Gubalafto Communication/ጉባላፍቶ ኮሙኒኬሽን

Gubalafto  Communication/ጉባላፍቶ ኮሙኒኬሽን This page is about gubalafto woreda Communication affairs office

05/06/2026
በሰሜን ወሎ ዞን ጉባላፍቶ ወረዳ በ7ኛው ሀገራዊ ምርጫ እና ቀጣይ ስራዎች ዙሪያ ከወረዳው ጠቅላላ አመራር ጋር ውይይት ተካሂዷል።‎‎ወልድያ፦ግንቦት 27/2018 ዓ.ም (ጉባላፍቶ ኮሙኒኬሽን)‎...
04/06/2026

በሰሜን ወሎ ዞን ጉባላፍቶ ወረዳ በ7ኛው ሀገራዊ ምርጫ እና ቀጣይ ስራዎች ዙሪያ ከወረዳው ጠቅላላ አመራር ጋር ውይይት ተካሂዷል።

‎ወልድያ፦ግንቦት 27/2018 ዓ.ም (ጉባላፍቶ ኮሙኒኬሽን)

‎የጉባላፍቶ ወረዳ አስተዳደር በ7ኛው ሀገራዊ ምርጫ እና ቀጣይ በሚሰሩ የልማትና የመልካም አስተዳደር ስራዎች ዙሪያ ከወረዳው ጠቅላላ አመራሮች ጋር የውይይት ተካሂዷል።

‎በሀገረ መንግስት ግንባታ ትልቅ ታሪክ ያለው ህዝባችን በ7ኛው ሀገራዊ ምርጫም ያሳየው ተሳትፎ በጣም የተሻለ እንደነበር የገለጹት የጉባላፍቶ ወረዳ ም/ዋና አስተዳዳሪ አቶ ሀብታሙ በየነ የምርጫ ሂደቱ ሰላማዊ እና ስኬታማ እንዲሆን አስተዋፅኦ ላበረከቱ ባለድርሻ አካላትም ምስጋና አቅርበዋል።

‎በበጀት አመቱ በእቅድ የተያዙ የልማትና የመልካም አስተዳደር ስራዎችን በውጤት በማጠናቀቅ ለቀጣይ ስራዎች ዝግጁ መሆን እንደሚገባ አቅጣጫ ተቀምጧል።

በሰሜን ወሎ ዞን ጉባላፍቶ ወረዳ ለ2018/19 የምርት ዘመን የማዳበሪያ ስርጭት ተጠናክሮ ቀጥሏል።
04/06/2026

በሰሜን ወሎ ዞን ጉባላፍቶ ወረዳ ለ2018/19 የምርት ዘመን የማዳበሪያ ስርጭት ተጠናክሮ ቀጥሏል።

🌴 የባሕር ዳር የኮሪደር እና የጣና ዳር ልማት የከተማዋን ገጽታ እየቀየረ ነው 🌴 በባሕር ዳር ከተማ በከፍተኛ ፍጥነት እና ጥራት እየተገነባ የሚገኘው የኮሪደር እና የጣና ዳር ልማት ፕሮጀክት...
03/06/2026

🌴 የባሕር ዳር የኮሪደር እና የጣና ዳር ልማት የከተማዋን ገጽታ እየቀየረ ነው 🌴

በባሕር ዳር ከተማ በከፍተኛ ፍጥነት እና ጥራት እየተገነባ የሚገኘው የኮሪደር እና የጣና ዳር ልማት ፕሮጀክት፤ ከተማዋን ለነዋሪዎች ምቹ፣ ለቱሪስቶች ደግሞ ተመራጭ እያደረጋት ይገኛል።

የዚህ ታላቅ ፕሮጀክት ዋና ዋና ስኬቶች እና ፋይዳዎች፦

🔹የቱሪዝም መነቃቃት፦ የዐይን ማረፊያ የኾኑ የመዝናኛ ስፍራዎች፣ የጣና ዳርቻ ዘመናዊ መንገዶች፣ የእግረኛ እና የብስክሌት መስመሮች የጎብኚዎችን ቆይታ ያራዝማሉ።
የዘንባባ ፓርክም ሙሉ በሙሉ ሳቢ ኾኖ ተጠናቅቋል።

🔹ውበት እና ደኅንነት፦ ለአረንጓዴ ልማት የተሰጠው ትኩረት ከተማዋን ውብ እና ንጹሕ ከማድረጉ ባለፈ፣ የዘመናዊ መንገድ መብራቶች መገጠማቸው የምሽት እንቅስቃሴን እና ደኅንነትን አሳድጓል።

🔹የኢኮኖሚ ዕድገት፦ የቱሪስት ፍሰቱ መጨመር ለሆቴሎች፣ ለትራንስፖርት እና ለአካባቢው ነጋዴዎች ሰፊ የሥራ ዕድል እና ከፍተኛ ገቢ እየፈጠረ ይገኛል።

🔹"የባሕር ዳር ኮሪደር ልማት የከተማዋን ገጽታ ከመቀየር ባለፈ፣ ለትውልድ የሚተርፍ አሻራም ነው።



#ኢትዮጵያንወደተምሳሌትሀገር

"ከጥንትም ለሀገረ መንግሥት ግንባታ ትልቅ አሻራ ያሳረፈው ሕዝባችን ትናንት ደግሞ ለዴሞክራሲ ሥርዓት ያለውን ቀናዒ ፍላጎት ለዓለም አሳይቷል"         ክቡር አረጋ ከበደየአማራ ክልል ርእ...
03/06/2026

"ከጥንትም ለሀገረ መንግሥት ግንባታ ትልቅ አሻራ ያሳረፈው ሕዝባችን ትናንት ደግሞ ለዴሞክራሲ ሥርዓት ያለውን ቀናዒ ፍላጎት ለዓለም አሳይቷል"

ክቡር አረጋ ከበደ
የአማራ ክልል ርእሰ መሥተዳድር

የመንግስት ሠራተኞችን ሙሉ መረጃ በዲጂታል መልኩ በማደራጀት የተቋማትን አሰራር ዘመናዊ፣ ፈጣንና ግልጽ እንዲሆን የሚያግዝ የመረጃ ምዝገባ እየተካሄደ መሆኑ ተገለፀ።ወልዲያ፥ ግንቦት 26/201...
03/06/2026

የመንግስት ሠራተኞችን ሙሉ መረጃ በዲጂታል መልኩ በማደራጀት የተቋማትን አሰራር ዘመናዊ፣ ፈጣንና ግልጽ እንዲሆን የሚያግዝ የመረጃ ምዝገባ እየተካሄደ መሆኑ ተገለፀ።

ወልዲያ፥ ግንቦት 26/2018 ዓ.ም (ጉባላፍቶ ኮምኒኬሽን)
‌‎
‎ የመንግስት ሠራተኞችን መረጃ ከቅጥር እስከ ስንብት በዘመናዊ ቴክኖሎጂ በመደገፍ በአንድ የተቀናጀ ስርዓት ለማስተዳደር የሚያስችል የሲቪል ሰርቪስ መረጃ አያያዝ ምዝገባ ስርዓት በጉባላፍቶ ወረዳ እየተካሄደ ነው።

‎ በጉባላፍቶ ወረዳ ገንዘብና ትብብር ጽ/ቤት የሂሳብ ባለሙያ ወ/ሮ አለም የማነ እንዳሉት፥ መረጃን በዲጂታል መልኩ መያዝ የመረጃ መጥፋትን እንደሚከላከል ገልጸው፤ በተለይም የቤተሰብ አባላት መረጃን አስቀድሞ ማስመዝገብ በጡረታ ጊዜ የሚከሰቱ እንግልቶችን እንደሚቀንስ ተናግረዋል።

‎የወረዳው ሲቪል ሰርቪስ ጽ/ቤት የሪፎርም ድጋፍ ክትትል ባለሙያ አቶ ፍቃዴድ አሰፋ በበኩላቸው፥ ስርዓቱ በአገር አቀፍና በክልል ደረጃ ያሉ የመንግስት ተቋማት የሰው ኃይል ሁኔታን በትክክል ለማወቅ እንደሚያግዝ ጠቅሰው፤ የሙያ ክፍተቶችን በመለየት ትክክለኛ ውሳኔ ለመስጠትና ለማስተዳደር የጎላ አስተዋፅኦ እንደሚኖረው አብራርተዋል።

‎የተቀናጀው የሲቪል ሰርቪስ መረጃ አያያዝ ስርዓት በመንግስት ተቋማት ውስጥ ግልጽነትን፣ ተጠያቂነትንና የአገልግሎት ቅልጥፍናን በማጠናከር ዘመናዊ የመንግስት አስተዳደር ለመገንባት ጠቃሚ መሠረት እንደሚሆን እንደሚኖረውም ባለሙያው አክለው ገልጸዋል።

‎የጉባላፍቶ ወረዳ ሲቪል ሰርቪስ ጽ/ቤት ሀላፊ አቶ ደስታው ታደሠ እንደገለጹት፣ የሠራተኞች መረጃ ከፋይዳ መታወቂያ ጋር ተገናኝቶ በሶፍት ኮፒ መያዙ የመረጃ ደህንነትን እንደሚያረጋግጥና የተለያዩ የአሰራር ብልሹነቶችን ለመከላከል እንደሚያግዝ አስታውቀዋል።

‎የሠራተኞች ማስረጃዎች በዲጂታል ፎርማት ስለሚያዙ በአካል ጉዳት፣ በስህተት ወይም በመጥፋት ምክንያት የሚፈጠር የመረጃ አደጋን ይቀንሳል ያሉት ሀላፊው፥ ስርዓቱ አንድ ሰራተኛ በተለያዩ መስሪያ ቤቶች በአንድ ጊዜ ተቀጥሮ ደሞዝ የሚከፈለውን ህገ-ወጥ አሰራር ለመከላከልም እንደሚያስችል አስረድተዋል።

‎በተጨማሪም የደረጃ እድገት፣ የደሞዝ ማስተካከያ፣ የበጀት ድጎማ እና የጡረታ አገልግሎቶች በፍጥነትና በተቀላጠፈ መልኩ እንዲከናወኑ የሚያግዝ መሆኑን የጠቆሙት ኃላፊው የመንግስት ሠራተኞችን ሙሉ መረጃ በዲጂታል መልኩ በማደራጀት የተቋማትን አሰራር ዘመናዊ፣ ፈጣንና ግልጽ እንዲሆን የሚያግዝ ሲሆን፣ በወረቀት ላይ የተመሰረተውን የቆየ አሰራር በመቀየር የመረጃ አያያዝ ችግሮችን ለመቅረፍ ከፍተኛ ሚና አለው ብለዋል።

03/06/2026
የፖለቲካ ፓርቲዎች ቅሬታዎች ካላቸው በሕጋዊ መንገድ ብቻ መፍታት ይኖርባቸዋል - የኢጋድ ታዛቢ ቡድን ******************የምሥራቅ አፍሪካ የልማት በይነ መንግሥታት (ኢጋድ) የምርጫ ...
03/06/2026

የፖለቲካ ፓርቲዎች ቅሬታዎች ካላቸው በሕጋዊ መንገድ ብቻ መፍታት ይኖርባቸዋል - የኢጋድ ታዛቢ ቡድን
******************

የምሥራቅ አፍሪካ የልማት በይነ መንግሥታት (ኢጋድ) የምርጫ ታዛቢ ቡድን 7ኛውን ጠቅላላ ምርጫ በተመለከተ ባወጣው መግለጫ፣ ተፎካካሪ የፖለቲካ ፓርቲዎች ከምርጫው ጋር ተያይዞ ለሚነሡ ማናቸውም ቅሬታዎች ሕጋዊ መንገዶችን ብቻ መከተል እንዳለባቸው አሳስቧል።

ዓለም አቀፉ ማኅበረሰብም ኢትዮጵያውያን በውስጥ ጉዳዮቻቸው ራሳቸው እንዲወስኑ ዕድል እንዲሰጥም ቡድኑ ጥሪ አቅርቧል።

ቡድኑ አክሎም በሂደቱ የሴቶች ተሳትፎ መሻሻል እንዳለበት ያመላከተ ሲሆን፣ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ በጀመረው የቴክኖሎጂ አጠቃቀም ማጠናከር እንዳለበት አስተያየቱን ሰጥቷል።

የፀጥታ አካላት ምርጫውን ሰላማዊ ለማድረግ የጀመሩትን ገለልተኛ የፀጥታ ጥበቃ ሥራ አጠናክረው ማስቀጠል እንዳለባቸውም ነው ታዛቢ ቡድኑ ያስገነዘበው።

የሲቪል ማኅበረሰብ ድርጅቶች በበኩላቸው በምርጫ ሂደቱ ያላቸውን ተሳትፎ በማሳደግ እና ለሕዝቡ የሚሰጡትን የግንዛቤ ማስጨበጥ ሥራ በማጠናከር በቅንጅት ሊሠሩ እንደሚገባ ጠቁሟል።

ከምርጫው በኋላም ቢሆን በኢትዮጵያ የንግግር እና የውይይት ባህል እንዲዳብር የድርሻቸውን ሊወጡ ይገባል ብሏል።

መንግሥት ለዴሞክራሲ ግንባታ እያደረገ ያለውን ዘርፈ ብዙ ድጋፍ አጠናክሮ እንዲቀጥል እና ሁሉም የኅብረተሰብ ክፍል በዴሞክራሲያዊ ሥርዓት ግንባታው ውስጥ ንቁ ተሳትፎ እንዲኖረው ጠንካራ ሥራ መሥራት እንዳለበት መግለጫው ተመላክቷል።

ለዚህም መንግሥት አስፈላጊውን ድጋፍ በማድረግ ዴሞክራሲያዊ ተቋማትን ይበልጥ ማጠናከር እንዳለበት አስምሮበታል።

ዓለም አቀፉ ማኅበረሰብ ኢትዮጵያውያን ለገጠሟቸው ችግሮች ራሳቸው መፍትሔ እንዲሰጡ እና የውስጥ ጉዳያቸውን በራሳቸው እንዲፈቱ ዕድል ሊሰጥ እንደሚገባ የኢጋድ ምርጫ ታዛቢ ቡድን ጥሪውን አቅርቧል።

ሕዝቡ ሕጋዊ ካልሆኑ ከማንኛውም ምንጮች ከሚወጡ መረጃዎች ራሱን እንዲጠብቅ ምርጫ ቦርድ አሳሰበ ********************** የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ መራጮች በትላንትናው ዕለት ...
02/06/2026

ሕዝቡ ሕጋዊ ካልሆኑ ከማንኛውም ምንጮች ከሚወጡ መረጃዎች ራሱን እንዲጠብቅ ምርጫ ቦርድ አሳሰበ
**********************

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ መራጮች በትላንትናው ዕለት ግንቦት 24 ቀን 2018 ዓ.ም በከፍተኛ ንቃት እና ትዕግሥት ድምፃቸውን ስለሰጡ አመስግኗል።

በምርጫ ሕጉ መሠረት ውጤት በቦርዱ ይፋ እስከሚሆን ድረስም በትዕግሥት እንዲጠብቁ እና ሌሎች አካላትም ያልተረጋገጡ መረጃዎችን ከማሰራጨት እንዲቆጠቡ፤ ሕዝቡም ከመሰል መረጃዎች ራሱን እንዲጠብቅ ቦርዱ አሳስቧል።

Address

Woldia

Opening Hours

Monday 09:00 - 17:00
Tuesday 09:00 - 17:00
Wednesday 09:00 - 17:00
Thursday 09:00 - 17:00
Friday 09:00 - 17:00

Telephone

+251333311822

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Gubalafto Communication/ጉባላፍቶ ኮሙኒኬሽን posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Organization

Send a message to Gubalafto Communication/ጉባላፍቶ ኮሙኒኬሽን:

Share