በወላይታ ዞን የብልፅግና ፓርቲ ቅ/ጽ/ቤት- Wolaita Zone Prosperity Party Branch office

  • Home
  • Ethiopia
  • Sodo
  • በወላይታ ዞን የብልፅግና ፓርቲ ቅ/ጽ/ቤት- Wolaita Zone Prosperity Party Branch office

በወላይታ ዞን የብልፅግና ፓርቲ ቅ/ጽ/ቤት- Wolaita Zone Prosperity Party Branch office we are in the community!

‎በምርጫው ላይ የታየው የአመራር የተግባርና የአስተሳሰብ አንድነት እና የህዝቡ የነቃ ተሳትፎ በልማት ሥራዎች ላይም ማስቀጠል ያስፈልጋል፦ ወ/ሮ እታገኝ ኃይለማርያም ‎‎ወላይታ ሶዶ፤ግንቦት 2...
04/06/2026

‎በምርጫው ላይ የታየው የአመራር የተግባርና የአስተሳሰብ አንድነት እና የህዝቡ የነቃ ተሳትፎ በልማት ሥራዎች ላይም ማስቀጠል ያስፈልጋል፦ ወ/ሮ እታገኝ ኃይለማርያም

‎ወላይታ ሶዶ፤ግንቦት 27/2018 በወላይታ ሶዶ ከተማ አስተዳደር 7ኛዉ ሀገራዊ ምርጫ አፈጻጸም ግምገማ እና ቀጣይ የመንግስትና የፓርቲ ሥራዎች ላይ ያተኮረ መድረክ ተካሂዷል ።

‎መድረኩን የመሩት የወላይታ ሶዶ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ ወ/ሮ እታገኝ ኃይለማርያም እንደተናገሩት 7ኛው ሀገራዊና ክልላዊ ምርጫ በተቀመጡ መንትያ ግቦች እንዲጠናቀቅ ያስቻሉ አካላትን አመስግነዋል።

‎ከንቲባዋ አያይዘውም በድህረ-ምርጫ ወቅት የሚሰሩ ሥራዎች ዙሪያ አመራሩ ልዩ ትኩረት ሰጥቶ መምራት እንዳለበትም አሳስበዋል።

‎የከተማ አመራር በሙሉ አቅም ወደ መደበኛ ሥራ መግባት ይገባል ያሉት ከንቲባ ወ/ሮ እታገኝ ከተረጂነት ወደ ምርታማነት ጉዞ፥ ሁሉም የገቢ አማራጮች አሟጥጦ መሰብሰብ ፣ የዲጂታል ፋይዳ መታወቂያ ሥርጭት እና ሌሎች ሥራዎች ላይ ልዩ ርብርብ ማድረግ እንዳለበትም አጽንኦት ሰጥተዋል።

‎በወላይታ ሶዶ ከተማ በምርጫው ላይ የታየው የአመራር የተግባርና የአስተሳሰብ አንድነት እንዲሁም የከተማ ነዋሪዎች የነቃ ተሳትፎ፥ እየተሰሩ ባሉት ልማት ሥራዎች ላይም ማስቀጠል እንዳለበትም ወ/ሮ እታገኝ አፅንኦት ሰጥቷል ።

‎በበጀት ዓመቱ ሲሰሩ የቆዩ የፓርቲና የመንግስት መደበኛ ሥራዎች ሳይንጠባጠቡ ተጠናክረው መቀጠል እንደሚገባ ያመላከቱት ከንቲባዋ በከተማችን አልፎ አልፎ የሚገነቡ ህገወጥ የቤት ግንባታ መከላከል እንዳለበትና እንዲሁም ያለ ምህረት ማረም እንደሚገባ አሳስበዋል አሳስበዋል ።

‎የወላይታ ሶዶ ከተማ ብልፅግና ፓርቲ ቅ/ጽ/ቤት ኃላፊ ረዳት ፕሮፌሰር ዘገየ ጳዉሎስ በበኩላቸው 7ኛው ሀገራዊና ክልላዊ ምርጫ በተቀመጡ መንትያ ግቦች እንዲጠናቀቅ ያስቻሉ አካላትን አመስግነዋል።

‎በሁሉም መዋቅር የተቋሙ ዕቅድ አፈጻጸም ያለበት ደረጃ በመገምገምና በምርጫ ሥራ የተጠቀምንበት አደረጃጀት በልማት ሥራዎች ላይ መድገም እንደሚገባ አሳስበዋል ።

‎በወላይታ ሶዶ ከተማ የተጀመሩ የተቀናጀ የኮሪደርና የወንዝ ዳሪቻ ልማት ሥራዎች በፍጥነትና በጥራት መመራት እንደሚገባ ያሳሰቡት ረዳት ፕሮፌሰር በዋናነት በከተማችን በመደበኛና በማዘጋጃ ቤታዊ ገቢ አሳባሰብ ላይ አመራሩ ማተኮር እንደሚገባ አሳስበዋል ።

‎በወላይታ ሶዶ ከተማ የተጀመሩ የልማት ሥራዎች ተጠናክሮ መቀጠል እንዳለበት ያሳሰቡት ረዳት ፕሮፌሰር በከተማችን ህዝቡ ያነሳቸው የልማትና የመልካም አስተዳደር ጥያቄዎች የዕቅድ አካል ተደርጎ ህብረተሰቡን በማሳተፍ መምራት እንዳለበትም አንስተዋል።

‎መደበኛ የፓርቲ መዋጮ ፣የፓርቲ ህንጻ ግንባታ ፣ አዲስ የፓርቲ አባላት የማፍራት፥ በሥራ ዕድል ፈጠራ ላይ የአካባቢው ፀጋ ተኮር በሆነ መልክ መመራት እንደሚገባ እና ኑሮ ዉድነት ለማረጋጋት የተጀመ የስንብት ገበያና ከተረጂነት ወደ ምርታማነት ተግባር በአመራር ቅኝት መመራት እንደሚገባ ረዳት ፕሮፌሰር አሳስበዋል ።

‎በመድረኩ የወላይታ ሶዶ ከተማ ከንቲባ ወ/ሮ እታገኝ ኃይለማርያም፥ የወላይታ ሶዶ ከተማ ብልፅግና ፓርቲ ቅ/ጽ/ቤት ኃላፊ ረዳት ፕሮፌሰር ዘገየ ጳዉሎስ ፣የከተማ አስተባባሪ ኮሚቴ አባላት፣ የከተማ፥ የክፍለ ከተማ እና የቀበሌ አመራሮች መሳተፍ ችለዋል ።


‎ !

‎በወላይታ ዞን በተፈጥሮ አደጋ ከቀያቸው ለተፈናቀሉ ወገኖች ለ2ኛ ዙር መልሶ ለማቋቋም ቀሪ ስራዎች መጠናቀቅ እንደሚገባ ተመላከተ፤‎‎ወላይታ ሶዶ፤ግንቦት 27/2018 የኢትዮጵያ ቀይ መስቀል ...
04/06/2026

‎በወላይታ ዞን በተፈጥሮ አደጋ ከቀያቸው ለተፈናቀሉ ወገኖች ለ2ኛ ዙር መልሶ ለማቋቋም ቀሪ ስራዎች መጠናቀቅ እንደሚገባ ተመላከተ፤

‎ወላይታ ሶዶ፤ግንቦት 27/2018 የኢትዮጵያ ቀይ መስቀል ማህበር ከወላይታ ዞን አስተዳደር ጋር በመተባበር ለ2ኛ ዙር መልሶ ለማቋቋም እያስገባ ያለውን የማህበሩ ቦርድ አባላት ግንባታው ያለበት ደረጃ ምልከታ አድርጓል።

‎በኢትዮጵያ ቀይ መስቀል ማህበር ወላይታ ዞን ቅርንጫፍ ጽ/ቤት የቦርዱ አባላት በማህበሩ ድጋፍ በተፈጥሮ አደጋ ከቀያቸው ለተፈናቀሉ ወገኖች ለ2ኛ ዙር መልሶ ለማቋቋም እየተሰሩ ያሉ ስራዎች መስክ ምልከታ አደርገዋል።

‎ለ2ኛ ዙር መልሶ ለማቋቋም 70 የሚጠጉ ቤቶች በኢትዮጵያ ቀይ መስቀል ማህበር ድጋፍ በተዘጋጀው በሰፈራ ቦታ ታቅዶ እየተሰራ መሆኑን ይታወሳል።

‎ግንባታውን በሁለት ወር ውስጥ እንዲጠናቀቅ የተጀመረ ቢሆንም በተለያዩ ምክንያት ግንባታው መጎተቱን ተገልጿል።

‎ለዚህም የቦርዱ አባላት ከኮንትራክተርና ሌሎች የሚመለከታቸው ባለድርሻ አካላት ጋር በመወያየት አቅጣጫ አስቀምጧል።

‎ቀሪ ስራዎች ጥራቱን በጠበቀ መልኩ በአጭር ጊዜ ውስጥ ልዩ ርብርብ ተደርጎ መጠናቀቅ እንዳለበትም የቦርዱ አባላት አጽንኦት ሰጥቷል።

‎በተፈጥሮ አደጋ ለተፈናቀሉ ዜጎችን መልሶ ለማቋቋም እየተሰሩ ያሉ ስራዎችን ለማየትና አስፈላጊ ድጋፍ ለማድረግ ያለመ ጉብኝት ማድረጉን ተገልጿል።

‎የሚገነቡ ቤቶች እና መሠረተ ልማቶች ለተፈናቃዮች ምቹና ዝግጁ እንዲሆኑ እየተሰሩ ያሉ ስራዎች መጠናቀቅ እንደሚገባም ተመላክቷል።

‎ለ2ኛ ዙር ተፈናቃዮች መልሶ ለማስፈር አስፈላጊ ዝግጅቶች እየተደረጉ ሲሆን በተለይም ጤና፣ ትምህርት እና ሌሎች አስፈላጊ አገልግሎት ሰጪ ተቋማትን ለማሟላት እየተሰራም ነው።

‎ለተፈናቃዮች የመኖሪያ ቤት ግንባታ፣ የንፁህ መጠጥ ወሃ፣ የሕክምና ተቋማት እና ሌሎች አስፈላጊ መሠረተ ልማትና አገልግሎት ሰጪ ተቋማት ግንባታ እየተጠናቀቀ ይገኛል።

‎በዞኑ ካዎ ኮይሻ ወረዳ በተከሰተው በመሬት መንሸራተት እና ናዳ ምክንያት ከቀያቸው ለተፈናቀሉት ወገኖች በአበላ አባያ ወረዳ አባያ ጮካሬ ጥጣ መንደር ላይ "ሰፈራ ጣቢያ" በተዘጋጀው ቦታ የመጀመሪያ ዙር ተፈናቃዮች ማስፈሩን ይታወሳል።


"7ኛው ጠቅላላ ምርጫ ሠላማዊና ዴሞክራሲያዊ ሆኖ በስኬት ተጠናቋል"- የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል የፖለቲካ ፓርቲዎች የጋራ ምክር ቤትግንቦት 27/2018 ዓ.ምየደቡብ ኢትዮጵያ ክልል የፖለቲካ ፓር...
04/06/2026

"7ኛው ጠቅላላ ምርጫ ሠላማዊና ዴሞክራሲያዊ ሆኖ በስኬት ተጠናቋል"- የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል የፖለቲካ ፓርቲዎች የጋራ ምክር ቤት

ግንቦት 27/2018 ዓ.ም

የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል የፖለቲካ ፓርቲዎች የጋራ ምክር ቤት 7ኛው ጠቅላላ ሀገራዊና ክልላዊ ምርጫ በስኬት መጠናቀቁን በማስመልከት መግለጫ ሰጥቷል።

ምክር ቤቱ በመግለጫው 7ተኛው ጠቅላላ ሀገራዊ ምርጫ ከዚህ ቀደም ከነበሩ የምርጫ ሂደቶች ሕብረተሰቡ በነፃነት ተሳትፎ ያደረገበት መሆኑን ገልጿል።

በክልሉ 22 የፖለቲካ ፓርቲዎች እና 2 የግል ዕጩዎች ለኢፌዴሪ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት እንዲሁም ለክልል ምክር ቤት መቀመጫዎች ጠንካራ ዝግጅት በማድረግ ወደ ምርጫው መግባታቸውን አስታውቋል።

በቅድመ ምርጫው ሂደትም ሁሉም የፖለቲካ ፓርቲዎች ሀገራዊና ክልላዊ ሚዲያዎችን በመጠቀም በምርጫ ቦርድ በተመደበላቸዉ ነፃ የአየር ሰዓት መሠረት ፕሮግራሞቻቸውን ማስተዋወቃቸዉን ጠቁሟል።

በምርጫዉ ዕለት ግንቦት 24/2018 ዓ.ም በክልሉ በሚገኙ 3 ሺህ 941 የምርጫ ጣቢያዎች ከምሽቱ 1 ሰዓት እስከ ምሽቱ 6 ሰዓት ህብረተሰቡ ለመረጠው የፖለቲካ ፓርቲ በሠላም ድምፅ ሲሰጥ መዋሉ መረጋገጡን በመግለጫው ጠቅሰዋል።

ምክር ቤቱ በብሔራዊ የምርጫ ቦርድ የሚሰጠውን የመጨረሻ ዉጤት በመጠባበቅ ላይ እንደሚገኝ በመግለፅ በምርጫዉ መንግስት ለመመስረት የሚያስችል ድምፅ ለሚያገኘዉ ፓርቲ ከወዲሁ የእንኳን ደስ አላችሁ መልዕክት አስተላልፏል።

የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል የፖለቲካ ፓርቲዎች የጋራ ምክር ቤት ሰብሳቢ አቶ ጎበዜ አበራ የ7ተኛው ጠቅላላ ምርጫ ሂደት ዉጤታማና ተሞክሮ የተወሰደበት እንደሆነ ተናግረዋል።

የክልሉ የፖለቲካ ፓርቲዎች የጋራ ምክር ቤት ም/ሰብሳቢ አቶ ሳጌ ሻምባ በበኩላቸው ምክር ቤቱ የዴሞክራሲ ግንባታ ተቋም በመሆን ከቅድመ ምርጫ ጀምሮ የነበሩ ሂደቶችን በስኬትና መምራቱን ገልፀዋል።

ምክር ቤቱ የጀመራቸውን የዴሞክራሲ ግንባታ ስራዎች በቀጣይም በተሻለ ተቋማዊ ጥንካሬ አጠናክሮ እንደሚቀጥል አስረድተዋል።

የክልሉ መንግስትን ጨምሮ አጠቃላይ የምርጫው ሂደት ሰላማዊና የተሳካ ሆኖ እንዲጠናቀቅ የበኩላቸውን ሚና ለተወጡ አካላት የጋራ ምክር ቤቱ ምስጋና አቅርቧል።

‎የወላይታ ሶዶ ከተማ ብልፅግና ፓርቲ ቅ/ጽ/ቤት 7ተኛዉ ሀገራዊ ምርጫ ሥራዎች አፈፃፃም በመገምገም የቀጣይ ትኩረት አቅጣጫዎች ላይ መክሯል ‎‎ወላይታ ሶዶ፤ግንቦት 26/2018 የወላይታ ሶዶ ...
03/06/2026

‎የወላይታ ሶዶ ከተማ ብልፅግና ፓርቲ ቅ/ጽ/ቤት 7ተኛዉ ሀገራዊ ምርጫ ሥራዎች አፈፃፃም በመገምገም የቀጣይ ትኩረት አቅጣጫዎች ላይ መክሯል

‎ወላይታ ሶዶ፤ግንቦት 26/2018 የወላይታ ሶዶ ከተማ ብልፅግና ፓርቲ ቅ/ጽ/ቤት 7ተኛዉ ሀገራዊ ምርጫ ሥራዎች አፈፃፃም በመገምገም የቀጣይ አቅጣጫዎች ላይ ውይይት አካሂዷል።

‎የወላይታ ሶዶ ከተማ ብልፅግና ፓርቲ ቅ/ጽ/ቤት ኃላፊ ረዳት ፕሮፌሰር ዘገየ ጳዉሎስ 7ኛው ሀገራዊና ክልላዊ ምርጫ በተቀመጡ መንትያ ግቦች እንዲጠናቀቅ ያስቻሉ አካላትን አመስግነዋል።

‎ኃላፊው አያይዘውም በድህረ-ምርጫ ወቅት የሚሰሩ ሥራዎች ዙሪያ አመራሩ ልዩ ትኩረት ሰጥቶ መምራት እንዳለበትም አሳስበዋል።

በወላይታ ሶዶ ከተማ የተጀመሩ የተቀናጀ የኮሪደርና የወንዝ ዳሪቻ ልማት ሥራዎች በፍጥነትና በጥራት መመራት እንደሚገባ ያሳሰቡት ረዳት ፕሮፌሰር በዋናነት በከተማችን በመደበኛና በማዘጋጃ ቤታዊ ገቢ አሳባሰብ ላይ አመራሩ ማተኮር እንደሚገባ አሳስበዋል ።

‎በበጀት ዓመቱ ሲሰሩ የቆዩ የፓርቲና የመንግስት መደበኛ ሥራዎች ሳይንጠባጠቡ ተጠናክረው መቀጠል እንደሚገባ ያመላከቱት ረዳት ፕሮፌሰር በከተማችን አልፎ አልፎ የሚገነቡ ህገወጥ የቤት ግንባታ መከላከል እንዳለበትና እንዲሁም ያለ ምህረት ማረም እንደሚገባ አሳስበዋል አሳስበዋል ።

‎የከተማ አመራር በሙሉ አቅም ወደ መደበኛ ሥራ መግባት ይገባል ያሉት ረዳት ፕሮፌሰር ፥ የዓመቱ ቀሪ ሥራዎች ላይ ልዩ ርብርብ ማድረግ እንዳለበትም እንዲሁም የሰንበት ገበያ ማጠናከር እንደማገባ አጽንኦት ሰጥተዋል።

‎በምርጫው ላይ የታየው የአመራር የተግባርና የአስተሳሰብ አንድነት እንዲሁም የከተማ ነዋሪዎች የነቃ ተሳትፎ ተጠናክሮ መቀጠል እንዳለበትም አሳስበዋል።

‎እያንዳንዱ ተቋም የተቋሙ ዕቅድ አፈጻጸም ያለበት ደረጃ በመገምገምና ቀጣይ ትኩረት አቅጣጫዎች ላይ ትኩረት በማድረግ ሊረባረብ እንደሚገባም አመላክተዋል።

በወላይታ ሶዶ ከተማ የተጀመሩ የልማት ‎ሥራዎች ተጠናክሮ መቀጠል እንዳለበት ያሳሰቡት ረዳት ፕሮፌሰር በከተማችን ህዝቡ ያነሳቸው የልማትና የመልካም አስተዳደር ጥያቄዎች የዕቅድ አካል ተደርጎ ህብረተሰቡን በማሳተፍ መምራት እንዳለበትም አንስተዋል።

‎በመጨረሻም ረዳት ፕሮፌሰር ቀጣይ መሰራት የሚገቡ ጉዳዮች ላይ ጠንከር ያሉ አቅጣጫዎችን አስቀምጠዋል።


!

የክልሉ መስተዳድር ምክር ቤት በ30ኛ መደበኛ ጉባኤው በቀጣይ 30 ቀናት እቅድ ስራዎች ዙሪያ በመምከር አቅጣጫ አስቀመጠየደቡብ ኢትዮጵያ ክልል መንግስት መስተዳድር ምክር ቤት በበይነ መረብ ባ...
03/06/2026

የክልሉ መስተዳድር ምክር ቤት በ30ኛ መደበኛ ጉባኤው በቀጣይ 30 ቀናት እቅድ ስራዎች ዙሪያ በመምከር አቅጣጫ አስቀመጠ

የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል መንግስት መስተዳድር ምክር ቤት በበይነ መረብ ባካሄደው 30ኛ መደበኛ ጉባኤው ከምርጫ ማግስት ባለው የአንድ ወር የቅድመ መንግስት ምስረታ ወቅት በሚከናወኑ የቀጣይ የአንድ ወር ስራዎች ዕቅድ ዙሪያ በመምከር ቀጣይ አቅጣጫን አስቀምጧል፡፡

በጉባኤው የክልሉን መንግስት የ2018 ያለፉ አስር ወራት አጠቃላይ ስራዎች ዕቅድ አፈፃፀም እንዲሁም እንደ ሀገር በወጥነት ለማሳካት የታለሙ ሀገራዊ የልማት ኢንሼቲቮች ታሳቢ ያደረገ የቀጣይ የአንድ ወር ስራዎች መሪ ዕቅድ ቀርቦ ሰፊ ውይይት ተደርጎበታል፡፡

ርዕሰ መስተዳድሩ በውይይቱ ወቅት፡- በ7ኛው ጠቅላላ ሀገራዊ ምርጫ ህዝቡ በቅድመ ምርጫና በምርጫው ሂደት ያሳየው አስደናቂ ንቁ ተሳትፎ እንዲሁም በድህረ ምርጫው የታየው ስክነትና ጨዋነት ምርጫው ፍጹም ሰላመዊ በሆነ መንገድ ዴሞክራሲያዊ ሂደቱን ጠብቆ በስኬት እንዲጠናቀቅ ማስቻሉን ገልፀው፤ ዕውቅናና ምስጋና ይገባዋል ሲሉ ተናግረዋል፡፡

በቅድመ ምርጫው የተሰሩ ስራዎች ሀገራዊ ምርጫውን እጅግ ሰላማዊ፤ ነፃ፤ ፍትሃዊ፣ ታአማኒ እና ዴሞክራሲያዊ ሆኖ በስኬት እንዲጠናቀቅ አስትዋፅኦ ማበርከቱን ጠቅሰው፤ የህዝቡን ሰላማዊና ጨዋነት የተሞላው ተሳትፎን ጨምሮ በሂደቱ የድርሻቸውን ለተውጡ አካላት በሙሉ ምስጋና አቅርበዋል፡፡

ርዕሰ መስተዳድሩ አጠቃላይ የምርጫው ውጤት በብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ተገልጾ የመንግስት ምስረታ እስከሚካሄድ ምንም መዘናጋት ሳይፈጠር በምርጫው አስደናቂ አኩሪ ተግባር የፈጸመው ህዝባችንን በልማትና በመልካም አስተዳደር ስራዎች ለመካስ በልዩ ትኩረት መስራት እንደሚገባ አሳስበዋል፡፡

ለዚህም የተጀመሩ የልማት ተግባራትን በማጠናከር ለህዝብ አዳጊ የልማት ጥያዌዎች ምላሽ መስጠት የሚያስችል በየዘርፉ የአንድ ወር እቅድ በማቀድ ለተግባራዊነቱ መረባረብ እንደሚገባ ተናግረዋል።

አክለው እቅዱ በተለይ በክብር ጠ/ሚ ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)፤ በየዘርፉ እምርታ ለማስመዝገብ እንደ ሀገር የተቀመጡ ሀገራዊ ግቦችን እንዲሁም በንቅናቄና በመደበኛ የሚመሩና የሚሰሩ ስራዎችን በመለየት እና ያሉ ተጨባጭ አቅሞችን ተጠቅሞ ፈጠራና ፍጥነት በታከለ አፈጻጸም ለውጤት ለማብቃት የሚያስችሉ ስልቶችን ታሳቢ ያደረገ ልሆን እንደሚገባም አስገንዝበዋል፡፡

ርዕሰ መስተዳድሩ የስራዎች አፈጻጸምን ለውጤት ለማብቃት በጠናካራ ድጋፍና ክትትል መደገፍ እንደሚገባም ጠቅሰው፤ በየደረጃው ያለው አመራር ከህዝብና ከመንግስት የተጣለበትን ከፍተኛ ኃላፊነት በአግባቡ በመወጣት፤ በቀሪ ጊዜያት የተሰነቁ ግቦችን ያለምንም መሸራረፍ በመፈጸምና በማስፈጸም የውጤት ዘላቂነትን ማረጋገጥ እንደሚገባው አሳስበዋል፡፡

መስተዳድር ምክር ቤቱ በስብሰባው በቀጣይ 30 ቀናት ሊሳኩ የሚገቡ እና በእጥፍ ለማሳደግ መሰራት የሚገባቸውን ተግባራት በመለየት ቀጣይ አቅጣጫ ያስቀመጠ ሲሆን ከነዚህም፡-

* በግብርና ልማት ዘርፍ በቀሪ የበልግና የቀጣይ የመኸር እርሻ ስራዎች ምርታማነትን የማሳደግ፤ በሌማት ትሩፋት በእጥፍ የማብዛት እንዲሁም ለአረንጓዴ አሻራ ስራዎች በትኩረት መስራት፤

* የገቢ አሰባሰብ ስራዎችን በልዩ ትኩረት በቅንጅት በመምራትና ኢኮኖሚው ከሚያመነጨው ገቢ ፍትሀዊ ግብር በመሰብሰብ የህዝብ የልማት ጥያቄዎችን በብቃት ለመመለስ የሚስችል የውስጥ አቅምን የማጠናከር ተግባራት፤

* አገልግሎት አሰጣጥ የማዘመን ስራዎችን የማጠናከር በተለይም በዲላ እና በአርባ ምንጭ ከተሞች የተጀመሩ የመሶብ የአንድ ማዕከል አገልግሎት መስጫ ማዕከላት ፈጥኖ በማጠናቀቅ

‎በወላይታ ዞን ብልፅግና ፓርቲ ቅርንጫፍ የሴቶች ክንፍ ጽ/ቤት ኃላፊ ወ/ሮ ጫልቱ ላምቤቦ ምርጫው በሰላምና በስኬት መጠናቀቁን አስመልክተው ለዞኑ ሴቶች የምስጋና መልዕክት አስተላለፉ‎‎ኃላፊዋ...
03/06/2026

‎በወላይታ ዞን ብልፅግና ፓርቲ ቅርንጫፍ የሴቶች ክንፍ ጽ/ቤት ኃላፊ ወ/ሮ ጫልቱ ላምቤቦ ምርጫው በሰላምና በስኬት መጠናቀቁን አስመልክተው ለዞኑ ሴቶች የምስጋና መልዕክት አስተላለፉ

‎ኃላፊዋ 7ኛው ሀገራዊና ክልላዊ ምርጫ በሠላምና በስኬት እንዲጠናቀቅ የዞኑ ሴቶች ላበረከቱት አስተዋጽኦ ልባዊ ምስጋናቸውን አቅርበዋል።

‎7ኛው ሀገራዊና ክልላዊ ምርጫ ነፃ ፣ሰላማዊና ፍትሃዊ እንዲሆን የዞኑ ሴቶች፣ በየደረጃው የሚገኙት የክንፉ አመራሮች፣ አባላትና ደጋፊዎች ሚና እጅግ የላቀና የሚመሰገን ነው ብለዋል።

‎የዞኑ ሴቶች ክንፍ አመራሮች ፣አባላትና ደጋፊዎች ያደረጉት ንቁ ተሳትፎ ከፍተኛ አስተዋፅኦ እንዳለው ጠቅሰው፣ በመራጮች ምዝገባ፣ በምርጫ ስነ-ምግባር ማክበር፣ ግንዛቤ በመፍጠርና በምርጫው በነቂስ በመሳተፍ ያሳዩትን ኃላፊነት አድንቀዋል።

‎የዞኑ ሴቶች ክንፍ አመራሮችና አባላት ያለባቸውን ተደራራቢ ኃላፊነት በብቃት ከመወጣት ባለፈ ለሀገር ሰላም፣ ልማትና ዴሞክራሲያዊ ሂደት ስኬት ያሳዩት ቁርጠኝነት በታሪክ የሚወሳ ነው ብለዋል።

‎በተለይም የለሊቱ ብርድ፣ የቀኑ ፀሐይ፣ በየምርጫ ጣቢያው የነበሩ ረጃጅም ሰልፎች ሳይበግራቸዉ በፅናት ድምፃቸውን ለሰጡ ነፍሰ-ጡር እናቶች፣ አራስ እናቶች፣ ከህመማቸው ጋር እየታገሉ ድምፃቸውን ለሰጡ ሴቶች በሙሉ ያላቸው ክብርና አድናቆታቸውን ገልጸዋል።

‎በቀጣይም ሴቶች ይህንን ንቁ ተሳትፎና ሀገራዊ ኃላፊነት በማስቀጠል በድህረ-ምርጫ ስራዎች፣ መንግስትን ለማፅናት በሚከናወኑ ተግባራትና በአጠቃላይ በሁለንተናዊ ብልፅግና ስራዎች ላይ ሚናቸውን እንዲወጡ ጥሪ አቅርበዋል።

‎የምርጫው ይፋዊ ውጤት በኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ እስኪገለፅ ድረስ ሁሉም ሴቶች ህግና ሥርዓትን በማክበር በትዕግስት እንዲጠባበቁ አሳስበዋል።

‎ኢትዮጵያውያን መርጠዋል፤
‎ኢትዮጵያ አሸንፋለች!

‎ፈጣሪ ኢትዮጵያንና ህዝቦቿን ይባርክ! አመሠግናለሁ።

‎ ጫልቱ ላምበቦ
‎የወላይታ ዞን ብልፅግና ፓርቲ ቅርንጫፍ የሴቶች ክንፍ ጽ/ቤት ኃላፊ

‎7ኛው ሀገራዊና ክልላዊ ምርጫ በሠላም እንዲጠናቀቅ ወጣቶች ላበረከቱት አስተዋጽኦ ወጣት ታደለ ሜጋ ምስጋና አቀረቡ‎‎የወላይታ ዞን ብልፅግና ፓርቲ ወጣቶች ክንፍ ቅ/ጽ/ቤት ኃላፊ ወጣት ታደለ...
03/06/2026

‎7ኛው ሀገራዊና ክልላዊ ምርጫ በሠላም እንዲጠናቀቅ ወጣቶች ላበረከቱት አስተዋጽኦ ወጣት ታደለ ሜጋ ምስጋና አቀረቡ

‎የወላይታ ዞን ብልፅግና ፓርቲ ወጣቶች ክንፍ ቅ/ጽ/ቤት ኃላፊ ወጣት ታደለ ሜጋ 7ኛው ሀገራዊና ክልላዊ ምርጫ በሠላም እንዲጠናቀቅ ወጣቶች ላበረከቱት አስተዋጽኦ ምስጋናቸውን አቅርበዋል።

‎መንግስት ምርጫውን ለማካሄድ ካቀደበት ጊዜ አንስቶ እስከሚካሄድ ድረስ ወጣቶች ያደረጉት አስተዋጽኦና ተሳትፎ እጅግ የሚደነቅና የሚመሰገን ነው።

‎ወጣቱ ሀገር ተረካቢ ብቻ ሳይሆን በሀገር ግንባታውም ግንባር ቀደም ሚና ይጫወታል፣ በዘንድሮ ምርጫ ወጣቶች በመራጭነት፣ በተመራጭነት፣ በምርጫ አስተባባሪነት እንዲሁም በታዛቢነት የሚጠበቅባቸውን እየተወጡ ምርጫው በሰላም እንዲጠናቀቅ በርካታ ኃላፊነት ተወጥቷል።

‎7ኛው ሀገራዊ ምርጫ በዴሞክራሲያዊ፣ ፍትሃዊና ነፃነቱን በጠበቀ መልኩ እንዲካሄድ በየደረጃው የሚገኙት የብልፅግና ፓርቲ ወጣቶች ክንፍ አመራሮች፣ አባላትና ደጋፊዎች ታሪካዊ ኃላፊነታቸውን በአግባቡ ተወጥተዋል።

‎በዚህ ታሪካዊ ስኬት ውስጥ የብልጽግና ወጣቶች ክንፍ አመራርና አባላት የነበራቸው ሚና እጅጉን የላቀ ነበር። ክንፉ በ7ኛው ምርጫ ወቅት የመራጮች ምዝገባ ንቅናቄን በባለቤትነት በመምራት፣ ወጣቱ የምርጫ ካርድ እንዲወስድና የዴሞክራሲ ባለቤት እንዲሆን በማድረግ በኩል አቻ የማይገኝለት ሥራም ሰርቷል፡፡

‎የንቃተ-ህሊና ግንባታ ሥራዎችን እስከ ታችኛው መዋቅር በማውረድ ወጣቱ በምክንያታዊነትና በሠላማዊ ምርጫ እንድካሄድ ተችሏል።

‎የወጣቶች የማይናወጥ ሰላም፣ ፍቅር፣ የጸና የአንድነት መንፈስ እና ልባዊ የሕግ አክባሪነት ለዚህ ታሪካዊ ስኬት ዋነኛውና የማይናጋው መሠረት ነው።

‎ይህ ምርጫ በሰላም መጠናቀቁ የዞናችን ወጣቶች የዴሞክራሲ ባሕልን እያዳበረና እያጠናከረ መምጣቱን፣ ለዘላቂ ሰላም ያለውን ፍጹም ቁርጠኝነት እና ለሀገር ግንባታ ያለውን ንቁ ተሳትፎ በግልጽ ያሳየበት ታላቅ ማረጋገጫ ነው።

‎ይህንን ያገኘነውን በጎ ተሞክሮ እና መልካም ልምድ ይበልጥ በማስቀጠል ለላቀ ሰላም፣ ለተፋጠነ ልማትና ለአጠቃላይ ብልፅግና በጋራ እንደምንሠራ ያለን እምነት ፍጹም ጽኑ ነው።

‎የምርጫው የመጨረሻ ውጤት በኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ በይፋ እስከሚገለጽ ድረስ ወጣቱ ትውልድ እንደተለመደው ሁሉንም አሰራር በማክበርና በመታገስ የበኩሉን አስተዋፅኦ እንዲወጣ እናሳስባለን።

‎ኢትዮጵያውያን መርጠዋል! ኢትዮጵያም አሸንፋለች!

‎የዞናችን ወጣቶች ተሳትፎ ለሁለንተናዊ ብልፅግናችን ዋስትና ነው!
‎ ታደለ ሜጋ
‎የወላይታ ዞን ብልፅግና ፓርቲ ቅርንጫፍ የወጣቶች ክንፍ ጽ/ቤት ኃላፊ

‎የወላይታ ዞን ብልፅግና ፓርቲ ቅ/ጽ/ቤት የምርጫ ሥራዎች አፈፃፃም በመገምገም በቀጣይ ሥራዎች ላይ መክሯል‎‎ወላይታ ሶዶ፤ግንቦት 26/2018 የወላይታ ዞን ብልፅግና ፓርቲ ቅ/ጽ/ቤት የምርጫ...
03/06/2026

‎የወላይታ ዞን ብልፅግና ፓርቲ ቅ/ጽ/ቤት የምርጫ ሥራዎች አፈፃፃም በመገምገም በቀጣይ ሥራዎች ላይ መክሯል

‎ወላይታ ሶዶ፤ግንቦት 26/2018 የወላይታ ዞን ብልፅግና ፓርቲ ቅ/ጽ/ቤት የምርጫ ስራዎች አፈጻጸም በመገምገምና በቀጣይ ሥራዎች ዙሪያ ውይይት አካሂዷል።

‎የወላይታ ዞን ብልፅግና ፓርቲ ቅ/ጽ/ቤት ኃላፊ ዶ/ር አማረ አቦታ 7ኛው ሀገራዊና ክልላዊ ምርጫ በሠላምና በስኬት እንዲጠናቀቅ ያስቻሉ አካላትን አመስግነዋል።

‎ኃላፊው አያይዘውም በድህረ-ምርጫ ወቅት የሚሰሩ ሥራዎች ዙሪያ አመራሩ ልዩ ትኩረት ሰጥቶ መምራት እንዳለበትም አሳስበዋል።

‎በበጀት ዓመቱ ሲሰሩ የቆዩ የፓርቲና የመንግስት መደበኛ ሥራዎች ሳይንጠባጠቡ ተጠናክረው መቀጠል እንዳለባቸውም ገልፀዋል።

‎በየደረጃው ያለው አመራር በሙሉ አቅም ወደ መደበኛ ሥራ መግባት ይገባል ያሉት ኃላፊው፥ የዓመቱ ቀሪ ሥራዎች ላይ ልዩ ርብርብ ማድረግ እንዳለበትም አጽንኦት ሰጥተዋል።

‎በምርጫው ላይ የታየው የአመራር የተግባርና የአስተሳሰብ አንድነት እንዲሁም የህዝቡ የነቃ ተሳትፎ ተጠናክሮ መቀጠል እንዳለበትም አሳስበዋል።

‎እያንዳንዱ ተቋም የተቋሙ ዕቅድ አፈጻጸም ያለበት ደረጃ በመገምገምና ቀጣይ ትኩረት አቅጣጫዎች ላይ ትኩረት በማድረግ ሊረባረብ እንደሚገባም አመላክተዋል።

‎በየአካባቢው ህዝቡ ያነሳቸው የልማትና የመልካም አስተዳደር ጥያቄዎች የዕቅድ አካል ተደርጎ ህብረተሰቡን በማሳተፍ መምራት እንዳለበትም አንስተዋል።

‎በመጨረሻም ኃላፊው ቀጣይ መሰራት የሚገቡ ጉዳዮች ላይ አቅጣጫዎችን አስቀምጠዋል።


#‎ኢትዮጵያ_አሸንፋለች!

ሕዝቡ ሉዓላዊ የስልጣን ባለቤትነቱን በተግባር አረጋግጧል!ግንቦት 24/2018 ኢትዮጵያውያን ከጫፍ እስከ ጫፍ በመውጣት በ7ኛው ጠቅላላ ምርጫ አዲስ ታሪክ ፅፈዋል። ይህ ታላቅ ሕዝባዊ ንቅናቄ ...
03/06/2026

ሕዝቡ ሉዓላዊ የስልጣን ባለቤትነቱን በተግባር አረጋግጧል!

ግንቦት 24/2018 ኢትዮጵያውያን ከጫፍ እስከ ጫፍ በመውጣት በ7ኛው ጠቅላላ ምርጫ አዲስ ታሪክ ፅፈዋል። ይህ ታላቅ ሕዝባዊ ንቅናቄ የሀገሪቱን የዲሞክራሲ ጉዞ ለማፅናትና ለማስቀጠል ያለውን ፅኑ ፍላጎት በግልፅ ያሳየበት ታሪካዊ አጋጣሚ ሆኖ ይመዘገባል። ሕዝቡ የምርጫ ካርዱን በጥንቃቄ አስቀምጦ በመያዝ በምርጫዉ እለት ድምፅ በመስጠት ሉዓላዊ የስልጣን ባለቤትነቱን በተግባር አረጋግጧል።

የፖለቲካ ሥልጣን ምንጭ ሕዝብ ብቻ መሆኑንም ዳግም ለመላው ዓለም በማሳየት፣ ኢትዮጵያን ከፍ ማድረግ ተችሏል። በዚህ ታሪካዊ ሂደት ውስጥ ዋነኛውና ብቸኛው አሸናፊ መላው የኢትዮጵያ ሕዝብ እና ሀገራችን ኢትዮጵያ ብቻ ናቸው። መራጩ ሕዝብ ሳይሰለች ከነጋት 10:00 ሰአት ጀምሮ ረጅም ሰልፎችን በመያዝ እስከ እኩለ ሌሊት ድረስ ድምፁን የሰጠው የፓርቲዎችን ድል ለመወሰን ብቻ ሳይሆን፣ የኢትዮጵያን ሉዓላዊነትና ክብር ከፍ ለማድረግ ነው። እናቶች፣ አባቶች፣ ወጣቶች፣ አካል ጉዳተኞች፣ እድሜ ጠገብ አዛዉንቶች፣ ሙሽሮች ሳይቀሩ በነቂስ ወጥተው ዲሞክራሲን ለማፅናት ያሳዩት ትዕግስት የኢትዮጵያን ብሔራዊ አንድነትና ጥንካሬ ለዓለም ያሳየ ታላቅ የድል ምዕራፍ ነው።

የዘንድሮው የምርጫ ሂደት ሙሉ በሙሉ ሰላማዊ፣ ስልጡን እና ፍፁም ዲሞክራሲያዊ በሆነ መንገድ መጠናቀቁ ለሀገራችን ትልቅ የሞራል ድል ሲሆን ሕዝቡ ያሳየው የሰለጠነ የፖለቲካ ባህል፣ መቻቻልና እርስ በርስ የመከባበር እሴት ኢትዮጵያን ሊከፋፍሉና ሊያዳክሙ ለሚፈልጉ ሀይሎች ሁሉ ግልጽ ምላሽ የሰጠ ታሪካዊ ድል ነው። ይህ ስልጡን የዲሞክራሲ ልምምድ አካሄድ ኢትዮጵያ በዲሞክራሲ ሥርዓት ግንባታ ረገድ የደረሰችበትን ጀረጃ በተግባር ያሳየና የሀገሪቱን ገጽታ በዓለም መድረክ ከፍ ያደረገ ልዩ ክስተት ነው።

ይህ ምርጫ ለአዲሲቷና ለበለፀገችው ኢትዮጵያ ጠንካራ መሰረት በመጣል ለነገዋ የበለፀገችና የተረጋጋች ሀገር ጠንካራ መሰረት የጣለ ታላቅ የስኬት ምዕራፍ ነው። 7ኛዉ ጠቅላላ ምርጫ የልዩነት ሳይሆን የኅብረት፣ የብጥብጥ ሳይሆን የሰላም መገለጫ በመሆኑ የሀገሪቱን የነገ ተስፋ ብሩህ አድርጎታል።

በመጨረሻም በተለያዩ ጫናዎች እና ፈተናዎች ሳይበገሩ ድምፄ ዋጋ አለዉ በማለት በታላቅ ሀገራዊ ክብር ፀንተዉ በመቆም በትዕግስት እስከ ሌሊት ተሰልፈው ድምፃቸውን ለሰጡ እና የኢትዮጵያና ህዝቦቿን ታላቅነት በተግባር ላገዘፉ ዜጎች ሁሉ ታላቅ ክብርና ምስጋና ይገባቸዋል።

ኢትዮጵያ መርጣለች!
ኢትዮጵያ ለዘላለም ታሸንፋለች!

በሰባተኛው ጠቅላላ ምርጫ ህዝቡ በዴሞክራሲ ባህል ግንባታ ላይ ያለውን ተሳትፎ እና ዴሞክራሲ የማጽና ጉዞ ያሳየበት ነው፦ የወላይታ ሶዶ ከተማ የፖለቲካ ፓርቲዎች የጋራ ምክር ቤትወላይታ ሶዶ፦ግ...
03/06/2026

በሰባተኛው ጠቅላላ ምርጫ ህዝቡ በዴሞክራሲ ባህል ግንባታ ላይ ያለውን ተሳትፎ እና ዴሞክራሲ የማጽና ጉዞ ያሳየበት ነው፦ የወላይታ ሶዶ ከተማ የፖለቲካ ፓርቲዎች የጋራ ምክር ቤት

ወላይታ ሶዶ፦ግንቦት 26/2018 ዓ ም የወላይታ ሶዶ ከተማ የፖለቲካ ፓርቲዎች የጋራ ምክር ቤት የሰባተኛው ጠቅላላ ምርጫ ድምጽ አሰጣጥ ሂደት መጠናቀቁን አስመልክቶ የጋራ መግለጫ ሰጥቷል።

የወላይታ ሶዶ ከተማ የፖለቲካ ፓርቲዎች የጋራ ምክር ቤት ሰብሳቢ ዶክተር ተመስገን ቶራ በጋራ በሰጡት መግለጫ እንደገለጹት በሰባተኛው ጠቅላላ ምርጫ ህዝቡ በዴሞክራሲ ባህል ግንባታ ላይ ያለውን ተሳትፎ ያሳየበት እንደነበር ተናግረዋል።

ህዝቡ በነቂስ ወጥቶ በመሳተፍ በሰላማዊ መንገድ ድምጹን ሲመርጥ መዋሉን ተናግረዋል ።

በከተማ ትላንት በስትያ በተካሔደው ጠቅላላ ምርጫ ላይ 16 የፖለቲካ ፓርቲዎች መሳተፋቸውን የገለጹት ዶክተር ተመስገን ምርጫው ከታወጀበት ጊዜ ጀምሮ የጋራ ምክር ቤቱ የላቀ ጥረት ሲያደርግ መቆየቱን ጠቁመዋል።

ምርጫ ለሀገረ መንግስት ግንባታ የጎላ አስተዋጽኦ እንደሚያበረክት የተናገሩት ሰብሳቢው ለዚህም የጋራ ምክር ቤቱ ምርጫው ሰላማዊ፣ዴሞክራሲያዊ እና ተአማኒነት ያለው ሆኖ እንዲጠናቀቅ በትኩረት ሲሰራ እንደነበር አስታውሰዋል።

ተፎካካሪ ፓርቲዎች የሀገሪቱን እና ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ያወጣውን ህግ እየተከተሉ መሄድ ተገቢ መሆኑን አብራርተዋል።

የጋራ ምክር ቤቱ በየጊዜው የሚፈጠሩ ችግሮችን በውይይት እየፈታ መምጣቱን ጠቅሰዋል።

ከትላንት በስትያ የተካሄደው ጠቅላላ ሀገራዊ ምርጫ ህዝቡ በነጻነት ወጥቶ በተረጋጋና ሰላማዊ በሆነ መንገድ ድምጽ ሲሰጥ መዋሉን ዶክተር ተመስገን በመግለጫቸው ጠቅሰዋል።

ምርጫ ሊያደናቅፍ የሚችል ችግር አለመግጠሙን የተናገሩት ሰብሳቢው ይህ ደግሞ ህዝቡ የሚፈልገውን ፓርቲ በነጻነት እንዲመርጥ አስችሎታል ሲሉም አብራርተዋል።

ህዝቡ የምርጫው ሂደት ሰላማዊ እንዲሆን ላደረገው የላቀ ጥረት ዶክተር ተመስገን በማመስገን በድምፅ ያሸነፈዉን ፓርቲ እንኳን ደስ ያላችሁ በማለት በፉክክሩ ያላሸነፈው በቀጣይ አቅዶ የሚሰራ ይሆናል ብለዋል።

የጋራ ምክር ቤቱ ምክትል ሰብሳቢ አቶ አገኘሁ ጴጥሮስ በበኩላቸው ሰባተኛው ጠቅላላ ምርጫ በዋና ዋና መመዘኛዎች ሲታይ ሰላማዊ፣ፍትሀዊ እና ተአማኒነት ያለው ምርጫ ነው ብለዋል።

በወላይታ ሶዶ ከተማ በገዢው ፓርቲ ፣በተፎካካሪ ፓርቲዎች እንዲሁም በመንግስት በኩል ምርጫውን ለማካሔድ የነበረው ዝግጅት ውጤታማ መሆኑን ጠቅሰዋል።

የምርጫው ሂደት ሰላማዊ እንደነበር የተናገሩት አቶ አገኘሁ በከተማችን 7ተኛው ሀገራዊ ምርጫ ላይ 16 የፖለቲካ ፓርቲዎች መፎካከራቸውን አስረድተዋል።

ምርጫ የዲሞክራሲ ስርአት ግንባታ መሰረት ነው ያሉት ምክትል ሰብሳቢው ዜጎች በመረጡት መንግስት የመተዳደር መብትን የሚያረጋግጥ ስለመሆኑም ጠቅሰዋል።

ዜጎች በምርጫ የሚያደርጉት ንቁ ተሳትፎ ለሰላም፣ ለልማት እና ለዴሞክራሲ ስርዓት ግንባታ የሚኖረው አበርክቶ ከፍተኛ መሆኑን አቶ አገኘሁ በመግለጫቸው አብራርተዋል።

ወላይታ ሶዶ ከተማ የተሞክሮ ማዕከል ለማድረግ የተጀመረው ጥረት ውጤታማ ነው ያሉት ምክትል ሰብሳቢው የሰላም እና የተረጋጋ የፖለቲካ ባህል ግንባታ ተምሳሌት መሆኑን ተናግረዋል።

የጋራ ምክር ቤት ም/ሰብሳቢ በመጨረሻም የከተማ ነዋሪዎች ብርድና ፀሐይ ሳይበግራቸው ከጧቱ 12:00 ሰዓት ጀምሮ እስከ እኩለ ለልት ድረስ በነቂስ ወጥቶ ለፈለጉት ፓርቲ ድምፅ በአግባቡ በመስጠት ሰለአሳያችሁት ትዕግሥትና ቆራጥነት በራሴና በጋራ ምክር ቤት ስም ምስጋናዬ እጅግ የላቀ ነው ብለዋል።

በመጨረሻም በወላይታ ሶዶ ከተማ የተካሄደው 7ተኛው ሀገራዊ ምርጫ ተከትሎ የከተማ ተፎካካሪ የፖለቲካ ፓርቲዎች የጋራ ምክር ቤት ባለሶስት የአቋም መግለጫ በመዉጣት አጠናቅቀዋል ።

በከተማችን የሚገኝ 16 የተፎካካሪ ፖለቲካ ፖርቲዎች በቅድመ ምርጫ ጊዜ በነጻነት የይምረጡኝ ምርጫ ቅስቀሳ እየተካሄደ መቆየቱን በመግለጫቸው ገልጿል።

በምርጫ ዕለትም የድምፅ አሰጣጥ ሂደት እጅግ በጣም ነጻ፥ ሰላማዊ፥ ፍትሃዊ እና በህዝብ ዘንድ ተአማኒነት ያተረፈ ሆኖ መጠናቀቁን ገልጿል ።

በከተማችን ወላይታ ሶዶ በድህረ ምርጫ ወቅትም ከፖሊቲካ ፓርቲዎች የቀረበው አንድም ቅሬታ አለመኖሩን የገለፁት ስብሳቢ ዶክተር ተመስገን በተለየ ሁኔታ ለሀገር ሽማግሌዎች፣ ለኃይማኖት መሪዎች፣ ለሴቶችና ወጣቶች፣ ለመንግስት ሠራተኞች፣ ለነጋዴ ማህበረሰብ፣ ለሁሉም ሚዲያ ተቋማት፣ ለመላው የወላይታ ሶዶ ከተማ ህዝባችን እስከ እኩለ ሌልት ብርድና ጨለማ በመቋቋም ድምፃችሁን ቀጣይ የሚመራ ፓርቲ በመምረጣቸው በራሴና በከተማ ፖለቲካ ፓርቲዎች በጋራ ምክር ቤት ስም ምስጋናውን በማቅረብ የሚመጣውን ዉጤት የጋራ ምክር ቤት ለመቀበል ዝግጁ መሆናቸውን ገልጿል ።

ግንቦት 26/2018 ዓ.ም
ወላይታ ሶዶ

Address

S**o
026

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when በወላይታ ዞን የብልፅግና ፓርቲ ቅ/ጽ/ቤት- Wolaita Zone Prosperity Party Branch office posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Organization

Send a message to በወላይታ ዞን የብልፅግና ፓርቲ ቅ/ጽ/ቤት- Wolaita Zone Prosperity Party Branch office:

Share