Gesuba town administration office

Gesuba town administration office Contact information, map and directions, contact form, opening hours, services, ratings, photos, videos and announcements from Gesuba town administration office, Government Organization, Sodo.

~~~~~~ ~~~~~~~ ~~~~~
A view of the overall activities of Gesuba city administration!
~~~~~~ ~~~~~~~ ~~~~~
Gessuba is located in the middle of the border areas around Ofa Woreda, Selamber, Bayra Koish

የገሱባ ከተማ ከንቲባ ክቡር አቶ ዴማ ኃይሌ ‎7ኛው  ሀገራዊ ምርጫ በሠላም መጠናቀቁን አስመልክተው  መላውን የከተማው ህዝብን  አመሰገኑ‎‎ግንቦት 25/2018 ዓ.ም. የገሱባ ከተማ ከንቲባ ...
02/06/2026

የገሱባ ከተማ ከንቲባ ክቡር አቶ ዴማ ኃይሌ ‎7ኛው ሀገራዊ ምርጫ በሠላም መጠናቀቁን አስመልክተው መላውን የከተማው ህዝብን አመሰገኑ

‎ግንቦት 25/2018 ዓ.ም. የገሱባ ከተማ ከንቲባ ክቡር አቶ ዴማ ኃይሌ 7ኛው ሀገራዊ ምርጫ በሠላም መጠናቀቁን አስመልክተው መላውን የከተማው ህዝብን አመሰግኗል።

‎ "ለሁሉም የጋራ የሆነችሁ ሃገራችን ኢትዮጵያ መርጣለች አሸንፋለችም!"

‎ ክቡር ከንቲባው 7ኛው ሀገራዊ ምርጫ ዴሞክራሲያዊና ተአማኒነት ያለው ምርጫ እንደሆነና እንዴ ከተማችንና እንዴ አከባቢያችን ፍፁም ሠላማዊ በሆነ መንገድ መጠናቀቁን ገልጿል።

‎ለነገው ትውልድ ምቹ ሀገር ለመፈጠር ሁሉም የከተማችን ህዝብ ሠላማዊ በሆነው መንገድ ምርጫውን በመምረጥ የዛሬውን ሳይሆን የነገው ሰንቃቸው በመታጠቅ፣የጸና ሀገር በቀል ጽናትን ማሳየት ችሏል ብሎዋል።

‎የከተማችን ህዝቦች በአጠቃላይ አረጋዎያን፣ ሴቶች ህጻናትን ተሸክሞ በመዉጣት፣ ወጣቶች፣ አካል ጉዳተኞች፣ ነፍሰ ጡር እናቶች እና አቅመ ደካሞችን ጨምሮ ከጠዋቱ 12፡00 ሰዓት ጀምሮ እስከ ምሽቱ 6፡00 ሰዓት ድረስ በመውጣት ለዚህ ታሪካዊ ምርጫ የራሳቸውን የዜግነት ግዴታቸውን ሰላማዊ በሆነ መንገድ መጠናቀቁን ከንቲባው አመስግነዋል።

‎ከንቲባው እንደገለፁት በከተማችን አጠቃላይ 13 የምርጫ ጣቢያዎች በሁሉም ምርጫው ሙሉ በሙሉ ሰላማዊ፣ ነጻና ያለምንም የጸጥታ ችግር እንዲጠናቀቅ ታላቅ ሚና ለተጫወቱት ለተከበረው የከተማችን ህዝብን ታላቅ ምስጋና አቅርቧል።

‎በተጨማሪ ለተፎካካሪ የፖለቲካ ፓርቲዎች ላሳዩት ሰላማዊና ህጋዊ የፉክክር መንፈስ፣ ብረዱን ተቋቁመው እየሠሩ ያሉ የምርጫ አስፈጻሚዎችና የሚዲያ ባለሙያዎች እንዲሁም ሌሎች ባለድርሻ አካለት ላሳያችሁት ቁርጠኝነትና የስራ ተነሳሽነት ፣ በየደረጃው ለሚገኙ የጸጥታ አካላት ሌሊትና ከቀን በመትጋት አስተማማኝ ሰላም በመፍጠራቸው፣ የአስተዳደር መዋቅሮች፣ የህዝብ ተወካዮች፣ ታዛቢዎችን፣ የሀገር ሸማገልዎች፣ የሀይማኖት መሪዎች ለምርጫው ሰላም ስትጸልዩ የቆያችሁ ምዕመናን ጨምሮ ፣ ያለውን ላቅ ያለ ክብርና ልባዊ ምስጋና አቅርቧል።

‎ከንቲባው በመጨረሻ እንደገለፁት በየምርጫ ጣቢያ ጊዜያዊ የምርጫ ውጤት የተለጠፈ ሰሌሆና የኢትዮጵያ ብሐራዊ ምርጫ ቦርድ ውጤት ይፋ እሰከሚደረገ ደረሰ በትዕግስት እንድተጠባበቁ አሳስበዋል።
‎ ክቡር አቶ ዴማ ኃይሌ
‎ የየገሱባ ከተማ ከንቲባ
‎ ግንቦት 25፣ 2018 ዓ.ም


በሕዝብ ተወካዮች ምክር  ቤት የመንግስት ልማት ድርጅቶች ቋሚ ኮሚቴ ስብሳቢ አቶ መለሰ መና በኦፋ ምርጫ ክልል በገሱባ ከተማ ምርጫ ጣቢያ በመገኘት ድምጻቸውን ሰጥተዋልአቶ አበባየሁ ኤርምያስ ...
01/06/2026

በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የመንግስት ልማት ድርጅቶች ቋሚ ኮሚቴ ስብሳቢ አቶ መለሰ መና በኦፋ ምርጫ ክልል በገሱባ ከተማ ምርጫ ጣቢያ በመገኘት ድምጻቸውን ሰጥተዋል

አቶ አበባየሁ ኤርምያስ በደቡብ ኢትዮጵያ ትራንስፖርት መንገድ ልማት ም/ቢሮ ኃላፊ በገሱባ ከተማ ብሃን ምርጫ ጣቢያ በመገኘት ድምጻቸውን ሰጡ

በኦፋ ምርጫ ክልል በመሃል ቡሻ ምርጫ ጣቢያ በመገኘት የወላይታ ዞን ረዳት መንግስት ተጠሪ ወ/ሮ ሠላማዊት ሳሙኤል ድምጻቸውን ሰጡ
01/06/2026

በኦፋ ምርጫ ክልል በመሃል ቡሻ ምርጫ ጣቢያ በመገኘት የወላይታ ዞን ረዳት መንግስት ተጠሪ ወ/ሮ ሠላማዊት ሳሙኤል ድምጻቸውን ሰጡ

‎ለአምስት ዓመት የሚያስተዳድረንን ፓርቲ በዴሞክራሲያዊ መንገድ መርጠናል፦በወላይታ ዞን የገሱባ ከተማ ነዋሪዎች‎‎መራጮቹ ድምጽ በሠጡበት ወቅት እንዳሉት ምርጫው ሠላማዊ በሆነ መንገድ እየተካሄ...
01/06/2026

‎ለአምስት ዓመት የሚያስተዳድረንን ፓርቲ በዴሞክራሲያዊ መንገድ መርጠናል፦በወላይታ ዞን የገሱባ ከተማ ነዋሪዎች

‎መራጮቹ ድምጽ በሠጡበት ወቅት እንዳሉት ምርጫው ሠላማዊ በሆነ መንገድ እየተካሄደ ነው።

‎7ኛው ጠቅላላ ሀገራዊ ምርጫ በኦፋ ምርጫ ክልል የገሱባ ከተማ ነዋሪዎች ድምጻቸውን በመሰጠት ላይ ይገኛሉ።

‎ዲሞክራሲያዊ ምርጫ ሕዝብ መሪዎቹን ወይም ተወካዮቹን በነፃነት፣ በፍትሃዊነት እና በምስጢራዊ ድምፅ የሚመርጥበት ሂደት ነው። ይህም የዴሞክራሲ መሠረታዊ ክፍል ነው።

‎በዚህ ምርጫ ክልል 112 የምርጫ ጣቢያዎች የሚገኙ ሲሆን መራጮችም ድምፅ መሰጠት ጀምረዋል

‎ዛሬ ሰኞ 24/9/2018 በሚካሄደው 7ተኛው ጠቅላላ ምርጫ ገሱባ ከተማ ነዋሪዎች በታላቅ የዴሞክራሲ ንቅናቄና በከፍተኛ ተነሳሽነት ለመሳተፍ ወደ ምርጫ ጣቢያው እየመጡ መሆኑን አስረድተዋል።

‎እያንዳንዱ የከተማዋ ነዋሪ የያዛት አንዲት ድምፅ የነገዋን ኢትዮጵያ መልክ የመወሰን ታላቅ ዋጋና ሚስጥር እንዳላት በጥልቀት ተረድቷል።

‎የገሱባ ነዋሪዎች በልበ-ሙሉነትና በብስለት የገለጿቸው ልብ የሚነኩ ወሳኝ መልዕክቶች፦

‎የዴሞክራሲ እምብርት ፡ ምርጫ የዴሞክራሲ ባህል የሚለመልምበትና ህጋዊ መንግስት ለመመስረት የሚሻገሩበት ብቸኛው ወሳኝ ድልድይ መሆኑን ያምናሉ።

‎የእምነት ካርድ ፡ በእጃቸው የያዟትን የምርጫ ካርድ ለከተማዋና ለሀገር መጻኢ እድል ይበጃል፣ የተሻለ ተስፋን ይዞ ይመጣል ለሚሉት ፓርቲ ብቻ በልበ-ሙሉነት ድምጽ ለመስጠት ቆርጠዋል።

‎የሰላም ጥበቃ ፡ ሂደቱ ፍጹም ፍትሃዊ፣ ሰላማዊና ዴሞክራሲያዊ ሆኖ እንዲጠናቀቅ እንደ ዜጋ የሚጠበቅባቸውን ታሪካዊ ድርሻ በከፍተኛ ሃላፊነት እየተወጡ እንደሚገኙ ጠቁመዋል

‎የብስለት መለኪያ ከምርጫው ማግስት የምርጫው ውጤት ይፋ እስኪሆን ድረስ በትዕግስት መጠበቅ እንደሚገባ ነዋሪዎች አስገንዝበዋል።

‎ !
‎ !
‎ #ምርጫ2018
‎ !

በገሱባ ከተማ አስተዳደር ባሉ  በሁሉም ምርጫ ጣቢያዎች መራጩ ህዝብ በነቂስ በመውጣት ከሌሊቱ 10 ሰዓት ጀምሮ የሰባተኛው ጠቅላላ ምርጫ ሀገራዊና ክልላዊ ምርጫ ድምጽ ለመስጠት እየተጠባበቀ ያ...
01/06/2026

በገሱባ ከተማ አስተዳደር ባሉ በሁሉም ምርጫ ጣቢያዎች መራጩ ህዝብ በነቂስ በመውጣት ከሌሊቱ 10 ሰዓት ጀምሮ የሰባተኛው ጠቅላላ ምርጫ ሀገራዊና ክልላዊ ምርጫ ድምጽ ለመስጠት እየተጠባበቀ ያለው ህዝብ ሰልፍ አሁናዊ ሁኔታ፤

!
!
#ምርጫ2018

27/05/2026
‎በገሱባ ከተማ አስተዳደር ህዝቡን ተጠቃሚ ያደረጉ የተለያዩ የልማት ስራዎች ተመርቀው ለህዝቡ አገልግሎት ለመስጠት ክፍት ሆነዋል ‎‎ገሱባ፤ግንቦት 19/2018 ዓ.ም በገሱባ ከተማ አስተዳደር ...
27/05/2026

‎በገሱባ ከተማ አስተዳደር ህዝቡን ተጠቃሚ ያደረጉ የተለያዩ የልማት ስራዎች ተመርቀው ለህዝቡ አገልግሎት ለመስጠት ክፍት ሆነዋል

‎ገሱባ፤ግንቦት 19/2018 ዓ.ም በገሱባ ከተማ አስተዳደር የኮሪደር ልማት እና የከተማ ማዘጋጃ ቤታዊ አገልግሎት ማዘመኛ ዲጂታል አገልግሎት በይፋ ተመርቀው ለአገልግሎት ክፍት ሆነዋል።

‎በአገልግሎት ማስጀመሪያ ላይ የተገኙት የዕለቱ ክቡር እንግዳ እና በምክትል ርዕሰ መስተዳድር ማዕረግ የዲላ ክላስተር አስተባባሪ እና የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ግብርና ቢሮ ኃላፊ ዶክተር መሪሁን ፍቅሩ ለከተሞች ዕድገት ገቢን በአግባቡ መሰብሰብ ወሳኝ መሆኑን ተናግረውነጋዴዎች ግብር በጊዜ እንዲከፍሉ አሳስበዋል።

‎ዶክተር መሪሁን አክለውም ማዘጋጃ ቤቱ ከሌብነት በፀዳ መልኩ አገልግሎት መስጠት እንዳለበትም በመግለጽ አገልግሎቱን የማዘመን የተቀላጠፈ እና ከሙስና የፀዳ አገልግሎት ለመስጠት እንደሚያግዝ አስረድተዋል።

‎በኢፌዴሪ የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የመንግስት የልማት ድርጅቶች ቋሚ ኮሚቴ ሰብሳቢ አቶ መለሰ መና መንግሥት ህዝብን ተጠቃሚ የሚያደርጉ በርካታ ፕሮጀክቶችን ሠርቶ ለአገልግሎት እያበቃ እንደሚገኝ ገልጸው ለከተማዋ ዕድገት ሁሉም እጅ ለእጅ ተያይዞ መሥራት እንደሚያስፈልግ አስረድተዋል።

‎የወላይታ ዞን ዋና አስተዳዳሪ ረዳት ፕሮፌሰር ሳሙኤል ተሰማ መንግሥት የህዝቡን የልማትና መልካም አስተዳደር ጥያቄዎች ደረጃ በደረጃ እየፈታ እንደሚገኝ ተናግረዋል።

‎ለከተማዋ እና ህዝብ ዕድገት ሁሉም በትብብር መሥራት እንደሚገባ ዋና አስተዳዳሪው ገልጸዋል።

‎የገሱባ ከተማ ከንቲባ አቶ ደማ ኃይሌ ያለ መላው የከተማው ህዝብ ተሳትፎ ልማት ዕውን አይሆንም ሲሉ ተናግረው ለተባበሩ የከተማው ህዝብ እንዲሁም ለነጋዴው ማህበረሰብ ምስጋና አቅርበዋል።

‎ከተማን ለነዋሪዎች ምቹ ማድረግ የከተሞች መዘመን ምልክት ነው ሲሉ ተናግረው ለነዋሪዎች ምቹ እና ፅዱ የማድረግ እና ቀልጣፋ አገልግሎት የመስጠት ሥራ ተጠናክሮ ይቀጥላል ሲሉ ተናግረዋል።

‎የፌደራል የክልል የዞን የገሱባ ከተማ እና የኦፋ ወረዳ አመራሮች የሚመለከታቸው ባለድርሻ አካላት እንዲሁም የአካባቢው ኅብረተሰብ በተገኙበት ለአገልግሎት ክፍት ሆነዋል።

ብልፅግና ፓርቲ ኢትዮጵያን ወደ ተምሳሌት ሀገር በማሻጋር በፅኑ መሠረት ላይ ለመገንባት እየሰራ ያለ ፓርቲ ነው፦የተከበሩ አቶ መለሰ መናገሱባ፤ግንቦት 15/2018 ዓም በወላይታ ዞን የኦፋ ወረ...
23/05/2026

ብልፅግና ፓርቲ ኢትዮጵያን ወደ ተምሳሌት ሀገር በማሻጋር በፅኑ መሠረት ላይ ለመገንባት እየሰራ ያለ ፓርቲ ነው፦የተከበሩ አቶ መለሰ መና

ገሱባ፤ግንቦት 15/2018 ዓም በወላይታ ዞን የኦፋ ወረዳ እና ገሱባ ከተማ አስተዳደር በጋራ የብልፅግና ፓርቲ ምርጫ ቅስቀሳና ህዝባዊ የድጋፍ ሰልፍ ተካሄደ።

በመርሃግብሩ በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የመንግሥት ልማት ድርጅቶች ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ሰብሳቢና የፌደራል ምክርቤት ዕጩ የተከበሩ አቶ መለሰ መና ብልጽግና ፓርቲ ለሀገር ሁለንተናዊ ዕድገት የሚሠራ ፓርቲ መሆኑን በመግለፅ መጪው ጊዜ ከብልጽግና ጋር ብሩህ ነው ብለዋል።

ዘላቂ ልማትና ሰላምን ለማስቀጠል ሕዝቡ ለፓርቲው ድምፁን እንዲሰጥ እና ብልጽግና ኢትዮጵያን ተምሳሌት ለማድረግና ተጨባጭ ለውጥ ለማምጣት እየተጋ ያለ ፓርቲ ነው ብለዋል።

የተጀመሩትን ሁለንተናዊ የብልጽግና ጉዞዎች ይበልጥ ለማስቀጠል ብልፅግና ፓርቲ ቁርጠኛ መሆኑን ገልፀው ህብረተሰቡ በመጪው የምርጫ ዕለት ድምጹን ለብልጽግና ፓርቲ በመስጠት አጋርነቱን እንዲያረጋግጥ አሳስበዋል ።

የዞኑ ብልፅግና ፓርቲ አደረጃጀት ዘርፍ ኃላፊና የክልል ም/ቤት ዕጩ ወ/ሮ ሰላማዊት ሳሙኤል ብልጽግናን መምረጥ ሠላምን መምረጥ ነው፤ ብልጽግና ፓርቲ የተረጋጋችና በአፍሪካ ብሎም በዓለም ተሰሚነት ያላት ሀገር እንድትሆን እየሰራ ነው ብለዋል።

ፓርቲው የዜጎችን እኩልነትና ፍትሐዊ ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ እየሰራ መሆኑን ጠቅሰው፣ መጪው ምርጫ ሰላማዊ፣ ዴሞክራሲያዊና ፍትሐዊ ሆኖ እንዲጠናቀቅ የፓርቲው አባልና ደጋፊዎች የበኩላቸዉን ሚና መወጣት እንደሚገባቸው አሳስበዋል።

የኦፋ ወረዳ ዋና አስተዳዳሪ አቶ አዲሱ ወርቁ ፓርቲው የጀመራቸውን ዘላቂ የልማትና የብልጽግና ጉዞዎች ዳር ለማድረስ የህዝቡ አንድነትና ድጋፍ ወሳኝ መሆኑን ገልጸዋል።

የገሱባ ከተማ ከንቲባ አቶ ዴማ ኃይሌ የተጀመረውን ለውጥ ይበልጥ ለማስቀጠል የብልጽግና ፓርቲን ይምረጡ! ምልክታችንም የስንዴ ነዶ ነው ሲሉ ጥሪ አስተላልፈዋል ።

በሰልፉ ላይ ታዳሚዎች ፓርቲው እያስመዘገባቸው ያሉትን የልማት ድሎች ይበልጥ ለማጽናት እና የጀመረውን የለውጥ ጉዞ እስከ መጨረሻው ለማስቀጠል ከፓርቲው ጎን በጽናት እንደሚቆሙ ቃል ገብተዋል።

በመርሃግብሩ በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የመንግሥት ልማት ድርጅቶች ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ሰብሳቢና የፌደራል ምክርቤት ዕጩ የተከበሩ አቶ መለሰ መና፣የክልሉ ትራንስፖርትና መንገድ ልማት ቢሮ ም/ኃላፊና የክልል ም/ቤት ዕጩ አቶ አበባየሁ ኤርሚያስ፣የክልል ዋና ኦዲተር መ/ቤት ዋና ኦዲተር አቶ ኢዮብ ዋቴ፣የዞን ብልፅግና ፓርቲ አደረጃጀት ዘርፍ ኃላፊና የክልል ም/ቤት ዕጩ ወ/ሮ ሰላማዊት ሳሙኤል፣የኪንዶ ዲዳዬ ወረዳ ዋና አስተዳዳሪና ክልል ም/ቤት ዕጩ አቶ አበበ ዋኬ፣የኪንዶ ዲዳዬ ወረዳ ብልፅግና ፓርቲ አደረጃጀት ዘርፍ ኃላፊና ክልል ም/ቤት ዕጩ ወ/ሮ መሰለች ቦጋለ፣የዞን አመራሮች፣የኦፋ ወረዳ ዋና አስተዳዳሪ አቶ አዲሱ ወርቁ፣የገሱባ ከተማ ከንቲባ አቶ ዴማ ኃይሌ ጨምሮ አስተባባሪ አካላት ፣ ከተለያዩ ማህበራዊ መሠረት የመጡ ህብረተሰብ ክፍሎች ተገኝተዋል።



"‎ብልፅግና በየአካባቢው ህዝቡን በማሳተፍ በሁሉም ዘርፍ የሚታይ ተጨባጭ ውጤት ያስመዘገበ ፓርቲ ነው"፦ አቶ ገብረመስቀል ጫላ‎‎ግንቦት 11/2018 ዓ.ም በገሱባ ከተማ አስተዳደር በልማትና ...
19/05/2026

"‎ብልፅግና በየአካባቢው ህዝቡን በማሳተፍ በሁሉም ዘርፍ የሚታይ ተጨባጭ ውጤት ያስመዘገበ ፓርቲ ነው"፦ አቶ ገብረመስቀል ጫላ

‎ግንቦት 11/2018 ዓ.ም

በገሱባ ከተማ አስተዳደር በልማትና በመልካም አስተዳደር እንዲሁም በወቅታዊ ሀገራዊና ከባቢያዊ ጉዳዮች ዙሪያ ከተለያዩ የኅብረተሰብ ክፍሎች ጋር የውይይት መድረክ ተካሂዷል።

‎ማጠቃለያ ሀሳብ የሰጡት የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ብልፅግና ፓርቲ ቅ/ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ገ/መስቀል ጫላ ብልፅግና በየአካባቢው ህዝቡን በማሳተፍ በሁሉም ዘርፍ የሚታይ ተጨባጭ ውጤት ያስመዘገበ ፓርቲ መሆኑን ገልፀዋል።

‎ፓርቲያችን ይህንን ልምዱን አጠናክሮ ያስቀጥላል ያሉት ኃላፊው፥ ለዚህም ህዝቡን ብልፅግናን በመምረጥና በማስመረጥ የተጀመሩ ስራዎችን ማስቀጠል ይጠብቅበታል ሲሉም አሳስበዋል።

‎ከኅብረተሰቡ ጋር አንድ በመሆን የተጀመሩ ሥራዎች በሙሉ አመርቂ ውጤቶች የተመዘገቡበትና እጅግ በጣም የሚበረታቱ መሆናቸውንም ጠቅሰዋል።።

‎በከተማው እየተከናወኑ ያሉ ሥራዎች ነጋዴዎችና የኅብረተሰብ ክፍሉ የሚያደርገው ሁሉ ከገሱባ ከተማ አቅም በላይ የሆነና ለሌሎች አከባቢዎች ምሳሌ ሊሆን የሚችል ነው ብለዋል።

‎የወላይታ ዞን የመንግሥት ረዳት ተጠሪ ወ/ሮ ሰላማዊት ሳሙኤል ህዝባችን የመደመጥ የመስራትና የመልማት ብሩህ መንገድ በመሆኑ ከህዝብ የሚነሱ ጥያቄዎች በሙላት መንገዱን ይዞ ተግባራዊ እንዲሆን እንሰራለን ብለዋል።

‎ብልጽግና ፓርቲ ከለውጡ ጊዜ ጀምሮ ባሉ ስምንት ዓመታት ያከናወናቸው በርካታ ተግባራት ለአብነትም በህዳሴ ግድብ ፤የሀገሪቱን ምርትና ምርታማነትን ለማሳደግ የተጀመረው የማዳበሪያ ፋብርካና ሌሎች በአጭር ጊዜ ከድህነት የምንወጣ መሆኑን አቶ ኢዮብ ዋቴ የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ኦዲተር ቢሮ ዋና ኦዲተር ጠቅሰዋል።

‎ከኅብረተሰቡ የሚነሱ ጥያቄዎችን ይዘን ውጤታማ ሥራዎች ለመሥራትና ለመተግበር በከፍተኛ ተነሳሽነት እንደሚሰራ የገሱባ ከተማ ከንቲባ አቶ ደማ ኃይሌ ጠቅሰዋል።




በገሱባ ከተማ አስተዳደር በወቅታዊ ሀገራዊና ከባቢያዊ ጉዳዮች ዙሪያ ልዩ ልዩ የኅብረተሰብ ክፍሎች ጋር የውይይት መድረክ በመካሄድ ላይ ይገኛል ።ገሱባ ግንቦት 11/2018 ዓ.ም በገሱባ ከተማ...
19/05/2026

በገሱባ ከተማ አስተዳደር በወቅታዊ ሀገራዊና ከባቢያዊ ጉዳዮች ዙሪያ ልዩ ልዩ የኅብረተሰብ ክፍሎች ጋር የውይይት መድረክ በመካሄድ ላይ ይገኛል ።

ገሱባ ግንቦት 11/2018 ዓ.ም በገሱባ ከተማ አስተዳደር በወቅታዊ ሀገራዊና ከባቢያዊ ጉዳዮች ዙሪያ ልዩ ልዩ የኅብረተሰብ ክፍሎች ጋር የውይይት መድረክ በመካሄድ ላይ ይገኛል ።

ባለፉት ጊዜያት የተከናወኑ ተግባራትን ፣ የተገኙ ድሎችንና ስኬቶችን በማውሳት መድረኩ ተጀምሯል።

ከተለያዩ የኅብረተሰብ ክፍል ጋር የሚደረገው የውይይት መድረክ በሚቀጥሉት ጊዜያት በከተማችን መንግሥት ለማከናወን ባቀዳቸው ጉዳዮች ሰፊው ጊዜ ተወስዶ እንደሚመከር ተገልጿል።

በመድረኩ ላይ የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ዋና የመንግሥት ተጠሪ አቶ ገብረመስቀል ጫላ የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ኦዲተር ቢሮ ዋና ኦዲተር አቶ ኢዮብ ዋቴ የወላይታ ዞን ረዳት የመንግሥት ተጠሪ ወ/ሮ ሰላማዊት ሳሙኤል ሌሎች ከፍተኛ የመንግሥት የሥራ ኃላፊዎች ከተለያዩ አደረጃጀት የመጡ የኅብረተሰብ ክፍሎች ተሳትፈዋል ።

Address

S**o

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Gesuba town administration office posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Share