Gurage Zone Job Creation and Enterprise Development Department

Gurage Zone Job Creation and Enterprise Development  Department Public enterprise

01/06/2026

የኢትዮጵያ ሕዝብ አስደናቂም ተአምረኛም ሕዝብ ነው። ከፈጣሪ በቀር ሕዝባችንን አሟልቶ ሊያውቅና ሊገመግም የሚችል ማን ነው? የዳበረ ባህል፣ ሀገር ወዳድና የወል መሻቱን መጠበቅ የሚችል ሕዝብ መሆኑን በዘንድሮው ምርጫ ዳግም ለዓለም አሳይቷል። በዛሬው ታሪካዊ ዕለት፡-

• የሌሊቱ ብርድና ጨለማ ያላስፈራቸው፣
• የቀትሩ ፀሐይና ድንገተኛ ዝናብ ያልበገራቸው
• ሠርግ፣ ኀዘን፣ ወሊድና ሌሎች ማኅበራዊ ሁነቶች ያላገዳቸው፣
• ረጃጅም ሰልፎች ያላታከታቸው፣
• የአካል ጉዳት ድምጽ ለመስጠት ያልገደባቸው፣
• ሕመም እና እርጅና የሀገር ተስፋን ከማየት ያላገዳቸው፣
• የነገ ሀገር ተረካቢ ጨቅላ ልጃቸውን ማዘል ያላደከማቸው፣
• ከምንም በላይ የጠላት ጩኸትና ማስፈራሪያ ያላስቆማቸው ዜጎች፤

በብዙ ውጣ ውረዶች መካከል (against all odds) ያሳያችሁት ጽናት ለዴሞክራሲና ለሀገር ሕልውና የተከፈለ ነውና ከልብ የመነጨ ምስጋና ይገባቸዋል፡፡

ይሄንን ሕዝብ ማገልገል መታደል ነውና ተመራጮች ያከበራችሁን አክብራችሁ ለዴሞክራሲ ሥርዓት ዋጋ የከፈለውን ይሄንን ሕዝብ በንጽሕና ለማገልገል ያብቃችሁ።

Uummanni Itoophiyaa dinqisiisaafi ajaa'ibsiisaadha! Uumaa malee uummata keenya guutummaan beekuufi gamaaggamuu kan danda'u eenyu? Aadaa gabbataa, uummata biyya jaallatuufi fedhiisaa waloo eeguu danda'u ta'uusaa filannoo baranaatiin irradeebiidhaan addunyaatti agarsiiseera. Guyyaa seena-qabeessa har'aatiin:
- Qorriifi dukkanni halkani kan isaani hin sodaachifne,
- Aduun saafaafi bokkaan tasaa kan isaan jilbeenfachiifne,
- Cidhi, gaddi, da'umsiifi taateewwan hawaasummaa kanbiroon kan isaan dhorkine,
- Hiriironni dhedheeroon kan isaan hin nuffisiifne,
- Qaama miidhamtummaan sagalee kennuuf kan isaan hin daangessine,
- Dhukkubniifi dullumni abdii biyyaa arguuf kan isaan hin dhowwine,
- Daa'imasaanii kichuu bor biyya dhaalu baatanii filuun kan isaan hin dadhabsiifne
- Hundumaa caalaa lammiilee iyyiifi sodaachiifni diinaa isaan hin dhaabsifne,
Ciminni bu'aa bayii hedduu keessatti agarsiiftan gatii diimokraasiifi jiraachuu biyyatiif kanfalame waan ta'eef galata guddaatu malaafi.

Uummata kana tajaajiluun carroomuu waan ta'eef filatamtoonni warra isin kabajan kabajjanii uummata sirna diimookraasiif gatii baase kana qulqullummadhaan tajaajiluuf isin haa gahu.

The people of Ethiopia are an extraordinary and remarkable people. Other than the Creator, who can truly know and assess our people in their entirety? Through this year’s election, Ethiopians have once again shown the world that they are a people with a rich culture, deep patriotism, and the ability to safeguard the common good.

On this historic day:

* Citizens who were not intimidated by the cold and darkness of the night,
* Who were not deterred by the midday sun or sudden rain,
* Whom weddings, funerals, childbirth, and other social obligations did not prevent from participating,
* Who were not wearied by long lines,
* Whose physical disabilities did not stop them from casting their vote,
* Those whose illness and old age did not prevent from witnessing the hope of their country,
* Who were not exhausted by carrying their infant children; the future inheritors of the nation,
* And above all, whom the shouting and threats of enemies could not intimidate or stop;

The perseverance you demonstrated amid many challenges and hardships, against all odds, was a contribution made for democracy and for the very survival of the nation. For this, you deserve heartfelt gratitude.

It is a privilege to serve such a people. Therefore, may those who have been elected honor the trust placed in them and serve this people, with integrity and sincerity! A people who have paid a great price for the democratic system. May you be worthy of that responsibility.

 ‎
30/05/2026



“የፀና ቃል፤ የላቀ እምርታ!"‎   ‎‎
30/05/2026

“የፀና ቃል፤ የላቀ እምርታ!"



30/05/2026

እሴት ሰንሰለትን መሠረት ያደረገ የሥራ ዕድል ፈጠራ ውጤት አምጥቷል

በሶማሌ ክልል እሴት ሰንሰለትን (Value-Chain) መሠረት ያደረጉ የሥራ ፈጠራ ተግባራት ውጤት እያስመዘገቡ መሆኑ ተገለጸ።

የሱማሌ ክልል ሥራና ክህሎት ቢሮ ምክትል ኃላፊ ወ/ሮ ሂቦ አህመድ ፤ ሥራዎቹ በፌዴራል መንግስት የሥራ ፈጠራ ፖሊሲዎችና የሪፎርም ሃሳቦች መሠረት የተከናወኑ መሆኑን ገልጸው ተግባራቱ የክልሉ መንግስት ለወጣቶች ሥራ ፈጠራና ለአካባቢ ኢኮኖሚ ማነቃቂያ ያለውን ጽኑ ቁርጠኝነት ያሳዩ መሆኑንም ጠቁመዋል።

እንደ ወ/ሮ ሂቦ አህመድ ማብራሪያ፣ የገበያ ተኮር የልማት አቅጣጫን መሠረት ያደረገው ይህ ፕሮግራም በጅግጅጋና በጎዴ ከተሞች በሙከራ ደረጃ ተተግብሯል። ፕሮግራሙ በወተት፣ በእንቁላል፣ በሽንኩርትና በሥጋ ምርቶች አቅርቦት ላይ ትኩረት አድርጎ ተሰርቷል።

በሂደቱ 28 አቅራቢዎች (Supply Side) እና 22 ፈላጊዎች (Demand Side) በማስተሳሰር ከ2,200 በላይ ለሚሆኑ የአካባቢው ማህበረሰብ አባላት በትስስሩ የሥራ ዕድል ተጠቃሚ ማድረግ ተችሏል፡፡

ይህ አሰራር የአካባቢውን የምርት አቅርቦት ሥርዓት እና የገበያ ትስስር በእጅጉ ከማሻሻሉም በላይ ለአምራቾች አስተማማኝ ገቢ መፍጠሩንና የግሉን ዘርፍ ተሳትፎ ማሳደጉን ገልጸዋል።

ሂደቱም ክልሉ ወደ ዘላቂና ገበያ-ተኮር የሥራ ፈጠራ ሥርዓት እየተሸጋገረ መሆኑን የሚያሳይ ነው ብለዋል።

ግንቦት 21/2018 ዓ.ም፤ የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር
ለወቅታዊ ትኩስ የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር
Official Website: mols.gov.et
Facebook: https://web.facebook.com/MolsFDRE
Telegram: https://t.me/FDRE_MoLSofficial
TikTok: tiktok.com/
Twitter / X: twitter.com/Jobs_ሚኒስቴር
WhatsApp: whatsapp.com/channel/0029VakCgcYI

ሳምንታዊ መልዕክትየኢንዱስትራላይዜሽን እመርታችን ኢትዮጵያን የአፍሪካ ተምሳሌት ሀገር የማድረግ ውጥናችን የሚሳካ መሆኑ ማሳያ ነው፤ፓርቲያችን ብልፅግና ቀምሮ በግልፅ ካስቀመጣቸው ፕሮግራሞች አ...
25/05/2026

ሳምንታዊ መልዕክት

የኢንዱስትራላይዜሽን እመርታችን ኢትዮጵያን የአፍሪካ ተምሳሌት ሀገር የማድረግ ውጥናችን የሚሳካ መሆኑ ማሳያ ነው፤

ፓርቲያችን ብልፅግና ቀምሮ በግልፅ ካስቀመጣቸው ፕሮግራሞች አንዱና ዋነኛው ኢኮኖሚን የተመለከተ ነው፡፡ የብልፅግና ፓርቲ የኢኮኖሚ ፕሮግራም ዓላማ ልማትና ፍትሃዊ ተጠቃሚነትን የሚያረጋግጥ አካታች የኢኮኖሚ ሥርዓት መገንባት ነው፡፡ ግቦቹም የብዝሃ ዘርፍ የኢኮኖሚ መዋቅር መገንባት፤ ጥራት ያለው የኢኮኖሚ ልማት እና ምርታማነትን መሰረት ያደረገ ማህበራዊ ፍትህ ማረጋገጥ፤ ሀብትና ፈጠራን የሚያሳድግ ዕውቀት-መር ኢኮኖሚ መገንባት እና ከተሜነት እና የከተማ ልማትን ማስፋፋት ናቸው፡፡

ኢኮኖሚው ከቆየበት የነጠላ-ዘርፍ ትኩረት ተላቆ ብዝሀ-ዘርፍ፣ ብዝሀ-ተዋንያን እና ብዝሀ-ተጠቃሚነት እንዲያረጋግጥ የተቀመጠለት የሪፎርም አቅጣጫ በመከተል እስካሁን አያሌ አስደናቂ ውጤቶች ማስመዝገብ ችሏል፡፡ ከእነዚህ የብዝሀ-ዘርፍ አውታሮች አንዱ የሆነው የማኑፋክቸሪንግ ኢንዱስትሪ ሲሆን በዚህ ውስጥም የኢትዮጵያ ታምርት ንቅናቄ እና የገጠር ኢንዱስትሪያላይዜሽን የ3-2-1 ኢኒሼቲቭ ጎልተው ይጠቀሳሉ፡፡ በነዚህ ንቅናቄዎች አማካኝነት ተኪ ምርት ከማምረት፣ በሚልዮኖች ለሚቆጠሩ ዜጎች የሥራ ዕድል ከመፍጠር፣ ምርትን ወደ ውጭ በመላክ የውጭ ምንዛሬ ከማግኘት፤ ሀብት ፈጠራና የቤተሰብ ብልፅግና ከማረጋገጥ አልፎ የኢትዮጵያ የኢኮኖሚ ሽግግርና ሉአላዊነት እየተገነባበት ይገኛል፡፡

በቅርቡ የገላን ጉራ የኢንዱስትሪ ፓርቲ ሥራ መጀመር እና በሞጆ ከተማ በአጭር ጊዜ ተገንብቶ ወደ ማምረት የገባው ግዙፍ የሴራሚክስ ማምረቻ ፋብሪካ የዚህ ውጤታማ የኢንዱስትራላዜሽን ጉዟችን ማሳያ ናቸው፡፡ ክቡር የፓርቲያችን ፕሬዝዳንት ዶ/ር አብይ አሕመድ በሞጆ የሴራሚክ ፋብሪካ ምረቃ መርሀግብር ላይ ተገኝተው ባስተላለፉት መልዕክት ኢትዮጵያ ከውጭ የሚገቡ ምርቶችን በሀገር ውስጥ በመተካት በሳለፍናቸው ዘጠኝ ወራት ውስጥ ብቻ ከ4.85 ቢልዮን ዶላር በላይ የውጭ ምንዛሬ ማዳን የተቻለበት መሆኑ ጠቅሰዋል፤ የሴራሚክ ፋብሪካው መከፈቱ የውጭ ምርት ጥገኝነት የሚቀንስ ብቻ ሳይሆን ኢትዮጵያ በዓለምአቀፍ ገበያ ውስጥ ተወዳዳሪ እንድትሆን የሚያስችላትም ጭምር መሆኑ ገልጸዋል፡፡

የማኑፋችሪንግ ኢንዱስትሪ ስኬቶች በአጠቃላይ ሲታይ በዘርፉ በ2010 በጀት ዓመት የነበሩትን 18,747 አምራች ኢንዱስትሪዎች በአሁን ወቅት 27,764 ማድረስ ተችሏል፡፡ የማምረት አቅም አጠቃቀም 2014 በጀት ዓመት ከነበረበት 46 በመቶ በ2018 ግማሽ ዓመት ወደ 66.3 በመቶ ደርሷል፡፡ የኤክስፖርት አፈፃፀም 2010 በጀት ዓመት ከነበረበት 308.12 ሚሊየን ዶላር የውጭ ምንዛሬ የተገኘ ሲሆን በ2017 በጀት ዓመት 380 ሚሊየን ዶላር ደርሷል፡፡ ባጠቃላይ የአምራች ኢንዱስትሪ የኢኮኖሚ ዕድገት 2010 በጀት ዓመት ከነበረበት 5.5 በመቶ በ2017 በጀት ዓመት ወደ 10.7 በመቶ በእጥፍ አድጓል፡፡

በቀጣይም የማኑፋክቸሪንግ ኢንዱስትሪ አማካኝ ዕድገት 22.9 በመቶ፤ የማኑፋክቸሪንግ ኢንዱስትሪ የኢኮኖሚ ድርሻ 17.2 በመቶ እና የማኑፋክቸሪንግ የወጪ ንግድ ገቢ 8.9 ቢሊዮን የአሜሪካ ዶላር ለማድረስ ታቅዶ እየተሰራ ይገኛል፡፡ ከዚህ በተጨማሪ የዘርፉ የሀገር ውስጥ ገበያ ድርሻ 60% እና የሚፈጠው የሥራ ዕድል 5 ሚሊዮን ለማድረስ ታቅዷል፡፡

ይህ በአጭር ጊዜ የተፈጠረ እመርታ ዘርፉ ለብዙ አስርት ዓመታት ሲያሳይ የቆየውን አዝጋሚ ለውጥ በመሰረታዊነት የቆየረ ነው፡፡ ይህም በትክክለኛ ዕሳቤ እና ፕሮግራም መመራት እንዲሁም ለሀገር ዕድገት በቅንነትና በቁርጠኝነት መሥራት እመርታዊ ለውጥን

25/05/2026
25/05/2026

Address

Wolkite

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Gurage Zone Job Creation and Enterprise Development Department posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Share