North wollo industry and investment department

North wollo industry and investment department Investment promotion service

11/03/2026

የሰሜን ወሎ ዞን ኢንዱስትሪ እና ኢንቨስትመንት መምሪያ የ መስክ ሪፖርት በመገምገም ላይ ይገኛል ።

በሰሜን ወሎ ዞን በበጀት አመቱ ሰባት ወራት ከ10 ቢሊየን ብር በላይ ካፒታል ላስመዘገቡ ባለሃብቶች የኢንቨስትመንት ፍቃድ መሰጠቱ ተገለፀ።ወልደያ:- የካቲት 21/2018 ዓ/ም  በሰሜን ወሎ ...
28/02/2026

በሰሜን ወሎ ዞን በበጀት አመቱ ሰባት ወራት ከ10 ቢሊየን ብር በላይ ካፒታል ላስመዘገቡ ባለሃብቶች የኢንቨስትመንት ፍቃድ መሰጠቱ ተገለፀ።

ወልደያ:- የካቲት 21/2018 ዓ/ም በሰሜን ወሎ ዞን በተያዘው በጀት ዓመት ያለፉት ሰባት ወራት ከ10 ቢሊየን ብር በላይ ካፒታል ላስመዘገቡ ባለሃብቶች የኢንቨስትመንት ፍቃድ መስጠት መቻሉን የዞኑ ኢንዱስትሪና ኢንቨስትመንት መምሪያ አስታወቀ።

በሃራ ከተማ አስተዳደር " ኢትዮጵያ ታምርት እኛም እንሸምት" ዞናዊ ማጠቃለያ መርሃ ግብር ተካሂዷል።

በዚሁ የማጠቃለያ መርሃ ግብር ወቅት የሰሜን ወሎ ዞን ኢንዱስትሪና ኢንቨስትመንት መምሪያ ኃላፊ አቶ ሞላ ደሱ በበጀት አመቱ ሰባት ወራት ከ10 ነጥብ 79 ቢሊየን ብር በላይ ካፒታል ላስመዘገቡ 146 አልሚ ባለሃብቶች ፈቃድ መውሰዳቸውን ተናግረዋል።

ፈቃድ የወሰዱ አልሚዎች ምርት ማምረት ሲችሉ ለ32 ሺህ ዜጎች የስራ እድል መፍጠር እንደሚችሉም ገልፀው በበጀት ዓመቱ ሰባት ወራት ብቻ ለ2 ሺህ 832 ስራ ፈላጊዎች በጊዚያዊና በቋሚ መፈጠር ተችሏል ብለዋል።

በበጀት ዓመቱ ሰባት ወራት ለአልሚዎች የተሰጠው ፍቃድ በማኑፋክቸሪንግ፣ በአገልግሎት፣ በማዕድን፣ በኮንስትራክሽን፣ በሆቴልና ቱሪዝም፣ በትምህርትና በግብርና ዘርፎች መሆኑን የገለፁት አቶ ሞላ ለእነዚህ የልማት ዘርፎችም 176 ነጥብ 78 ሄክታር መሬት በሳይት ፕላን ለኢንቨስትመንት መመላከት መቻሉን ተናግረዋል።

የኢትዮጵያ ታምርት እኛም እንሸምት መርሃ ግብር ለኢንቨስትመንት ፍሰቱ መጨመር አስተዋጽኦ እያበረከተ ነውም ብለዋል።

በዞኑ ኢንቨስት ለሚያደርጉ ባለሃብቶች ልዩ ድጋፍ መደረጉን የተናገሩት ደግሞ የሰሜን ወሎ ዞን ብልፅግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ከድር ሙስጦፋ ናቸው።

ባለሃብቶች የሚሰጣቸውን መሬት ለታለመለት ዓላማ በፍጥነት እንዲያውሉ ድጋፍና ክትትል እየተደረገ እንደሚገኝ የገለፁት አቶ ከድር በኢንቨስትመንት ዘርፍ የሚታይ የአገልግሎት አሰጣጥ ችግሮችን ለመፍታትም በቅንጅት እንደሚሰራ አስረድተዋል።

ኢንቨስትመንት ያለ ዘላቂ ሰላም ውጤታማ አይሆንም ያሉት አቶ ከድር ለአካባቢው ሰላም መምጣት የሁሉም ሰው ቅንጅታዊ ስራ ተጠናክሮ ሊቀጥል እንደሚገባ ተናግረዋል።

የአማራ ክልል ፕላንና ልማት ቢሮ ምክትል ኃላፊ አቶ ጥላሁን ፈንታው በበኩላቸው ለኢንዱስትሪ ልማት የሚለዩ ቦታዎች በጥንቃቄ እንድለዩ ሊሰራ ይገባል ብለዋል።

በአምራች ኢንዱስትሪው ዘርፍ አላሰራ የሚሉ ማነቆዎችን በመፍታት አልሚዎች ተጠቃሚ እንድሆኑ ለማድረግ በተለይ የብድር አገልግሎትና የመሬት አቅርቦትን ፈጣን ምላሽ መስጠት ከአመራሩ ይገባል ያሉት የአማራ ክልል መሬት ቢሮ ምክትል ኃላፊ አቶ ሰይፉ ሰይድ ናቸው።

በማጠቃለያ መርሀ ግብሩ የተሳተፉ አልሚ ባለሃብቶች እየገጠማቸው ያሉ የግንባታ ማቴሪያል፣ የወለድ አልባ ብድርና የከተማው የመስሪያ ቤት መዋቅር ችግር እንድፈታ መንግስትን ጠይቀዋል።

በሆቴል ቱሪዝም ዘርፍ በተሰጣቸው ምቹ ቦታ ላይ ከ21 ሚሊዮን ብር በላይ ወጭ በማድረግ የነዳጅ ማደያ ገንብተው ያጠነቀቁት አቶ ሙስጦፋ ሞላ ማደያውን አገልግሎት ለማስጀምር መዘጋጀታቸውን ተናግረዋል።

በዞናዊ "ኢትዮጲያ ታምርት እኛም እንሸምት" ማጠቃለያ መርሃ ግብር በሃራ ከተማ እየተሰሩ ያሉ የወልደያ ሙስሊሞች አትክልትና ፍራፍሬ ልማት፣ የነዳጅ ማደያ ግንባታና በቀጣይ ሊሰራ የታቀደለትን የላስቴ ገራዶ 122 ሄክታር መሬት ስፋት ያለውን የኢንዱስትሪ መንደር ተጎብኝቷል።

የሰሜን ወሎ ዞን ኢንዱስትሪና ኢንቨስትመንት መምሪያ የ2018ዓ.ም ኢትዮጵያ ታምርት እኛም እንሸምት ዞናዊ የማጠቃለያ መድረክ ቅደመ ዝግጅት ሥራ ሀራ ከተማ
27/02/2026

የሰሜን ወሎ ዞን ኢንዱስትሪና ኢንቨስትመንት መምሪያ የ2018ዓ.ም ኢትዮጵያ ታምርት እኛም እንሸምት ዞናዊ የማጠቃለያ መድረክ ቅደመ ዝግጅት ሥራ

ሀራ ከተማ

ቀን 6/06/2016የሰሜን ወሎ ዞን ኢንዱስትሪ እና ኢንቨስትመንት መምሪያ በወቅታዊና መደበኛ ተግባራት ዙሪያ በ ሀራ ከተማ አሰተዳደር በቸክሊስት የተደገፈ ልዩ ድጋፍ ተደርጓል ።
13/02/2026

ቀን 6/06/2016
የሰሜን ወሎ ዞን ኢንዱስትሪ እና ኢንቨስትመንት መምሪያ በወቅታዊና መደበኛ ተግባራት ዙሪያ በ ሀራ ከተማ አሰተዳደር በቸክሊስት የተደገፈ ልዩ ድጋፍ ተደርጓል ።

13/02/2026
ቀን 5/06/2016የሰሜን ወሎ ዞን ኢንዱስትሪ እና ኢንቨስትመንት መምሪያ በወቅታዊና መደበኛ ተግባራት ዙሪያ በቆቦ ከተማ አሰተዳደር በቸክሊስት የተደገፈ ልዩ ድጋፍ አደረገ ።
13/02/2026

ቀን 5/06/2016
የሰሜን ወሎ ዞን ኢንዱስትሪ እና ኢንቨስትመንት መምሪያ በወቅታዊና መደበኛ ተግባራት ዙሪያ በቆቦ ከተማ አሰተዳደር በቸክሊስት የተደገፈ ልዩ ድጋፍ አደረገ ።

የራያ ቆቦ ወረዳና የቆቦ ከተማ አስተዳደር በጋራ < ኢትዩጲያ ታምርት እኛም እንሸምት >  በሚል መሪ ቃል የባለሃፍቶችና የባለድርሻ አካላት የንቅናቄ መድርክ ጥር 30 /018 ዓ/ም አካሄዱ ።...
08/02/2026

የራያ ቆቦ ወረዳና የቆቦ ከተማ አስተዳደር በጋራ < ኢትዩጲያ ታምርት እኛም እንሸምት > በሚል መሪ ቃል የባለሃፍቶችና የባለድርሻ አካላት የንቅናቄ መድርክ
ጥር 30 /018 ዓ/ም አካሄዱ ።
በመድረኩ አጋር አካላት - ባንኮች ፣የሃይማኖት አባቶች ፣ ባለሃፍቶች እና የራያ ቆቦ ወረዳ ስራ አስፈጻሚወችና እና የሚመለከታቸው አመራሮች እንዲሁም የቆቦ ከተመ አስተዳደር ሁሉም ስራ አስፈጻሚወችና የሚመለከታቸው አመራሮች ተገንተዋል ።
በመድረኩ የመወያያ ሰነድ ቀርቦ ውይይት የተደረገ ሲሆን
መድረኩን የራያ ቆቦ ወረዳ ዋና አስተዳዳሪ አቶ መኮነን አጥናፊ የቆቦ ከተማ ዋና ከቲባ አቶ ሃይላብ ወንድሙ እና የሁቱ ወረዳ ኢንዱስትሪና ኢንቨስትመንት ጽ/ቤት ሃላፋወች በጋራ መርተውታል
በውይይቱ የተለያዩ ሃሳበች የተነሱ ሲሆን ዋና ዋናወቹ
✔️ሁሉም መሬት የወሰደ ባለሃፍት ወደ ስራ መግባት አለበት ወደ ስራ በማይገቡ በላሃፍቶች በመመሪያው መሰረት እርምጃ መወሰድ አለበት
✔️ ወደ ስራ ለመግባት መሰረተ ልማቶች መሟላት መቻል አለበት እና ሌሎቹም ተነስተው የማደማደሚያ ሃሳብ ተሰጥቶ በመጨረሻም የተሻለ አፈጻጸም ያላቸው ባላሃፍቶች የውቅና የመስክር ወረቅት ተሰጥቷቸዋል
===ኢትዩጲያ ታምርት እኛም እንሸምት=====

የጉባላፍቶ ወረዳ ኢንዱስትሪና ኢንቨስትመንት ፅ/ቤት   > በሚል መሪ ቃል የኢትዮጵያ ታምርት የባለ ሀብት ንቅናቄ መድረክ አካሄደ።የወረዳው የኢንቨስትመንት ፍሰት እንዲሻሻል ሁሉም ባለድርሻ አ...
08/02/2026

የጉባላፍቶ ወረዳ ኢንዱስትሪና ኢንቨስትመንት ፅ/ቤት > በሚል መሪ ቃል የኢትዮጵያ ታምርት የባለ ሀብት ንቅናቄ መድረክ አካሄደ።
የወረዳው የኢንቨስትመንት ፍሰት እንዲሻሻል ሁሉም ባለድርሻ አካላት የራሳቸውን አስተዋጽኦ ማበርከት እንደሚጠበቅባቸውም ተገልጿል ።

ወልዲያ፦ ጥር /2018 ዓ.ም

የጉባላፍቶ ወረዳ ኢንዱስትሪና ኢንቨስትመንት ጽ/ቤት "ኢትዮጵያ ታምርት እንኛም እንሸምት" በሚል ሀሳብ ከባለሀብቶች፣ከአጋርና ባለድርሻ አካላት ጋር የንቅናቄ መድረክ አካሂዷል። በመድረኩ "ኢትዮ ታምርት እኛም እንሸምት" ንቅናቄ ያመጣው ለውጥ በስፋት ቀርቧል።

የጉባላፍቶ ወረዳ ኢንቨስትመንትና ኢንዲስትሪ ጽ/ቤት ሀላፊ አቶ አለሙ ሹምየ የወረዳው ኢንቨስትመንት እንዲሻሻል ሁሉም ባለድርሻ አካላት የራሳቸውን አስተዋፅኦ ማበርከት እንዳለባቸው ገልፀው አምራች አካላት በወረዳው ተሰማርተው በመስራት ለማህበረሰባችን አቅም እንድተሆኑና የማልማት ስራ እንድትሰሩ ብለዋል።

ጉባላፍቶ ወረዳ የብዙ ፀጋ ባለቤት እነደሆነ የገለፁት አቶ አለሙ በወረዳው ለኢንቨስትመንት ምቹ የሆኑ የተጠኑና የተለዩ መሬቶች በመኖራቸው በማዕድን ሀብት ፣ በእንጨትና ብረታብረት ፣በውሃ ሀብት፣ በአትክልትና ፍራፍሬ ምርት እና በሌሎችም በወረዳችን የተዘጋጁ በርካታ የኢንቨስትመንት አማራጮችን ተጠቅማችሁ እንድትሰሩ ሲሉ ጥሪያቸውን አስተላልፈዋል።

የጉባላፍቶ ወረዳ ምክትል ዋና አስተዳዳሪ አቶ ሀብታሙ በየነ የጉባላፍትቶ ወረዳን ፀጋ ወስዶ አጥሮና ከልሎ በመያዝ እንዲሁም ቦታውን ለታለመለት አላማ ባለማዋል የምትንቀሳቀሱ አካላት በመገፋፋት የሚመጣ ለውጥ ስሌለ ችግሮችን በመፍታት፣በመደጋገፍ የተመሰረተ ልማት ማልማትና መሰራት ይጠበቅብናል በማለት አሳስበዋል።

የውይይቱ ተሳታፊዎች በበኩላቸው የፀጥታው ሁኔታ፣ የባንኮች ቶሎ ብድር አለመስጠት እና የወለድ ከፍ ማለት የጀመርነውን የኢንቨስትመንት ስራ ለመሰራት ማነቆ ሆኖብናል ያሉ ሲሆን የወረዳው የኢንቨስትመንት ቦርድ አባላት ከባንኮች ጋር ትስስር ፈጥሮ በብድር በኩል የሚታየውን ችግሮች እንዲፈታልንና ብድር ተመቻችቶልን ወደ ልማት እንድንገባ በማለት አሳውቀዋል። በተጨማሪም ወረዳው ለኢንቨስትመንት አማራጩ ምቹ ሁኔታን በመፍጠርና ከ 3ኛ ወገን ነፃ የሆነ መሬት አዘጋጅቶ ለልማት ማቅረቡ የሚመሰገን ጉዳይ መሆኑን ገልፀዋል።

የሰሜን ወሎ ዞን ፕላን እና ልማት መምሪያ ሀላፊ አቶ ደሳለ ባዬ የኢንቨስትመንት ሁኔታውን ለማነቃቃት ኢትዮጵያ ታምርት እኛም እንሸምት በሚል መሪ ሀሳብ የተካሄዱ መድረኮች አበረታች ውጤት እያመጡ መሆኑን በመግለፅ የሚገጥሙ ችግሮችን በጋራ በመፍታት በወረዳው ያለውን የኢንቨስትመንት እንቅስቃሴ ማሳደግ ይገባል ብለዋል።

07/02/2026

Address

Adago Infront Of Higher Court
Woldia
789

Opening Hours

Monday 09:00 - 17:00
Tuesday 09:00 - 17:00
Wednesday 09:00 - 17:00
Thursday 09:00 - 17:00
Friday 09:00 - 17:00

Telephone

+251920150340

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when North wollo industry and investment department posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Organization

Send a message to North wollo industry and investment department:

Share