South Ethiopia Regional State Office Of The President

South Ethiopia Regional State Office Of The President ይህ በደቡብ ኢትዮጵያ ክልላዊ መንግስት የርዕሰ መስተዳድር ጽ/ቤት ትክክለኛ የፌስቡክ ገፅ ነው።
(6)

01/06/2026

የኢትዮጵያ ሕዝብ አስደናቂም ተአምረኛም ሕዝብ ነው። ከፈጣሪ በቀር ሕዝባችንን አሟልቶ ሊያውቅና ሊገመግም የሚችል ማን ነው? የዳበረ ባህል፣ ሀገር ወዳድና የወል መሻቱን መጠበቅ የሚችል ሕዝብ መሆኑን በዘንድሮው ምርጫ ዳግም ለዓለም አሳይቷል። በዛሬው ታሪካዊ ዕለት፡-

• የሌሊቱ ብርድና ጨለማ ያላስፈራቸው፣
• የቀትሩ ፀሐይና ድንገተኛ ዝናብ ያልበገራቸው
• ሠርግ፣ ኀዘን፣ ወሊድና ሌሎች ማኅበራዊ ሁነቶች ያላገዳቸው፣
• ረጃጅም ሰልፎች ያላታከታቸው፣
• የአካል ጉዳት ድምጽ ለመስጠት ያልገደባቸው፣
• ሕመም እና እርጅና የሀገር ተስፋን ከማየት ያላገዳቸው፣
• የነገ ሀገር ተረካቢ ጨቅላ ልጃቸውን ማዘል ያላደከማቸው፣
• ከምንም በላይ የጠላት ጩኸትና ማስፈራሪያ ያላስቆማቸው ዜጎች፤

በብዙ ውጣ ውረዶች መካከል (against all odds) ያሳያችሁት ጽናት ለዴሞክራሲና ለሀገር ሕልውና የተከፈለ ነውና ከልብ የመነጨ ምስጋና ይገባቸዋል፡፡

ይሄንን ሕዝብ ማገልገል መታደል ነውና ተመራጮች ያከበራችሁን አክብራችሁ ለዴሞክራሲ ሥርዓት ዋጋ የከፈለውን ይሄንን ሕዝብ በንጽሕና ለማገልገል ያብቃችሁ።

Uummanni Itoophiyaa dinqisiisaafi ajaa'ibsiisaadha! Uumaa malee uummata keenya guutummaan beekuufi gamaaggamuu kan danda'u eenyu? Aadaa gabbataa, uummata biyya jaallatuufi fedhiisaa waloo eeguu danda'u ta'uusaa filannoo baranaatiin irradeebiidhaan addunyaatti agarsiiseera. Guyyaa seena-qabeessa har'aatiin:
- Qorriifi dukkanni halkani kan isaani hin sodaachifne,
- Aduun saafaafi bokkaan tasaa kan isaan jilbeenfachiifne,
- Cidhi, gaddi, da'umsiifi taateewwan hawaasummaa kanbiroon kan isaan dhorkine,
- Hiriironni dhedheeroon kan isaan hin nuffisiifne,
- Qaama miidhamtummaan sagalee kennuuf kan isaan hin daangessine,
- Dhukkubniifi dullumni abdii biyyaa arguuf kan isaan hin dhowwine,
- Daa'imasaanii kichuu bor biyya dhaalu baatanii filuun kan isaan hin dadhabsiifne
- Hundumaa caalaa lammiilee iyyiifi sodaachiifni diinaa isaan hin dhaabsifne,
Ciminni bu'aa bayii hedduu keessatti agarsiiftan gatii diimokraasiifi jiraachuu biyyatiif kanfalame waan ta'eef galata guddaatu malaafi.

Uummata kana tajaajiluun carroomuu waan ta'eef filatamtoonni warra isin kabajan kabajjanii uummata sirna diimookraasiif gatii baase kana qulqullummadhaan tajaajiluuf isin haa gahu.

The people of Ethiopia are an extraordinary and remarkable people. Other than the Creator, who can truly know and assess our people in their entirety? Through this year’s election, Ethiopians have once again shown the world that they are a people with a rich culture, deep patriotism, and the ability to safeguard the common good.

On this historic day:

* Citizens who were not intimidated by the cold and darkness of the night,
* Who were not deterred by the midday sun or sudden rain,
* Whom weddings, funerals, childbirth, and other social obligations did not prevent from participating,
* Who were not wearied by long lines,
* Whose physical disabilities did not stop them from casting their vote,
* Those whose illness and old age did not prevent from witnessing the hope of their country,
* Who were not exhausted by carrying their infant children; the future inheritors of the nation,
* And above all, whom the shouting and threats of enemies could not intimidate or stop;

The perseverance you demonstrated amid many challenges and hardships, against all odds, was a contribution made for democracy and for the very survival of the nation. For this, you deserve heartfelt gratitude.

It is a privilege to serve such a people. Therefore, may those who have been elected honor the trust placed in them and serve this people, with integrity and sincerity! A people who have paid a great price for the democratic system. May you be worthy of that responsibility.

በክልላችን ድምጽ የመስጠት ሂደቱ ምሽቱን ተጠናክሮ ቀጥሏልበታሪካዊው 7ኛው ጠቅላላ ሀገራዊ ምርጫ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ የድምጽ አሰጣጥ ሂደቱን እስከ እኩሌ ሌሊት ማራዘሙን ተከትሎ፤ ...
01/06/2026

በክልላችን ድምጽ የመስጠት ሂደቱ ምሽቱን ተጠናክሮ ቀጥሏል

በታሪካዊው 7ኛው ጠቅላላ ሀገራዊ ምርጫ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ የድምጽ አሰጣጥ ሂደቱን እስከ እኩሌ ሌሊት ማራዘሙን ተከትሎ፤ በክልላችን አርባ ምንጭ፤ ወላይታ ሶዶ እና ዲላን ጨምሮ በተለያዩ አካባቢዎች የድምጽ አሰጣጥ ሂደቱ ምሽቱንም ተጠናክሮ ቀጥሏል፡፡

ድምጻችን መፃይ የሀገራችንን ዕጣ ፈንታ በመወሰኑም ሆነ በዴሞክራሲያዊ ስርዓት ግንባታ ሂደት ዋጋ አለው ያሉ መራጮች፤ በክልላችን ምሽቱንም ዴሞክራሲያዊ የዜግነት መብታቸውን ተጠቅመው ድምጻቸውን በመስጠት ላይ ይገኛሉ፡፡

#ኢትዮጵያ እየመረጠች ነው!

#ኢትዮጵያ ታሸንፋለች!

01/06/2026

የሀገራችንን የዲሞክራሲ ልምምድ እድገት ያሳየ ምርጫ …

የድምፅ የመስጠት ሂደቱ እስከ ዕኩለ ለሊት 6:00 ሰዓት ድረስ ተራዝሟል በድጋሚ የተሰጠ መግለጫየኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ዛሬ ሰኞ ግንቦት 24 ቀን 2018 ዓ.ም. ከማለዳ 12:00 ሰዓ...
01/06/2026

የድምፅ የመስጠት ሂደቱ እስከ ዕኩለ ለሊት 6:00 ሰዓት ድረስ ተራዝሟል

በድጋሚ የተሰጠ መግለጫ

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ዛሬ ሰኞ ግንቦት 24 ቀን 2018 ዓ.ም. ከማለዳ 12:00 ሰዓት ጀምሮ እስከ ምሽት 12:00 ሰዓት የ7ኛውን ጠቅላላ ምርጫ ድምፅ የማስፈጸም ሂደት ላይ እንደነበር ይታወቃል። ቦርዱ በሥምሪት ላይ ያለው የክትትል ቡድኑ ያቀረበለትን ሪፖርት ተመልክቶ የሚከተለውን ወሥኗል።

በኢትዮጵያ የምርጫ፣ የፖለቲካ ፓርቲዎች ምዝገባና የምርጫ ሥነ-ምግባር ዐዋጅ 1162/2011 አንቀጽ 49(4) መሠረት ቦርዱ የምርጫው ነፃና ፍትሐዊነት ይበልጥ ያሰፍናል ብሎ ካመነ የድምፅ መስጫ ሰዓቱን ሊያራዝም እንደሚችል በግልጽ ይደነግጋል። በመሆኑም የድምፅ መስጫ ሂደት ባልተጠናቀቀባቸው የምርጫ ጣቢያዎች ላይ ድምፅ የመስጠት ሂደቱ እስከ ዕኩለ ለሊት 6:00 ሰዓት ድረስ የተራዘመ መሆኑን ቦርዱ ያሳውቃል።

ማሳሰቢያ: የተመዘገቡ መራጮች መርጠው የተጠናቀቁባቸው ጣቢያዎች ላይ አስፈጻሚዎች የድምፅ ቆጠራ ሂደቱን እንዲያከናውኑ ቦርዱ ያስታውሳል።

የኢትዮጵያ ምርጫ ቦርድ

01/06/2026

ርዕሰ መስተዳድር ጥላሁን ከበደ በአርባምንጭ ምርጫ ክልል የመራጭነት ድምጻቸውን በሰጡበት ወቅት ካስተላለፉት መልዕክት፦

 #ኢትዮጵያእየመረጠችነው ለፈተናዎች የማትንበረከከው፣ አይበገሬነቷን ያፀናችው ኢትዮጵያ ዛሬም እንደ ትናንቱ ከሩቅም ከቅርብም የተደቀኑባትን ተግዳሮቶች እየተሻገረች ዴሞክራሲያዊ ባህልን መገንባ...
01/06/2026

#ኢትዮጵያእየመረጠችነው

ለፈተናዎች የማትንበረከከው፣ አይበገሬነቷን ያፀናችው ኢትዮጵያ ዛሬም እንደ ትናንቱ ከሩቅም ከቅርብም የተደቀኑባትን ተግዳሮቶች እየተሻገረች ዴሞክራሲያዊ ባህልን መገንባት እንደምትችል በ7ኛው ሀገራዊ ምርጫ ተግባራዊ ምላሽ ሰጥታለች፡፡

በታሪካዊው የዛሬው 7ኛው ጠቅላላ ሀገራዊ ምርጫ 80 የግል ተወዳዳሪዎችን ጨምሮ የ42 የፖለቲካ ፓርቲዎች ተወካዮች፤ በአጠቃላይ 10 ሺህ 4 መቶ 38 ዕጩ ተወዳዳሪዎች የሚወዳደሩ ሲሆን፤ ሀገሩን ያስቀደመው መራጩ ሕዝብ በሁሉም የሀገሪቱ ክፍሎች በምገኙ ምርጫ ጣቢያዎች ከንጋት ቀድሞ ድምጽ በመስጠት ላይ ይገኛል፡፡

በምርጫው ከሃምሳ አራት ሚሊዮን በላይ (54,057,861) ዜጎች የመራጭነት ካርድ ወስደው በድምፃቸው መፃይ የሀገራቸውን ኢጣ ፈንታ ለመወሰን ወደየምርጫ ጣቢያዎቻቸው በመትመም ላይ ሲሆኑ፤ ከማለዳው 12፡00 ሰዓት አስከ ምሽቱ 12፡00 ሰዓት በሚካሄድው ምርጫ በድምጻቸው ታሪክ ይሰራሉ ተብሎ ይጠበቃል፡፡

#ኢትዮጵያእየመረጠችነው!

ኢትዮጵያ በድምጻችን ታሸንፋለች

"ሁሉም ህብረተሰብ በነቂስ በመውጣት ሀገር የየሚያሻግር የኢትዮጵያን ብልፅግና የሚያረጋግጥ ፓርቲን በመምረጥ የታሪክ አካል ሊሆኑ ይገባል " አፈ ጉባኤ አቶ ታገሰ ጫፎ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ...
01/06/2026

"ሁሉም ህብረተሰብ በነቂስ በመውጣት ሀገር የየሚያሻግር የኢትዮጵያን ብልፅግና የሚያረጋግጥ ፓርቲን በመምረጥ የታሪክ አካል ሊሆኑ ይገባል " አፈ ጉባኤ አቶ ታገሰ ጫፎ

የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አፈ ጉባኤ አቶ ታገሰ ጫፎ በትውልድ ቦታቸው በአርባ ምንጭ ከተማ ጫሞ ምርጫ ጣቢያ በመገኘት ድምፅ ሰጥተዋል።

ዋና አፌ ጉባኤው በዚህ ወቅት እንደገለፁት በ7ኛው ሀገራዊ ምርጫ በርካታ መራጭ ተመዝግቦ በነቂስ በመውጣት እየመረጠ መሆኑ ከበፊቱ ምርጫ ለየት እንደሚያደርገው ገልፀው ይህ የሀገራችን ዲሞክራሲያዊ ልምምድ እያደገ እንደመጣ ማሳያ ነው ሲሉ ተናግረዋል።

በተጨማሪ በ7ኛው ሀገራዊ ምርጫ 42 ፖለቲካ ፓርቲዎች የተሳተፉበት፤ የምርጫ ክርክሮችን በምርጫ ቦርድ መሪነት የተካሄደበት ፣ የተሻሉ አሰራሮች በምርጫ ቦርድ የተካተቱበት በመሆኑ የዘንድሮውን ምርጫ ለየት እንደሚያደርገው ገልፀዋል።

የሀገራችን ህገ መንግስት መሰረት ስልጣን የሚያዘው በመሆኑ ምርጫ በተሳካ ሁኔታ እንዲካሄድ የሁሉም ኃላፊነት ሊሆን እንደሆነ ገልፀው ይህን ለማደናቀፍ መሞከር ኢ-ህገመንግስታዊ እና ሀገር እንዳትሻገር የማድረግ እኩይ እርምጃ መሆኑን ተናግረዋል።

ሀገር ወደፊት እንድትቀጥል በሚደረገው ሂደት ሁሉም የማህበረሰብ ክፍል በነቂስ ወጥተው ሀገር የየሚያሻግር መንግስት የሚያፀና፣ የኢትዮጵያን ብልፅግና የሚያረጋግጥ የፖለቲካ ፓርቲን በመምረጥ የታሪክ አካል መሆን
እንደሚጠበቅባቸው ተናግረዋል።

#ርዕሰመስተዳድርጽቤት

ምርጫው ዴሞክራሲን በመትከል ሀገር የምናሻግረበት በመሆኑ መራጩ ሕዝብ በነቂስ በመሳተፍ ታሪክ መስራት ይገባዋል -ርዕሰ መስተዳድር ጥላሁን ከበደ ርዕሰ መስተዳድር ጥላሁን ከበደ በ7ኛው ጠቅላላ...
01/06/2026

ምርጫው ዴሞክራሲን በመትከል ሀገር የምናሻግረበት በመሆኑ መራጩ ሕዝብ በነቂስ በመሳተፍ ታሪክ መስራት ይገባዋል -ርዕሰ መስተዳድር ጥላሁን ከበደ

ርዕሰ መስተዳድር ጥላሁን ከበደ በ7ኛው ጠቅላላ ሀገራዊ ምርጫ በጋሞ ዞን በአርባ ምንጭ ከተማ የመራጭነት ካርዳቸውን በመጣል ድምጽ ሰጥተዋል፡፡

ክቡር ርዕሰ መስተዳድሩ ለክልሉ ሕዝብ ምክር ቤት በሚወዳደሩበት ምርጫ ክልል፤ በአርባ ምንጭ ከተማ በጫሞ ካምፓስ ምርጫ ጣቢያ በመገኘት የመራጭነት ካርዳቸውን ተጠቅመው ድምጽ መስጠት ችለዋል፡፡

ርዕሰ መስተዳድሩ ድምጻቸውን በሰጡበት ወቅት፤ 7ኛው ጠቅላላ ሀገራዊ ምርጫ ፍጹም ሰላማዊ፤ ነፃ፤ ፍትሃዊና ታአማኒ ሆኖ በስኬት በማጠናቀቅ በኢትዮጵያ የዴሞክራሲ ስርዓት ግንባታ ሂደት አዲስ የታሪክ ምዕራፍ የምንከፍትበት ይሆናል ሲሉ ተናግረዋል፡፡

እንደ ሀገር ለምርጫው ዴሞክራሲያዊ ሆኖ በስኬት መጠናቀቅ ነፃና ገለልተኛ ምርጫ አስፈጻሚ ተቋማትን ከመገንባትና ከማጠናካር ጀምሮ ሰፊ ዝግጅት ሲደረግ መቆየቱንም ገልፀዋል፡፡

ምርጫ ዜጎች ሕገ-መንግስታዊ ስርዓቱ ያጎናፀፋቸውን የዜግነት መብት በአግባቡ ተጠቅመው በካርዳቸው የሚሽቱን አካል በነፃነት በመምረጥ፤ የሕዝብ ሉዓላዊ የሥልጣን ባለቤትነትን የሚያረጋግጡበት እና በድምጻቸው መንግስት በመመስረት ሀገር የሚያሻግሩበት ወሳኝ የዴሞክራሲ ሂደት መሆኑንም በአጽንኦት ገልፀዋል፡፡

በተለይ የበርካታ ብዝኃ ማንነቶች ባለቤት በሆነችው ሀገራችን ምርጫ ዴሞክራሲያዊ ስርዓትን የምንገነባበት ከመሆኑም ባሻገር ሀገራዊ አንድነታችንን የምናጠናክርበት ሂደት ነው ያሉት ርዕሰ መስተዳድሩ፤ መራጩ ህዝብ በምርጫው በነቂስ በመሳተፍ፤ በካርዱ ዴሞክራሲን በመትከል ሀገራዊ አንድነትን እንዲያጠናክር ጥሪ አቅርበዋል፡፡

ርዕሰ መስተዳድሩ የምርጫ ዴሞክራሲያዊነት በቅድመ ምርጫ፤ በምርጫ እና በድህረ-ምርጫ ሂደት ባሉ ነገሮች የሚወሰን መሆኑንም ጠቅሰው፤ የቅድመ ምርጫ ሂደትን እጅግ ሰላማዊ፤ ነፃና ፍትሃዊ በሆነ ሂደት በስኬት በመሻገር ለዛሬው ታሪካዊ ድምጽ መስጫ ዕለት መብቃት መቻሉንም ገልፀዋል፡፡

የዛሬው የድምጽ መስጫም ሆነ የድህረ-ምርጫው ሂደት፤ 7ኛው ጠቅላላ ሀገራዊ ምርጫ ኢትዮጵያዊያን በሰለጠነ መንገድ፤ በሰከነ ፍትሃዊና ተአማኒ ምርጫ ዴሞክራሲያዊ ስርዓት መገንባት እንደሚንችል ለተቀረው አለም የምናሳይበት ታሪካዊ አጋጣሚ ነው ሲሉም አክለዋል፡፡

የምርጫው ውጤት ምንም ሆነ ምን በሂደቱ ኢትዮጵያ እና ኢትዮጵያዊያን ያሸንፋሉ ያሉት ርዕሰ መስተዳድሩ፤ እንደ ሀገር ውደቀታችንን የሚሹ አፍራሽ ኃይሎች ወደ ኋላ ሊጎትቱን በሚጥሩበት በዚህ ወቅት፤ ካርድ የወሰዱ ከ54 ሚሊዮን በላይ ኢትዮጵያዊያን በዚህ ታሪካዊ ምርጫ በድምጻቸው ዴሞክራሲን በመትከል ሀገር እንዲያጸኑ በድጋሚ ጥሪ በማስተላለፍ ሃሳባቸውን አጠቃለዋል፡፡

#ርዕሰመስተዳድርጽቤት

01/06/2026

እኔ ዛሬ የሚያሳስበኝ...

የተከበሩ ታገሰ ጫፎ እና ርዕሰ መስተዳድር ጥላሁን ከበደ በ7ኛው ጠቅላላ ሀገራዊ ምርጫ ድምጽ ሰጡ የሕዝብ ተወካዮች ም/ቤት አፈ ጉባኤ የተከበሩ ታገሰ ጫፎ እና ርዕሰ መስተዳድር ጥላሁን ከበደ...
01/06/2026

የተከበሩ ታገሰ ጫፎ እና ርዕሰ መስተዳድር ጥላሁን ከበደ በ7ኛው ጠቅላላ ሀገራዊ ምርጫ ድምጽ ሰጡ

የሕዝብ ተወካዮች ም/ቤት አፈ ጉባኤ የተከበሩ ታገሰ ጫፎ እና ርዕሰ መስተዳድር ጥላሁን ከበደ በ7ኛው ጠቅላላ ሀገራዊ ምርጫ በጋሞ ዞን በአርባ ምንጭ ከተማ የመራጭነት ካርዳቸውን በመጣል ድምጽ ሰጥተዋል፡፡

ክቡር አፈ ጉባኤው ለሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት እንዲሁም ክቡር ርዕሰ መስተዳድሩ ለክልሉ ሕዝብ ምክር ቤት በሚወዳደሩበት ምርጫ ክልል፤ በአርባ ምንጭ ከተማ በጫሞ ካምፓስ ምርጫ ጣቢያ በመገኘት ድምጽ የሰጡ ሲሆን፤ በዚህም የዜግነት መብታቸውን ተጠቅመው ታላቅ ሀገራዊ ሃለፊነት መወጣት ችለዋል፡፡

በተጨማሪም የተከበሩ አቶ ብርሃኑ ዘውዴ የክልሉ ከተማና መሰረተ ልማት ቢሮ ኃላፊ እንዲሁም የጋሞ ዞን ዋና አስተዳዳሪ ደምሴ አድማሱ (ዶ/ር)፤ ለክልሉ ሕዝብ ምክር ቤት በሚወዳደሩበት በዚሁ ምርጫ ክልል፤ በጫሞ ካምፓስ ምርጫ ጣቢያ ተገኝተው ድምጽ በመስጠት የዚህ ታሪካዊ ሁነት አካል መሆን ችለዋል፡፡

በታሪካዊው የዛሬው 7ኛው ጠቅላላ ሀገራዊ ምርጫ 80 የግል ተወዳዳሪዎችን ጨምሮ የ42 የፖለቲካ ፓርቲዎች ተወካዮች፤ በአጠቃላይ 10 ሺህ 4 መቶ 38 ዕጩ ተወዳዳሪዎች የሚወዳደሩ ሲሆን፤ ሀገሩን ያስቀደመው መራጩ ሕዝብ በሁሉም የሀገሪቱ ክፍሎች በምገኙ ምርጫ ጣቢያዎች ከንጋት ቀድሞ ድምጽ በመስጠት ላይ ይገኛል፡፡

በምርጫው ከሃምሳ አራት ሚሊዮን በላይ (54,057,861) ዜጎች የመራጭነት ካርድ ወስደው በድምፃቸው መፃይ የሀገራቸውን ኢጣ ፈንታ ለመወሰን ወደየምርጫ ጣቢያዎቻቸው በመትመም ላይ ሲሆኑ፤ ከማለዳው 12፡00 ሰዓት አስከ ምሽቱ 12፡00 ሰዓት በሚካሄድው ምርጫ በድምጻቸው ታሪክ ይሰራሉ ተብሎ ይጠበቃል፡፡

#ኢትዮጵያ እየመረጠች ነው!

#ኢትዮጵያ በድምጻችን ታሸንፋለች!

#ርዕሰመስተዳድርጽቤት

Address

Wolaita S**o
S**o
1000

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when South Ethiopia Regional State Office Of The President posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Organization

Send a message to South Ethiopia Regional State Office Of The President:

Share