Gurage Zone Plan and Economic Development Department

Gurage Zone Plan and Economic  Development  Department Gurage zone Plan

28/05/2025
15/03/2022

ልብ ብለው ያንብቡ!!
❀━┅┉┈ ┈┉┅━❀
ልጁ ነገውን ሚስት ሊያገባ ሽር ጉድ ላይ ሳለ እናት ድንገት ከዚህ አለም በሞት ትለየውና የሰርጉን ፕሮግራም ወደ አመት አዘዋወረው ። የማይደርስ የለምና ያ የቀጠሮ ቀን አመቱን አክብሮ ብቅ አለ ። ልጁም የሚፈልጋትን ሴት አገባ ። ያን ግዜ አባት በባዶ ቤት ብቻቸውን ሊቀሩ ተገደዱ ።

ምክንያቱም ባለቤታቸው ከሞተች በኋላ ከዚህ አንድ ልጃቸው ሌላ ማንም አልነበራቸውም ። ልጅም ከአዲሷ ሚስቱ ኑሮ ጀመረ ። ልጁ አንዳንዴ ሚስቱን ይዟት አባቱን ሊጠይቅ ይመጣል ። አንዳንዴ ደሞ እሱ አባቱን ጠይቆ እስኪመለስ እሷ ቤተሰቦቿ ዘንድ ትጠብቀዋለች ። ብዙ ግዜ የሷን ቤተሰቦች ብቻ እንዲጠይቅ ታስገድደው ነበር ።

በዚህ መልኩ አምስት አመታት ተቆጠሩ ። በዚህ መሀከል እኚህን ምስኪን አባት በእርጅና ላይ በሽታው አዳከማቸው ። የአባቱ ሁኔታ ያሳሰበውም ልጅ አባቱን ቤት ሊወስዳቸው እና ሙሉ እንክብካቤ እንዲደረግላቸው ሲጠይቃቸው ። የልጁ ሚስቱ ዘንድ ተቀባይነት የሌለው እንግዳ እንዳይሆኑ ስለስጉ ጥያቄውን አልተቀበሉትም ። ከዚያም የረጅም ግዜ የልጃቸው ውትወታ ለጥያቄው እጅ እንዲሰጡ አደረጋቸውና ልጃቸው ቤት ቀሪ ዘመናቸውን ሊያጠናቅቁ ብቅ አሉ ።

ያን ግዜ የልጃቸው ሚስት ደስታ ራቃት ። ሁለት አይነት ምግብ ማብሰል ጀመረች ለሽማግሌው በግዴለሽነት ትሰራና ታቀርብላቸው ነበር ። አባት ምግብ ብቻቸውን መብላት ቢከብዳቸው እንኳን ከልጃቸውና ከልጅ ልጆቻቸው አብረው መብላት አትፈቅድላቸውም ነበር ። የሚስቱ እና ያባቱ ሁኔታ ትንግርት የሆነበትም ልጅ በሁለት መዕበላት ውስጥ ሆኖ ይናወጥ ጀመር ከአባቴ ልሁን ወይስ ከሚስቴ !!!

ያን ግዜ ሚስት እንድ ሀሳብ ሰነዘረች ፦"ለምን ሚስት አናመጣላቸውም እነሱንም ትንከባከባለች እኛም እንገላገላለን" አለች ። ልጅም በዚህ እድሜያቸው አግብተው መኖር እንደማይችሉ ስላመነ አንድ አማራጭ ፊቱ ላይ ድቅን አለለት ። አረጋውያን ማቆያ/ሰው የሌላቸው ሽማግሌዎች የሚኖሩበት ድርጅት ውስጥ ሊወስዷቸው ወሰኑ እና ይዘዋቸው ሄዱ ። ልጁም ለዘመናት አብሮት የኖረውን የገዛ አባቱን በገዛ እጁ ገብቶ ማያውቅበት ግቢ ውስጥ አስገብቶት እንባውን እያፈሰሰ ተመለሰ ።

አባቱን እዛ ግቢ ውስጥ ካስገባቸው በኋላ በሳምንቱ ሊጠይቃቸው ወደ ግቢው ሲገባ አባት በብጣሽ ወረቀት መልዕክት አስቀምጠውለት ከዚህ አለም በሞት ተለይተዋል ። መልዕክቱ እንዲህ ይል ነበር ፦

"ልጄ !!! ካሳለፍኳቸው ምርጥ ግዜያት ሁሉ ደስ የሚለኝ ድሮ ከስራ ስገባ አንተ ያለህበት ክፍል ገብቼ ላንተ መጫወቻዎችን ጣፋጭ ነገሮችን ስሰጥህ ነበር ።

ልጄ !!! ካሳለፍኳቸው ምርጥ ግዜያት ሁሉ ደስ የሚለኝ ዋና ላስለምድህ ገንዳ ውስጥ አንተን ተሸክሜ ምዋኝበት ግዜ ነበር።

ልጄ !!! ካሳለፍኳቸው ምርጥ ግዜያት ሁሉ ደስ የሚለኝ አንተ ህፃን እያለህ ቢሮ ይዤህ ስሄድ አንተም ቢሮ ውስጥ የሚጠቅሙኝን ወረቀቶች ስትቀዳድድብኝ በፍቅር ፈገግ እያልኩ የምመለከትህ ግዜ ነበር ።

ልጄ !!! በህይወቴ ካሳለፍኳቸው ምርጥ ግዜያት ሁሉ ደስ የሚለኝ ላንተ የምትፈልገውን ሁሉ ልብስ ልገዛ በኪሴ ያለውን ብር ባጠቃላይ ሳወጣ እና አንተ አምሮብህ እኔ ደሞ የተቀደደ ልብስ ስለብስ ነበር ።

ልጄ አሁን እኔ አንተን አልወቅስህም ። ነገር ግን በእንባ ተሞልቼ ይሄን ምፅፍልህ የኔ መጨረሻ እንዲህ ይሆናል ብዬ አስቤ ስለማላውቅ ነው ። የህይወቴ መጨረሻ ባንተ እቅፍ እንዲሆን ነበር ምኞቴ ። ውድ አባትህ" እንብቦ እንደጨረሰ እንባውን እያፈሰሰ ፀፀቱን ተሸክሞ ወጣ ።
___________
በህይወት እስካላችሁ ድረስ አባታችሁን እናታችሁን እያገለገላችሁ ኑሩ ። ""ቆም ብለክ አስብ አስቢ ።


ፌስቡክን ለመታወቅ ሳይሆን ያወቅነውን ለማሳወቅ እንጠቀም ፡፡ ማወቅ መልካም ነው ያወቁትን ማሳወቅ ደግሞ ፍፁም በጎነት ነው ፡፡ በምድር ላይ የምናደርጋቸው ነገሮች ሁሉ በሰማይ ላይ የዘላለም ደመወዝ ሆነው ይከፈሉናል ፡፡ ሁሌም ቢሆን ከክፋት ይልቅ በጎ በጎውን ነገር እናስብ መልካምነት ለራስ ነውና ፡፡

ስለዚህ አንተም ይህ አሁን ያነበብከው መጣጥፍ ትምህርት ሰጪ ሆኖ ካገኘኅው አንተም ዘመዶችህ እንዲያነቡትና ትምህርት እንዲወስዱ ዘንድ ሼር ያድርጉላቸው።
▬▬ Share ▬▬▬▬
ለተጨማሪ እውቀት እና ጠቃሚ የቴክኖሎጂ መረጃ ለማግኘት በዚ የቴሌግራም ቻናላችንን ከታች ባለዉን ሊንክ በመጫን ማግኘት ይችላሉ።
here it is
https://t.me/Information_Science_Technology
በተጨማሪም የዩቲዩብ ቻናላችንን Subscribe በማድርጉ ሌሎች መረጃዎች ይሸምቱ
┈┈┈┈••●◉❖◉●••┈┈┈
👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇
https://www.youtube.com/channel/UCpKx7Pd_viT9nnmheRu6o8Q

26/04/2021

በቅርብ ቀን የዞኑን የካፕታል ፕሮጀክት አፈፃፀም ይዘን እንቀርባለን፡፡
ላይክ ሼር ማድረግዎን አይርሱ!!

Address

Wolkite

Opening Hours

Monday 09:00 - 17:00
Tuesday 09:00 - 17:00
Wednesday 09:00 - 17:00
Thursday 09:00 - 17:00
Friday 09:00 - 17:00
Saturday 09:00 - 17:00
Sunday 09:00 - 17:00

Telephone

+251942539468

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Gurage Zone Plan and Economic Development Department posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Organization

Send a message to Gurage Zone Plan and Economic Development Department:

Share