14/03/2026
4/7/2018 ዓ.ም
አለም አቀፍ የሴቶች ቀን (ማርች 8) ተከበረ።
የሴቶች ቀን (ማርች 8) በዓለም ለ115ኛ በኢትዮጵያ ደግሞ ለ50ኛ ጊዜ " የሴቶች ድምፅ ለእኩልነትና ለበለፀገች ኢትዮጵያ" በሚል መሪ ቃል በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ዋና ኦዲተር መስሪያ ቤት ተከብሯል ።
ወ/ሮ ገነት ደምስ የመስሪያ ቤቱ የሴቶችና ህጻናት ጉዳዮች ተወካይ ዓለም አቀፍ የሴቶች ቀን መከበር ሴቶች በተዛቡ አመለካከቶች የተነሳ የሚደርሱባቸውን ልዩ ልዩ ጥቃቶች በመታገል ፍትህ ፣ሰላም ፣ልማትና ሁሉ አቀፍ የሆነ እድገትና ተጠቃሚነት እንዲረጋገጥ ያስቻለ ንቅናቄ እንደሆነ ገልፀዋል።
በሀገራችን ሴቶች የሚያገል የጭቆና ጊዜያቶች የተሻገርን ቢሆንም አሁንም ቢሆን ህግን ከማስከበር አንፃር ,የውሳኔ ሰጭነት ጉዳይ ትኩረት ሊሰጠው እንደሚገባ ተናግረዋል።
ከዚህ ቀደም የነበሩ ሴቶች የሚደርስባቸውን ዘርፈ ብዙ ጥቃትና ችግሮች በመቋቋም አሁን ላይ የመጡ ለውጦች ማስቀጠልበቀጣይም ሁለንተናዊ ተሳትፏቸውን ለማሳደግ መረባረብ ይገባልም ሲሉ ተሳታፊዎች ሀሳባቸውን ገልፀዋል።