የሰሜን ወሎ ዞን ብልፅግና ፓርቲ ደጋፊዎች ገፅ

  • Home
  • Ethiopia
  • Woldia
  • የሰሜን ወሎ ዞን ብልፅግና ፓርቲ ደጋፊዎች ገፅ

የሰሜን ወሎ ዞን ብልፅግና ፓርቲ ደጋፊዎች ገፅ Prosperity party is ruling party committed to realize Ethiopia's PROSPERITY.

01/07/2025
01/07/2025
በአፋር እና አማራ ክልል አጎራባች ወረዳ ስለ ሰላም የሚመክር ውይይት ተካሄደ። ሰኔ 23/2017 ዓ.ምበሰሜን ወሎ ዞን በራያ ቆቦ ወረዳ በ023 ወርቄ ቀበሌ የአፋር አማራ እርቀ የሰላም ውይይ...
01/07/2025

በአፋር እና አማራ ክልል አጎራባች ወረዳ ስለ ሰላም የሚመክር ውይይት ተካሄደ።

ሰኔ 23/2017 ዓ.ም

በሰሜን ወሎ ዞን በራያ ቆቦ ወረዳ በ023 ወርቄ ቀበሌ የአፋር አማራ እርቀ የሰላም ውይይት ተካሂዷል።

በውይይቱ የሰሜን ወሎ ዞን መጂሊስ ሃላፊ ሸህ ሺኩር ሲራጂ ሙሃመድ፣ የራያ ቆቦ ወረዳ ዋና አስተዳዳሪ አቶ መኮነን አጥናፉ የአውራ ወረዳ ምክትል አስተዳዳሪና የሰላምና ፀጥታ ሃላፊ አቶ ሙሃመድ ኢብራሂም የአውራና የራያ ቆቦ አመራሮች፣ የሃይማኖት አባቶች፣ የሃገር ሽማግሌዎች፣የሰላም ኮሚቴወችና የአካባቢው ማህበረሰብ ተገኝተዋል።

የአፋር ክልል ከአማራ ክልል በደቡብና ሰሜን ወሎ በሰፋት እንደሚዋሰንና በራያ ቆቦ ወረዳም በዞን አራት አውራና ጎሊና ወረዳዎች ጋር እንደሚዋሰንም አውስተው በነዚህ አዋሳኝ ቀበሌወቹ በሚገኙ ህዝቦች መካከል በእንሰሳት ዘረፋ፣ በግጦሺ ሳር፣ በግድያ እንዲሁም በቂምና ጥላቻ ምክኒያት አላስፈላጊ ግጭት በተለያየ ጊዜ ሲፈጠር መቆየቱን የራያ ቆቦ ወረዳ ዋና አስተዳዳሪ አቶ መኮነን አጥናፉ ተናግረዋል።

በራያ ቆቦ አዋሳኝ የሚገኙ የአፋር ቀበሌ ነዋሪ ህዝቦች በጋብቻ፣ በስጋና በዘር የተዛመዱ ስለሆነ የእርስ በርስ መገዳደሉ እንደማያስፈልግና ከዚህ በፊት የነበር ቂምና ጥላቻን በመተው ዘላቂ ሰላም መምጣት አለበት ያሉት የአውራ ወረዳ ምክትል አስተዳዳሪና የሰላምናፀጥታ ሃላፊ አቶሙሃመድ ኢብራሂም ናቸው።

በውይይቱ የተገኙት የሰሜን ወሎ ዞን መጂሊስ ሃላፊ ሸህ ሺኩር ሲራጃ የተጀመረው የሁለቱ ክልሎች የህዝብ ውይይት እስከታችኛው ማህበረሰብ ድረስ ምክክር በማድረግ ዘላቂ ሰላም በማስፈን ህዝቦቹ በልማትና በመልካም አስተዳደር ማስተሳሰር ይገባል ብለዋል።

በውይይቱ ከሁለቱም ወረዳ የተወከሉ የሰላም ኮሚቴወችና የሃይማኖት አባቶች ከዚህ ቡኋላ ምንም አይነት ግጭት እንዳይፈጠር ማህበረሰቡን በማወያየት የተሻለ ሰራ በቁርጠኝነት እንሰራለን ሲሉ ቃል ገብተዋል።

ለራያ አላማጣ ወረዳ ነዋሪዎች የማዳበሪያ ስርጭት ተካሄደ፡፡ሰኔ 23/2017 ዓ.ምየሰሜን ወሎ ዞን ግብርናና ገጠር ልማት መምሪያ ለራያ አላማጣ አርሶ አደሮች ዩርያ 1127 ኩንታል እና ዳፕ 3...
30/06/2025

ለራያ አላማጣ ወረዳ ነዋሪዎች የማዳበሪያ ስርጭት ተካሄደ፡፡

ሰኔ 23/2017 ዓ.ም

የሰሜን ወሎ ዞን ግብርናና ገጠር ልማት መምሪያ ለራያ አላማጣ አርሶ አደሮች ዩርያ 1127 ኩንታል እና ዳፕ 355 ኩንታል
በአጠቃላይ 1482 ኩንታል ማዳበሪያ በወረዳው ለሚገኙ 5 ቀበሌዎች ውስጥ ለ1330 አርሶ አደሮች የተሰራጨ መሆኑን የወረዳው የግብርና ጽ/ቤት ኋላፊ አቶ ጣውየ ግዴ ተናግረዋል፡፡

ነፍጥ አንግበው በጫካ ሲንቀሳቀሱ የነበሩ የታጠቁ ሃይሎች በሰላማዊ መንገድ እጅ  ሰጡ። በሰሜን ወሎ በጋዞ   ራሱን የአማራ ፋኖ  ወሎ ዕዝ  የደጋው መብረቅ ክ/ጦ ብሎ የሚጠራው ቡድን አባል ...
30/06/2025

ነፍጥ አንግበው በጫካ ሲንቀሳቀሱ የነበሩ የታጠቁ ሃይሎች በሰላማዊ መንገድ እጅ ሰጡ።

በሰሜን ወሎ በጋዞ ራሱን የአማራ ፋኖ ወሎ ዕዝ የደጋው መብረቅ ክ/ጦ ብሎ የሚጠራው ቡድን አባል የነበረ
1 አቶ በየነ ሁንያለው ከአንድ ሰደፍ ክላሽና 18መሰል ጥይት ይዞ
2 እባቡ ማርየ የአባት አርበኛ ሰብሳቢ ጀሌውን
3 ረ/ሳ ካህሊው ርዕይ ኢሳያስ የጥናት ሻለቃ አስተዳደር የነበረ ጀሌውን መንግሰት የሰጠውን የሰላም አማራጭ በመቀበል ለወረዳው የፀጥታ ሃይል እጃቸውን ሰጥተዋል ።

መንግስት አሁንም ለሰላም በሩ ክፍት በመሆኑ ታጥቃችሁ በጫካ ያላችሁ ታጣቂዎች ለሰላም ቅድሚያ በመስጠት እጃችሁን እንዲትሰጡ ዛሬም ጥሪ እያስተላለፉ ነው !!!

30/06/2025
29/06/2025

Address

Woldia

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when የሰሜን ወሎ ዞን ብልፅግና ፓርቲ ደጋፊዎች ገፅ posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Share