22/04/2026
በቆቦ ከተማ ለተደራጁ ለአስራ ሶስት ማህበራት 312 አባላት የቤት መስሪያ ቦታ መሰጠቱ ተገለፀ ።
ሚያዝያ 13/2018 ዓ.ም በእርክብክቡ ቦታ የቆቦ ከተማ አስተዳደር ዋና ከንቲባ አቶ ሀይለአብ ወንድሙ፣ የብልጽግና ፓርቲ ን/ቅ/ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ አበበ ይመር፣ የቆቦ ከተማ ብልፅግና ፓርቲ ፓለቲካ ዘርፍ ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ሰለሞን አምሃ ጨምሮ ለሎች አስተባባሪና ባለድርሻ አካላት ተገኝተዋል።
መንግስት ከምንጊዜውም በላይ ዘጎች የከተማ መሬት ተጠቃሚ እንድሆን በልዩ ትኩረት እየሰራ እንዳለ የቆቦ ከተማ ዋና ከንቲባ አቶ ሀይለአብ ወንድሙ ተናገሩ።
ከተማችን የጀመረችውን ልማት አጠናክሮ ለማስቀጠል፣ ሰላሟን ለማስጠበቅ ማህበረሰቡ ኃላፊነቱን መወጣት እንዳለበት ክቡር ከንቲባው መልዕክት አስተላልፈዋል።
በዚህ መሠረት ለሀገር ትልቅ ውለታ የከፈሉ የቀድሞ ሰራዊት አባላቶችና ለሌሎች አሰራ ሁለት ማህበራት ለ312 ግለሰቦች ቤት መስሪያ ቦታ እርክብክብ ተደርጎላቸዋል።
መንግስት ለዜጎች ባመቻቸው ፖሊሲና ስትራቴጂ መሰረት ተደራጅተው ለቆጠቡ አሰራ ሶስት ማህበር ከይገበኛል ነፃ የሆነ መሬት በስማቸው መተላለፉ ትልቅ ስኬት እንደሆነ የቆቦ ከተማ መሬት ጽ/ቤት ኃላፊ አዲሱ ወዳጆ ዶ/ር ተናግሯል።
በማህበር ለተደራጁ አካላት በከተማ መሬትን እንዲያገኙ በተደነገገው መሠረት በዛሬው ዕለት የእርክብክብ ስራው ተፈጽሟል ያሉት አዲሱ ወዳጆ ዶ/ር ለቀጣዩም ተጠናክሮ የሚቀጥል ተግባር ነውም ብለዋል።
በመጨረሻም የማህበሩ አባላቶችም እጅግ በጣም ደስተኛ መሆናቸውን ገልጾ ለተመቻቸው ምቹ ዕድልና ስኬት መንግስትንና ባለድር አካላትን አመስግነዋል።
ዘገባው የሰሜን ወሎ የመንግስት ኮሙኒኬሽን ነው።