03/06/2023
በወረታ ከተማ ጥራቱን የጠበቀና በደቡብ ጎንደር ዞን የመጀመሪያው ዘመናዊ የወጣቶች መዝናኛ ማዕከል ተገንብቶ በቅርቡ ለወጣቶች ክፍት እንደሚሆን ተገለጸ።
በአገራች ኢትዮጵያ ብሎም በክልላች በተለያዩ ቦታዎች ሁለገብ የወጣቶች መዝናኛ ማዕከላት በስፋት ባለመገንባታቸውና ባለመኖራቸው የተነሳ የነገ አገር ተረካቢ ትውልዶችና ልማታዊ ወጣቶች በተለያዩ አልባሌና አላስፈላጊ ቦታዎች ጊዜያቸውን በማሳለፍ ለአዕምሯዊና ስነልቦናዊ ችግር እየተጋለጡ በተለያዩ ጊዚያት ወጣቶች ለሰላም ዘብ ከመቆም ወደ የጥፋት ኃይልነት የማዘንበል አዝማሚያ ከልማታዊነት ይልቅ ወደ አፍራሽ ሃይልነት ተለውጠው በወጣትነታቸው ዘመን ለአገራቸው ማድረግ የሚገባቸውንና አገራዊ ግዴታቸውን ሳይወጡ መቆየታቸው የማይዘነጋና የቅርብ ጊዜ ትዝታችን ነው።
በወረታ ከተማም በመልካም ስነምግባር የታነጹ በስነልቦና የተገነቡና በአዕምሮ የበለጸጉ ወጣቶችን ለማፍራት መንግስት በሚያደርገው እንቅስቃሴ ውስጥ የወረታ ከተማ አስተዳደር የበኩሉን ድርሻ ለመወጣት የወረታ ከተማ ሁለገብ የወጣቶች መዝናኛ ማዕከል አስፈላጊ መሆኑን በመገንዘብ በ5.5 ሚሊዮን ብር በላይ ወጭ በማድረግ ሁለገብ የወጣቶች መዝናኛ ማዕከል በመገንባት ና በቅርቡ ለወጣቶች ክፍት እንደሚሆን የወረታ ከተማ አስተዳደር ከተማና መሠረተ ልማት ጽ/ቤት ዋና ስራ አስኪያጅ አቶ አሳምኗል አየሁ ገልጸዋል።
የመዝናኛ ማዕከሉም በደቡብ ጎንደር ዞን ውስጥ የመጀመሪያው ጥራቱን የጠበቀ ውብ ፣ማራኪ ና ዘመናዊ ሁለገብ የወጣቶች መዝናኛ ማዕከል መሆኑንና በውስጡም የተለያዩ በስፖርታዊ እንቅስቃሴዎችና የአካል ብቃት እንቅስቃሴ የሚደረግባቸው ጅምናዜሞች፣ የፑል አገልግሎት፣ ደረጃውን የጠበቀና የተሟላ ቤተ መፅሃት፣ መፀዳጃ ቤት፣ ጥራቱን የጠበቀ የካፌ አገልግሎት፣ ሌሎችንም አገልሎቶች የሚሰጥ ሁለገብ የመዝናኛ ማዕከል መሆኑንና ግንባታውም 100% የተጠናቀቀ መሆኑን ስራ ዋና አስኪያጁ ጨምረው አብራርተዋል።
የወረታ ከተማ አስተዳደር ተቀዳሚ ምክትል ከንቲባ አቶ ብርሃኑ ያዜ በበኩላቸዉ ይህን ዘመናዊ ሁለገብ የመዝናኛ ማዕከል ለመገንባት ከተማ አስተዳደሩ ከፍተኛ በጀት በመመደብና ማዕከሉ እንዲገነባ የሆነበት ምክንያት ከቅርብ ጊዜ በፊት ለከተማችን ወጣቶች መዝናኛ የሚሆን ካፌና የተለያዩ ስፖርታዊ ና የአካል ብቃት እንቅስቃሴዎች ማድረጊያና አነስተኛ ቤተመጽሃፍት ያለው ማዕከል ተገንብቶ እንደነበር ተናግረዋል።
ይሁን እንጅ ከተማ አስተዳደሩ ለማዕከሉ አስፈላጊውን ቁሳቁስ አሟልቶ ወጣቶቹ በማዕከሉ ከሚዝናኑ ወጣቶች የገቢ በማግኘት እራሳቸውን ተጠቃሚ የሚያደርጉበትአስረድተዋል። የስራ ዕድል የፈጠረላቸው ቢሆንም በወቅቱ ወጣቶቹ ሰበብ አስባብ በመፍጠር እራሳቸውን እንኳ በፋይናንስ ማስተዳደር ባለመቻላቸው ማዕከሉ የሚጠበቅበትን አገልግሎት ለከተማው ወጣቶች ሳይሰጥ ቆይቷል ሲሉ ከንቲባው
በመሆም በከተማችን በስነምግባር የታነጸ ፣በስነልቦናው ጠንካራና አምራች ልማታዊ ወጣት ለመፍጠር ያስችል ዘንድ በከተማችን ደረጃውን የጠበቀና የተሟላ የወጣቶች መዝናኛ ማዕከል ገንብተን ለወጣቶች አገልግሎት እንዲውልና ወጣቶች እየተዝናኑ እውቀት እንዲጨብጡበት ሁኔታዎች ተመቻችተዋል ብለዋል።
የመረጃ ምንጭ፦ የወረታ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ ጽ/ቤት የመንግስት ኮሙኒኬሽን ቡድን