ሰሜን ወሎ ዞን ሲቪል ሰርቪስ መምሪያ north wollo zone civil service departmet

  • Home
  • Ethiopia
  • Woldia
  • ሰሜን ወሎ ዞን ሲቪል ሰርቪስ መምሪያ north wollo zone civil service departmet

ሰሜን ወሎ ዞን ሲቪል ሰርቪስ መምሪያ north wollo zone civil service departmet Contact information, map and directions, contact form, opening hours, services, ratings, photos, videos and announcements from ሰሜን ወሎ ዞን ሲቪል ሰርቪስ መምሪያ north wollo zone civil service departmet, Public Service, 0333311007, Woldia.

11/09/2023

ለመላው ኢትዮጽያዊያን 2016 መልካም አድስ ዓመት
እንዲሆንላችሁ እንመኛለን!!

27/10/2022
"ለኢትዮጵያ እቆማለሁ ፣ ድምጼን አሰማለሁ !"በሚል መሪ ቃል የምእራባውያንን ያልተገባ ጣልቃ ገብነት የሚቃወም ታላቅ ሰላማዊ ሰልፍ በወልዲያ ከተማ ተካሄደ ።ጥቅምት 13 ቀን 2015 ዓ.ም (...
23/10/2022

"ለኢትዮጵያ እቆማለሁ ፣ ድምጼን አሰማለሁ !"በሚል መሪ ቃል የምእራባውያንን ያልተገባ ጣልቃ ገብነት የሚቃወም ታላቅ ሰላማዊ ሰልፍ በወልዲያ ከተማ ተካሄደ ።

ጥቅምት 13 ቀን 2015 ዓ.ም (ወልድያ ኮምኒኬሽ) በሰልፉ ላይ የወልድያ ከተማና አካባቢው ህዝብ ፣ የዞን ፣ የከተማ አስተዳደርና የጉባላፍቶ ወረዳ አስተዳደር አመራሮች ፣ የሀይማኖት አባቶች የሀገር ሽማግሌዎች የተገኙ ሲሆን በዚህ ታላቅ የተቃውሞ ሰልፍ የሰሜን ወሎ ዞን ዋና አስተዳዳሪ ዲያቆን ተስፋሁን ባታብል ፣ የወልድያ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ ዶክተር ዳዊት መለስ መልእክት አስተላልፈዋል ።

ጠላት እንዳሰበው ሳይሆን አሁን ስላገኘነው ድል እንኳን ደስ አላችሁ ያሉት የሰሜን ወሎ ዞን ዋና አስተዳዳሪ ዲያቆን ተስፋሁን ባታብል ሀገራችን ኢትዮጵያ በጀግኖች አባቶቻችን መስዋዕትነት ነፃነቷን ጠብቃ ታፍራና ተከብራ የኖረች የአይበገሬነት ተምሳሌት የስልጣኔ መነሻና ምድረ ቀደምት ሀገር መሆኗ ይታወቃል ያሉት ዋና አስተዳዳሪው አሸባሪውና ወራሪው ቡድን በከፈተብን ጦርነት በተፈጠረው የሰላም ችግር መንግስታችን ያለ ቅድመ ሁኔታ በአፍሪካ ህብረት በኩል ለመደራደር አቋም መያዙ ይታወቃል ።

የውጭ ሀይሎች በተለይም የምእራባውያን ሀገራት በኢትዮጵያ ላይ የያዙት አቋም ሉአላዊ በሆነ ሀገር የውስጥ ጉዳይ ላይ ጣልቃ መግባት ኢፍትሐዊ አካሄድ ስለሆነ ቆም ብለው ራሳቸውን እንዲመለከቱ ድምጻችንን እናሰማለን ብለዋል ።

ኢትዮጵያን ለማፍረስ ለሚሰሩ ታሪካዊ ጠላቶቻችን የትሮይ ፈረስ በመሆን ጦርነት የከፈተብንን አሸባወሪውን ቡድን በመመከትና የኢትዮጵያን ሉአላዊነት ለማስከበር የወገን ጦር በርካታ መስዋዕትነት እየከፈለ ይገኛል ያሉት የከተማ አስተዳደሩ ከንቲባ ዶክተር ዳዊት መለስ የከተማችን ማህበረሰብ ደከመኝ ፣ ሰለቸኝ ሳይል ላለፉት ሁለት ወራት ደጀንነቱን በብቃት እየተወጣ ይገኛል ብለዋል። አያይዘውም የከተማዋ ህዝብ ለወገን ጦር እያሳየ ላለው ያላቋረጠ ድጋፍ በከተማ አስተዳደሩ ስም ምስጋና አቅርበው ደጀንነቱ የኢትዮጵያ ሉአላዊነት እስከመጨረሻው እስከሚረጋገጥ ድረስ ተጠናክሮ ይቀጥላል ብለዋል ።

በዛሬው የተቃውሞ ሰልፍ ላይ ከተላለፉ መፎክሮች (slogan) መካከል
✍️ የትግራይ ህዝብ ጠላታችን ሁኖ አያውቅም ፣
✍️ሉአላዊነታችንን በሰብዓዊ እርዳታ ስም አናስደፍርም ፣
✍️ከኢትዮጵያ ጎን ለሚቆሙት ክብር አለን ፣
✍️ሉአላዊነታችንን አክብሩ ፣
✍️ራያ የትግራይ ጎረቤት እንጂ ትግሬ ሁኖ አያውቅም ፣
✍️የአሜሪካና የሌሎች ምእራባውያን ሀገሮች ጣልቃ ገብነት ይቁም ፣
✍️ለዘላቂ ሰላም ህወሃት ትጥቅ ይፍታ የሚሉት የሚገኙባቸው ሲሆን ሰልፉ በተያዘለት ፕሮግራም መሰረት ተካሂዶ ያለምንም የፀጥታ ችግር በሰላም ተጠናቋል ።

21/07/2022

ውጤታማ ሲቪል ሰርቪስ ስርዓት በመዘርጋት የደንበኞችን አርካታ እናረጋግጣለን!

በሀገራችን የሲቪል ሰርቪሱን የአሠራር ስርዓት ለማሻሻልና ለመቀየር የሚያስችል የተለያዩ ሀገራትን ተሞክሮ በመውሰድ ተግባራዊ ሲደረጉ ቆይቷል፤ አሁንም የለውጥ ሪፎርሙን ያሳልጣሉ ተብሎ የሚታመንባቸውን የመሠረታዊ የስራ ለውጥ ትግበራ እንደ ሀገር እየተተገበረ ይገኛል፡፡ ይህ የትግበራ ማዕቀፍ ስራና ሰራተኛን ሊያገናኙ የሚችሉ የለውጥ ሪፎርሙ አንድ አካል ተደርጎ እየተሰራበት ነው፡፡

የሲቪል ሰርቪስ ዋነኛ ተልዕኮው የተቋማት የለውጥ ሪፎርሞችን በታቀደና በተጠና መንገድ እንዲተገበሩ አስቻይ ሁኔታዎችን በማመቻቸት ቀልጣፋ፣ ጥራትና ብቃት ያለው አገልግሎት ለተገልጋዩ ማህበረሰብ ምቹ መደላድልን መፍጠር ነው::

የተቋማትን ሁለንተናዊ የአሰራር ስርዓት በማሻሻልና የተገልጋዩን ማህበረሰብ እርካታ ለማስገኘት የሲቪል ሰርቪስ ተቋም ቁልፍ ድርሻ አለው፡፡ ይህ ተቋም የሲቪል ሰርቪሱን የአሠራር ስርዓት በማዘመን ረገድ አዎንታዊ ሚና ይጫወታል፡፡

የሲቪል ሰርቪስ ተቋማት የሚመሩበትን ልዩ ልዩ አዋጆችና መመሪያዎችን በየጊዜው ተግባራዊ ማድረግ የሚጠበቅበት ሲሆን፣ በአሠራር ሂደት ለሚያጋጥሙ ችግሮችም የመፍትሄ አቅጣጫዎችንና አዎንታዊ እርምጃዎችን ይወስዳል፡፡

በሰርቪስ ማሻሻያ ፕሮግራም የለውጥ አመራር ትግበራዎች ነቅሶ በማውጣት በኩል የሚታዩ ጅምር ስራዎች ቢኖሩም ወጥነት ባለው መንገድ በመስራት በኩል ግን ውስንነት ያለበት ነው፡፡

በመንግስት ተቋማት አገልግሎት አሰጣጥ ላይ የሚታዩ ችግሮች በለውጥ ሪፎርሙ ላይ አሉታዊ ተፅዕኖች ያሳደሩ ናቸው፡፡ ለዚህ መሠረታዊ ችግር መፈጠር ዋነኛው ምክንያት የሲቪል ሰርቪስ ማሻሻያ ፕሮግራም ትግበራ ላይ ትኩረት ሰጥቶ በመስራት በኩል አሁንም ያልተሻገርነው ችግር እንዳለ ያመላክታል፡፡

የሲቪል ሰርቪስ ሪፎርም ለመተግበር የሚያስችል የአሠራር ስርዓት ለተቋማት ቢዘረጋም፣ በአተገባበሩ ላይ በተለይም በተቋማት የውይይት መድረኮች አስፈላጊነት ላይ ለፈጻሚው ሠራተኞች በቂ ግንዛቤ ባለመፈጠሩ ምክንያት ተግባሩን የፖለቲካ ማስፈፀሚያ አድርጎ የመውሰድ ዝንባሌዎች በስፋት ሲንፀባረቁ ተስተውሏል፡፡

የሲቪል ሰርቪስ አገልግሎት አሰጣጥ የደንበኞች እርካታና ፍላጎት መለኪያ ተቀምጦለት የሚሰራበት ሂደት የዘርፉ ዋነኛ ተልዕኮ ነው፡፡ በመሆኑም በአገልግሎት አሰጣጥና በተገልጋይ ደንበኞች የሚኖረው የስራ መስተጋብር ቀጣይና ተከታታይነት ባለው መንገድ እንዲተገበር ተቋማዊ አሠራርን በማዘመንና ቀልጣፋ ሲቪል ሰርቪስ አገልግሎት በመስጠት የሚታዩ የአሠራር ጉድለቶችን ማረም ይጠይቃል፡፡

በዞናቸን የሲቪል ሰርቪስ ሪፎርም በውጤታማነት ከማስቀጠል አኳያ ቀደም ሲል የሲቪል ሰርቪስ ሪፎርም አተገባበር ላይ በየሩብ ዓመቱ ጠንካራ ድጋፍና ክትትል የሚደረግበት ሁኔታ ስለነበር በተቻለ መጠን ችግሮች በየጊዜው ለማየትና ፈጥኖ ለማሻሻል እድል የሚሰጥ ነበር፡፡ ከቅርብ ዓመታት ወዲህ ይህንን ተልዕኮ ይፈጽም የነበረው ቡድን በአዋጅ በመታጠፉ ምክንያት በሲቪል ሰርቪስ ሪፎርሙ ላይ አሉታዊ ተፅዕኖ ማሳረፉ አልቀረም፡፡

ይህንን መሠረታዊ ችግር በድጋሜ ያጤነው የክልሉ የሲቪል ሰርቪስና የሰው ኃብት ልማት ኮሚሽን የሲቪል ሰርቪስ ሪፎርም በውጤታማት ለማስቀጠል የሪፎርም ክትትልና ድጋፍ ቡድንን በድጋሜ አደራጅቷል፡፡ የዚህ ቡድን በአዲስ መልክ መደራጀት ተቋማት በስታንደርዳቸው መሠረት የታቀዱ ተግባራትን ከዓላማና ግባቸው አንፃር እየመዘኑና ጉድለቶችን እያረሙ የሚሄዱበት የአሠራር ስርዓት ስለሚዘረጋ ውጤታማ የሲቪል ሰርቪስ ተግባራዊ ለማድረግ አቅም ይሆናል፡፡

ተቋማት ጥራት፣ብቃትና ነ

*************ከዚህ በታች ያለውን ሊንክ በመጫን የቴሌግራም ቻናላችንን በመቀላቀል የተለያዩ መረጃዎችን ማለትም መመሪያ፣ማብራሪያ ፣ዝውውር፣ቅጥር፣እና ሌሎችንም ማግኘት የምትችሉመሆኑን እ...
15/02/2022

*************ከዚህ በታች ያለውን ሊንክ በመጫን የቴሌግራም ቻናላችንን በመቀላቀል የተለያዩ መረጃዎችን ማለትም መመሪያ፣ማብራሪያ ፣ዝውውር፣ቅጥር፣እና ሌሎችንም ማግኘት የምትችሉመሆኑን እያሳወቅን ለሌሎችም እንዲደርስ ሸር ላይክ በማድረግ ለሁሉም አድርሱ።

******************የኮንትራት ቅጥር*********
28/03/2021

******************የኮንትራት ቅጥር*********

************** የውስጥ ዝውውር ማስታወቂያ********
18/03/2021

************** የውስጥ ዝውውር ማስታወቂያ********

×××××××××××   የቅጥር ማስታወቂያ።×××××××××
18/03/2021

××××××××××× የቅጥር ማስታወቂያ።
×××××××××

የውሰጥ ዝውውር ማስታወቂያ
03/03/2021

የውሰጥ ዝውውር ማስታወቂያ

የውጭ ዝውውር ማስታወቂያ
12/02/2021

የውጭ ዝውውር ማስታወቂያ

መረጃውን  # Share /ሸር/ በማድረግ ለሌሎችም የተሻለ ስራ ለሚፈልጉ ወገኖቻችን እናካፍል። መልካምነት ለራስ ብቻ ሳይሆን ለሌሎችም ማሰብ ነው።የሥራ ማስታወቂያ መረጃዎችና የሲቪል ሰርቪስ ...
06/02/2021

መረጃውን # Share /ሸር/ በማድረግ ለሌሎችም የተሻለ ስራ ለሚፈልጉ ወገኖቻችን እናካፍል። መልካምነት ለራስ ብቻ ሳይሆን ለሌሎችም ማሰብ ነው።
የሥራ ማስታወቂያ መረጃዎችና የሲቪል ሰርቪስ መመሪያዎችን ለመከታተል ለምትፈልጉ በሙሉ
Please Join here..
በፌስቡክ ገፅ...
እንዲሁም
በቴሌግራም ቻናል...

ክፍት የሥራ ቦታ ማስታወቂያና ሌሎችም መመሪያዎችን ማግኘት ይችላሉ።

የዝውውር ማስታወቂያ..!!
26/01/2021

የዝውውር ማስታወቂያ..!!

Address

0333311007
Woldia

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when ሰሜን ወሎ ዞን ሲቪል ሰርቪስ መምሪያ north wollo zone civil service departmet posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Share

Category