Wolaita Zone Police Department new

Wolaita Zone Police Department new Contact information, map and directions, contact form, opening hours, services, ratings, photos, videos and announcements from Wolaita Zone Police Department new, Government Official, south Ethiopia wolaita zone, Sodo.

የወላይታ ዞን ፖሊስ መምሪያ በበዴሳ ከተማ አስተዳደር  በህገ ወጥ መንገድ ሲጓጓዝ የነበረ ኮንትሮባንድ ተያዘ።ወላይታ ሶዶ ግንቦት 28/2018 ዓ/ም(ወዞፖመም)የወላይታ ዞን ፖሊስ መምሪያ ከፌ...
05/06/2026

የወላይታ ዞን ፖሊስ መምሪያ በበዴሳ ከተማ አስተዳደር በህገ ወጥ መንገድ ሲጓጓዝ የነበረ ኮንትሮባንድ ተያዘ።

ወላይታ ሶዶ ግንቦት 28/2018
ዓ/ም(ወዞፖመም)

የወላይታ ዞን ፖሊስ መምሪያ ከፌ/ል ፖለስ በተሰጠዉ መረጃ መሠረት ከበዴሳ ከተማ ፖሊስ ጋር ባደረገዉ የመንገድ ላይ ፍተሻ ከሀዋሳ ወደ ወላይታ ሲጓዝ የነበረ አይሱዙ የህዝብ ማመላለሻ ሠ/ቁጥር ኮድ 3-04839 ደህ ተሽከርካሪ ሞባይል በቁጥር 400 ፓዉር ባንክ 14 በዴሳ ከተማ ሲደርስ ከ3 ተጠርጣሪዎች ጋር መያዙን የወላይታ ዞን ፖሊስ መምሪያ ዋና አዛዥ ኮማንደር ንጋቱ ጌታቸዉ ተናግረዋል።

ኮንትሮባንድ ዕቃዉ ልያዝ የቻለዉ ከጦቃሚ በተሰጠ መረጃ መሠረት መሆኑን የተናገሩት አዛዥ ጥቆማ ከተሰጠበት ሰዓት ጀምሮ ከበዴሳ ከተማ ፖሊስ ጋር በመሆን ከፍተኛ የመንገድ ላይ ፍተሻ በማድረግ እንደሆነ ተናግረዋል።

ኮንትሮባንድ እና ህገ ወጥ ንግድ ለሀገር ኢኮኖሚ ዕድገት ፀር እንደሆነ የተናገሩት አዛዡ በዞናችን ዉስጥ ህገ ወጦችና ኮንትሮባንድስቶች መተላለፊያ መንገድ የላቸዉም ብሏል።

ጥቆማዉ ከደረሰበት ሰዓት ጀምሮ ጉዳዩን በቅርበት ሲከታተሉ እንደነበረ የተናገሩት አዛዡ ለዚህ ተግባር ስምሪት በመዉሰድ የሥራ ኃላፊነታቸዉን የተወጡ የበደሳ የፖሊስ አመራርና አባላትን ያመሰገኑት ስሆን በቀጣይም በትኩረት መሠራት እንዳለበት አጽንኦት ሰጥተዋል።

በወንጀል ተጠርጥሮ በተያዙ ግለሰቦች ላይ ፖሊስ ከጉሙሩክ ኮሚሽን ሀዋሳ ቅርንጫፍ ጋር በመነጋገር ምርመራዉን አጣርቶ ለህግ የሚያቀርብ መሆኑን ተናግረዋል።

በመጨረሻም ኮንትሮባንድና ህገ ወጥ ንግድ ለሀገር ኢኮኖሚ ዕድገት ፀር መሆኑን በመገንዘብ የተለያዩ የመረጃ ምንጮችን በመጠቀም ለኮንትሮባንድስቶች የማይመች አካባቢ ለመፍጠር በቁርጠኝነት እንደሚሰሩ አረጋግጠዋል።

በጀግንነት መጠበቅ በሰብአዊነት ማገልገል!!

02/06/2026
7ተኛዉ አገራዊ ጠቅላላ ምርጫ በዞናችን ባሉት  16 ወረዳ እና 10 ከተማ አስተዳደር ያለ ምንም የጸጥታ ችግር በሠላም ተጠናቀቀወላይታ ሶዶ ግንቦት 25/2018 ዓ/ም(ወዞፖመም)በወላይታ ዞን ...
02/06/2026

7ተኛዉ አገራዊ ጠቅላላ ምርጫ በዞናችን ባሉት 16 ወረዳ እና 10 ከተማ አስተዳደር ያለ ምንም የጸጥታ ችግር በሠላም ተጠናቀቀ

ወላይታ ሶዶ ግንቦት 25/2018 ዓ/ም(ወዞፖመም)

በወላይታ ዞን 7ተኛዉ አገራዊ ጠቅላላ ምርጫ ያለ ምንም የጸጥታ ችግር በሠላም መጠናቀቁን የወላይታ ዞን ፖሊስ መምሪያ ዋና አዛዥ ኮማንደር ንጋቱ ጌታቸዉ ገልጸዋል።

ምርጫዉ በዞኑ በ16 ወረዳ እና 10 ከተማ አስተዳደር በ13 ምርጫ ክልል በ981 ምርጫ ጣቢያ ህዝቡ በሠላም የፈለገዉን ፓርቲ የመምረጥ ዴሞክራሲያዊ መብቱን በመጠቀም ከጧቱ 12.00 እስከ ሌሊቱ 6.00 ሰዓት በሠላማዊ መንገድ ድምጹን ሲሰጥ ማምሸቱን የተናገሩት አዛዡ ህዝቡ በምርጫ ጣቢያ ላሳዩት ትዕግስት አመስግነዋል።

የድምፅ አሰጣጥ ሂደቱ ፍጹም ሠላማዊ፣ነፃና በህዝብ ዘንድ ቁቡልነት ያለዉ እንዲሆን ፖሊስ የምርጫ ሥነ-ምግባር ህግን ባከበረ ሁኔታ ከቅድመ ምርጫ ጀምሮ ተገቢዉን ጥበቃ ሲያደርግ መቆየቱን የተናገሩት አዛዡ መላዉ የዞኑ ህዝብ ከፖሊስ ጎን በመሆን ላደረገዉ ድጋፍ አመስግነዋል።

ፖሊስ የፀጥታ አካላትን በማስተባበር ቀንና ሌሊት የመራጩን ህዝብ እና የምርጫ ቁሳቁስ ደህንነት ለመጠበቅ ያሳየዉ ቁርጠኝነት የሚደነቅ እንደሆነ የተናገሩት አዛዡ ለሥራዉ ስኬት ከፖሊስ ጎን በመሆን ድጋፍ ያደረጉ አካላትን ሁሉ በዞኑ ፖሊስ መምሪያና በራሱ ስም አመስግኗል።

በመጨረሻም በድምፅ አሰጣጥ ሂደት ያሳዩትን ትዕግስትና ጨዋነት ዉጤቱ ተቆጥሮ በይፋ እስከሚገለጽ ድረስ በተለመደዉ ጨዋነት በትዕግስት እንድጠባበቁ ጥሪ አቅርበዋል።

በጀግንነት መጠበቅ በሰብአዊነት ማገልገል!!

''7ተኛዉ ሀገራዊ ጠቅላላ ምርጫ በሠላም እንዲጠናቀቅ አስፈላጊው ቅድመ ዝግጅት ተደርጓል'' - የወላይታ ዞን ፖሊስ መምሪያ ዋና አዛዥ ኮማንደር ንጋቱ ጌታቸዉ።ወላይታ ሶዶ ግንቦት 23/2018...
31/05/2026

''7ተኛዉ ሀገራዊ ጠቅላላ ምርጫ በሠላም እንዲጠናቀቅ አስፈላጊው ቅድመ ዝግጅት ተደርጓል'' - የወላይታ ዞን ፖሊስ መምሪያ ዋና አዛዥ ኮማንደር ንጋቱ ጌታቸዉ።

ወላይታ ሶዶ ግንቦት 23/2018 ዓ.ም (ወዞፖመም) ምርጫው ሠላማዊ ሆኖ እንዲጠናቀቅ በዞኑ ፖሊስ መምሪያ አስፈላጊው ዝግጅት መደረጉን ገልጻል የዞኑ ፖሊስ አዛዥ።

ምርጫዉ ፍጹም ሠላማዊ ሆኖ እንዲጠናቀቅ ፖሊስ ከቅድመ ምርጫ ጀምሮ እሰከ ድህረ ምርጫ ድረስ በዞኑ ሥር ባሉት 16 ወረዳ እና 10 ከተማ አስተዳደር ከሚመለከታቸው አካላት ጋር በቅርበት እየሰራ መሆኑን ተናግረዋል።

በዞናችን ባሉት በ13 ምርጫ ክልልና በ980 ምርጫ ጣቢያዎች ምርጫ ሂደት ያለምንም የፀጥታ ችግር እንዲጠናቀቅ የፀጥታ መዋቅር መላው ህዝብን ፣ ተፎካካሪ ፖርቲን ፣ የምርጫ አስፈጻሚዎችን ፣ የምርጫ ቁሳቁስ ፣ የምርጫ ጣቢያ ፣ የዕጩ ተወዳዳሪዎችን ደህንነት በአስተማማኝ ሁኔታ መጠበቅ እንዲሁም መራጩ ህዝብ ወጥተው መርጦ በሠላም እንድገባ የማድረግ ሥራ በጥብቅ ድስፕሊን መሠራት እንዳለበት አንስተዋል ።

7ኛው ሀገራዊ ጠቅላላ ምርጫ በሠላም እንዲጠናቀቅ ኮማንድ ፖስት ተደራጅተው ኮማንድ ፖስት በሁሉም አከባቢ ተቋቋመው ሥራ መጀመሩን ገልጿል ።

በእያንዳንዱ ምርጫ ጣቢያ የምርጫ ቁሳቁስ የማድረስ ሥራ በተሳካ ሁኔታ መከናወኑን ያነሱት አዛዥ በእስካሁኑ ሂደት ምንም ዓይነት የፀጥታ ችግር አለመኖሩን ተናግረዋል።

ፖሊስ የምርጫ ሂደቱን የሚያደናቅፉ ሠላማዊ ሆኖ እንዳይጠናቀቅ ለማወክ የሚፈልጉ ጸረ ሠላም ኃይሎች ካጋጠሙ በመከታተል አስፈላጊዉን እርምጃ ለመውሰድ ዝግጅት መደረጉን ገልጸዋል።
ፖሊስ የምርጫ አስፈፃሚዎችን፣ መራጮች እና የምርጫ ቁሳቁስ ደህንነት በመጠበቅ በዞኑ የሚገኙ ከ980 በላይ ምርጫ ጣቢያዎች ሠላማዊ ሆነው እንዲጠናቀቅ ኮማንድ ፖስት ተቋቁሞ እየሰራ መሆኑን አንስተዋል ።

ኮማንድ ፖስቱ ምርጫው ተጠናቆ ውጤት ይፋ እስኪሚደረግ ድረስ ሥራውን በተቀናጀ መልኩ እንደሚያከናውን ጠቁመዋል።

መላው ሠላም ወዳድ የዘናችን ህዝብም በሙሉ በፀጥታ መዋቅር ጎን በመቆም ትብብርና እገዛ እንዲያደርጉ ጥርን አስተላልፏል ።

ዘገባው የወላይታ ዞን ፖሊስ መምሪያ ነው።

7ኛው ሀገራዊ ምርጫ ሰላማዊ ሆኖ እንዲጠናቀቅ ዘንድ ለቦዳቲ ከተማ እና ዳሞት ጋሌ ወረዳ ፀጥታ አባላት የስራ ስምሪት ኦሬንተሽን ተሰጠወላይታ ሶዶ ፤ ግንቦት ፤ 21/2018 ዓ.ም (ወዞፖመም)...
29/05/2026

7ኛው ሀገራዊ ምርጫ ሰላማዊ ሆኖ እንዲጠናቀቅ ዘንድ ለቦዳቲ ከተማ እና ዳሞት ጋሌ ወረዳ ፀጥታ አባላት የስራ ስምሪት ኦሬንተሽን ተሰጠ

ወላይታ ሶዶ ፤ ግንቦት ፤ 21/2018 ዓ.ም (ወዞፖመም)

በወላይታ ዞን 7ኛው ሀገራዊ ጠቅላላ ምርጫ ፍጹም ሰላማዊ ሆኖ እንዲጠናቀቅ ዘንድ ለቦዳቲ ከተማ እና ዳሞት ጋሌ ወረዳ ፖሊስ አመራርና አባላት የፀጥታ ስራ ስምሪት እና ኦሬንተሽን ተሰጥቷል።

ኦሬንተሽን መድረኩን የወላይታ ዞን ህ/ግ/ገ/ግ/ዲቪዥን ኃላፊ ም/ኮ/ር ኡፋይሳ ቀልቱ እና በዞኑ ፖሊስ የሙስና ወንጀሎች ምርመራ ድቪዥን ኃላፊ ኢ/ር አስታርቀኝ ጆርጌ በጋራ ሰጥተዋል።

የወላይታ ዞን ህ/ግ/ገ/ግ/ዲቪዥን ኃላፊ ኮ/ር ኡፋይሳ ቀልቱ እንዳሉት ይህ የስራ ስምሪት እና ኦሬንተሽን በፖሊስ አመራርና አባል ፍጹም ተፈጻሚ የሚሆን የመጨረሻው እንደሆነ ገልጸዋል።

ሁሉም የፀጥታ ሀይል በተመደበበት የምርጫ ጣቢያ እጅግ ጥብቅ በሆነ ዲሲፕሊን የምርጫ ቦርዱ በተቀመጡ ህግና ስርዓት በጠበቀ መልኩ ሀላፊነቱን መወጣት ግዴታው እንደሆነ አስገንዝበዋል።

በምርጫው ሂደት ወቅት በጣቢያው በፖሊስ አማካኝነት እንደ ድንገት ችግሮች ቢፈጠር እንኳን ፖሊስ ተጠያቂ መሆኑን ተገንዝቦ ለስራ ትኩረት ሰጥቶ መስራት አለበት ብሏል።

በዋናነት ምርጫው ፍጹም ሰላማዊ ፤ ፍትሐዊ ፤ ነፃና ተዓማኒ መሆን እንዲችል ፖሊስ ነፃና ገለልተኛ ሆኖ ጥበቃ ማድረግ ይኖርበታል ተብሏል።

በምርጫ ጣቢያው በእለቱ ለሌሎች ችግሮች ቢከሰቱ ፖሊስ የምርጫ ጣቢያውን ሀላፊ ፍቃድና ማመልከቻ ታሳቢ አድርጎ የጥበቃ ስራውን ማከናወን እንዳለበትም አሳስበዋል ።

የወላይታ ዞን ፖሊስ የሙስና ወንጀሎች ምርመራ ድቪዥን ኃላፊ ኢ/ር አስታርቀኝ ጆርጌ በበኩላቸዉ ጊዜው በሀገር ጉዳይ ላይ እጅግ አስፈላጊና ወሳኝ ምዕራፍ በመሆኑ ፖሊስ ሰላም ለመጠበቅ ቁርጠኛ ሆኖ እንዲንቀሳቀስ መልዕክት አስተላልፏል።

7ኛው ሀገራዊ ምርጫ ፍጹም ሰላማዊ ፤ ፍትሐዊነት የተረጋገጠ ፤ ነጻና በህዝብ ዘንድ ቅቡልነት ያለው ሆኖ መጠናቀቅ ስላለበት ለዚሁ ስራ የተመደበ ሁሉም የፀጥታ አካል የምርጫ ቦርድ ህግና ስርዓት አክብሮ በተመደቡበት በተጠንቀቅ ላይ በመሆን ግዴታውን እንዲወጣ አመራር ሰጥቷል።

7ተኛዉ አገራዊ ጠቅላላ ምርጫ በሠላም እንዲጠናቀቅ ከዞን ወደ ወረዳና ከተማ አስተዳደር ለተመደቡ አባላት የሥራ ስምሪት እና ኦረንተሽን ተሰጠወላይታ ሶዶ ግንቦት 19/2018 ዓ/ም (ወዞፖመም)...
28/05/2026

7ተኛዉ አገራዊ ጠቅላላ ምርጫ በሠላም እንዲጠናቀቅ ከዞን ወደ ወረዳና ከተማ አስተዳደር ለተመደቡ አባላት የሥራ ስምሪት እና ኦረንተሽን ተሰጠ

ወላይታ ሶዶ ግንቦት 19/2018 ዓ/ም (ወዞፖመም)

ለሰባተኛዉ አገራዊ ጠቅላላ ምርጫ ከወላይታ ዞን ፖሊስ መምሪያ የተመደቡ የፖሊስ አባላት የሥራ ስምሪት እና ኦረንተሽን የሰጡት የወላይታ ዞን ፖሊስ መምሪያ ዋና አዛዥ ኮማንደር ንጋቱ ጌታቸዉ ምርጫዉ በሠላም እንዲጠናቀቅ በእያንዳንዱ ምርጫ ጣቢያ የተመደቡ የፖሊስ አባላት ነፃ እና ገለልተኛ መሆን እንዳለባቸዉ ተናግረዋል።

ከቅድመ ምርጫ ጀምሮ እስከ ድህረ ምርጫ ድረስ በተመደባችበት ምርጫ ጣቢያ የተሰጠዉን የሥራ ኃላፊነት ስትወጡ በቅንነትና በታማኝነት የምርጫ ህጉን ባከበረ ሁኔታ መሆን እንዳለብን አጽንኦት ሰጥተዋል።

ምርጫዉ በሠላም እንዲጠናቀቅ የምርጫ ቁሳቁስ ጥበቃ በተጠናከረ ሁኔታ መሆን እንዳለበት ያነሱ አዛዡ በሁሉም ምርጫ ጣቢያ የተመደቡ የፖሊስ አባላት ከግንቦት 21/2018 ዓ/ም ጀምሮ ወደ ምርጫ ጣቢያ በመግባት የአካባቢዉን ነባራዊ ሁኔታ ጋር በመተዋወቅ የሥራ ግዴታዉን መወጣት እንደሚገባ ተናግረዋል።

የመራጩን ህዝብ፣የፖሌትካ ፓርቲዎች፣የዕጩ ተፎካካሪዎች፣የምርጫ አስፈጻሚዎች ደህንነት እና የምርጫ ቁሳቁስ በሙሉ በአስተማማኝ ሁኔታ መጠበቅ እንዳለበት ተናግረዋል።

የጸጥታ ሥራ ሲሰራ ፍጹም ገለልተኛ መሆን ከማንኛዉም ፓርቲ ዉግንና ነጻ በመሆን በገለልተኝነት ከአድልዎ ነጻ በመሆን ሁሉንም እኩል ማየት እንደሚገባ አሳስበዋል።

ሁሉም ተፎካካሪ ለእኛ እኩል ናቸዉ ያሉት አዛዡ እኩል ማስተናገድ እኩል እይታ ማየት የምርጫ ሥነ ምግባር ህግ ብቻ መሠረት አድርጎ መሠራት አለበት ብለዋል።

በምርጫ ጣቢያ የተመደቡ አመራርና አባላት የሥራ ምደባ የሰጡት የወላይታ ዞን ፖሊስ መምሪያ ማህረሰብ አቀፍ ወንጀል መከላከል ዲቪዥን ኃላፊ የሆኑት ኮማንደር ዘዉዱ ኩሩ በበኩላቸዉ ሁሉም የተጣለበትን የሥራ ኃላፊነት በከፍተኛ ጥንቃቄ እንዲወጡ አሳስበዋል።

በመጨረሻም በምርጫ ጣቢያ የተመደቡ የፖሊስ አመራርና አባላት ሠላማዊ ምርጫ እንዲካሄድ የተጣለባቸዉን ኃላፊነት ለመወጣት ዝግጁ እንደሆኑ በመግለጽ የተጠናከረ ጥበቃ ለማድረግ ያላቸዉን ቁርጠኝነት አረጋግጠዋል።

በመድረኩ የወላይታ ዞን ፖሊስ መምሪያ ዋና አዛዥ ኮማንደር ንጋቱ ጌታቸዉን ጨምሮ የዞኑ ፖሊስ መምሪያ ማኔጅሜንት አካላት እና የዞኑ ፖሊስ መምሪያ አባላት ተገኝተዋል።

ከደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ፖሊስ ኮሚሽን ለ1447ኛ ጊዜ የኢድ አል አድሀ (አረፋ) በዓል በሚከበርበት ወቅት ሊወሰዱ የሚገቡ የጥንቃቄዎች መልእክት ተላልፏል።ወላይታ ሶዶ ግንቦት 17/2018 ዓ/...
26/05/2026

ከደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ፖሊስ ኮሚሽን ለ1447ኛ ጊዜ የኢድ አል አድሀ (አረፋ) በዓል በሚከበርበት ወቅት ሊወሰዱ የሚገቡ የጥንቃቄዎች መልእክት ተላልፏል።

ወላይታ ሶዶ ግንቦት 17/2018 ዓ/ም (ወ.ዞ.ፖ.መም)

የአረፋ በዓል (ኢድ አል አድሀ) ሲከበር ማህበራዊ ትስስርን ለማጠናከርና ሰላማዊ በዓል ለማሳለፍ ከጉዞ፣ከጤናና ከግዥ ጋር የተያያዙ የጥንቃቄ እርምጃዎችን መውሰድ ወሳኝ ነው።

ለ1447ኛ ጊዜ የሚከበረው የአረፋ በዓል በሰላምና በደስታ ተከብሮ እንዲጠናቀቅ የሚከተሉትን ዋና ዋና ነጥቦች መተግበር ይመረጣል።

አላስፈላጊ የሆነ የታሪፍ ጭማሪ እንዳይኖርና ከቦታ ቦታ ሲንቀሳቀሱ ጥንቃቄ ማድረግና የአከባቢው የትራንስፖርት አካላት የሚያስተላልፉትን መመሪያ መከተል ያስፈልጋል።

አሽከርካሪዎች ፍጥነትን በመቆጣጠር፣የአልኮል መጠጥ ጠጥቶ ከመንዳት በመቆጠብ፣ተገቢውን የትራፊክ ህግና ደንብ በማክበርና እረፍት በመውሰድ የትራፊክ አደጋን መከላከል ይገባል።

በተለይም በገበያ ቦታዎችና በህዝብ ማመላለሻዎች ላይ የኪስ አውላቂዎችን ለመከላከል የገንዘብና የቁሳቁስ ጥንቃቄ ማድረግ ይገባል።

የበዓሉ ማዕከላዊ መልዕክት የሆነውን መረዳዳትና መደጋገፍን ከግምት ውስጥ በማስገባት በሰላማዊ መንፈስ ማክበር።

ለበዓሉ ማድመቂያ ቤት ውስጥ የሚከናወኑ የምግብ ዝግጅቶችን ስናዘጋጅ ከከሰል ጭስና ከኤሌክትሪክ አደጋ እራሳችንና ቤተሰቦቻችንን ልንጠብቅ ይገባል።

በሪፖርተር ኢትዮጵያ ወንድሙ!!

የበጎ ፌቃደኛ ወጣቶች አደረጃጀት ከፖሊስ አባላት ጋር በመሆን በሆቢቻ ከተማ ዉስጥ የማታ ሮንድ ሥራ እየሠሩ መሆናቸዉ ተገለጸወላይታ ሶዶ፣ ግንቦት 17/2018 ዓ/ም (ወዞፖመም)በወላይታ ዞን ...
26/05/2026

የበጎ ፌቃደኛ ወጣቶች አደረጃጀት ከፖሊስ አባላት ጋር በመሆን በሆቢቻ ከተማ ዉስጥ የማታ ሮንድ ሥራ እየሠሩ መሆናቸዉ ተገለጸ

ወላይታ ሶዶ፣ ግንቦት 17/2018 ዓ/ም (ወዞፖመም)

በወላይታ ዞን ሆቢቻ ወረዳ የበጎ ፌቃደኛ ወጣቶች አደረጃጀት ከፖሊስ አባላት ጋር በመሆን በሆቢቻ ከተማ ዉስጥ የማታ ሮንድ ሥራ እየሰሩ መሆናቸዉን የሆቢቻ ወረዳ ፖሊስ አዛዥ ረ/ኢ/ር ተስፋዬ ሎሃ ገልጸዋል።

የሆቢቻ ወረዳ ፖሊስ በሆቢቻ ከተማ ዉስጥ የወጣቶች አደረጃጀት አስተባባሪዎች የከተማዉን ሠላም ለማረጋገጥ የጀመሩት የማታ ሮንድ ስራ ተጠናክሮ መቀጠሉ ተገልጿል።

የአካባቢው ሰላም ለመጠበቅና ለማጽናት በትኩረት እየተሰራ መሆኑን የተናገሩት አዛዡ ለነዋሪዎች ሰላም የሰፈነበት ከተማ እንድትሆን የፖሊስ አባላት ከወጣት አደረጃጀት ጋር በመቀናጀት የከተማዉን ፀጥታ ዘላቂና አስተማማኝ ለማድረግ እየሰሩ መሆኑን ተናግረዋል።

ሠላም የሰፈነበት አካባቢን ለመፍጠር ህዝባዊ አደረጃጀቶችን በተለይ ወጣቱን ባለቤት ማድረግ ወሳኝ እንደሆነ የተናገሩት አዛዡ የወጣቶች ጠንካራ አደረጃጀት የወንጀል ድርጊትን ለመከላከል ወሳኝ መሆኑን በመገንዘብ የከተማዉ ወጣቶች ከፖሊስ ጎን መሠለፋቸዉን አድንቀዋል።

በመጨረሻም በማታ ሮንድ ሥራ ላይ የተሰማሩ ወጣቶች ወንጀልን ለመከላከል ከፖሊስ ጎን በመሆናቸዉ መደሰታቸዉን ተናግረዋል።

!!

"በስራዎቻችሁ፣ በእውቀታችሁና በደማችሁ የተገነባችውን ሀገር አብርታችሁ በመጠበቅ፣ በማጽናት፣ ማሳደግ የእናንተ የትውልዱ ኃላፊነት ነው"  ክቡር የኢ.ፌ.ዲ.ሪ ፕሬዚዳንት ታየ አፅቀ ሥላሴ   ...
23/05/2026

"በስራዎቻችሁ፣ በእውቀታችሁና በደማችሁ የተገነባችውን ሀገር አብርታችሁ በመጠበቅ፣ በማጽናት፣ ማሳደግ የእናንተ የትውልዱ ኃላፊነት ነው" ክቡር የኢ.ፌ.ዲ.ሪ ፕሬዚዳንት ታየ አፅቀ ሥላሴ
፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠
ወላይታ ሶዶ፣ ግንቦት 15 ቀን 2018 ዓ.ም:- ክቡር የኢ.ፌ.ዲ.ሪ ፕሬዚዳንት ታየ አፅቀ ሥላሴ በስራዎቻችሁ፣ በእውቀታችሁና በደማችሁ የተገነባችውን ሀገር አብርታችሁ በመጠበቅ፣ በማጽናት፣ ማሳደግ የእናንተ የትውልዱ ኃላፊነት ነው ያሉት የኢትዮጵያ ፖሊስ ዩኒቨርሲቲ የ2018 ዓ.ም የተማሪዎች የምረቃ መርሃ ግብር ላይ ነው::

ባለፉት ዓመታት በትምህርትና ስልጠና ያሳለፋችሁት ጊዜ ውጤታማ እንደነበር ተማምነናል። የትምህርቱ የአእምሮና የአካል ፈተና አልፋችሁ ይህን ክብር በመጎናጸፋችሁ ድጋሚ እንኳን ደስ አላችሁ ካሉ በኋላ ይህ የሙያችሁና የሕይወታችሁ የመጀመሪያ ምዕራፍ ሲሆን፣ ሀገራችሁን በታማኝነትና በልበ ሙሉነት ለማገልገል ዝግጁ የሆናችሁበትና ይህንኑም ለመፈጸም አዲስ እውቀትና የስራ ዝግጁነት ያገኛችሁበት በመሆኑ ልትኮሩበትና ታላቅ ቦታም ልትሰጡት ይገባል ብለዋል።

የሀገራችን የፖሊስ ተቋም በአሁኑ ወቅት የደረሰበትን የእድገት ደረጃ ስንመለከት፣ በተምሳሌትነት የምንጠቅሰው ታላቅ ስኬታማ ተቋም መሆኑንና የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ ከሀገራችን አልፎ በአካባቢያችንና በአህጉራችን ደረጃ ስሙን በጉልህ እያስመዘገበ እንደሚገኝ ተናግረው ለዚህም እንደ ትልቅ አብነት መጥቀስ ያለብን ጉዳይ፣ ተቋሙ በዓለም አቀፍ የሰላም ማስከበርና የጸጥታ ጉዳዮች ላይም በተሟላ ዲሲፕሊንና ንቃት የሀገራችንን የፖሊስ ሙያዊ ብቃት ለዓለም ማሳየት የቻለ ተወዳዳሪ ተቋም መሆኑን ገልፀዋል።

የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ በአሁኑ ወቅት በሰው ኃይል ልማት፣ በዘመናዊ ቴክኖሎጂ እንዲሁም እጅግ the በዘመኑ ትጥቆችና መሣሪያዎች በተለይም ፖሊስ አፕሊኬሽን (Police application) በዓለም እጅግ በጣም ጥቂት ሀገራት ብቻ ያላቸው ነው ያሉት ክቡር የኢ.ፌ.ዲ.ሪ ፕሬዚደንት የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ እዚህ ደረጃ ላይ በመድረሱ ላቅ ያለ ምስጋና አቅርበዋል።

እነዚህ ዘመናዊ ትጥቆችና መሣሪያዎች ከውስጥም ይሁን ከውጭ የሚነሱ ማናቸውንም ፀረ-ሰላምና የሽብር ኃይሎች፣ የሀገራችንን እድገት፣ የሕዝባችንን መለወጥ የማይሹ ባላንጣዎች፣ ጋሻ ጃግሬዎችና ተላላኪዎችን በብቃት ለመከላከልና ለማክሸፍ የሚያስችል ሙሉ አቅም የፈጠረ፣ የሀገር መከታ እንዲሆን ማስቻሉን ጨምረው ገልፀዋል።

የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ ጠቅላይ አዛዥ ክቡር ኮሚሽነር ጀነራል ደመላሽ ገ/ሚካኤል በበኩላቸው የዛሬውን ምርቃት የተለየ የሚያደርገው የ117ኛ የኢትዮጵያ ፖሊስ የምስረታ በዓል እያከበርንበት ባለበት ግዜና በቀጣይ ሳምንት 7ኛው ሀገራዊ ምርጫ ለማድረግ በዝግጅት ላይ በመሆናችን ነው ብለዋል።

ሀገራዊ ምርጫውን ሰላማዊና ነጻ በሆነ መልኩ እንዲካሄድ ለማድረግ ከዚህ በፊት ከነበረው ተሞክሮ በመነሳት የነበረውን ጠንካራና ደካማ ጎን በመገምገም፣ ስልጠና በመስጠት፣ አስፈላጊውን ትጥቅና ቴክኖሎጂ በማሟላት ዝግጅታችንን ያጠናቀቅን በመሆኑ ሂደቱ ፍጹም ሰላማዊ በሆነ ሁኔታ እንዲካሄድ የሀገራችን ሕዝቦች እንደተለመደው ሁሉ ከጎናችን እንዲቆሙ እና በምርጫው የሚፎካከሩ የገዥውም ሆነ የተፎካካሪ ፓርቲዎች እና ደጋፊዎቻቸው የሀገራችን የፀጥታ ኃይሎች ሕግን ለማስከበር በሚያደርጉት እንቅስቃሴ ከጎናችን እንዲሆኑ ጥሪ አቅርበዋል፡፡

ክቡር ኮሚሽነር ጀነራል አያይዘውም የዛሬ ምረቃ ተራ የትምህርት ማጠናቀቂያ ማረጋገጫ የምንሰጥበት መድረክ አይደለም፤ ይልቁንም የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ ላለፉት ዓመታት ያካሄደው መጠነ-ሰፊና ሥር-ነቀል የሪፎርም ጉዞ ያፈራቸውን አንጸባራቂ ፍሬዎች በተግባር የምናይበት ታሪካዊ ዕለት ነው ሲሉ ገልፀዋል።

የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ፣ የሀገራችንን ወቅታዊና መጻኢ ፍላጎቶች ታሳቢ በማድረግ ባከናወናቸው ስትራቴጂካዊ የለውጥ ሥራዎች ዛሬ ላይ ተቋማዊ ቁመናውን በእጅጉ አሳድጓል።

በአስተሳሰብ፣ በአደረጃጀት፣ በትጥቅና በቴክኖሎጂ አጠቃቀም ረገድ ፍጹም ዘመናዊ፣ ገለልተኛና ለህዝብ አገልጋይ የሆነ የፖሊስ ሠራዊት መገንባት ችለናል ብለዋል።

የኢትዮጵያ ፖሊስ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዝዳንት ዶክተር ታምራት ሙሉጌታ የሥልጠና ሪፖርት ባቀረቡበት ወቅት የኢትዮጵያ ፖሊስ ዩኒቨርሲቲ የፖሊስ ተቋማችንን በዕውቀት፣ በክህሎትና በሥነ-ምግባር በበለጸገ፣ በዘመናዊ ቴክኖሎጂ በሰለጠነ የሰው ኃይል ለማጠናከር የተጣለበትን ሀገራዊ አደራ ለመወጣት ታሪካዊ ምዕራፍ ላይ ይገኛል ብለዋል።

የኢትዮጵያ ፖሊስ ዩኒቨርሲቲ የሪፎርም ሥራዎችንና የትምህርት ጥራትን በማሻሻል፣ ለህገ-መንግስቱ መከበር የሚተጋ፣ ሰብአዊ መብቶችን የሚያከብርና ዘመኑ የሚጠይቀውን ዕውቀትና ክህሎት የታጠቀ ፕሮፌሽናል የፖሊስ ሠራዊትና አመራር ለመፍጠር አጫጭር ትምህርትና ስልጠናዎች ጨምሮ እስከ ሦስተኛ ዲግሪ ድረስ እያስተማረ እንደሚገኝ ተናግረዋል።

የሆቢቻ ወረዳ ፖሊስ ወንጀልን በጋራ እንከላከል በሚል መሪ ቃል ባለ ሁለት እግር ሞቴር ሳይክል አሽከርካሪዎች ጋር ዉይይት መድረክ አካሄዱወላይታ ሶዶ፣ ግንቦት 14/2018 ዓ.ም(ወዞፖመም) በ...
22/05/2026

የሆቢቻ ወረዳ ፖሊስ ወንጀልን በጋራ እንከላከል በሚል መሪ ቃል ባለ ሁለት እግር ሞቴር ሳይክል አሽከርካሪዎች ጋር ዉይይት መድረክ አካሄዱ

ወላይታ ሶዶ፣ ግንቦት 14/2018 ዓ.ም(ወዞፖመም)

በወላይታ ዞን የሆቢቻ ወረዳ ፖሊስ ወንጀልን በጋራ እንከላከል በሚል መሪ ቃል ባለ ሁለት እግር ሞቴር ሳይክል አሽከርካሪዎች ጋር ዉይይት መድረክ መካሄዱን የሆብቻ ወረዳ ፖሊስ አዛዥ
ም/ኢ/ር ተስፋዬ ሎሃ ተናግረዋል።

የሆቢቻ ወረዳ ሠላምና ጸጥታ ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ፍቃዱ ላብሶ በበኩላቸው ለሠላም ዘብ ለመሆን የባለሁለት እግር ሞተር አሽከርካሪዎች ድርሻ ከፍተኛ ነዉ ብለዋል።

7ኛውን ሀገራዊና ክልላዊ ምርጫ ለማሳካት አከባቢው ሠላም እንድሆን የየራሳችን ድርሻ እንወጣለን ያሉት ኃላፊዉ ህብረተሰቡ ተፈቃቅረው ተዋድደው ተከባብረው ለመኖር ሠላም ከሁሉም መቅደም ያለበት ጉዳይ ነው ብለዋል።

የሆቢቻ ወረዳ ፖሊስ አዛዥ ም/ኢ/ር ተስፋዬ ሎሃ በበኩላቸው 7ኛው ሀገራዊና ክልላዊ ምርጫ ጋር ተያይዘው ምርጫው ፍጹም ሠላማዊ፣ ፍታዊ፣ ነፃ እና ታዓማኒ እንድሆን የወረዳው ፖሊስ የራሱን ዝግጅት ጨርሷል።

አክለው የሆቢቻ ወረዳ ባለ ሁለት እግር ሞቴር ሳይክል አሽከርካሪዎች ከወንጀል የፀዱ እና ብቁ ዜጋ ሆነው እንድቀጥሉ አክለው ህግ ከሁሉም በላይ መሆኑን ጭምር ለተሽከርካሪዎች አብራርቷል።

አሽከርካሪዎች የህዝብ ጥቅም ማስቀደምና ለህዝብ አገልግሎት እንድትቆሙ ጥሪውን አስተላልፏል።

የሆቢቻ ወረዳ ትራፍክ ፍሰት ቁጥጥሪ አደጋ መከላከል ኃላፊ ረዳት ሳጅን ዳይሰ ዳርጮ በበኩላቸው የትኛውም አሽከርካሪ ፍጥነቱን ቀንሰው በማሽከርከር ከትራፍክ አደጋ አስከፍነት መከላከል ይቻላል ብለዋል።

አክለው ሁሉም አሽከርካሪዎች መንጃ ፍቃድ ይዘው ህጋዊ ሆነው ማሽከርከር እንዳለባቸዉ የተናገሩት ማንም ህግ ጥሰው ከተገኙ ህግ እንደሚጠየቅ አክለዋል።

ረ/ሳ ዳይሴ ሁሉም አሽከርካሪዎች የህዝብ ጥቅም ማስቀደምና የራስ ጥቅም ፈላጊዎች ስግብግብ ሹፌሮች ከድርግታችሁ እንድትቆጥቡ መልዕክት አስተላልፏል።

ህብረተሰቡ ከታርፍ በላይ እየከፈሉ ትራፍክ ገብተው ስጠይቅ የዉሸት መሬጃ እየሰጡ እና ህዝቡ ከሹፌሮች ጋር ከታርፍ በላይ ለመክፈል ዉል ገብተው የሚመጡበት አግባቦች የህግ ጥሰት መሆኑን ጭምር አብራርቷል

በመርሃ ግብሩ የሆቢቻ ወረዳ ሠላምና ጸጥታ ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ፍቃዱ ላብሶ፣ የሆቢቻ ወረዳ ፖሊስ ጽ/ቤት አዛዥ ም/ኢ/ር ተስፋዬ ሎሃ፣ የሆቢቻ ወረዳ ትራፍክ ፍሰት ቁጥጥሪ አደጋ መከላከል ኃላፊ ረዳት ሳጅን ዳይሰ ዳርጮ እና አጠቃላይ ባለሁለት እግር ሞተር ተሽከርካሪዎች አባላቶች በሙሉ ተገኝተዋል።

Address

South Ethiopia Wolaita Zone
Sodo

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Wolaita Zone Police Department new posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Share