የጉራጌ ዞን ገቢዎች መምሪያ / Gurage Zone Revenue Department

የጉራጌ ዞን ገቢዎች መምሪያ / Gurage Zone Revenue Department Contact information, map and directions, contact form, opening hours, services, ratings, photos, videos and announcements from የጉራጌ ዞን ገቢዎች መምሪያ / Gurage Zone Revenue Department, Government Organization, Welkite, Welk'it'e.

ነገ ኢትዮጵያ ትመርጣለች፤ ኢትዮጵያ ታሸንፋለች!********************ነገ ግንቦት 24 ቀን 2018 ዓ.ም ከ54 ሚሊዮን በላይ ኢትዮጵያውያን ዲሞክራሲያዊ መብታቸውን ተጠቅመው በመምረ...
31/05/2026

ነገ ኢትዮጵያ ትመርጣለች፤ ኢትዮጵያ ታሸንፋለች!
********************

ነገ ግንቦት 24 ቀን 2018 ዓ.ም ከ54 ሚሊዮን በላይ ኢትዮጵያውያን ዲሞክራሲያዊ መብታቸውን ተጠቅመው በመምረጥ ሉዐላዊነታቸውን ለዓለሙ ማህበረሰብ ያረጋግጣሉ። 7ኛው ጠቅላላ ምርጫ የኢትዮጵያውያን ብሔራዊ ጥቅም እና ሉዐላዊ ጉዳይ ነው።

ይህ ታሪካዊ ዕለት የዜግነት ግዴታችንን በክብር የምንወጣበት እና የነገዋን ኢትዮጵያ ዕጣ ፈንታ የምንወስንበት ወሳኝ ምዕራፍ ነው።

እያንዳንዱ ዜጋ ወደ ኮሮጆው የሚከተው የድምፅ ካርድ፣ የሀገርን ሰላም፣ ዕድገትና የህዝቦችን አንድነት የሚገነባ ጠንካራ የመሠረት ጡብ ነው።

አባቶቻችን "ድር ቢያብር አንበሳ ያስር" ብለው በተረትና ምሳሌ እንዳስተማሩን፣ የ54 ሚሊዮን ዜጎች ድምፅ በአንድነት ሲዋሃድ የድህነትን፣ የመከፋፈልንና የኋላቀርነትን ጠንካራ ሰንሰለት በጥሶ መጣል የሚችል የማይበገር አገራዊ አቅም ይፈጥራል።

ምርጫ የሃሳብ ልዕልና የሚረጋገጥበት የሰለጠነ መድረክ እንጂ የጥልና የልዩነት ማራዘሚያ አይደለም። የፖለቲካ ልዩነቶቻችንን በምርጫ ካርድ እንጂ በግጭት የማንፈታበትን ዴሞክራሲያዊ ባህል በተግባር ልናሳይ ይገባል።

ዛሬ የምንመርጠው ተወዳዳሪን ወይም የፖለቲካ ፓርቲን ብቻ ሳይሆን፣ ለልጆቻችን በኩራት የምናስረክባትን ጽኑ እና የበለፀገች ሀገር መሠረት ጭምር መሆኑን መዘንጋት የለብንም።

ስለዚህ፣ ሁላችንም በማለዳ በነቂስ ወጥተን፣ በሰላምና በጨዋነት ድምፃችንን እንስጥ! ድምፃችን ዴሞክራሲያዊ መብታችን ብቻ ሳይሆን፣ መጻኢዋን ኢትዮጵያ የማነፅ ኃይላችን ነው።

ከምንም በላይ ሀገራችንን እናስቀድም፤ የፖለቲካ ውድድሩ ሲያበቃ ለዘለዓለም አብሮን የሚዘልቀው የማይናወጠው ኢትዮጵያዊነታችን ነውና።

#ኢትዮጵያ #ምርጫ #ኢትዮጵያትመርጣለች #ኢትዮጵያታሸንፋለች #በምርጫብቻ

እንኳን ለ1447ኛው የኢድ አል አድሃ (አረፋ) በዓል አደረሳችሁ!  ኢድ ሙባረክ !!                 የጉራጌ ዞን ገቢዎች መምሪያ
27/05/2026

እንኳን ለ1447ኛው የኢድ አል አድሃ (አረፋ) በዓል አደረሳችሁ! ኢድ ሙባረክ !!

የጉራጌ ዞን ገቢዎች መምሪያ

ለመላው የእስልምና እምነት ተከታዮች በሙሉ  እንኳን ለአረፋ በዓል በሰላም አደረሳችሁ እያለ የጉራጌ ዞን ገቢዎች መምሪያ መልካም ምኞቱን ይገልፃል።ማንኛውም ግብይት ሲፈፅሙ በደረሰኝ በማድረግ ...
25/05/2026

ለመላው የእስልምና እምነት ተከታዮች በሙሉ እንኳን ለአረፋ በዓል በሰላም አደረሳችሁ እያለ የጉራጌ ዞን ገቢዎች መምሪያ መልካም ምኞቱን ይገልፃል።
ማንኛውም ግብይት ሲፈፅሙ በደረሰኝ በማድረግ በብልፅግና የተጀመሩ የልማት ስራዎች ላይ አሻራዎን ያሳርፉ !!!
መልካም የአረፋ በዓል!!!

22/05/2026
ጉራጌ ዞን የጉንችሬ ከተማ የአረፋ በዓል የእርድ እንስሳት ግብይት ወቅት ተገቢውን የበረት አ/ሎት በመስጠት ጥሩ ገቢ ተሰብስቧል!!!
22/05/2026

ጉራጌ ዞን የጉንችሬ ከተማ የአረፋ በዓል የእርድ እንስሳት ግብይት ወቅት ተገቢውን የበረት አ/ሎት በመስጠት ጥሩ ገቢ ተሰብስቧል!!!

22/05/2026

ግብይት ሲፈፅሙ በደረሰኝ በማድረግ ለዞኑ ልማት አስተዋጽኦ ያበርክቱ!!!!
የጉ/ዞ/ገ/መምሪያ

“የክልሉን ብሎም የሀገርን የመልማት ጥያቄ ለመመለስ ገቢን በተገቢው ልክ ለመሰብሰብ እንሰራለን”- ወ/ሮ ቀመሪያ ረሻድ (የማእከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ገቢዎች ቢሮ ኃላፊ)ግንቦት 13/2018 ዓ....
21/05/2026

“የክልሉን ብሎም የሀገርን የመልማት ጥያቄ ለመመለስ ገቢን በተገቢው ልክ ለመሰብሰብ እንሰራለን”
- ወ/ሮ ቀመሪያ ረሻድ (የማእከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ገቢዎች ቢሮ ኃላፊ)

ግንቦት 13/2018 ዓ.ም (የገቢዎች ሚኒስቴር)

የማእከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ገቢዎች ቢሮ ባለፉት ዓመታት በተቋሙ ባከናወነው የሪፎርም እና አገልግሎት አሰጣጥን የማዘመን ስራ ገቢ የመሰብሰብ አቅሙ እያደገ መሆኑን የቢሮው ኃላፊ ወ/ሮ ቀመሪያ ረሻድ ገለጹ።

ቢሮ ኃላፊዋ ቢሮው እንደአዲስ ስራ ከጀመረበት 2016 ዓ.ም ጀምሮ ገቢን የመሰብብ አቅሙ እያደገ መምጣቱን ገልጸው በተያዘው በጀት ዓመት መጀመሪያ ታቅዶ የነበረውን 23.7 ቢሊየን ብር የመሰብሰብ እቅድ በመከለስ እና 27 ቢሊየን ለመሰብሰብ በማቀድ በ10 ወራት ውስጥ 21 ቢሊየን ብር መሰብሰብ መቻሉን ገልጸዋል።

አፈጻጸሙ ከባለፈው ዓመት ተመሳሳይ ወቅት ጋር ሲነጻጸርም የ8 ቢሊየን ብር ብልጫ አለው ብለዋል።

ለክልሉ የገቢ እድገት የክልሉ ርዕሰ መስተዳደር፣ በየደረጃው ያለ አመራር፣ የሴክተሩ አመራር እና ሰራተኛ እንዲሁም የግብር ከፋዩ ሚና ከፍተኛ እንደሆነ ገልጸው ላበረከቱት አስተዋጽኦ ምስጋና አቅርበዋል።

የተገኘው ውጤጥ ጥሩ ቢሆንም የክልሉን የልማት ጥያቄ ብሎም የሀገርን የመልማት እና የመበልጸግ ፍላጎት ለማሳካት ከዚህም በላይ ገቢን በተገቢው ልክ ለመሰብሰብ እንደሚሰራም ጠቁመዋል።

ግብር ከፋዩ ወደተቋሙ መምጣት ሳያስፈልገው ባለበት ሆኖ የሚስተናገድበት የታክስ የመረጃ ቴክኖሎጂን የማሳደግ ስራ እንዲሁም የሰው ኃይሉን ክሕሎት የማሳደግ ስራ መከናወኑን የገለጹት ወ/ሮ ቀመሪያ በቀጣይም አገልግሎት አሰጣጥን የበለጠ ቀልጣፋ እና ተደራሽ የማድረግ ስራ ተጠናክሮ እንደሚቀጥል ጠቁመዋል።

ኃላፊዋ አያይዘውም የገቢ መሰረትን ለማስፋት ብሎም የቢሮውን ገቢ የመሰበሰብ አቅምን በቀጣይነት ለማሳደግ ቢሮው ከክልሉ የፋይናንስ ቢሮ፣ በክልሉ ካሉ ዩንቨርሲቲዎች እና ከዘርፉ ባለሙያዎች ጋር በጋራ የክልሉን የገቢ አቅም ለማጥናት ቅድመ ዝግጅት ስራ እየተሰራ መሆኑን የገለጹት ሲሆን በጥናት ላይ በመመርኮዝ የግብር ከፋዮችን ደረጃ የማሻሻል ስራ ይሰራል ብለዋል።

በተጨማሪም ቢሮው ከገቢዎች ሚኒስቴር ጋር በጋራ እያከናወናቸው ያሉትን ስራዎች አጠናክሮ እንደሚቀጥል አሳውቀው የሚደረገው ድጋፍም ይበልጥ እንደሚጠናከር ያላቸውን እምነት ገልጸዋል።

ቢሮ ኃላፊዋ ለግብር ከፋዮች ባስተላለፉት መልእክትም ታክስን በታማኝነት እና በወቅቱ የመክፈል እንዲሁም በግብይት ወቅት ደረሰኝ የመስጠት እና የመቀበል ባህልን በማሳደግ የክልሉን ገቢ በተገቢው ልክ ለመሰብሰብ የሚደረገውን ጥረት እንዲደግፍ ጥሪ አቅርበዋል።

21/05/2026
የጉራጌ ዞን ገቢዎች መምሪያ የባለፉት ወራት የገቢ አፈፃፀም እና የቀጣይ ሁለት ወራት የገቢ እቅድ ስራ ተገመገመ።ግንቦት 11/2018፤ጉራጌ ዞን ገቢዎች መምሪያ የማእከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ገቢ...
19/05/2026

የጉራጌ ዞን ገቢዎች መምሪያ የባለፉት ወራት የገቢ አፈፃፀም እና የቀጣይ ሁለት ወራት የገቢ እቅድ ስራ ተገመገመ።

ግንቦት 11/2018፤ጉራጌ ዞን ገቢዎች መምሪያ

የማእከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ገቢዎች ቢሮ ምክትል ቢሮ ሀላፊ አቶ ደግፍ መለስ በተገኙበት ዛሬ ግንቦት 11/2018 በጉራጌ ዞን ገቢዎች መምሪያ ከዞንና ከተማ ማኔጅመንት ጋር የበጀት ዓመቱ 10 ወራት አፈፃፀም እና በቀጣይ 2 ወራት የሚሰበሰብ የገቢ እቅድ ላይ ውይይት እየተደረገ ይገኛል።

በቀጣይ የበዓል ወቅት እንደመሆኑ ትኩረት ተደርጎ የሚሰራባቸው የገቢ ዘርፎች ተለይተው እንደሚገመገሙ የተጠቆመ ሲሆ የበረት ገቢና የተጨማሪ እሴት ታክስ በአግባቡ ለመሰብሰብ የደረሰኝ ቁጥጥር ስራ ተጠናክሮ ይሰራል ተብሏል።በተለይም የወልቂጤ ከተማ የማዘጋጃ ቤት ገቢ አሰባሰብ ጋር ትኩረት የሚፈልግ መሆኑ ተነስቷል።

18/05/2026

የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ገቢዎች ቢሮ እስከ አሁን 21 ቢሊየን ብር ገቢ መሰብሰቡን አስታወቀ፡፡ዘጋቢ ፡ አብደላ በድሩ #ደሬቴድ የቪዲዮና .....

Address

Welkite
Welk'it'e

Telephone

+251113302254

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when የጉራጌ ዞን ገቢዎች መምሪያ / Gurage Zone Revenue Department posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Share