15/09/2026
ቲጋገዞት የበጎ አድራጎት ማህበር ለ220 ተማሪዎች የመማሪያ ቁሳቁስ ድጋፍ ማድረጉን ገለጸ፡፡
ቃዋቆቶ መስከረም 5/2019 አልቾ ኮሙኒኬሽን
በአልቾ ውሪሮ ወረዳ ቃዋቆቶ ከተማ ላይ የሚገኘው ቲጋገዞት የበጎ አድራጎት ማህበር ለ220 ተማሪዎች የመማሪያ ቁሳቁስ ድጋፍ ማድረጉን ገልጿል፡፡
ማህበሩ ከአባላቱ እና ከተለያዩ የበጎ አድራጊ ግለሰቦች በተገኘ የገንዘብ ድጋፍ ለ220 ከተለያዩ ትምህርት ቤቶች ለተውጣጡ ተማሪዎች ድጋፍ ማድረጉን አስታውቋል፡፡
በድጋፉ ወቅት የተገኙት የአልቾ ውሪሮ ወረዳ ዋና አስተዳዳሪ ወ/ሮ መህድያ ሀሰን ቲጋገዞት የበጎ አድራጎት ማህበር ከተመሰረተ ጀምሮ የትምህርት ቁሳቁስ ድጋፍን ጨምሮ አቅመ ደካማ ግለሰቦችን በተለያዩ ጊዜያት በማገዝ ረገድ ውጤታማ ስራዎች እያከናወነ መሆኑን ገልጸዋል፡፡
ማህበሩ እንደ ወረዳ ከመንግስት ጎን በመቆም በወረዳው አስተዳደር ተደራሽ ያልሆኑ ግለሰቦችን እያገዘ መሆኑን የተናገሩት ወ/ሮ መህድያ እየተረገ ላለው ድጋፍ በወረዳው አስተዳደር ስም ምስጋና አቅርበዋል፡፡
ተማሪዎች መማር እየፈለጉ በቁሳቁስ እጥረት ምክንያት ከትምህርት ገበታቸው እንዳይርቁ ተደራሽ መሆን እንዳለበት በመጥቀስ ማህበሩ መጪው ትውልድ ላይ የሚሰራውን ስራም አጠናክሮ እንዲያስቀጥል የወረዳው ዋና አስተዳዳሪ ወ/ሮ መህድያ ጥሪ አስተላልፈዋል፡፡
የአልቾ ውሪሮ ወረዳ ወጣቶች እና ስፖርት ጽ/ቤት ዋና ሃላፊ አቶ ሰማን ኸይረዲን በበኩላቸው በጎነት የህሌና ስራ መሆኑን በመጥቀስ ማህበሩ እያገዘ ያለው ተማሪዎችን ሳይሆን ማህበረሰብን መሆኑን ተናግረዋል፡፡
በተቋም ደረጃ ማህበሩን አስፈላጊ በሆነ መልኩ የማገዝና የማደራጀት ስራ እንደሚሰራም አቶ ሰማን አስታውቀዋል፡፡
የማህበሩ ሰብሳቢ ተወካይ የሆኑት አቶ ሳቢት መሀመድ ተማሪዎች በትምህርት ቁሳቁስ እጥረት ከትምህት እንዳይሰተጓጎሉ ገንዘብ በማሰባሰብ ሂደት ለተሳተፉ የማህበሩ አባላት እና በሂደቱ የተሳተፉ ግለሰቦችን ምስጋና አቅርበዋል፡፡
በድጋፉ ወቅት የአልቾ ውሪሮ ወረዳ ዋና አስተዳዳሪ ወ/ሮ መህድያ ሀሰን የአልቾ ውሪሮ ወረዳ ወጣቶችና ስፖርት ጽ/ቤት ሃላፊ አቶ ሰማን ኸይረዲን የወረዳው ትምህርት ቤቶች ጽ/ቤት ዋና ሃላፊ አቶ ካሚል ፈረጃ የሰራተኛ እና ማህበራዊ ጉዳዮች ጽ/ቤት ሃላፊ ወ/ሮ ሳረት ረዲ የወጣቶች ክንፍ ሃላፊ ወ/ሪት መህድያ ኡስማንን ጨምሮ የማህበሩ ሰብሳቢዎች እና አባላቶች ተገኝተዋል፡፡