሆነ ገልጿል።

ከዚህ አንጻር ዛሬ የገቡ ተሽከርካሪዎች በርካቶቹ በ50% ታሪፍ ጭማሪ ብቻ ጭነው ወደ ዞኑ ገብተዋል።

ይህ ማለት ፤ቀደም ሲል በኢ-መደበኛው ከወጣው የታሪፍ ዝርዝር ብር ከ5000 -7000 አንጻር ሲታይ ዞኑ ከባድርሻ አካላት ጋር የወሰደው የአማራጭ እትምጃ ከወዲሁ ምን ያህል ለውጥ ማምጣት እንደተቻለ ማየት ተችሏል።

በሌላ መልኩ አማራጭ ተዘጋጅቷል ማለት መደበኛ ስምሪት የለም ማለት አይደለም፤ መደበኛ ስምሪት ደንብ አክብሮ በታሪፍ እና በጭነት ልክ እንዲሰራ የሚደረግ ጥረት እንደሆነ እንዳይዘነጋ።

ተጓዦች በቁጥር ሃምሳና ፤ ስልሳ ሆነው በሚከተሉት ቁጥሮች በመደወል የጉዞ አገልግሎት ማግኘት ይችላሉ!!
0940997733/0904023031/0941440066/0941339955 ይደውሉ ፤ተሳፋሪው ካለበት ድረስ ባሶቹን ማቅረብ ይቻላል።

በተጨማሪም አየር ጤና ዘነበወርቅ አዲስ ከተማ መናኸሪያዎች ከነገ ጠዋት ጀምሮ የተሻለ አገልግልት ይሰጣሉ ።

አላማችን ሕዝብን ማገልገል ነው !

የጉራጌ ዞን ትራንስፖርትና መንገድ ልማት መምሪያ!

1447ኛዉ የኢድአል አድሀ አረፋ በአልን ምክንያት በማድረግ የአካል ጉዳተኞች እና የተረጂ የማህበረሰብ ክፍል የአልባሳት ድጋፍ መደረጉ የጌታ ወረዳ ሰራተኛና ማህበራዊ ልማት ጉዳዮች ጽህፈት ቤ...
23/05/2026

1447ኛዉ የኢድአል አድሀ አረፋ በአልን ምክንያት በማድረግ የአካል ጉዳተኞች እና የተረጂ የማህበረሰብ ክፍል የአልባሳት ድጋፍ መደረጉ የጌታ ወረዳ ሰራተኛና ማህበራዊ ልማት ጉዳዮች ጽህፈት ቤት ገለፀ

15/9/2018ዓ.ም(ቋንጤ)
ጽህፈትቤቱ ከቡርሐን ኢስላማዊ ድርጅት እና ከወረዳው እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት ጋር በመተባበር ለበርካታ አካል ጉዳተኞች እና ተረጂ የማህበረሰብ ክፍሎች የአልባሳት ድጋፍ ተደረገ ።

የጌታን ወረዳ ሰራተኛና ማህበራዊ ልማት ጽህፈት ቤት ሀላፊ ወ/ሮ ደስታ ገብሬ በበኩላቸው ተቋሙ ከተመሰረተ ጀምሮ በርካታ ድጋፎች እየሰራ እያደረገ ነዉ ብለዋል ።

የድርጅቱ ስራ አስጋጅ አቶ ቢላል ዘበርጋ በበኩላቸዉ የድርጅቱ አበይትና ጥልቅ ማህበረሰባዊ ስራዎች
​ቡርሓን እስላማዊ ድርጅት ከተመሰረተ ገና አንድ ዓመት ገደማ ቢሆነውም፣ በጉራጌ ዞን ጌታ ወረዳና በተለያዩ አካባቢዎች ያከናወናቸው ተግባራት ግን ከተቋቋመበት እድሜ በላይ እጅግ ግዙፍ፣ ጥልቅና ተአምራዊ ናቸው ብለዋል

ቡርሓን ኢስላማዊ ድርጅት​የነጻነት አዋጅ የወለደው፣ ለትውልድ ግንባታ የቆመ የለውጥ ብርሃን ነው ብለዉ በጌታ ወረዳ ለሚገኙ ከ370 በላይ ለሚሆኑ አቅመ-ደካማ ቤተሰቦችና የወላጅ አልባ (የየቲም) ህፃናት የተደረገው የበዓል ልብስ ድጋፍ የድርጅቱን ለቀጣይም በት/ት፣በጤና አጠናክረን እንቀጥላለን ብለዋል ።

​ይህ የበጎ አድራጎት ስራ የአንድ ጊዜ ብቻ ሳይሆን፣ በየዓመቱ ተጠቃሚ የሚሆኑ ሰዎችን ቁጥር በከፍተኛ ደረጃ እያሳደገ የሚቀጥል ዘላቂ ፕሮጀክት ነው ብለዉ ማህበረሰቡ የኢድአል አድሀ አረፋ በአልን ሲያከብር በመደጋገፍ ሊሆን ይገባል ብለዋል ።

እርዳታ የተደረገላቸው አካላት በበኩላቸው በተደረገላቸው ድጋፍ ተደስተው ድጋፉ ላደረጉላቸው አካላት አመስግነዋል ሲል የዘገባው የጌታ ወረዳ መ/ኮ/ጉ/ጽ/ቤት ነዉ።ለተጨማሪ መረጃዎች፦
https://t.me/+6-UPogtuRUM1YmU0
https://www.tiktok.com/.werda?_r=1&_d=e9bdl0cgjekh13&sec_uid=MS4wLjABAAAAwF7OIEYX7RB76QIqwzgMZgpHO_VjiSZQ4-E1i6jR0eWZqozqOvW0hw5M8ALgCT0V&share_author_id=7449340183399597061&sharer_language=en&source=h5_m&u_code=e9bdlei6573062×tamp=1778603343&user_id=7264799121750492165&sec_user_id=https://youtu.be/Aiz_lJ5Jkw0?si=AD9e1hhU3E

22/05/2026

ለዒደል-አድሃ አረፋ በዓል ከአዲስ አበባ ወደ ጉራጌ ዞን የምትመጡ እንግዶች ባስ የምታገኙባቸው አካባቢዎችን የጉራጌ ዞን መንገድ ትራንስፖርት መምሪያ ኃላፊ አቶ የህያ ሱልጣን ገልፀዋል፣

1. ገደባኖ ጉታዘር ወለኔ ወረዳ፡- ከአዲስ አበባ መነሻ ቦታ አየር ጤና ሳሚ ካፌ ፊትለፊት ታክሲ ተራ እና ሁለቱ ዋናው መነኻሪያዎች
Ø መሀል አምባ
Ø ኢንጌ
Ø ኮምቦል እና ሌሎቹም

2. ጉንችሬ፣ እኖር እና እኖር ኤነር መገር ወረዳ፡- ከአዲስ አበባ መነሻ ቦታ አየር ጤና ሳሚ ካፌ ፊትለፊት ታክሲ ተራ እና ሁለቱ ዋናው መነኻሪያዎች
Ø ጉንችሬ
Ø ወርቃት
Ø ጠረደ
Ø ጉስባጃይ
Ø ወይራ
Ø ሚቄ እና ሌሎቹም

3. ጉመርና አረቅጥ፡- ከአዲስ አበባ መነሻ ቦታ አየር ጤና ሳሚ ካፌ ፊትለፊት ታክሲ ተራ እና ሁለቱ ዋናው መነኻሪያዎች
Ø ቦሌ ማዞሪያ
Ø ቦሌ
Ø አረቅጥ
Ø ባድ
Ø ጀምቦሮ እና ሌሎቹም

4. ቸሃ እና እምድብር፡- ከአዲስ አበባ መነሻ ቦታ አየር ጤና ሳሚ ካፌ ፊትለፊት ታክሲ ተራ እና ሁለቱ ዋናው መነኻሪያዎች
Ø አፍጥር
Ø የፌቅጠረቅ
Ø እምድብር
Ø መገናሴ
Ø የጆካእ እና ሌሎቹም

5. እዣ እና አገና፡- ከአዲስ አበባ መነሻ ቦታ አየር ጤና ሳሚ ካፌ ፊትለፊት ታክሲ ተራ እና ሁለቱ ዋናው መነኻሪያዎች
Ø ቦዥባር
Ø ወርት
Ø አስታዘር
Ø አገና እና ሌሎቹም

6. ጌታ ወረዳ፡- ከአዲስ አበባ መነሻ ቦታ አየር ጤና ሳሚ ካፌ ፊትለፊት ታክሲ ተራ እና ሁለቱ ዋናው መነኻሪያዎች
Ø ቀቡል
Ø እስኩት
Ø ቋንጤ
Ø ቡራት እና ሌሎቹም

7. ሙህር አክሊል፡- ከአዲስ አበባ መነሻ ቦታ አየር ጤና ሳሚ ካፌ ፊትለፊት ታክሲ ተራ እና ሁለቱ ዋናው መነኻሪያዎች
Ø መዞር
Ø አበጀ
Ø ሀዋሪያት
Ø ቃያ ገበያ እና ሌሎቹም

8. ወልቂጤ እና አበሽጌ፡- ከአዲስ አበባ መነሻ ቦታ አየር ጤና ሳሚ ካፌ ፊትለፊት ታክሲ ተራ እና ሁለቱ ዋናው መነኻሪያዎች
Ø ወልቂጤና በዙሪያው ያሉ ቀበሌዎች
Ø ጣጤሳ

9. እንደጋኝ፡- ከአዲስ አበባ መነሻ ቦታ አየር ጤና ሳሚ ካፌ ፊትለፊት ታክሲ ተራ እና ሁለቱ ዋናው መነኻሪያዎች

መሆናቸውን ታውቆ ያልተካተቱ ቦታዎች ካሉ በተጠቀሱት የስምሪት መስመሮች ላይ ተዳብሎ ስምሪት የሚሰጥ መሆኑ ታውቆ ለማግጓዝ ዝግጁ እንዲሆን ይደረግ፡፡

የጥቆማ ስልክ
0940997733 (ሙሉጌታ ደሳለኝ)
0904023031(ሰለሞን ከድር)

መረጃው የጉራጌ ዞን መንገድ ትራንስፖርት መምሪያ ነው።

ለ1447ተኛው ዓመተ ሂጅራ የአረፋ በዓልን ምክኒያት በማድረግ ከአዲስ አበባ ወደ ጉራጌ ዞን የምትገቡ እንግዶቻችን ወደ ሃገር ቤት በምትመጡበት ወቅት ለርቀቱ የምትከፍሉትን የዋጋ ታሪፍ ከስር ...
22/05/2026

ለ1447ተኛው ዓመተ ሂጅራ የአረፋ በዓልን ምክኒያት በማድረግ ከአዲስ አበባ ወደ ጉራጌ ዞን የምትገቡ እንግዶቻችን ወደ ሃገር ቤት በምትመጡበት ወቅት ለርቀቱ የምትከፍሉትን የዋጋ ታሪፍ ከስር በተያያዘው ሰንጠረዥ ተቀምጧል!!

እባኮትን ለበዓል ከአዲስ አበባ ወደ ዞናችን ሲመጡ በህገ ወጥ ደላሎች ከታሪፍ በላይ እንዳይከፍሉ ይጠንቀቁ!!

#ከአዲስ አበባ መነሻ ቦታ አየር ጤና ሳሚ ካፌ ፊትለፊት ታክሲ ተራ እና ሁለቱ ዋናው መነኻሪያዎች ላይ ከግንቦት 16 ጀምሮ ባሶች ተዘጋጅተው ይጠብቋችኋል

ለበለጠ መረጃ

የጥቆማ ስልክ
0940997733 (ሙሉጌታ ደሳለኝ)
0904023031(ሰለሞን ከድር)

የጌታ ወረዳ ብልፅግና ፓርቲ ፅ/ቤት  የ7ኛው ዙር ሀገራዊ ምርጫ የክላስተሮችና የወረዳው የድጋፍ ሰልፍና የምርጫ ቅድመ ዝግጅት ከጠቅላላ የወረዳው አመራሮችና ከሁሉም ቀበሌ የመጡ ኮር አመራሮች...
22/05/2026

የጌታ ወረዳ ብልፅግና ፓርቲ ፅ/ቤት የ7ኛው ዙር ሀገራዊ ምርጫ የክላስተሮችና የወረዳው የድጋፍ ሰልፍና የምርጫ ቅድመ ዝግጅት ከጠቅላላ የወረዳው አመራሮችና ከሁሉም ቀበሌ የመጡ ኮር አመራሮች ጋር ውይይት አካሄደ።

‎ግንቦት 14/09/2018(ቋንጤ)

‎የጌታ ወረዳ ብልፅግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት አጠቃላይ በክላስተርና በወረዳው የተደረጉ የድጋፍ ሰልፎችና የምርጫ ቅድመ ዝግጅት ያለበት ሁኔታ የሚያሳይ ውይይት በቋንጤ ከተማ አካሂዷል።

‎የወረዳው ፓርቲ ጽ/ቤት ባለፉት ቀናት በ4 ክላስተሮች የብልፅግና ፓርቲ አባላትና ደጋፊዎች የ7ኛው ጠቅላላ ምርጫ መወዳደሪያ ምልክት፣ ማኒፌስቶና በምርጫ ክልሉ የሚወዳደሩ ዕጩዎችን የማስተዋወቅና የቅስቀሳ መርሐ-ግብር ማካሄዱ ይታወቃል።

እነዚህ መድረኮችና በቋንጤ ከተማ የተካሄደው ታላቅ ህዝባዊ የድጋፍ ሰልፍ አፈፃፀም የወረዳና የቀበሌ አመራሮች በተገኙበት በጥልቀት ተገምግማል።

የፓርቲው አባልና ደጋፊዎች በእነዚህ መድረኮችና የድጋፍ ሰልፍ ወቅት ያሳየው ስነ-ምግባርና ፍፁም የሆነ ድጋፍ ልዩ እንደነበር የተገለፀ ሲሆን በቀጣይም ህዝቡ በነቂስ በመውጣት በምርጫው እለት በጊዜ ወጥቶ ድምፁን እንዲሰጥ ማድረግ ያስፈልጋል ተብሏል።

በመድረኩም የወረዳው ዋና አስተዳዳሪ አቶ በህሩ ኸይረዲንና የወረዳው ብልፅግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ሀላፊ አቶ ዘውዱ ዘፕሬን ጨምሮ አጠቃላይ የወረዳ አመራርና የቀበሌ ኮር አመራሮች ተገኝተዋል ሲል የዘገባው የጌታ ወረዳ መንግስት ኮምኒኬሽን ጉዳዮች ጽ/ቤት ነዉ።

‎ለተጨማሪ መረጃዎች፦
https://t.me/+6-UPogtuRUM1YmU0
https://www.tiktok.com/.werda?_r=1&_d=e9bdl0cgjekh13&sec_uid=MS4wLjABAAAAwF7OIEYX7RB76QIqwzgMZgpHO_VjiSZQ4-E1i6jR0eWZqozqOvW0hw5M8ALgCT0V&share_author_id=7449340183399597061&sharer_language=en&source=h5_m&u_code=e9bdlei6573062×tamp=1778603343&user_id=7264799121750492165&sec_user_id=https://youtu.be/Aiz_lJ5Jkw0?si=AD9e1hhU3E

7ኛው ሀገራዊ ምርጫ ፍጹም ሰላማዊ፣ ዴሞክራሲያዊና ተአማኒነት ያለው ሆኖ በስኬት እንዲጠናቀቅ የጸጥታ አካላ በትጋት መስራ እንደሚገባ የጌታ ወረዳ ሚልሻ ጽህፈት ቤት አሳሰበ ።14/9/2018ዓ...
22/05/2026

7ኛው ሀገራዊ ምርጫ ፍጹም ሰላማዊ፣ ዴሞክራሲያዊና ተአማኒነት ያለው ሆኖ በስኬት እንዲጠናቀቅ የጸጥታ አካላ በትጋት መስራ እንደሚገባ የጌታ ወረዳ ሚልሻ ጽህፈት ቤት አሳሰበ ።

14/9/2018ዓ.ም(ቋንጤ )
ጽህፈት ቤቱ የ2018ዓ.ም ሀገራዊምርጫና የአረፋ በአልን አስመልክቶ ለፀጥታ አካላት የስልጠና እና የስምሪት መድረክ በቋንጤ ከተማ ተካሄደ ።

በስልጠናው መድረክ የተገኙት የወረዳው ምክትል አስተዳዳሪ እና ትምህርት ጽህፈት ቤት ሀላፊ አቶ ሀብቱ ወ/የሱስ በበኩላቸው ከፊታችን ያለው ምርጫ ፍጹም ሰላም እንዲሆን የፀጥታ አካላት ሚና ከፍተኛ ነው ብለዉ ስራቸውን በተገቢው መስራት አለባቸው ብለዋል

አቶ ሀብቱ አያይዘውም ሚሊሻ በምርጫው ሂደት ምርጫውን ነፃና ዲሞክራሲያዊ ከማድረግ አንፃር ወሳኝ ሚና እንዳለው አንስተው ተጋግዞ መስራት እንደሚገባ አሳስበዋል ።

የጌታ ወረዳ ሚልሻ ጽህፈት ቤት ሀላፊ አቶ መላኩ ሀብቴ ሚልሻ ለህገመንግስት ታማኝና በህገ መንግስት መሰረት የሚወጡ ህጎች ተገዢ የሆነ ለሙያው በቂ የሆነ ስልጠና የተሰጠው ብቃት ያለው አካል ነው ብለዋል ።

አያይዘውም ሚሊሻ ለህዝብ አገልጋይ ሰብአዊና ዴሞክራሲያዊ መብቶች የሚያስከብርና የሚያስከብር የህዝብ ሰላም የሚያረጋግጥ ሀይል መሆኑ አስገንዝበዋል ።

ይህን ታላቅ ሀይል ከፊታችን ያለዉ ሀገራዊ ምርጫ እና 1447ኛዉ የኢድአል አድሀ አረፋ በአል በሰላም እንዲጠናቀቅ የበኩላቸውን አስተዋጽኦ እንዲያደርጉ ም አሳስበዋል

የዲሞክራሲያዊ ምርጫና የምርጫ ሂደት የህዝብ ልዋላዊነት ማረጋገጫ ነው ብለዉ ፍጹም ሰላማዊ እንዲሆን የፀጥታ አካላት በተገቢው መስራት ይኖርባቸዋል ያሉት ደግሞ የወረዳው ምክትል ኢንስፔክተር ደምስ በርታ ናቸዉ ።

የበአል ከከተማ ወደ ቄዉ የሚገቡ የወረዳዉ ተወላጆች በአሉን በሰላም እንዲያከብሩ ሁሉንም የፀጥታ አካላት በትኩረት ሊሰሩ ይገባል ብለዋል ።

አክለዉም የምርጫ እቃዎች አጠባበቅ አንጻር ስር በስር መጠበቅ እንደሚገባ አንስተው ሰራዊቱ ለሁሉም ነገር መዘጋጀት አለበትም ብለዋል ።

ተሳታፊዎች በበኩላቸው 7ተኛዉ ሀገራዊ ምርጫና 1447ኛዉ የኢድአል አድሀ አረፋ በአል በሰላም እንዲጠናቀቅ የበኩላቸውን እንደሚወጣም ተናግሯል ። ዘገባው የወረዳው መ/ኮ/ጉ/ጽ/ቤት ነው ።

‎ለተጨማሪ መረጃዎች፦
https://t.me/+6-UPogtuRUM1YmU0
https://www.tiktok.com/.werda?_r=1&_d=e9bdl0cgjekh13&sec_uid=MS4wLjABAAAAwF7OIEYX7RB76QIqwzgMZgpHO_VjiSZQ4-E1i6jR0eWZqozqOvW0hw5M8ALgCT0V&share_author_id=7449340183399597061&sharer_language=en&source=h5_m&u_code=e9bdlei6573062×tamp=1778603343&user_id=7264799121750492165&sec_user_id=https://youtu.be/Aiz_lJ5Jkw0?si=AD9e1hhU3E

በወረዳችን የተጀመሩ የልማት ስራዎች ሊቀጥሉ የሚችሉት 7ተኛው ጠቅላላ ምርጫ በሰላማዊ መንገድ ሲጠናቀቅ ነው ሲሉ የጌታ ወረዳ ነዋሪዎች ገለጹ።ግንቦት 13/2018(ቋንጤ)በጉራጌ ዞን ጌታ ወረዳ...
21/05/2026

በወረዳችን የተጀመሩ የልማት ስራዎች ሊቀጥሉ የሚችሉት 7ተኛው ጠቅላላ ምርጫ በሰላማዊ መንገድ ሲጠናቀቅ ነው ሲሉ የጌታ ወረዳ ነዋሪዎች ገለጹ።

ግንቦት 13/2018(ቋንጤ)

በጉራጌ ዞን ጌታ ወረዳ ሀገራዊ ለውጡ እውን የሆነበትን 8ኛ ዓመትና ሰባተኛውን ሀገራዊ ጠቅላላ ምርጫ በማስመልከት የብልጽግና ፓርቲ የድጋፍ ሰልፍ በቋንጤ ከተማ ተካሂዷል።

በምርጫ ዜጎች የራሳቸውን ድምፅ በመስጠት በሀገራቸው ፖለቲካ ላይ እንዲሳተፉ ምቹ እድል ይፈጥራል።

ትክክለኛ እና ፍትሃዊ ምርጫ ለሰላም፣ ለእድገት እና ለመንግስታዊ እምነት መጠናከር በጣም አስፈላጊ ሲሆን ዜጎች የሚወክላቸውን እጩ የሚመርጡበት የዲሞክራሲ ግንባታ ማሳያ ነው።

በመሆኑም 7ኛው ሀገራዊ ምርጫ ሰላማዊና ዲሞክራሲያዊ ሆኖ እንዲጠናቀቅ አበክረን እንሰራለን ሲሉ በጉራጌ ዞን የጌታ ወረዳ የህብረተሰብ ክፍሎች ተናግረዋል።

አቶ ታረቀኝ ገብሬ፣አቶ ኑር ሰፋ ቢረዳ፣አቶ ተመስገን ንዳና አማን አውል የጌታ ወረዳ ነዋሪዎች ሲሆኑ በሰጡት ሀሳብ የዘንድሮ ምርጫው ሰላማዊ እንዲሆንና ድምጻችን ለመረጥነው ፓርቲ ለመስጠት ተዘጋጅተናል ብለዋል።

ህብረተሰቡ በሀገሪቱ በቅርቡ በሚካሄደው 7ኛ ሀገራዊ ጠቅላላ ምርጫ ካርድ ከመውሰድ ባሻገር ማህበረሰቡ ስለ ምርጫው ምንነትና አስፈላጊነት በቂ ግንዛቤ እንዲኖረው የበኩላቸው ሚና እየተወጡ መሆናቸውን ተናግረዋል።

የወጣቶች ተሳትፎ በምርጫ ሂደት ውስጥ እጅግ ጠቃሚ ሲሆን ወጣቶች በንቃት በመሳተፍ የሀገራቸውን የወደፊት አቅጣጫ ሊያስወስኑ እንደሚገባ የቀበሌው ነዋሪዎች አመላክተዋል።

በወረዳው ሁለንተናዊ ልማት ላይ ውይይቶችን ማጠናከር፣ቅንጅታዊ አሰራር ማስፈን፣ባለሀብቱን በልማት ማሳተፍ ይገባል ሲሉ አንስተዋል።

ሀሳብ ሰጪዎቹ አክለውም ከቅርብ ጊዜ ጀምሮ በወረዳው እየተሰሩ ያሉ የልማት ስራዎች አድንቀው በሁሉም ዘርፍ ማህበረሰቡን ተጠቃሚ የሚያደርጉ ስራዎች መሰራታቸው ጠቁመዋል።

ስለሆነም ምርጫው በተቀመጠለት የጊዜ ገደብ ያለምንም የፀጥታ ችግር በሰላም እንዲጠናቀቅ እና ለመራጭነት የተመዘገበ ህዝብ በሙሉ ካርዱን ሳይባክን የሚወክለውን ተወዳዳሪ መምረጥ ይጠበቅበታል ብለዋል።

በቀጣይ በቀበሌያቸው የጀመሯቸው የማህበረሰቡን ተጠቃሚነት የሚያረጋግጡ የልማት ስራዎች ተጠናክረው እንዲቀጥሉ ጠይቀው እነሱም የበኩላቸው እንደሚወጡ ተናግረዋል።

‎ለተጨማሪ መረጃዎች፦
https://t.me/+6-UPogtuRUM1YmU0
https://www.tiktok.com/.werda?_r=1&_d=e9bdl0cgjekh13&sec_uid=MS4wLjABAAAAwF7OIEYX7RB76QIqwzgMZgpHO_VjiSZQ4-E1i6jR0eWZqozqOvW0hw5M8ALgCT0V&share_author_id=7449340183399597061&sharer_language=en&source=h5_m&u_code=e9bdlei6573062×tamp=1778603343&user_id=7264799121750492165&sec_user_id=https://youtu.be/Aiz_lJ5Jkw0?si=AD9e1hhU3E

Address

Geta
Wolkite

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when በጉራጌ ዞን የጌታ ወረዳ የመንግስት ኮምንኬሽን ጉ/ጽ/ቤት posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Share