16/09/2026
በደቡባዊ ሲዳማ ዞን ዳራ ኦትልቾ ወረዳ የ2018 ዓ.ም የከረምት ወራት ልዩ ልዩ የስፖርት ሻምፒዮና መዝግያ መርሃግብር በደማቅ ሁኔታ ተጠናቀቀ።
〰️〰️〰️〰️〰️〰️〰️〰️〰️〰️〰️〰️〰️
በደቡባዊ ሲዳማ ዞን ዳራ ኦትልቾ ወረዳ የ2018 ዓ.ም የከረምት ወራት ልዩ ልዩ የስፖርት ሻምፒዮና መዝግያ መርሃግብር የዞን ዋና አስተዳዳሪውን ጨምሮ የዞን ከፍተኛ ባለስልጣናትና የስራ ኃላፊዎች፣ የወረዳው የፊት አመራሮች እና የስፖርት አፍቃሪያን በተገኙበት በደማቅ ሁኔታ ተጠናቅቋል።
በሥነሥርዓቱ ላይ ተገኝተው መልዕክታቸውን ያስተላለፉት የደቡባዊ ሲዳማ ዞን ዋና አስተዳዳሪ ክቡር አቶ መንገሻ ፊታሞ፣ የክረምት ስፖርት ሻምፒዮና ከመደበኛ የስፖርት ውድድርነቱ ባለፈ፣ ወጣቶቻችን በክረምት ወራት ጊዜያቸውን በበጎ ተግባር፣ በጤናማ የአካል ብቃት እንቅስቃሴና እርስ በርስ በመቀራረብ እንዲያሳልፉ ትልቅ ዕድል የፈጠረ ውድድር እንደሆነ ገልፀው፣ ተጫዋቾች በሜዳ ላይ ያሳዩት ፉክክር፣ የወንድማማችነት መንፈስ እና የአሸናፊነት ስነ-ልቦና ከወረዳው አልፎ ለዞናችንም ብሩህ ተስፋ በጉልህ ያሳየ ነው ብለዋል።
አስተዳዳሪው ጨምሮ ፣ "ዛሬ ዋንጫና ሜዳሊያ ተሸላሚ የሆናችሁ ክለቦችና ስፖርተኞች እንኳን ደስ አላችሁ። በዚህ መድረክ ላይ የተሸነፈ የለም፤ ዋናው አሸናፊ የወረዳችን እና የህዝባችን አንድነት፣ ሰላምና ስፖርታዊ ጨዋነት ነው" ብለው፤ ስፖርት የአካልና የአዕምሮ ጤና ብቻ ሳይሆን የሰላምና የህዝቦች ትስስር ድልድይ በመሆኑ፣ ይህንን የወንድማማችነት እሴት ይዛችሁ ልትቀጥሉ ይገባል በማለት መልዕክታቸውን አስተላልፏል።
የዳራ ኦትልቾ ወረዳ ዋና አስተዳዳሪ አቶ ሙሉነህ ክአሞ ለአንድ ወር ያህል በታላቅ ድምቀት፣ በሰላምና በስፖርታዊ ጨዋነት ሲካሄድ የቆየው የ2018 ዓ.ም የክረምት ወራት ልዩ ልዩ የስፖርት ሻምፒዮና ውድድር ዛሬ በድል በመጠናቀቁ የተሰማቸውን ታላቅ ደስታ በማብሰር፣ በአሁኑ ጊዜ የሲዳማ ክልልና ህዝብ ብራንድ የሆነው የሲዳማ ቡና የስፖርት ክለብ የተመሠረተበት ስፍራ በመሆኑ ወጣቶች አሁንም በርትቶ በመስራት ለዞን፣ ለክልል ከዚያም አለፈው በሀገር አቀፍና በአለም ደረጃ መጫወት የሚያስችላቸውን አቅም መፍጠር እንደሚገባቸው አሳስበዋል።
በመድረኩ፣ ለውድድሩ አሸናፊዎች የሜዳሊያና የማበረታቻ ሽልማት ከተበረከተላቸው በኋላ፤ ውድድር በሰላም እንዲጠናቀቅ አስተዋጽኦ ላደረጉ የወረዳው አመራሮች፣ የፀጥታ አካላትና የበኩላቸውን ኃላፊነት ለተወጡ አካላት የእውቅናና የምስጋና ወረቀት ተበርክቶላቸዋል።