Wolkite Agricultural Research Center/ ወልቂጤ ግብርና ምርምር ማዕከል

  • Home
  • Ethiopia
  • Wolkite
  • Wolkite Agricultural Research Center/ ወልቂጤ ግብርና ምርምር ማዕከል

Wolkite Agricultural Research Center/ ወልቂጤ ግብርና ምርምር ማዕከል Vision

To see improved livelihood of all Ethiopians engaged in agriculture, agro-pastoralism, and
(1)

የወልቂጤ ግብርና ምርምር ማዕከል በኮፒያ (KOPIA) ፕሮጀክት ድጋፍ፣ ለቀቤና ልዩ ወረዳ እና አበሽጌ ወረዳ አርሶ አደሮችና ባለሙያዎች በሽንኩርት ዘር አመራረት ቴክኖሎጂ ዙሪያ ስልጠና ሰጠ።...
09/05/2026

የወልቂጤ ግብርና ምርምር ማዕከል በኮፒያ (KOPIA) ፕሮጀክት ድጋፍ፣ ለቀቤና ልዩ ወረዳ እና አበሽጌ ወረዳ አርሶ አደሮችና ባለሙያዎች በሽንኩርት ዘር አመራረት ቴክኖሎጂ ዙሪያ ስልጠና ሰጠ።

​የስልጠናው ዋና ዋና ነጥቦች፦
​የሽንኩርት ዘር እና የኮረት አመራረት ዘዴዎች።
​ከመሬት ዝግጅት እስከ ምርት አሰባሰብና ድህረ ምርት አያያዝ።

​በአመራረት ሂደት ላይ ለሚገጥሙ ተግዳሮቶች ከወልቂጤ እና ከመልካሳ ምርምር ማዕከል ተመራማሪዎች ማብራሪያ ተሰቷል።

​ይህ ስልጠና አርሶ አደሩ ጥራት ያለው የሽንኩርት ዘር በራሱ ማምረት እንዲችልና የምግብ ዋስትናን ለማረጋገጥ የሚደረገውን ጥረት የሚያግዝ ነው።

25/03/2026

በወልቂጤ ግብርና ምርምር ማዕከል የዝርያ ማሻሻያ ምርምር ስራዎች Ethiopian Institute of Agricultural Research - EIAR

23/03/2026

ኮኮክ ዶሮ ዝርያ ተመራጭ የሚሆንባቸው ምክንያቶች
koekoek breed
Ethiopian Institute of Agricultural Research - EIAR

13/03/2026

Journal Club Series II, Wolkite Agricultural Research Center
short Video

We were honored to host Journal Club Series II, where Dr. Diriba Geleti, Deputy Director General for Research at the Eth...
11/03/2026

We were honored to host Journal Club Series II, where Dr. Diriba Geleti, Deputy Director General for Research at the Ethiopian Institute of Agricultural Research (EIAR), delivered an inspiring seminar at the Wolkite Agricultural Research Center (WkARC).

His presentation was titled:
“𝕃𝕖𝕒𝕕𝕚𝕟𝕘 𝔸𝕘𝕣𝕚𝕔𝕦𝕝𝕥𝕦𝕣𝕒𝕝 ℝ𝕖𝕤𝕖𝕒𝕣𝕔𝕙 ℙ𝕣𝕠𝕘𝕣𝕒𝕞𝕤: 𝔸𝕟 𝕀𝕟𝕥𝕖𝕘𝕣𝕒𝕥𝕚𝕧𝕖 𝔾𝕖𝕟𝕖𝕣𝕒𝕝𝕚𝕤𝕥 𝔸𝕡𝕡𝕣𝕠𝕒𝕔𝕙.”

The core message of the presentation was why a Generalist approach matters in R4D (Research for Development). Dr. Geleti emphasized that leadership in R4D requires moral integration—the ability to integrate ideas, align teams, and bring together different perspectives. This integrated approach helps create practical solutions and greater impact for farmers and society.
Ethiopian Institute of Agricultural Research - EIAR

በኢትዮጵያ የግብርና ምርምር ኢንስቲትዩት የወልቂጤ ግብርና ምርምር ማዕከል፣ 50% የሆልስቴን ፍሬዝያን (HF) የደም መጠን ያላቸውን የተሻሻሉ ጊደሮችና ወይፈኖችን በጉራጌ፣ በምስራቅ ጉራጌ እ...
09/03/2026

በኢትዮጵያ የግብርና ምርምር ኢንስቲትዩት የወልቂጤ ግብርና ምርምር ማዕከል፣ 50% የሆልስቴን ፍሬዝያን (HF) የደም መጠን ያላቸውን የተሻሻሉ ጊደሮችና ወይፈኖችን በጉራጌ፣ በምስራቅ ጉራጌ እና በስልጤ ዞኖች ለሚገኙ አርሶ አደሮች በዛሬው ዕለት አሰራጭቷል።

ይህ ተግባር የተከናወነው በኢትዮጵያ የግብርና ምርምር ኢንስቲትዩት እና በግብርና ሚኒስቴር የእንስሳትና ዓሣ ሃብት ልማት ሴክተር (LFSDP) ትብብር ሲሆን፤ 100 የቦረና ጊደሮችን ከሆልስቴን ፍሬዝያን ጋር በማዳቀል የተገኙ ውጤቶች ናቸው። በዚህም በሁለተኛ ዙር ለወተት መንድር መነሻ የሚሆኑ ጊደሮች እና በከተማ ግብርና ማደለብ ስራ ላይ ለተሰማሩ አርሶ አደሮች ወይፈኖች ተሰራጭተዋል።

በዕለቱ የጉራጌ ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ ላጫ ጋሩማ፣ የማዕከላዊ ኢትዩጵያ ክልል ግብርና ቢሮ ምክትል እና የእንስሳት እና ዓሣ ሃብት ዘርፍ ኃላፊ አቶ ኢያሱ ተረፈ፣ የኢትዮጵያ የግብርና ምርምር ኢንስቲትዩት የምርምር ምክትል ዋና ዳይሬክተር ዶ/ር ዲሪባ ገለቲ፥ የአበሽጌ ወረዳ ዋና አስተዳደሪ አቶ ካሱ ጁዋር፥ የLFSDP ፕሮጀክት ብሔራዊ አስተባባሪ ዶ/ር ቶማስ ቸርነት ፣ በኢትዮጵያ የግብርና ምርምር ኢንስቲትዩት የእንስሳት ምርምር ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር ዶ/ር አስቻለው ላቀው፥ የምርምር ማዕከላት ዳይሬክተሮች፥ ተመራማሪዎች፥ ሌሎች ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች እና አርሶ አደሮች ተሳፋፊ ሆነዋል።

ይህ በቦረና እና በሆልስቴን ፍሬዝያን ዝርያ ማዳቀል የተገኘው ውጤት፣ የአርሶ አደሩን ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ ትልቅ ፋይዳ አለው። ከፍተኛ የመንግስት የስራ ኃላፊዎች በተገኙበት በነበረው መርሃ ግብር፣ በቀጣይ የምርምር ስራዎች ላይም የጋራ መግባባት ተፈጥሯል።

በተያያዘ በማዕከሉ ዙርያ ለሚገኙ አርሶ አደሮች የኮኮክ ዶሮ ዝርያም በዕለቱ አሰራጭቷል

09/03/2026
የወልቂጤ ግብርና ምርምር ማዕከል የዶሮ ዝርያዎችን እያሰራጨ ነው! ​ማዕከላችን በከተማ ግብርናን ለማስፋፋት እና የአርሶ አደሩን ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ ባከናወነው ተግባር፤ በ5 ወረዳዎች እና ...
01/03/2026

የወልቂጤ ግብርና ምርምር ማዕከል የዶሮ ዝርያዎችን እያሰራጨ ነው!

​ማዕከላችን በከተማ ግብርናን ለማስፋፋት እና የአርሶ አደሩን ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ ባከናወነው ተግባር፤ በ5 ወረዳዎች እና በሁለት ከተሞች ለሚገኙ 116 ለሚበልጡ አርሶ አደሮች ከ 3,000 በላይ የኮኮክ (Potch Koekoek) እና የ DZD-White የዶሮ ዝርያዎችን አሰራጭቷል።

​የስርጭቱ ዋና ዓላማ፡
🐤​የኮኮክ ዶሮ ዝርያን በከተማ ግብርና ማስፋት።
🐤​የ DZD-White ዝርያን ለአርሶ አደሩ ማስተዋወቅ።
🐤​ዝርያዎቹ በተለያዩ ወረዳዎች ያላቸውን ምርታማነት መገምገም።

​ጫጩቶቹ ከአንድ ቀን እድሜያቸው ጀምሮ በማዕከላችን ለሁለት ወራት አስፈላጊው እንክብካቤ ተደርጎላቸው ለተጠቃሚዎች እንዲደርሱ ተደርጓል።

የተሰራጨባቸው ወረዳዎች፦ አበሽጌ፣ ደቡብ ሶዶ፣ ገ/ጉ/ወለኔ፣ ጎሮ ወረዳ፣ ቀቤና ልዩ ወረዳ እንዲሁም ወልቂጤ እና ቡታጅራ ከተሞች።

​የኮኮክ (Potch Koekoek) ዶሮ ዝርያ ልዩ ጥቅሞች፡
​ይህ የዶሮ ዝርያ በአነስተኛ ወጪ ከፍተኛ ምርት ለሚፈልጉ አርሶ አደሮችና የከተማ ነዋሪዎች ተመራጭ ነው፦
​🐤 ሁለገብ ምርት፡ ለስጋም ሆነ ለእንቁላል ምርት የሚውል ዝርያ ነው።
​🐤 ከፍተኛ እንቁላል፡ በአርሶ አደር አያያዝ በዓመት 180-200 እንቁላል ይጥላሉ።
​🐤ጥንካሬ፡ በሽታን የመቋቋም አቅማቸው ከሌሎች ዝርያዎች በ 80% ይበልጣል።
​🐤ቆጣቢ፡ በአነስተኛ የመኖ አቅርቦት የተሻለ ምርት ይሰጣሉ።
​🐥 ቀጣይነት፡ እንቁላሉን በሀገር በቀል ዶሮዎች ወይም በማሽን በማስፈልፈል ዝርያውን በቀላሉ ማስቀጠል ይቻላል።
​🐤ክብደት፡ በ 5 ወር እድሜያቸው ወንዶቹ 2-2.5 ኪ.ግ፣ ሴቶቹ ደግሞ 1.8-2 ኪ.ግ ይመዝናሉ።
​🐤ለገበያ ተመራጭ፡ እድሜያቸው ቢገፋም ላባቸው ስለማይረግፍ በገበያ ላይ ከፍተኛ ተፈላጊነት አላቸው።

በቀጣይ ከቢሾፍቱ ግብርና ምርምር ማከል ጋር በመሆን ዶሮ ላይ የምንሰራውን ስራ አጠናክረን የምንቀጥል ይሆናል

ስለ እንሰት ጥቅም እና ስለ ዋናው ተግዳሮቱ (የእንሰት አጠውልግ በሽታ) ዝርዝር መረጃ እንደሚከተለው ቀርቧል፦ እንሰት ከሥሩ እስከ ቅጠሉ ጥቅም ላይ የሚውል ድንቅ ተክል ነው።ሀ.   (Food...
19/02/2026

ስለ እንሰት ጥቅም እና ስለ ዋናው ተግዳሮቱ (የእንሰት አጠውልግ በሽታ) ዝርዝር መረጃ እንደሚከተለው ቀርቧል፦

እንሰት ከሥሩ እስከ ቅጠሉ ጥቅም ላይ የሚውል ድንቅ ተክል ነው።
ሀ. (Food Security)
የረሃብ መከላከያ፡ እንሰት ድርቅን የመቋቋም ከፍተኛ አቅም አለው። ሌሎች ሰብሎች በዝናብ እጥረት ሲጠቁ እንሰት ግን ለረጅም ጊዜ ውሃ አቆይቶ ስለሚቆይ በችግር ጊዜ ደራሽ ነው።
የተለያዩ የምግብ አይነቶች፡ ከእንሰት የሚገኙት ቆጮ፣ ቡላ እና አሚቾ (የእንሰት ስር) ከፍተኛ የኃይል ምንጭ (Carbohydrates) ናቸው።
የመቆየት አቅም፡ የተፋቀ እንሰት (ቆጮ) ጉድጓድ ውስጥ ተቀብሮ ለበርካታ ዓመታት ሳይበላሽ ሊቆይ ይችላል።
ለ.
የእንሰት ቅጠል እና የግንዱ ክፍል ለከብቶች በተለይም በደረቅ ወቅት ተመራጭ መኖ ነው። የእንሰት ዝቃጭ (ቆጮ ተጨምቆ የቀረው) ለከብቶች ማድለቢያነት ያገለግላል።
ሐ.
ቃጫ (Fiber)፦ ከእንሰት የሚወጣው ቃጫ ለገመድ፣ ለጆንያ እና ለምንጣፍ ስራ ከፍተኛ ጥራት ያለው ግብዓት ነው።
ቅጠል፦ ምግብ ለማብሰል ፣ ለማሸጊያነት፣ ለቤት ክዳን ።
መ.
እንሰት ዘላቂ ተክል በመሆኑ የአፈር መሸርሸርን ይከላከላል። ከፍተኛ የውሃ ይዘት ስላለውም በአካባቢው ላይ እርጥበትን የመጠበቅ እና አፈርን የማበልጸግ ባህሪ አለው።

ሠ . #ለመድሀኒትነት
በተለይም የእንስት አሚቾ በርካታ ጠቀሜታዎች እንዳሉትና ለክምና አገልግሎት የሚውሉ የተለዩ ዝርያዎች እንዳሉ ይታመናል::

2. (Enset Bacterial Wilt)
ይህ በሽታ በአሁኑ ወቅት የኢትዮጵያ የእንሰት ህልውና እየተፈታተነ ያለ ትልቁ ጠላት ነው።
መንስኤው (Cause) በሽታው የሚመጣው Xanthomonas campestris pv. musacearum በሚባል ባክቴሪያ ነው።
እንዴት ይተላለፋል?

፦ በበሽታው የተጠቃን ተክል የነካ ቢላዋ፣ ማጭድ ወይም አካፋ ሳይታጠብ ጤናማውን ተክል ሲነካ።

፦ በሽታ ካለበት አካባቢ ችግኝ አምጥቶ መትከል።

#እንስሳት፦ የታመመ ተክል የበሉ ከብቶች ወደ ጤናማው ማሳ ሲገቡ ወይም በሰገራቸው አማካኝነት።

#ሰው፦ በጫማ ወይም በልብስ አማካኝነት ባክቴሪያውን በማጓጓዝ።

ምልክቶቹ

የውስጠኛው ወጣት ቅጠል በድንገት መጠውለግ እና ቢጫ መሆን።
ተክሉ ውሃ እንደጠማው ሆኖ ዝልፍልፍ ማለት።
ግንዱ ሲቆረጥ የሚወጣው ፈሳሽ ቢጫ እና ዝልግልግ መሆን።
በመጨረሻም ተክሉ ሙሉ በሙሉ ደርቆ ይሞታል።

3. ( )
ለበሽታው እስካሁን ፍጹም መድኃኒት አልተገኘለትም፤ ዋናው መፍትሔ መከላከል ብቻ ነው።
መሣሪያዎችን ማጽዳት (Disinfection)፦ ከማንኛውም ስራ በኋላ መሳሪያዎችን በእሳት ማቃጠል ወይም በፀረ-ተባይ/ አልኮል ማጠብ።
በሽታውን ለይቶ ማጥፋት (Eradication)፦ በሽታው የታየበትን ተክል ወዲያውኑ ነቅሎ በማሳው ዳርቻ ላይ ጉድጓድ ውስጥ ቀብሮ ማቃጠል።
የንክኪ ቁጥጥር፦ የታመመ ተክል ያለበት ማሳ ውስጥ እንስሳት እንዳይገቡ መከልከል።
ጤናማ ችግኝ መጠቀም፦ ምንጩ የማይታወቅ ወይም የታመመ ችግኝ በፍጹም አለመትከል።

የወልቂጤ ግብርና ምርምር ማዕከል፣ በሶዶ ወረዳ ዳጬ ሐሙስ ቀበሌ እና በእዣ ወረዳ የስራይ ቀበሌ ለሚገኙ አርሶ አደሮች፣ የእንሰት አጠውልግ (Enset Bacterial Wilt) በሽታን ለመከላ...
17/02/2026

የወልቂጤ ግብርና ምርምር ማዕከል፣ በሶዶ ወረዳ ዳጬ ሐሙስ ቀበሌ እና በእዣ ወረዳ የስራይ ቀበሌ ለሚገኙ አርሶ አደሮች፣ የእንሰት አጠውልግ (Enset Bacterial Wilt) በሽታን ለመከላከል የሚያስችል የማሳ ንፅህና (Phyto-sanitary) አጠባበቅ ስልጠና ተሰጥቷል!

ዓላማ፦ የስልጠናውና የንቅናቄው ዋና ዓላማ መፍጠር ነው።

የእንሰት አጠውልግ በሽታ መንስኤ ምንድን ነው?
በሽታው የሚከሰተው በባክቴሪያ አማካኝነት ሲሆን በሳይንሳዊ አጠራሩም Xantomonas campestris በመባል ይታወቃል፡፡ በሽታው በዋናነት በተበከሉ የእርሻ መሳሪያዎች፣ በበሽታው በተያዙ የእንሰት ችግኞች፣ በእንስሳት፣ እና ጥንቃቄ በጎደለው የሰዎች እንቅስቃሴ አማካኝነት ይዛመታል።


✅ የእርሻ መሳሪያዎች ንፅህና፦ ለእርሻ ስራ የምንጠቀምባቸውን ቢላዋ፣ ማጭድ፣ የእንስት መፋቂያዎች፣ ማረሻ እና ሌሎች መሳሪያዎች ከእያንዳንዱ ስራ በኋላ በእሳት በማቃጠል ወይም በአልኮል ማፅዳት።
✅ በበሽታው የተጠቁ ተክሎችን ከማሳ ማስወገድ፦ በበሽታው የተጠቃን ተክል ወዲያውኑ ነቅሎ ማቃጠል ወይም በጥልቀት መቅበር። በሽታው እንዳይዛመት የተጠቃውን ተክል በቦታው መተው፣ ለከብቶች መመገብ፣ ወይም በፍጹም መፋቅ የለብንም።
✅ ከበሽታ የጸዳ ንጹህ የእንሰት ችግኝ መጠቀም፦ የእንሰት ችግኞችን ስንተክል በሽታ ከሌለበት አስተማማኝ ምንጭ መሆኑን ማረጋገጥ።
✅ በሽታውን መቋቋም የሚችሉ የእንሰት ዝርያዎችን መትከል፦ በአካባቢው ከሚለሙ የእንሰት ዝርያዎች በሽታውን መከላከል የሚችሉ ዝርያዎችን መርጦ ማባዛት እና መትከል።
✅ ተሳትፎአዊ የማህበረሰብ ንቅናቄን መፍጠር፦ ማሳችን ከበሽታው ነጻ ቢሆንም በአካባቢያችን በሽተኛ ተክል (ማሳ) ካለ በቀላሉ ወደ ማሳችን ሊመጣ ስለሚችል እና በግል መከላከል ውጤታማ የማያደርግ በመሆኑ በሽታውን በጋራ ንቅናቄ መከላከል ያስፈልጋል።

ይህ የማሳ ንፅህና ተግባር መንደሩ ሙሉ በሙሉ ከበሽታው ነፃ እስከሚሆን ድረስ መቀጠል ያለበት ሲሆን ለዚህም በወረዳ እና ቀበሌ ደረጃ አስፈጻሚ ግብረ-ሃይል ተቋቁሟል፣ ሁሉም የማህበረሰብ ክፍል በንቃት መሳተፍ እንደሚጠበቅባቸው መግባባት ተፈጥሯል።

Address

Wolkite Zone
Wolkite

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Wolkite Agricultural Research Center/ ወልቂጤ ግብርና ምርምር ማዕከል posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Organization

Send a message to Wolkite Agricultural Research Center/ ወልቂጤ ግብርና ምርምር ማዕከል:

Share