Central Ethiopia Water,Irrigation and Mine Bureau

Central Ethiopia  Water,Irrigation and Mine  Bureau Contact information, map and directions, contact form, opening hours, services, ratings, photos, videos and announcements from Central Ethiopia Water,Irrigation and Mine Bureau, Government Organization, Wolkite.

በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል በተለያዩ ከተሞች  የመሰረተ ልማት አውታሮች ተደራሽነት አፈጻጸም ላይ ያተኮረ የምክክር መድረክ ተካሄደ መስከረም 6/2019)በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል  የኢትዮጵያ ...
16/09/2026

በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል በተለያዩ ከተሞች የመሰረተ ልማት አውታሮች ተደራሽነት አፈጻጸም ላይ ያተኮረ የምክክር መድረክ ተካሄደ

መስከረም 6/2019)በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል አገልግሎት እና በኢትዮ ቴሌኮም ተቋማት አፈጻጸም ላይ ያተኮረ መድረክ በዱራሜ፣በወራቤ፣በሀላባ፣እና በሳጃ ከተሞች ተካሂዷል።

የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ርዕሰ መስተዳደር ልዩ አማካሪ ንጉሴ አስረስ (ዶ/ር) እንደተናገሩት፣ የኃይል እጥረትና መቆራረጥ በከተሞች ዲጂታል ትራንስፎርሜሽንና ልማት ትልቅ ማነቆ መሆኑን ገልጸው፣ ችግሩን በዘላቂነት ለመፍታት የተቀመጡ አቅጣጫዎችን አስተላልፈዋል።

የመሰረተ ልማት አውታሮችን ከስርቆትና ውድመት የመጠበቅ፣ በየደረጃው ከህብረተሰቡና ከአመራሩ ጋር የውይይት መድረኮችን የማመቻቸት እንዲሁም በኤሌክትሪክ መስመሮች ላይ ተግዳሮት የሆኑ ዛፎችን በኮማንድ ፖስት አስተባባሪነት እልባት መስጠት እንደሚገባም ጠቅሰዋል።

የተቃጠሉ ትራንስፎርመሮችን የመተካት፣ አገልግሎቱን አስተማማኝ ለማድረግ የሚያስችሉ የቅድመ ጥገና ሥራዎችን የማከናወን እና የኃይል መቆራረጥ ችግሮችን መፍታት የሚያስችል መድረክ መሆኑንም አብራርተዋል።

ከኢትዮ ቴሌኮም የአገልግሎት ጥራትንና ተደራሽነትን ከማረጋገጥ አንጻር ተቋሙ የኔትዎርክ መሠረተ ልማቶችን ደረጃ የማስፋፋትና የማሻሻል ተግባራት ላይ በትኩረት እየሰራ እንደሚገኝ ተጠቁሟል።

በተለይም በከፍተኛ ሁኔታ እየጨመረ የመጣውን የደንበኞች ቁጥርና የዳታ ፍላጎት ለማስተናገድ የሚከናወኑ የኔትዎርክ አቅም ማሳደጊያ ሥራዎች፣ የትራፊክ መጨናነቅ በሚበዛባቸው አካባቢዎች የሚፈጠሩ የአገልግሎት መቋረጦችንና የጥራት መውደቅን በዘላቂነት መፍታት የሚያስችል መድረክ መሆኑም ተመላክቷል።

የክልሉ መንግስት ኮምኒኬሽን

የሴቶችና ህፃናትን ሁለንተናዊ ተጠቃሚነት ይበልጥ ለማረጋገጥ አደረጃጀቶችን ማብቃት ይገባል :-ምክትል ርዕሰ መስተዳድር አንተነህ ፈቃዱ( መስከረም 6/2019) የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ሴቶች...
16/09/2026

የሴቶችና ህፃናትን ሁለንተናዊ ተጠቃሚነት ይበልጥ ለማረጋገጥ አደረጃጀቶችን ማብቃት ይገባል :-ምክትል ርዕሰ መስተዳድር አንተነህ ፈቃዱ

( መስከረም 6/2019) የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ሴቶችና ህፃናት ጉዳይ ቢሮ ''የተቀናጀ አቅም ፣የተረጋገጠ እኩልነት ለሴቶችና ህፃናት ብሩህ ነገ !'' በሚል መሪ ቃል ሴክቶራያል ጉባኤውን በወራቤ ከተማ አካሂዷል።

ቢሮው በ2018 በጀት አፈፃፀምና በ2019 በጀት ዓመት እቅድ ላይ ከባለድርሻ አካላት ጋር መክሯል።

የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ምክትል ርዕሰ መስተዳድር ፣የማህበራዊ ክላስተር አስተባባሪና የትምህርት ቢሮ ኃላፊ አቶ አንተነህ ፈቃዱ ባስተላለፉት መልዕክት የሴቶችና ህፃናትን ሁለንተናዊ ተጠቃሚነት ይበልጥ ለማረጋገጥ የአደረጀጀቶችን አሰራር ዲጂታላይዝ በማድረግ በእውቀትና በክህሎት ማብቃት ይገባል ብለዋል።

በፆታዊ ጥቃትና ጎጂ ልማዳዊ ድርጊት ላይ የሀይማኖት ተቋማትን በማሳተፍ ይበልጥ መስራት ይገባል ያሉት ምክትል ርዕሰ መስተዳድሩ ያለዕድሜ ጋብቻና የሴት ልጅ ግርዛት ነፃ የሆኑ ቀበሌያትን ለመፍጠር የተጀመረው ስራ መጠናከር አለበት ሲሉም አክለዋል።

የሴቶች አደረጃጀት ከ1 ቢሊዮን ብር በላይ እንዲቆጥቡ በማድረግ ኢኮኖሚያዊ ተጠቃሚነታቸውን ለማረጋገጥ የተሰራው ስራ አበረታች መሆኑን ያነሱት ምክትል ርዕሰ መስተዳድሩ የሴቶች ልማት ህብረት ለክልሉ ሁለንተናዊ ዕድገት ትልቅ አቅም በመሆናቸው በሁሉም የልማት አቅጣጫ ማሳተፍ እንደሚገባ አመላክተዋል።

ህገወጥ ፍልሰትን ለመከላከል በቅንጅት መስራት ይገባል ያሉት አቶ አንተነህ በውጭ ሀገር የስራ ዕድልም ቢሆን ተወዳዳሪና የተሻለ ተጠቃሚ እንዲሆኑ አስቀድሞ ማብቃት እንደሚገባ ተናግረዋል።

ለሀገር ግንባታና ለትውልድ ቀረፃ የሴቶች አበርክቶ የላቀ በመሆኑ በቀጣይም ተሳትፎና ተጠቃሚነታቸውን በሁሉም ዘርፍ ማረጋገጥ እንደሚያስፈልግ ገልፀዋል።

የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ሴቶችና ህፃናት ጉዳይ ቢሮ ሀላፊ ወይዘሮ ዘቢባ መሀመድናስር እንደገለፁት መንግስት የሴቶችንና ህፃናትን ሁለንተናዊ ተሳታፊነትና ተጠቃሚነትን ለማረጋገጥ እንዲሁም መብትና ደህንነትን ለማስጠበቅ ህጎችንና ደንቦችን በማውጣትና መዋቅራዊ አሰራሮችን በማጠናከር በርካታ ተግባራትን እያከናወነ ይገኛል ብለዋል።

የባለድርሻ አካላት ሚና በማላቅና ለዘርፍ ተገቢውን ትኩረት በመስጠት የሴቶችንና ህፃናትን ኢኮኖሚያዊ፣ማህበራዊና ፓለቲካዊ ተሳትፎና ተጠቃሚነትን ማረጋገጥ ተችሏል ብለዋል።

የገበያ ትስስር በመፍጠር፣ ሴቶችን በማስቆጠብ፣ የተለያዩ ድጋፎችን በማድረግና ህጻናት የፈጠራ ስራዎቻቸውን እንዲያወጡ በማድረግ ተወዳዳሪ ማድረግ ተችሏል።

የሀገራችንንና የክልሉን ሁለንተናዊ ብልጽግና እውን ለማድረግ የሴቶች አደረጃጀት ይበልጥ ማጠናከር ይገባል ያሉት ወይዘሮ ዘቢባ የሴቶች ልማት ህብረት መረጃን ዲጂታላይዝ በማድረግ ወደ ዳታ ቤዝ የማስገባት ስራ በትኩረት እየተሰራ ይገኛል ብለዋል።

በሴቶችና ህፃናት ላይ የሚፈፀሙ ፆታዊ ጥቃቶችንና ጎጂ ልማዳዊ ድርጊቶችን በተቀናጀ መልኩ የመከላከል ስራ እየተሰራ መሆኑን የተናገሩት ሀላፊዋ ጥቃት የደረሰባቸው ሴቶችና ህጻናት የአንድ ማዕከል አገልግሎት እንድያገኙ የማድረግ እንዲሁም ነባር አንድ ማዕከሎችን የማጠናከር ስራ በልዩ ትኩረት እየተሰራም ነው ብለዋል።

መድረኩ ቀጣይ ጥንካሬዎችን በማስቀጠል ውስንነቶች በጋራ ማረም የሚያስችል መግባባት የተፈጠረበት መሆኑን ተናግረው ሴቶችን በስልጠና የማብቃትና በየደረጃው ድጋፍ የማድረግ ስራው ተጠናክሮ የሚሰራ መሆኑን ተናግረዋል።

የመድረኩ ተሳታፊዎች በሰጡት አስተያየት የሴቶች ሁለንተናዊ ተጠቃሚነት ላይ አበረታች ውጤቶች መመዝገባቸውን ገልፀው አሁንም በየአካባቢው የሚስተዋሉ ያለአቻ ጋብቻና የሴት ልጅ ግርዛት ላይ በቁርጠኝነት መስራት እንደሚጠበቅ ተናግረዋል።

ቢሮው የላቀ አፈፃፀም ላስመዘገቡ ለዞኖች፣ለልዩ ወረዳ እና ባለድርሻ አካላት የእውቅናና ሰርተፍኬት ሽልማት አበርክቷል።

የክልሉ መንግስት ኮምኒኬሽን

የብሔራዊ አንድ ቋት ፕሮግራም የጋራ ግምገማ ተካሄደመስከረም 4/2019 ዓ.ም. (ው.ኢ.ሚ) — በውሃና ኢነርጂ ሚኒስቴር እየተተገበረ የሚገኘው የብሔራዊ አንድ ቋት ፕሮግራም (One WASH N...
14/09/2026

የብሔራዊ አንድ ቋት ፕሮግራም የጋራ ግምገማ ተካሄደ

መስከረም 4/2019 ዓ.ም. (ው.ኢ.ሚ) — በውሃና ኢነርጂ ሚኒስቴር እየተተገበረ የሚገኘው የብሔራዊ አንድ ቋት ፕሮግራም (One WASH National Program) የማስጀመሪያ የጋራ ግምገማ መድረክ ተካሄደ።

በጋራ ግምገማው ላይ የመጠጥ ውሃና ሳኒቴሽን ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታ ክቡር አምባሳደር ዶ/ር አስፋው ዲንጋሞ ተገኝተው የፕሮግራሙን አፈጻጸም፣ ያስመዘገበውን እድገት እና በቀጣይ ሊሰራባቸው የሚገቡ ጉዳዮችን አስመልክተው ንግግር አድርገዋል።

አምባሳደር ዶ/ር አስፋው በንግግራቸው፣ ፕሮግራሙ ከጊዜ ወደ ጊዜ መሻሻልና የተሻለ አፈጻጸም እያሳየ መምጣቱን ገልጸዋል። ይህም ከአጋር ድርጅቶች ጋር የተጠናከረ ቅንጅትና ትብብር በመኖሩ የተገኘ ውጤት መሆኑን አመልክተዋል።

በመድረኩ የፕሮግራሙ አስተባባሪ አቶ አብይ ግርማ የፕሮግራሙን አፈጻጸም በዝርዝር አቅርበዋል። በተጨማሪም ፕሮግራሙ በቀጣይ የሚያተኩርባቸውን ዋና ዋና ጉዳዮች አብራርተዋል።

የጋራ ግምገማው በፕሮግራሙ አፈጻጸም የተመዘገቡ ውጤቶችን፣ ያጋጠሙ ተግዳሮቶችን እና በቀጣይ ትኩረት ሊሰጣቸው የሚገቡ ጉዳዮችን በጋራ በመወያየት የፕሮግራሙን አፈጻጸም የበለጠ ለማጠናከር ያለመ መሆኑ ተገልጿል።

በመድረኩ ከአጋር ድርጅቶች፣ ከሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ ባለሙያዎች እንዲሁም ከጤናና ትምህርት ሚኒስቴሮች የተውጣጡ የፕሮግራሙ አስፈጻሚዎች ተሳትፈዋል። ተሳታፊዎቹም በፕሮግራሙ አፈጻጸም፣ በተገኙ ውጤቶች፣ በተግዳሮቶች እና በቀጣይ የሚያስፈልጉ የሥራ አቅጣጫዎች ላይ ጠቃሚ ሀሳቦችና አስተያየቶችን አቅርበዋል።

የጋራ ግምገማው በተለያዩ አካላት መካከል ያለውን ቅንጅትና ትብብር በማጠናከር፣ የተገኙ ውጤቶችን በመገምገም እና ያሉ ተግዳሮቶችን በጋራ በመፍታት የብሔራዊ አንድ ቋት ፕሮግራምን የበለጠ ውጤታማና ዘላቂ ለማድረግ ጠንካራ መሠረት የሚጥል መሆኑ ተገልጿል።

ው/ኢ/ሚ

ታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ የኃይል አቅርቦቱን በእጥፍ በማሳደግ የቀጣናውን የኢኮኖሚና የኃይል ትስስር እያጠናከረ ነውመስከረም 4፣ 2019 (ኤፍ ኤም ሲ) ታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ የሀ...
14/09/2026

ታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ የኃይል አቅርቦቱን በእጥፍ በማሳደግ የቀጣናውን የኢኮኖሚና የኃይል ትስስር እያጠናከረ ነው

መስከረም 4፣ 2019 (ኤፍ ኤም ሲ) ታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ የሀገሪቱን የኤሌክትሪክ ኃይል አቅርቦት ከእጥፍ በላይ ከማሳደግ ባለፈ የቀጣናውን የኃይል ትስስር እያጠናከረ ነው አሉ የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል ዋና ሥራ አስፈጻሚ ኢንጂነር አሸብር ባልቻ፡፡

ዋና ሥራ አስፈጻሚው እንደገለጹት፤ ታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ የኢትዮጵያውያን ጽናት፣ አንድነትና ቁርጠኝነት በተግባር የተገለጠበት ዳግማዊ ዓድዋ ነው፡፡

የግድቡ ግንባታ ኢትዮጵያ በራሷ አቅም የላቀ ስኬት ማስመዝገብ እንደምትችል ለዓለም ያስመሰከረችበት፤ ብሎም አዲስ የታሪክ ምዕራፍ የከፈተ ታላቅ ፕሮጀክት ነው ማለታቸውን ኢዜ ዘግቧል፡፡

ግድቡ ተመርቆ ወደ ሙሉ ሥራ ከገባበት ጊዜ ጀምሮ የሀገሪቱን የኃይል ማመንጨት አቅም በእጥፍ ከመጨመሩም በላይ፤ ኢትዮጵያ ከዘርፉ የምታገኘውን የውጭ ምንዛሬ ገቢ በእጅጉ ማሳደጉን ገልጸዋል።

ኢትዮጵያ፤ ፈተናን ወደ ዕድል ቀይራ ወደ ከፍታ የምትጓዝ ሀገርየአንድ ሀገር እውነተኛ አቅም የሚለካው በተመቻቸ ሁኔታ ውስጥ በሚታለም ህልም ሳይሆን፤ በፈተናዎች መካከል ተስፋን ሰንቆ የዕድል ...
12/09/2026

ኢትዮጵያ፤ ፈተናን ወደ ዕድል ቀይራ ወደ ከፍታ የምትጓዝ ሀገር

የአንድ ሀገር እውነተኛ አቅም የሚለካው በተመቻቸ ሁኔታ ውስጥ በሚታለም ህልም ሳይሆን፤ በፈተናዎች መካከል ተስፋን ሰንቆ የዕድል መንገዶችን በመጥረግ በሚደረግ የጽናት ጉዞ ነው።

የታሪክና የጽናት ምድር የሆነችው ኢትዮጵያም በተደራራቢ የኢኮኖሚ፣ የማኅበራዊና የልማት ፈተናዎች ማዕበል ውስጥ አልፋ፤ የመዋቅራዊና የዘርፍ ማሻሻያዎችን መሠረት በመጣል የዕድገት መንገዷን በአዲስ መንፈስ እያደሰች ትገኛለች።

ይህ የትራንስፎርሜሽን ጉዞ የአንድ ዘርፍ ጊዜያዊ ስኬት ሳይሆን፤ በግብርና፣ በማዕድን፣ በኃይል፣ በዲጂታል ኢኮኖሚና በግሉ ዘርፍ ንቁ ተሳትፎ የሚታይ ሁለገብ እና ሰፊ የለውጥ ጉዞ ነው።

እንደ ዓለም አቀፉ የገንዘብ ድርጅት እና የዓለም ባንክ ገለጻ፤ ኢትዮጵያ ከፈረንጆቹ 2024 ጀምሮ ያስጀመረቻቸው ሁለገብ ሀገር በቀል የኢኮኖሚ ማሻሻያዎች ዘርፈ ብዙ ውጤት በማምጣት የፋይናንስ ዘርፉን ያጠናከሩ ናቸው።

እነዚህ መዋቅራዊ ማሻሻያዎች የውጭ ምንዛሬ እጥረትን በመቅረፍ የወጪ ንግድን ማደራጀት መቻላቸውንም ተቋማቱ በመረጃቸው ገልጸዋል።

በተጨማሪም የመንግሥትን የሀገር ውስጥ ገቢ የማሰባሰብ አቅም ማሳደግ፣ የወጪ ንግድ አፈጻጸምን ማሻሻል፣ የውጭ ምንዛሬ መጠባበቂያዎችን ማሳደግና የግሉ ዘርፍ የኢንቨስትመንት አቅምን ማጠናከር ላይ አዎንታዊ ውጤቶች እየታዩ ነው።

ከማክሮ ኢኮኖሚው ጎን ለጎን፣ በትራንስፖርትና በኃይል ማመንጨት ዘርፎች እየተከናወኑ ያሉ የነዳጅ ድጎማ ማሻሻያዎች እና የታዳሽ ኃይል ኢንቨስትመንቶች ለሀገሪቱ የረጅም ጊዜ ዕድገት ጠንካራ መሠረት እየጣሉ ነው።

በተመሳሳይ የዲጂታል ሽግግሩ ኢኮኖሚውን ከባህላዊ አሠራር ወደ ቴክኖሎጂ ተኮር አሰራር እያሸጋገረ ይገኛል።

በዚህም የዲጂታል ኢኮኖሚ ዕድገትን፣ የኢንዱስትሪ ማምረትን፣ የማዕድን ቁፋሮንና የግብርና ምርታማነትን እንደ ቀዳሚ የልማት ዘርፎች በማስቀመጥ አዳዲስ አቅሞችን ፈጥሯል።

ይሁንና ይህን የተገኘ አዎንታዊ የዕድገት እንቅስቃሴ ወደ ዘላቂ እና ሁሉን አቀፍ ብልጽግና ለመቀየር ሰፊ የሥራ ዕድል ፈጠራ፣ የሰው ኃይል ልማት፣ የግሉ ዘርፍ ንቁ ተሳትፎ፣ የምርታማነት ማደግና የዜጎች የኑሮ ደረጃ ማሻሻል ወሳኝ ይሆናሉ።(ኤፍ.ኤም.ሲ)

የርዕሰ መስተዳድር እንዳሻው ጣሰው (ዶ/ር) የአዲስ አመት እንኳን አደረሳችሁ መልዕክት፣"እንኳን ለዘመን መለወጫ በዓል በሠላም አደረሳችሁ! አደረሰን !ለመላዉ የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ሕዝቦ...
10/09/2026

የርዕሰ መስተዳድር እንዳሻው ጣሰው (ዶ/ር) የአዲስ አመት እንኳን አደረሳችሁ መልዕክት፣

"እንኳን ለዘመን መለወጫ በዓል በሠላም አደረሳችሁ! አደረሰን !

ለመላዉ የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ሕዝቦች እና ለመላዉ ኢትዮጵያውያን ፣ እንኳን ለ2019 አዲስ ዓመት የዘመን መለወጫ በዓል በሠላም አደረሳችሁ! አደረሰን ! በማለት የመልካም ምኞት መልዕክቴን በአክብሮት አቀርባለሁ።

የዘመን መለወጫ በዓል ፣ከአሮጌዉ ዓመት ወደ አዲስ ዓመት መሸጋገራችንን ማብሰሪያ ብቻ ሳይሆን ፣አዳዲስ ዉጤቶችን የመጨበጥ ጉጉትን የሚያስተጋባ ፣ የተስፋና የመነቃቃት መንፈስን ከፍ የሚያደርግ ነዉ።

የአዲስ ዓመት ማብሰሪያ በሆነዉ በወረሃ መስከረም፣ ምድሩም ተጨማሪ የዉበት ሸማ ይደርባል_በአደይ አበባ ይፈካል፤ይደምቃል፤ ማሳዎችን የሸፈነዉ ምርትም በአይን እይታ ያጠግባል።ይህ ድባብም ለዜጎች የሐሴትና የተስፋ መንፈስ ያጎናጽፋል።

የዘመን መለወጫ በዓል ከትዉፊታዊ እና ማህበራዊ እሴቶቹ ባሻገር፣በግለሰብ፣ በቤተሰብ፣ በቡድን፣በተቋም እና በሀገር ደረጃ ባለፋዉ ዓመት ያመለጡ ዕድሎችን ለማካካስ፣ ለአዳዲስ ውጤቶችም ለመትጋት የብርታትና የጽናት መንፈስ ከፍ የሚልበት ነዉ። በመሆኑም በአዲሱ ዓመት ዉስንነቶችን ለማረም፣ አዳዲስ ዉጤቶችን ለመጨበጥ የትጋትና የብርታት ወኔ ደርበን መንቀሳቀስ ይኖርብናል።

የዘንድሮዉን የዘመን መለወጫ በዓል እያከበርን የምንገኘው ፣ሀገራችን ኢትዮጵያ ሰባተኛዉን ሀገራዊ እና ክልላዊ ምርጫ በሠላም ባጠናቀቀችበት ፣ታሪካዊዉ ሀገራዊ የምክክር ኮሚሽን ጉባኤ በስኬት ተጠናቅቆ ‘በምክክር የፀናች ሀገር ‘ለመገንባት ታሪካዊ መግባባት ላይ በተደረሰበት ማግስት መሆኑ የተለየ ያደርገዋል።

ሀገራችን ኢትዮጵያ ዘርፈ ብዙ ስኬቶችን እያስመዘገበች በምትገኝበት ተጨባጭ ሁኔታ ዉስጥ ሆነን፣ ወደ አዲሱ ዓመት ሽግግር ስናደርግ፣ ተደማሪ አዳዲስ ዉጤቶችን በማስመዝገብ፣ ኢትዮጵያ የጀመረችዉን የእመርታ ጉዞ እና የማንሰራራት ዘመን ወደ ከፍታ ማማ ለማሻገር ፣ በተሠለፍንባቸዉ መስኮች የበኩላችንን ለማበርከት መረባረብ ይጠበቅብናል ።

የተከበራችሁ መላዉ የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ሕዝቦች!፣
የክልሉ መንግስት የሕዝቦችን ሁለንተናዊ ተሳትፎ እና ተጠቃሚነት ለማሻሻል የጀመረዉን ጥረት የሕዝብ፣ የመንግስት እና የሌሎችንም አካላት አቅሞችን በማስተባበር አጠናክሮ የሚቀጥል መሆኑን በዚህ አጋጣሚ አረጋግጣለሁ፤ መላዉ ሕብረተሰብም ከመንግስት ጎን በመሰለፍ ድጋፉን አጠናክሮ እንዲቀጥል ጥሪ አቀርባለሁ !

መልካም አዲስ ዓመት!"

ግልፀኝነት ላይ የተመሰረተ የፋይናንስ አሰራር በመከተሉ የውሃ ፕሮጀክቶች አፈፃፀምን እያሻሸለ መምጣቱ ቢሮው አስታወቀ።ጳጉሜ 5/2018 ዓ,.ም (ወልቂጤ)የክልሉ ውሃ፣ መስኖና ማዕድን ልማት ቢ...
10/09/2026

ግልፀኝነት ላይ የተመሰረተ የፋይናንስ አሰራር በመከተሉ የውሃ ፕሮጀክቶች አፈፃፀምን እያሻሸለ መምጣቱ ቢሮው አስታወቀ።

ጳጉሜ 5/2018 ዓ,.ም (ወልቂጤ)
የክልሉ ውሃ፣ መስኖና ማዕድን ልማት ቢሮ የፋይናንስ ዳይሬክቶሬት የተጠናቀቀው 2018 በጀት ዓመት እቅድ አፈጻጸም ሪፖርት አስመልክቶ የቢሮው የስራ ሃላፊዎች ፣ ማናጅመንት አባላትና የዳይሬክቶሬቱ ፈፃሚዎች በተገኙበት ውይይት አካሂዷል።

በመድረኩ የተገኙት የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ውሃ ፣መስኖና ማዕድን ልማት ቢሮ ኃላፊ አቶ ዳዊት ኃይሉ በተጠናቀቀው በጀት ዓመት እንደ ቢሮ በሁሉም ዘርፋ ለተመዘገበው ውጤት ቀልጣፋና ግልፀኝነት የሰፈነበት የፋይናንስ አሰራር ስርዓት ተግባራዊ በመደረጉ እንደሆነ ገልፀዋል።

ስራን ተከፋፍሎ በስነ-ምግባር የመመራትና ያለፉትን አመታት ክፍተቶች ለመዝጋት ከሚመለከታቸው ባለድርሻ አካላት በመቀናጀት ለማሳለጥ የተኬደበት ርቀት ይከሰት የነበረን የሃብት ብክነት ከማስቀረት ባሻገር በመንግስትና በፕሮግራም የተመደቡ በጀቶችን በአግባቡ በማስተዳደር በመጠጥ ውሃ ፕሮጀክቶች ግንባታ አፈፃፃም መሻሻልና ለተለያዩ አገልግሎቶች የሚውሉ ዘመናዊ መሳሪያዎችን በማስገባት ረገድ በተጠናቀቀው በጀት ዓመት ከፍተኛ ውጤት መመዝገቡን አቶ ዳዊት ገልፀዋል።

ከክልሉ ፋይናንስ ቢሮ፣ ከቢሮው የዘርፍ ስራ ክፍሎች እና የበጀትና እቅድ ክትትል ቁጥጥር ግብረ መልስ ዳይሬክቶሬት ጋር የታየው መናበብ እና የመረጃ አደረጃጀት የ2018 በጀት አመት ሂሳብ በወቅቱ እንዲዘጋ ከማስቻሉ ባሻገር በጀት ለታለመለት አላማ እንዲውል አድርጓል ብለዋል።

በቀጣይም ችግር ውስጥ የነበሩ የንፁህ መጠጥ ውሃ ፕሮጀክቶችን ውጤታማ ለማድረግ ከክፍያና ግዢ ጋር የተያያዙ አሰራሮችን ቀረብ ብሎ በመደገፍ የተሻለ ውጤት ለማስመዝገብ እንደሚሰራ አመላክተዋል።

በቢሮው የፋይናንስ ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር ወ/ሮ አስናቀች ሌሞሳ ሪፓርቱን ባቀረቡበት ወቅት እንደገለፁት በኤስ ዲ ጂ እና በመደበኛ የበጀት አሰራር ዳይሬክቶሬቱ በ2018 የተሻለ አፈፃፀም ማስመዝገብ መቻሉን በክልሉ ፋይናንስ ቢሮ መረጋገገጡን ገልፀዋል።

ቀደም ሲል በተለያዩ ምክንያቶች አመታዊ የሂሳብ ሪፖርቶች ዘግይተው ይዘጉ እንደነበር የገለፁት ወ/ሮ አስናቀች በ2018 በጀት ዓመት ከክልል ፋይናንስና ከቢሮው ሚመለከታቸው ዘርፎች በነበረው ቅንጅታዋ አሰራርና መናበብ ችግሮችን መሻገር መቻላቸውን ገልፀዋል።

የቢሮ የስራ ሃላፊዎች እያጋጠሙን የነበሩ ችግሮችን ከፈፃሚ ባሞያዎችና በየደረጃው ከሚመለከታቸው ባለድርሻ አካላት በቅንጅት ተናቦ ለመፍታት በወሰዱት ቁርጠኛ አመራር፣ የባለሙያው የስራ ተነሳሽነት እና የክልሉ ድጋፋዊ ክትትል ለስራው መሳካት የላቀ ድርሻ እንዳለው ተናግረዋል።

የመድረኩ ተሳታፊዎች በሰጡት አሰተያየት ከዚህ ቀደም እንደ ፋይናንስ ዘርፍ ያጋጥሙ የነበሩ ውዝፍ ችግሮችን በቅንጅት ለመፍታትና ህብረተሰቡን ተጠቃሚ የሚያደርጉ የጋራ መፍትሄዎችና አቅጣጫዎች በማስቀመጥ የተሰሩ ስራዎች አበረታች መሆናቸውን ገልፀው በቀጣይነት ባለሙያው በውስን በጀት የተለያዩ ስራዎችን አቀናጅቶ የመፈፀም ልምዱን እንዲያዳብር የድርሻቸውን እንደሚወጡ ተናግረዋል።

በመጨረሻም በቢሮው የፋይናንስ ዳይሬክቶሬት የ2018 በጀት ዓመት አፈፃፀም ሪፖርት ቀርቦ ውይይት ውይይት ተደርጎበታል።

በመድረኩ በቢሮ ኅላፊ ማዕረግ ምክትል ቢሮ ኃላፊና የውሃ ሀብት አስተዳደር ዘርፍ ሃላፊ ወ ሮ አለይካ ሽኩር ፣ ምክትል ቢሮ ኃላፊ አየለ ኬርጋ (ኢ/ር)፣ የቢሮ ኃላፊ አማካሪ አቶ ሀይሌ ደዊ፣ የቢሮው ማኔጅመንት አባላት እና የፋይናንስ ዳይሬክቶሬት ሰራተኞች ተገኝተዋል ።

ጳጉሜን 5/2018 - "የነገ ቀን" የነገዋ የበለጸገች ዲጅታል ኢትዮጵያ! ዛሬ በኢትዮጵያ ልዩ የቀን አቆጣጠር ጳጉሜን 5/2018 ነው። በተሰናባቹ 2018 አመት መጠናቀቂያ፣ በአዲሱ 2019 ...
10/09/2026

ጳጉሜን 5/2018 - "የነገ ቀን"

የነገዋ የበለጸገች ዲጅታል ኢትዮጵያ!

ዛሬ በኢትዮጵያ ልዩ የቀን አቆጣጠር ጳጉሜን 5/2018 ነው። በተሰናባቹ 2018 አመት መጠናቀቂያ፣ በአዲሱ 2019 ዋዜማ ላይ ሆነን ስኬቶቻችንና የሚጎድሉንን መልስ ብለን በማጤን፣ የመጪውን ጊዜ ተስፋዎቻችን ደግሞ በማለም "በነገ ቀን" ልዩ ድባብ ውስጥ እንገኛለን። ይህ ልዩ እለት መላው ኢትዮጵያዊያን እጅ ለእጅ ተያይዘው ለተሻለች ሀገር ግንባታ በጋራ መቆማቸውን የሚያሳዩበት ነው።

እንደሚታወቀው አጠቃላይ የሀገራችን የለውጥ ጉዞ የመጪዋን የበለጸገች ዲጅታል ኢትዮጵያ እውን ማድረግ ነው።በመደመር መንግሥት እሳቤ መሰረት ለዚህ ሀገራዊ ራዕይ ስኬት በራስ አቅምና ጸጋ ሁለንተናዊ ብልጽግናን ከማረጋገጥ ባልተናነሰ መልኩ የዲጅታል ኢትዮጵያ እውን መሆን ትልቅ ትኩረት የተሰጠው ሆኖ እናገኘዋለን ።

በዚህ ረገድ እንደ ከተረጅነት ወደ ምርታማነት ካሉ አዳዲስ አሰራሮችና የልማት ስልቶች ሁሉ ለዲጅታል ኢትዮጵያ ስኬት የሚያግዙ ልዩ ልዩ ኢንሼቲቮች ተነድፈው መተግበር ከጀመሩ አመታት ተቆጥረዋል ።

በተለይም የዲጅታል ኢትዮጵያ 2030 ኢንሼቲቭ ከእነዚህ ሀገራዊ የዘርፉ ንቅናቄዎች ውስጥ ትልቁ እንደሆነ ይታወቃል። ፋይዳ- የብሄራዊ መታወቂያ ፕሮግራም፣ የዲጅታል ኢኮኖሚና መሰረተ ልማት ግንባታ፣ የኢትዮ ኮደርስ ስልጠና፣ መሰብ የአንድ ማዕከል አገልግሎት ኢንሼቲቮች ለነገዋ ኢትዮጵያ ዲጂታላይዜሽን ትልቅ ፋይዳ ያላቸው ናቸው።

የዘመኑ ግድ የሆነውን ዲጅታል ስርኣት በማፋጠን ሀገራዊ ኢኮኖሚን ለማጎልበት ብሎም የዲጅታል አሰራርን በመዘርጋት የመልካም አስተዳደር ክፍተቶችን ለመቅረፍ ሰፊ ስራ እየተሰራ ይገኛል ። በዜጎች መካከል የዲጅታል ክህሎትን በማስረጽ ዘመናዊ አሰራሩ የነገዋ ኢትዮጵያ ጽኑ መሰረት ሆኖ ለሀገራችን ማንሰራራት የማይተካ ሚናውን እንዲወጣ መንግሥት ያላሰለሰ ጥረት እያደረገ ይገኛል ።

እንደ ሀገር ከልማዳዊ አሰራር ወጥተን ወደ ዲጅታል ትራንስፎርሜሽን ለመሸጋገር ቁርጠኝነታችንን የምናረጋገጥበት፣ አስተማማኝ የሳይበር ደህንነት የምንገነባበትና ቀጣዩ ትውልድ የዘመኑ ቴክኖሎጂ ባለቤት እንዲሆን ዝግጁነታችንን ከወዲሁ የምናሳይበት ነው።

የነገዋን የበለጸገች ዲጅታል ኢትዮጵያ የመፍጠር ሃላፊነት የሁሉም ዜጎች ነው!!

09/09/2026

በክልሉ መንግሥት ካፒታል ፕሮጀክት የተገነባው የሀንገዳ ንፁህ የመጠጥ ውሃ ፕሮጀክት በዶ/ር መሀመድ ኑሪዬ በምክትል ርዕሰ መስተዳድር ማዕረግ የመሰረተ ልማት ክላስተር አስተባባሪና የክልሉ ትራንስፖርትና መንገድ ልማት ቢሮ ኃላፊ ተመርቆ ለአገልግሎት ክፍት ተደርጓል።
Tv

ርዕሰ መስተዳድር እንዳሻው ጣሰው (ዶ/ር)የ'ኅብር  ቀንበማስመልከት ያስተላለፉት መልዕክትብዝሃነታችንን የኅብረ ቀለማት እና የዉበት ምንጭ፣ ኅብረ ብሔራዊ አንድነታችንን ደግሞ የጥንካሬ ካዝማ ...
09/09/2026

ርዕሰ መስተዳድር እንዳሻው ጣሰው (ዶ/ር)የ'ኅብር ቀን
በማስመልከት ያስተላለፉት መልዕክት

ብዝሃነታችንን የኅብረ ቀለማት እና የዉበት ምንጭ፣ ኅብረ ብሔራዊ አንድነታችንን ደግሞ የጥንካሬ ካዝማ በማድረግ፣ ዘላቂ ሠላሟ እዉን የሆነ ፣በልጆቿ ጥረት አዳዲስ የታሪክ ገፆችን እየፃፈች የምትገኝ ኅብረ_ ብሔራዊት ኢትዮጵያን ለመገንባት ቃላችንን የምናድስበት ዕለት ነዉ የዛሬዉ የ'ኅብር 'ቀን።

ኅብረ ብሔራዊት ኢትዮጵያን የሚያፀና አስተሳሳሪ የጋራ ትርክት ለመገንባት፣በብሔራዊ መግባባት ላይ የተመሠረተ ፣ ቅቡልነትን ያተረፈ ሀገረ መንግስት እና ጠንካራ ሀገር ለመገንባት የጀመርነዉን የምክክር፣ የንግግርና የመደማመጥ አዲስ የታሪክ ምዕራፍ ስኬታማ በማድረጉ ሂደት የየበኩላችንን ለመወጣት ዝግጁ መሆናችንን የምናረጋግጥበትም ነዉ የ'ኅብር' ቀን ።

የዘርፈ ብዙ ብዝሃነት ባለቤቶች፣ ልዩ ልዩ ፀጋዎች የተቸሩን ህዝቦች፣ እና በመልካም እሴቶች የተሳሰረ ማህበራዊ መስተጋብር ያለን ህዝቦች ነን። እነዚህን ኅብራዊ አቅሞችን አስተባብረን ለሁለንተናዊ ብልጽግና እንተጋለን ።

Address

Wolkite

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Central Ethiopia Water,Irrigation and Mine Bureau posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Shortcuts

Share