የወልድያ ከተማና መሰረተ ልማት መምሪያ

የወልድያ ከተማና መሰረተ ልማት መምሪያ የተሟላ መሰረተ ልማት በከተማችን በመዘርጋት ወልድያን ተመራጭ ከተማ እናደርጋለን!!

11/04/2026
የወልድያ ከተማ አስተዳደር ተቀዳሚ ምክትል ከንቲባ የእንኳን አደረሳችሁ መልክት
10/04/2026

የወልድያ ከተማ አስተዳደር ተቀዳሚ ምክትል ከንቲባ የእንኳን አደረሳችሁ መልክት

1 ሺህ 447ኛው የዒድ አል ፈጥር በዓል በወልድያ ከተማ በደማቁ  ተከበረ ።የወልድያ ከተማ አስተዳደር ተቀዳሚ ምክትል ከንቲባ አቶ ዱባለ አብራሬ በበዓሉ ላይ ተገኝተው የእንኳን አደረሳችሁ መ...
20/03/2026

1 ሺህ 447ኛው የዒድ አል ፈጥር በዓል በወልድያ ከተማ በደማቁ ተከበረ ።

የወልድያ ከተማ አስተዳደር ተቀዳሚ ምክትል ከንቲባ አቶ ዱባለ አብራሬ በበዓሉ ላይ ተገኝተው የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት አስተላልፈዋል።

ህዝበ ሙስሊሙ በረመዳን ወር ሲሰራው የነበረውን የመረዳዳት ፣ የመጠያየቅ፣ የመደጋገፍ እና ለአላህ የመታዘዝን የተቀደሰ ተግባር በበዓሉም ሊያስቀጥሉ ይገባል ብለዋል።

ሀገራችን በሁሉም መስክ ህክምና የምታደርግበት ፈታኝ ጊዜዋ ነው ያሉት ከንቲባው ለአንዲት ሀገራችን ሀገራዊ ጥሪ በአንድነት ሀገራዊ ምላሽ በመስጠት የብልጽግና ጉዛችን ማረጋገጥ ይገባናል ሲሉ ተደምጠዋል።

ከንቲባው አክለውም ከተማችን ከጉስቁልናዋ በማላቀቅ ለኗሪዎቿ ምቹ ለማድረግ የተለያዩ ልማቶች እየተሰሩ መሆኑን ገልጸው ህዝበ ሙስሊሙም ሆነ የከተማዋ ኖሪዎች ሁለንተናዊ አስተዋጽኦ እና ድጋፍ እንዲያበረክቱ ጥሪ አስተላልፈዋል።

በዓሉን ሲያከብር ያገኘነው ካሊድ አብዱ አሊ የወልድያ ሙስሊም ወጣቶች ካውንስል ከህብረተሰቡ በመሰብሰብ ለተቸገሩ በመርዳት ረመዳንን ሲያፈጥሩ እንደነበር ገልጸው በበዓሉም መጠያየቃችን ይቀጥላል ነው ያለው።

ለመላው የእስልምና እምነት ተከታዬችም የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት አስተላልፏል።

በበዓሉ ላይ የአብክመ እስልምና ጉዳይ ከፍተኛ ምክር ቤት የሐጂና ኡምራ ዘርፍ ኀላፊ ሸህ ማህመድ ኑርየ ፣ የወልድያ ከተማ አስተዳደር ተቀዳሚ ምክትል ከንቲባ አቶ ዱባለ አብራሬ ፣የወልድያ ከተማ የእስልምና ምክር ቤት መሪዎች፣ ታላላቅ የእምነቱ አባቶች የሃይማኖቱ ተከታዮች እና ተጋባዥ እንግዶች ተገኝተዋል።

ለመላው የእስልምና እምነት ተከታዮችእንኳን ለ1447ኛው የኢድ አል ፈጥር በዓል አደረሳችሁ!ኢድ ሙባረክ!በዓሉ የሰላም፤ የፍቅር፤ የአንድነት እንዲሆን እመኛለሁ!አቶ ዱባለ አብራሬየወልድያ ከተማ...
19/03/2026

ለመላው የእስልምና እምነት ተከታዮች
እንኳን ለ1447ኛው የኢድ አል ፈጥር በዓል አደረሳችሁ!

ኢድ ሙባረክ!

በዓሉ የሰላም፤ የፍቅር፤ የአንድነት እንዲሆን እመኛለሁ!

አቶ ዱባለ አብራሬ
የወልድያ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ

የከንቲባችን ቀጣይ የልማት ጉዞ መዳረሻ ምን ይሆን ይሆን??? የወልድያ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ  አቶ ዱባለ አብራሬ ስራ ከጀመሩበት እለት ጀምሮ ከተማዋን ለመለወጥ በርካታ ማህበራዊ እና ኢኮ...
16/03/2026

የከንቲባችን ቀጣይ የልማት ጉዞ መዳረሻ ምን ይሆን ይሆን???

የወልድያ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ አቶ ዱባለ አብራሬ ስራ ከጀመሩበት እለት ጀምሮ ከተማዋን ለመለወጥ በርካታ ማህበራዊ እና ኢኮኖሚያዊ ፕሮጀክቶች እንዲሰሩ የአደረጉ ሲሆን ከእነዚህ ውስጥም በግንባታ ላይ ያሉ እና የተጠናቀቁ ፕሮጀክቶች መካከል የተወሰኑት

👉የ30ሜ ቀለበት መንገድ ፕሮጀክት ስራ
👉ቁሞ የነበረውን የአስፓልት መንገድ ማስጀመር እና አፈጻጸሙን 95%መድረስ መቻል
👉የኮሪደር ልማት ፕሮጀክት በ3ቱም ክፍለ ከተማ
👉 ለስራ አጥ ዜጓች ለተለያዩ አገልግሎት የሚውሉ ሼዶች ግንባታ
👉የዶ/ር አረጋ ይርዳው አደባባይ እና የሆስፒታል ድልድይ ጥገና ስራዎች
👉የአያሙሌ ቤተመጽሃፍት ግንባታ
👉የንግድ ማዕከል ግንባታ
👉የሳይንስ ካፌ ግንባታ ስራ
👉የመሳለሚያ ጤና ጣቢያ ግንባታ
👉የመላካ ቆሌ ት/ቤት ተጨማሪ የመማሪያ ብሎክ እና አጥር ግንባታ
👉የኢሚግሬሽን እና ዜግነት አገልግሎት በከተማችን ስራ እንዲጀምር ማስጀመር
👉የሲቲ ስካን ማሽን ማስመጣት እና ስራ ማስጀመር
👉የመሶብ አገልግሎት ግንባታ
👉የስማርት ሲቲ ፕሮጀክት ስራ
👉የየጁ ገበታ የወንዝ ዳር ልማት ፕሮጀክት ዲዛይን ስራ
👉የታላቁ ራስ አሊ አደባባይ ግንባታ ዲዛይን እና ቦታ እርክክብ
👉የአፓርታማ ግንባታ ለማስጀመር የዲዛይን ስራ
👉የወልድያ መነሃሪያ ግንባታ ለማስጀመር የዲዛይን ስራ
👉የድጅታል አድራሻ ስርዓት ትግበራ ማስጀመር
👉የኤሌክትሪክ አውቶብሶች ወደ ከተማችን በማስመጣት እና ኤሌክትሪክ ቻርጅ በመትከል ስራ ማስጀመር
👉የገጠር ቀበሌዎች የ24 ሰዓት የመብራት እና የንጹህ መጠጥ ውሃ ተጠቃሚ ማድረግ
👉 የገጠር ቀበሌዎችን እርስ በእርስ እና ከከተማው ጋር እንዲገናኙ የጠጠር መንገድ ስራዎች ተጠቃሾች ሲሆኑ
አሁን ደግሞ የከተማዋ መገለጫ የሆነውን :-
👉 የሸህ መሀመድ ሁሴን አላሙዲ ስታዲየም ለማስጠገን ጥገነውን ለአብከመ ወጣቶች እና ስፖርት እስረክበዋል ።
ቀጠዩ ፕሮጀክታቸው የወልድያ እና አጓራባች ከተሞች ህዝብ የማያነሱት የዘወትር ጥያቄ የወልድያ ኤር ፖርት ይሆን ይሁን ???

የወልድያ ከተማና መሰረተ ልማት መምሪያ
መጋቢት 7/2018

የወልድያ ሽህ ሙሐመድ ሁሴን አሊ አላሙዲን ስታዲዬም ከሦስተኛ ወገን ነጻ ተደርጎ  ከክልሉ መንግስት ጋር ለጥገና ርክክብ ተደረገ። በርክክቡ የወልድያ ከተማ አስተዳደር ተቀዳሚ ምክትል ከንቲባ ...
16/03/2026

የወልድያ ሽህ ሙሐመድ ሁሴን አሊ አላሙዲን ስታዲዬም ከሦስተኛ ወገን ነጻ ተደርጎ ከክልሉ መንግስት ጋር ለጥገና ርክክብ ተደረገ።

በርክክቡ የወልድያ ከተማ አስተዳደር ተቀዳሚ ምክትል ከንቲባ አቶ ዱባለ አብራሬ ስታዲየሙን ቶሎ ብሎ ወደ ስራ ለማስገባት የክልሉ መንግስት አስፈላጊ ሁኔታዎችን በፍጥነት እንዲመቻች ጠይቀዋል።

የአብክመ ባህልና ቱሪዝም ስፖርት ቢሮ ኃላፊ አቶ መልካሙ ፀጋዬ ስቴዲዬሙ የደረሰበትን ጉዳት ለመመለስ የተለያዩ ስራዎችን እንደጀመሩ ገልፀው ጥገናውን በአጭር ጊዜ ለማከናዎን ወደ ሥራ እንገባለን ብለዋል።

በኢ.ፌ.ዲ.ሪ የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት  የሰሜን ውሎ ዞን ተመራጭ የህዝብ እንደራሴዎች  እና የበጀትና ፋይናንስ ቋሚ ኮሚቴ ሰብሳቢ  እንዲሁም የኮሚቴው አባለት በወልድያ ከተማ አስተዳዳር ...
05/03/2026

በኢ.ፌ.ዲ.ሪ የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የሰሜን ውሎ ዞን ተመራጭ የህዝብ እንደራሴዎች እና የበጀትና ፋይናንስ ቋሚ ኮሚቴ ሰብሳቢ እንዲሁም የኮሚቴው አባለት በወልድያ ከተማ አስተዳዳር የተሰሩትን የመሰረተ ልማት ስራዎችን
1. የንግድ ማዕከል
2.አያሙሌ ቤተመጽሀፍት
3.ሳይስ ከፌ
4.የኮሪደር ልማት ስራዎች
5.የመሸጫ ሱቆች
6.የመሶብ አገልግሎት መስጫ ግንባታ እና ሌሎችንም ስራዎች ጉበኝት አደረጉ

ቀን 20/06/2018 ዔ/ም 4ኛ ዙር የመሬት ሊዝ ጨረታ ማስተዋቂያ የወልድያ ከተማና መሰረተ ልማት መምሪያ የከተማ ቦታን በሊዝ ስለመያዝ በሚደነግገው  አዋጅ ቁጥር 721/2004 አንቀጽ 8 ...
27/02/2026

ቀን 20/06/2018 ዔ/ም

4ኛ ዙር የመሬት ሊዝ ጨረታ ማስተዋቂያ

የወልድያ ከተማና መሰረተ ልማት መምሪያ የከተማ ቦታን በሊዝ ስለመያዝ በሚደነግገው አዋጅ ቁጥር 721/2004 አንቀጽ 8 ንዑስ አንቀጽ 1 መሰረት በበጀት አመቱ 4ኛ ዙር የሊዝ ጨረታ ለንግድ እና ለመኖሪዬ አገልግሎት የሚውሉ ቦታዎችን አዘጋጅቶ ለተጫራቾች አቅርቧል።
በመሆኑም እነዚህን ቦታዎች በሊዝ ጨረታ ለመሳተፍ የሚፈለግ ማንኛውም አካል ከ20/06/2018 ዓ.ም ጀምሮ እስከ 04/ 07/2018 ዓ/ም በአሉት 10 ተከታታይ የስራ ቀናት የቦታውን ዝርዝር መረጃ እና የጨረታ ሰነድ የማይመለስ ብር 1000.00/ አንድ ሽህ ብር /ጓማጣ ጉባላፍቶ ፖሊስ ጣቢያ ጎን የድሮው ከንቲባ ጽ/ ቤት ከነበረው የከተማ መሬት ግብይት እና አሰጣጥ ቡድን ዘወትር በስራ ሰአት በመምጣት በመግዛት መወዳደር የምትችሉ መሆኑን እንገልጻለን፡፡

የወልድያ ከተማና መሰረተ ልማት መምሪያ
የካቲት 20/2018 (ወልድያ)

የወልድያ ከተማ አስ/ር የዲጅታል አድራሻ ስርአት ስራ የንቅናቄ መድረክ አካሄደ። የወልድያ ከተማ አስተዳደር የዲጅታል አድራሻ ስርአት የማስጀመሪያ የንቅናቄ መድረክ እና ግንዛቤ ማስጨበጫ ዉይይ...
22/02/2026

የወልድያ ከተማ አስ/ር የዲጅታል አድራሻ ስርአት ስራ የንቅናቄ መድረክ አካሄደ።

የወልድያ ከተማ አስተዳደር የዲጅታል አድራሻ ስርአት የማስጀመሪያ የንቅናቄ መድረክ እና ግንዛቤ ማስጨበጫ ዉይይት የወልድያ ከተማ አስተዳደር ተ/ም/ ከንቲባ አቶ ዱባለ አብራሬ እና በብልጽግና ፓርቲ የወልድያ ከተማ አስተዳደር ብልጽግና ፓርቲ ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ተስፋየ ገብሬ መድረኩን በመምራት ከጠቅላላ አመራሩ ጋር ውይይት ተካሂዷል።

በዚህ የድጅታል አድራሻ ስርአት ከተማችን ለጀመረችው የስማርት ሲቲ ተግባር የላቅ አስተዋጾ የአለው ሲሆን
#.ለኦለይን አገልግሎት/ delivery /
#.ቀልጣፋ የአንቡላንስ አገልግሎት ለመስጠት
#.የእሳት አዳጋ ሲከሰት ቶሎ ለመድረስ
#.የንግድ አገልግሎቱን ቀልጣፋ ለማድረግ
#.የታክስ ስርአቱን በአድራሻ ለመምራት እና ለማዘመን
#.ለቱሪስት አገልግሎት
#.ለሆቴሎች
በአጠቃላይ የተማችንን የድጅታላይዜሽን ስራ የሚያቀላጥፍ ሲሆን በከተማው ውስጥ ያሉ ዋና ዋና አደባባዮች፤ መንገዶች ፣መንግስታዊ እና መንግስታዊ ያልሆኑ ተቋማት ፤የሃይመኖት ተቋማት፤ የድርጅት እና የመኗሪያ ቤቶች ምዝገባ እና ኮድ የመስጠት ስራ የሚሰራ ሲሆን ይህንን ስራ የሚሰሩ ባለሙያዎች ለሚያደርጉት ስምሪት ሁሉም አመራርና መላው ማህበረሰብ የድርሻውን እንዲወጣ ጥሪ ቀርቧል።

የወልድያ ከተማ አስተዳደር ተ/ም ከንቲባ አቶ ዱባለ አብራሬ በ2ኛው ዙር እየተሰሩ የአሉትን :-1.ከጎንደር በር እትጌ መዝናኛ2.ከአዳጎ ጣይቱ ብጡል ኮሪደር ልማት ስራዎች *.የከተማና መሰረተ...
20/02/2026

የወልድያ ከተማ አስተዳደር ተ/ም ከንቲባ አቶ ዱባለ አብራሬ በ2ኛው ዙር እየተሰሩ የአሉትን :-
1.ከጎንደር በር እትጌ መዝናኛ
2.ከአዳጎ ጣይቱ ብጡል
ኮሪደር ልማት ስራዎች
*.የከተማና መሰረተ ልማት መምሪያ ኃላፊዎች
*.የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት የወልድያ ድስትሪክት ኃላፊዎች
*.የወልድያ ዉሃና ፍሳሽ አገልግሎት ኃላፊዎች
*.ስራዎን የሚሰሩ ኮንትራክተሮች
*.የክፍለ ከተማ አመራሮች እ
*.የቀበሌ አመራሮቸሸን እና ሌሎች የሚመለከታቸው አካላት ጋር በመሆን የመስክ ጉብኝት አደረጉ።
ከንቲባው በመስክ ጉብኝታቸው ስራውን በአጭር ጊዜ ለማጠናቀቅ እንዲቻል በስራው ላይ የአገጠሙ ችግሮችን እንዲፈቱ ለሚመለከታቸው አካላት መመሪያ የሰጡ ሲሆን በአጠቃላይ የኮሪደር ልማት ስራው በጥሩ ሁኔታ ላይ የሚገኝ በመሆኑ ተጠናክሮ እንዲቀጥል አሳስበዋል።
የካቲት 13/2018 ዓ/ም

የወልድያ ከተማ አስተዳደር ምክር ቤት ለወልድያ ከተማ አስተዳደር ተቀዳሚ ምክትል ከንቲባ አቶ ዱባለ አብራሬ እውቅና እና  ሽልማት ሰጠ።ም/ቤቱ ባከሄደው  4ኛ ዙር 13ኛዓመት 40ኛ መደበኛ ጉ...
14/02/2026

የወልድያ ከተማ አስተዳደር ምክር ቤት ለወልድያ ከተማ አስተዳደር ተቀዳሚ ምክትል ከንቲባ አቶ ዱባለ አብራሬ እውቅና እና ሽልማት ሰጠ።

ም/ቤቱ ባከሄደው 4ኛ ዙር 13ኛዓመት 40ኛ መደበኛ ጉባኤው ላይ የሰጠው እውቅና እና ሽልማት የተከበሩ አቶ ዱባለ አብራሬ በከተማዋ ለአመጡት ዘረፈ ብዙ ማህበራዊ እና ኢኮኖሚያዊ ለወጥች ነው።

3ኛ ዙር የመሬት ሊዝ ጨረታ ማስተዋቂያ የወልድያ ከተማና መሰረተ ልማት መምሪያ የከተማ ቦታን በሊዝ ስለመያዝ በሚደነግገው  አዋጅ ቁጥር 721/2004 አንቀጽ 8 ንዑስ አንቀጽ 1 መሰረት በበ...
11/02/2026

3ኛ ዙር የመሬት ሊዝ ጨረታ ማስተዋቂያ

የወልድያ ከተማና መሰረተ ልማት መምሪያ የከተማ ቦታን በሊዝ ስለመያዝ በሚደነግገው አዋጅ ቁጥር 721/2004 አንቀጽ 8 ንዑስ አንቀጽ 1 መሰረት በበጀት አመቱ 3ኛ ዙር የሊዝ ጨረታ ለንግድ እና ለመኖሪዬ አገልግሎት የሚውሉ ቦታዎችን አዘጋጅቶ ለተጫራቾች አቅርቧል።
በመሆኑም እነዚህን ቦታዎች በሊዝ ጨረታ ለመሳተፍ የሚፈለግ ማንኛውም አካል ከ05/06/2018 ዓ.ም ጀምሮ እስከ 18/ 06/2018 ዓ/ም በአሉት 10 ተከታታይ የስራ ቀናት የቦታውን ዝርዝር መረጃ እና የጨረታ ሰነድ የማይመለስ ብር
1000.00/ አንድ ሽህ ብር /ጓማጣ ጉባላፍቶ ፖሊስ ጣቢያ የድሮው ከንቲባ ጽ/ ቤት ከነበረው የከተማ መሬት ግብይት እና አሰጣጥ ቡድን ዘወትር በስራ ሰአት በመምጣትበመግዛት መወዳደር የምትችሉ መሆኑን
እንገልጻለን፡፡

የወልድያ ከተማና መሰረተ ልማት መምሪያ

የካቲት 04/2018 (ወልድያ)

Address

Woldia

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when የወልድያ ከተማና መሰረተ ልማት መምሪያ posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Share