11/04/2026
እንኳን ለጌታችንና ለመድሃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ የስቅለት እና ትንሳዔ በዓል አደርሳችሁ ፣ አደርሰን !!
➾ የትንሳኤ በዓል ጌታችንና መድሃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በምድር ላይ ለሰው ልጆች ደህንነት ሲል ያጋጠመውን መከራ፣ ይቅር ባይነት፣ ስቃይና ግርፋት በፅናት ተቋቁሞና ሞትን አሸንፎ የዲያብሎስን ቀንበር ሰብሮ የሰውን ልጅ ወደ ብርሃን ያሻገረበት የፅናት፣ የአሸናፊነትና የነፃነት በዓል ተምሳሌት ነው
➾ ትንሳዔ ኢየሱስ ክርስቶስ በሰሙነ ህማማት የተቀበላቸውን ግርፋት፣እርዛት፣ችንካር እና የእሾህ አክሊሊል በትዕግስት አልፎ በሰው ልጆች ሁሉ የሚታየውን ቀቢጸ ተስፋነት አስወግዶ የተስፋ ጮራ የዘራ ታላቅ የምስራች በዓል ነው ።
➾ የመረዳዳት፣የመደጋገፍና የመተባበር ባሕልና እሴት ባለቤት ሲሆን በዓሉን ሲከብር በሃይማኖቱ አስተምህሮ መሠረት የተቸገሩ ወገኖችን በማሰብ በአብሮነትና በመደጋገፍ የምናከብርው በዓል ነው ።
በመጨረሻም በዓሉ ከፍታን እና ርህራሄን የምናሳይበት፣እርስ በርስ የምንረዳዳበት፣ያለው ከሌለው ተባብሮ የሚያልፍበት በዓል እንዲሆን ከልብ እንመኛለን ።
" ባህላችን ለዘላቂ ሠላማችን "
የጉባላፍቶ ወረዳ ባህል ቱሪዝምና ስፖርት ፅ/ቤት