28/10/2025
የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ሠላምና ፀጥታ ቢሮ ኃላፊ ሆነው ለተሾሙት አቶ አቤንኤዘር ተረፈ እና ምክትል ቢሮ ሀላፊና የግጭት አፈታትና መከላከል ዘርፍ ሀላፊ አቶ መንግስቱ መጃ ከቢሮ ማናጅመንት አባላት እና አጠቃላይ ሠራተኞች ጋር ትውውቅ አደረጉ።
ጥቅምት 18/2018 ዓ.ም ወ/ሶዶ
አዲስ የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ሠላምና ፀጥታ ቢሮ ሀላፊ ሆነዉ የተሾሙት አቶ አቤንኤዘር ተረፈ እና ምክትል የቢሮ ሀላፊ አቶ መንግስቱ መጃ ከቢሮ ማናጅመንት አባላት እና ከአጠቃላይ ሠራተኞች ጋር ትውውቅና የቀጣይ ሥራዎች ዙሪያ ውይይት አድርገዋል።
የቢሮው ማናጅመንት አካላት እና ሠራተኞች አዲስ ለተሾሙት ኃላፊዎች መልካም የሥራና የትጋት ጊዜ እንዲሆን ምኞታቸውን ገለፀዋል።
የቢሮው ኃላፊዉም ለተደረገላቸዉ አቀባበል ምስጋናቸውን አቅርበው በቀጣይ ጊዜ ከሰክተሩ ተልዕኮና ግቦች አንጻር የሚታይ ውጤት ለማስመዝገብና ከመንግስትና ከህዝብ የሚጠበቅበትን ሀላፊነት ለመወጣት ከአጠቃላይ ሠራተኞችና ከባለድርሻ አካላት ለውጥ ለማምጣት በቅንጅት እንደሚሠሩም ጠቁመው ቢሮው ላደረገላቸው አቀባበል አመስግነዋል።
በትዉዉቅ መድረክ አዲሱ ተሿሚዎች፣ የቢሮዉ ም/ሀላፊ አቶ በቀለ ሎኮርማ፣ የማኔጅመንት አባላትና አጠቃላይ ሠራተኞች ተገኝተዋል።